Get Mystery Box with random crypto!

TEAM HUDA

የቴሌግራም ቻናል አርማ re_ya_zan — TEAM HUDA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ re_ya_zan — TEAM HUDA
የሰርጥ አድራሻ: @re_ya_zan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K
የሰርጥ መግለጫ

"أَفَلَا تَعْقِلُونَ"
"አታስተነትኑምን?"
አንብቡ! ራሳችሁን፣ በዙሪያችሁ ያሉትን ነገሮች፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ፅሁፎችን.... አንብቡ! አስተንትኑ! ጠይቁ!

Big thanks for joining!
All team huda!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-09 15:07:01 #ያስ:- <<ደስ የሚል ስራ ነበር..... ሁላችንንም ቃላችን የምንሞላ ያድርገን.... >>
#ሪዛል:- <<ሳህ.... በእርግጥ እንደዛሬው ባሉ የደስታ ቀናቶች የምንሰራቸው ጥፋቶች እየገዘፉ መጥተዋል። ድንበር ከማለፍ ይሰውረን>>
#ያስ:- <<አሚን.... መድረኩን ሀዘን በሀዘን አደረግነው መሰለኝ.... የዝግጅታችን ማብቂያ ላይ ያለውን ስጦታ አሁን እናስቀድመው እንዴ? >>
#ሪዛል:- <<ከቤት እንዲያሰናብቱን ከፈለግሽ ....

ባይሆን ጭምጭምታውን አድርሰናቸው እንዲጠብቁን እንጋብዛቸው። >>
#ያስ:- <<እሱም ጥሩ ....

ቤተሰቦቻችን..... ባለፉት 9 ቀናት ወደናንተ ስናደርሳቸው የነበሩት ጥያቄዎች ይታወሳሉ....>>
#ሪዛል:- <<....ሃሃህ.... ሀተታ ሳታበዢ ወደ ገደለው ግቢ >>
#ያስ:- <<ልመጣ አይደል...

በእርግጥ እንደሚያስሽልም ቀድመን የተናገርን ባይሆንም፤ ቀኑ ግን ዓረፋ በመሆኑ 9ኙንም ቀናት የተሳተፋቹና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 3 አንባቢያንን በዝግጅታችን ማብቂያ ላይ የምንሸልም ይሆናል...>>
#ሪዛል:- <<እስከዛው የትም እንዳትሄዱ ... ወደቀጣይ መሰናዶዎቻችን እናልፋለን...>>
#ያስ:- <<ማሻአለህ.... ሳናስበው ወደ ማብቂያው እየተንደረደርን እንገኛለን ...>>
#ሪዛል:- <<ከዛ ወደ ኬኩ.... ማነው.... ያው ወደዒዳችን >>
#ያስ:- <<ኢንሻአላህ ... ቀጣዩን ጉዞ ከታደምሽ በኋላ ያልሞላላቸውን ሚስኪን ወንድምና እህቶችሽን እያካፈልሽ እንዲሆን ቀድሜ ሳስታውስሽ በታላቅ ደስታ ነው ...>>
#ሪዛል:- <<ኢንሻአላህ..... ፍትህን ካስተማሩን ነብይ የተማርነው እሱንም አይደል። (ያሳጣሽኝን ከመድረክ ስንወርድ እንተሳሰባለን )>>
#ያስ:- <<ያድርሰን .... ለአሁን ብዙ አናስጠብቃቸው.... ወደ ሩህ ጉዞ... >>

@Re_ya_zan
179 views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:57:02 #ሪዛል:- <<ተመልሰናል ቤተሰቦቻችን.... ከወንድም ሪያድ ጋር በነበራቹ ቆይታ እንደተጠቀማቹበት አንጠራጠርም። >>
#ያስ:- <<ማሻአላህ በጣም ደስ በሚል መልኩ ብዙ ቁምነገሮችን አስተላልፎልናል። ስለ ወጣቱ ትውልድ እና ወደፊት ስላለሙት የምርምር ማዕከል የተነሳው ሃሳብ፤ በሁላችንም ውስጥ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው... አይመስልሽም?>>
#ሪዛል:- <<ልክ ነሽ። አሁን ላይ ትውልዱን በቁርዐን ለማነፅ የሚያደርጉት ርብርብም ቢሆን ቀላል የሚባል አይደለም .... አላህ ይጨምርላቸው።>>
#ያስ:- <<አሚን ። በድጋሚ እህት ሂባ ላስታደመችን ድንቅ ቆይታ እናመሰግናለን
ወደ ቀጣዩ እንለፍ?>>
#ሪዛል:- <<መርሃባ....
ቤተሰቦቻችን በንባብ ቆይታቸው ትንሽ ሳናደክማቸው አልቀረንም። አይኖቻቸውን አሳርፈው በድምፅ በታጀበ ጉዞ አብረውን የሚንሳፈፉበትን ዝግጅት እናድርሳቸው.... >>
#ያስ:- <<በደስታ....
ቀጣዩ መሰናዶአችን የሚሆነው በድምፅ የሚርቀብልን የግጥም ፅሁፍ ነው። ማዳመጫዎቻችሁን እያስተካከላቹ ጠብቁን.... መልካም ጊዜ.... >>

@Re_ya_zan
170 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:47:02 #ሂባ: እኛም እናመሰግናለን፤ ወዐለይከ ሰላም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

እንግዲህ ከወንድም ሪያድ ጋር በነበረን ሰፋ ያለ ቆይታ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እደያዝን አልጠራጠርም። ሳይሰስት ከህይወት ተሞክሮ እንካችሁ ስላለን እንዲሁም እዚህ ከሁዳ ቤት ስለተገኘልን በራህማኑ ስም እያመሰገንን እንግዳችንን እንሸኝና እዚሁ ላይ የምናቆም ይሆናል። በሌላ እንግዳ እሰከምንገናኝ ራህማኑ ይጠብቅልኝ።ከቀሪ የሁዳ መሰናዶ ጋ ፏ በሉልኝ

ዒዱኩም ሰዒድ ወሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ...

@Re_ya_zan
170 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:46:02 #ሪያድ: ቀላል የማይባል ተፅእኖ አለው። እሳት የሚባል ጊዜ ነው፤ በጣም አዳጋች፣ በጣም ፈታኝ የሆነ ጊዜ። ይሄን ጊዜ ተቋቁሞ ማለፍ በጣም ፅናት ይፈልጋል፤ እኔ ተቋቁሜ አልፌዋለሁ። ወላሁ አዕለም አላህ ነው ሚዛኑን የሚለካው ግን በጣም እጥራለሁኝ ይሄ ጊዜ እንዳይፈትነኝ እራሴን ለመቋቋም በጣም እጥራለሁ፤ አንዳንድ ፈተናዎችን መውደቅ አይቀርም ከብዙ ነገር ከኢባዳም አኳያ ከብዙ ነገር መውደቄ አይቀርም፤ በዛው ልክ ደሞ አልሀምዱሊላህ። የሚጠበቅብኝን ያክል ሳይሆን የሆነ ነገር በዚህ እድሜዬ ለማሳረፍ ሞክሬአለው ከዚህ የተሻለ ነገር አልም ነበር ያ ያልሆነው ደሞ በራሴ ስንፍና ነው። አላህ ትንሿን ነገር በረካ ሞልቷባት እንደ ትልቅ ነገር እንዲቆጥርልኝ ዱዐ እንድታረጉልኝ... በዚህ አጋጣሚ የምጠይቃቹ ወጣትነት ላይ አንደኛ ጉልበቱ አለ፤ ለምሳሌ በዚህ ሰአት ያለኝ አቅም ከዚህ በፊት አልበረኝም፣ ወደፊትም አይኖረኝም። አሁን ላይ ትልቅ አቅም አለ፤ ያንን የመጠቀም እና ያለመጠቀም ጉዳይ ነው። ስለዚህ ወጣትነትን በአግባቡ እየተጠቀምኩ አይደለም፤ ግን ልጠቀም ካልኩ ወጣትነት የፈጠረብኝ እድል ቀላል የሚባል አይደለም። በዛው ልክ ደግሞ ያመጣብኝ እሳቱ ደሞ ቀላል አይደለም ሁለቱንም መቋቋም እንዲሰጠኝ ደሞ እንደተለመደው በዱአ

#ሂባ: እንደው እዝች ዱንያ ላይ ትልቁ ፊትና ምንድነው ባንተ እይታ?
#ሪያድ: እዚህ ዱኒያ ላይ ትልቁ ፈተና ረሱል የተናገሩት ንግግር አለ <<የገንዘብ እና የሴት ፈተና>>። እኔ አልሀምዱሊላህ ወደ ትዳር በጊዜ ገብቻለው፤ የሴት ፈተናን ከአሁኑ ወደ ጎን ያሸሸሁት ይመስለኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዱኒያ ፈተና ደሞ አላህ ይጠብቀን!

#ሂባ: ፋሊስጢም ሲነሳ ሪያድ አብሮ ይነሳል፤ ብዙዉን ጊዜ በፊሊስጢም ዙሪያ ስትፅፍ ትስተዋላለህ ከምን የተነሳ ነው?
#ሪያድ: በነገራችን ላይ ፁሁፍ ላይ ያለ ሰው፤ እነካካለው የሚል ሰው መሰረታዊ የሆኑ የፍትህ ጉዳዮች ላይ ስስ ነው ብዬ ነው የማስበው፤ አዛኝነት ይኖራል። አላህ ከአዛኞች ያድርገን!
ፀሀፊዎች ምናልባት እኔንም ሸንቆጥ ሳያደርገኝ አይቀርም ከልጅነቴ ጀምሮ አንዳንድ የምሰማቸው ዜናዎች የሚፈጥሩብኝ ነገሮች ነበሩ። በተለይ ነገሮች ካለፉ በኋላ፣ የሶሪያ ችግር ከተፈጠረ በኋላ መፅሀፌ ላይም ፅፌዋለው... የከንአን ናፍቆት ጋር፤ አላህ ካለ የሚወጣ ረጅም ልብ ወለድ ታሪክ ነው። አልጀዚራ ላይ ያየሁት ዜና ትልቅ ተፅእኖ ፈጥሮብኛል፤ አንድ ህፃን ሲናገር <<ምንበላው የለንም ተቸገርን>> ብሎ ሲያለቅስ አየሁት። ይሄ ህፃን ልጅ ነው... ቤተሰብ እንዳያጣ በተሰበረ አንደበት ሲያወራ አየሁት። ሶሪያዊ ነው እና የዚህ ሶርያዊ መበደል መነሻው እዛች ፊሊስጢን የምትባል ከተማ ውስጥ እንዳለ ተረዳሁ፤ ስለዚህ የኢትዮጲያ ሙስሊም ገዳይ አይደለም፣ በመላው አለም ያለ ችግር ሊፈታ የሚችለው እዛች ፊሊስጢን ላይ ያለ ችግር ሲፈታ ነው ብዬ ማመን ጀመርኩኝ። ስለዚህም ትግሌ ነገሬም ሁሉ ፍሊሲጢን ላይ ያለው ችግር ለመፍታት ነው። ኢንሻ አላህ አላህ ከፈቀደው የሚሳካ ይመስለኛል፣ በዛው አያይዤ እፅፋለሁ ያው መፃፍ ነው የምችለው። ከዛ ውጪ ሪያድ እንደሪያድ የተሰጠውን አቅም ተጠቅሜ እዛ ቦታ ላይ የተቻለኝን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ።

#ሂባ: ኢላህ በፊልስጢምና ህዝቦቸቿ ላይ እዝነቱን ያውርድልን

መነሻችን እንጂ መዳረሻችን ባልታወቀባት ዱንያ ላይ አሁን ላይ ከምትሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ ምን የተለየ ስራ ሰርተህ ማለፍን ትፈልጋለህ?
#ሪያድ: ምድር ላይ ፍትህን አስፍሬ ማለፍ ነው የምፈልገው። ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት አቅሳን መክፈት ይህን ስል ሙስሊሞች በእውቀትም በሁሉም ነገር የዳበሩ እንዲሆኑ የሙስሊሞች ጥናትና ምርምር ማዕከል ከወንድሞቼ ጋር እናቋቁማለን ብዬ አስባለሁ። ኢንሻላህ እውን ይሆናል በተለይ የሙስሊሞች ጥናትና ምርምር ማዕከል ሰፊ ፕሮጀክት ነው። እሱን አሳክተን በዛ ውስጥ የሚመጣው ትውልድ ስለ ፉልስጢን፣ ስለአለም እያሰበ ለህዝብ ፍትህ የሚጨነቅ ትውልድ እንደምናፈራ ምንም አይነት ጥርጥር አይኖረንም ኢንሻአላህ። አንዳንዴ ህልሞች ስናልማቸው እሩቅ ይመስላሉ ግን ሁሉንም ነገር ምድር ላይ ያደረጉት ሰዎች ናቸው። ያው ከአላህ በታች...በዚህ መንገድ ላይ ሳላሳካው እንኳን ብሞት እዳሳካሁት ሁሉ ይሰማኛል። ኢንሻአላህ ህልሜ ነው!

#ሂባ: ሪያድ ከረሱል ሲራ(ታሪክ)የትኛው ይበልጥ ይዐጅበዋል? የትኛውስ ይበልጥ ያሳዝነዋል?
#ሪያድ: ከረሱል ታሪክ ውስጤን የሚነካኝ ወላሂ የዳሩ ሰውር ታሪክ ነው። ዳሩሰውር ላይ የአቡበከር ፍቅር መስዋትነቱ ሁሉነገሩ ብቻ እዛ ውስጥ ያለው ታሪክ ለኔ የተለየ ነው... ወደ መዲና ሲሄዱ ሂጅራ ላይ ያለው ታሪክ ማለት ነው፣ ለኔ በጣም ትልቅ ቦታ አለው። ወደ ሃገራቸው የተመለሱበትን ሁኔታ ደግሞ ለኔ በጣም የሚያስደንቀኝ ታሪክ ነው። እንደ ድል ታሪክ ደግሞ ወደ መዲና ድል አድርገው ባለድል ተከታዮቻቸውን ይዘው ሲገቡ አንገታቸው ደፍተው የገቡበት ተናናሽነት ሁሌም በሁላችንም ዘንድ እንዲኖር እመኛለሁ።

#ሂባ: እንደው ከዝች ፈታኝ ዱንያ አንተን ከሁሉም በላይ ምን ያስፈራሃል?
#ሪያድ: እኔ ነገር አልወድም። ከሰው ጋር ብዙ መነካካት አይመቸኝም ከሁሉም ጋ በሚቻለው መልኩ ተግባብቶ ማለፍ ነው በምችለው መልኩ። እንዳልኩሽ ህልሜ ላይ ግን ምንም አይነት ፍርሃት የለብኝም በማይሆን ነገር ላይ ግን ራሴን መሰዋት ማድረግ አልፈልግም። መጎዳት አልፈልግም፣ በኢስላም መንገድ ላይ ከሆነ ምንም የሚያስፈራኝ የለም። ዱንያ ላይ ማጣትን አልወድም ትንሽ ይጨንቀኛል ሳጣ ኪሴ ባዶ ሲሆን ነፍሴ ትጨነቃለች መውጣት ሁላ ያስጠላኛል ምናምን... ሲኖረኝ ደግሞ ደስ ይለኛል። በቃ ረሃ መሆን ነው ይሄ ጭንቅ መተሳሰር ምናምን ሚባል ነገሮችን አልወድም ሁሌ ፍሪደም (ነፃ መሆን) ነው የምሻው ኢንሻአላህ! እንደዛ እንድንሆን

#ሂባ: ግጥም ላይ የዳበረ እውቀት እንዳለህ ይነገራል። ስነ ፁሁፍ ለሪያድ ምን የተለየ ነገር አለው? በዚሁ አጋጣሚ ከሰሞኑን መፀሃፉ የማሳተም ጭምጭምታ ደርሶኛል እውነት ነው?
#ሪያድ: የዳበረ እውቀት ይኑረኝ አይኑረኝ የግጥም አንባቢዎቼ ናቸው ይህን ነገር ሊፈርዱ የሚችሉት። እኔ መግጠም እወዳለሁ እሞክራለሁም። ስነፁሁፍ ለኔ የተለየ ነገር አለው። የህይወቴ ትልቅ ቦታ ነው፣ ህይወቴም ነው፣ ህይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ከጠያቂ በቀር የሚያውቀው ያለ አይመስለኝም። እና መፅሀፍ የማሳተም ጭምጭምታ ሳይሆን አንድ አሳትሜያለ፣ <ኢንቢያ> የተሰኘች የግጥሞችና የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነች 2007 የታተመች አለች። ከዛ ባሻገር አላህ ካለ በቅርቡ <የመራመድ እውነት> የተሰኝ ግጥም መደብልና የሃሳብ ማዕድ የያዘች መፀሃፍ ወደ ተደራሲያን የማደርስ ይመስለኛል። ከዛ ባሻገር ደግም <ኢክራም ናፍቆት> የተሰኘ በፊልስጢም ታሪክ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን የረዥም ልብወለድ ስራ የተሰራ ነው። መታረም ብቻ የሚቀራቸው ናቸው። <አድል ሰአት> የአጭር ልቦለድም... በተከታታይነት ይወጣሉ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው። የገንዘብ ምናምን ችግሮች ይኖራሉ እነሱ ነገሮች ተሟልተው ሁሉም ወደ አንባቢያን እነደሚደርሱ እምነቴ ነው።

#ሂባ: ጥበቃችንን ጉጉት ያዘለ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት በቶሎ እንድታደርሱልን ምኞታችን ነው እንደው ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት ካለ መድረኩን ልልቅቅልህ
#ሪያድ: ሂባ በጣም ነው የማመሰግነው።
ያው የተለየ ሃሳብ የለውም ግን ይጠቅማል ብላቹ ያላቹትን ትንሽም ብትሆን ውሰዱ ካልሆነ ተውት ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ!
160 views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:45:04 ከእንግዳ ጋ
( ሂባ ሁዳ)

መወደድ የተወፈቃቸው ከላይ ሁኖ....ትዕዛዙን ሊፈፅሙ ...የራስ ስጋን ያኽል ነገር ሊያርዱ ስለት ማጅራቱ ላይ ሲያሳርፉ....ጀነት የደለበው በግ ምትክ ሁኖ ሲቀረብ! እኛም እቺን ክስተት እንዘክር ዘንዳ የዛሬዋ ቀን ላይ ላደረሰን ጌትዬ ሃምድ ይድረሰው። ገደብ...ስፍር.. ቁጥር የሌለው እዝነትና በረከት ለናንተ ውድ የሁዳ ቻናል ቤተሰቦቻችን ያውርድልን። አሚን እያልን

እነሆ ከተለመደው አጥር ያለ ቆይታ ወጣ ብለን፤ ሰፋ ያለ ጊዜን ወስደን፤ ለዛሬ ተመራጭ ካደረግነው እንገዳ ጋ የሰከነ ቆይታ እያደረግን፤ ከህይወት ባህሩ እየጨለፍን፤ የምንኮመኩምበት ሰአት ላይ ደርሰናል፤ እስከ ፕሮግራማችን ፍፃሜ አብራቹን እንድትቆዩ ግብዣዬ ነው። ወደ እንግዳዬ...

#ሂባ: ፕሮግራማችን ከመጀመሩ በፊት እንደ ህይወት ውድ ከሆነ ጊዜ ላይ ከእኛ ጋር ሰዐታትን ለማሳለፉ እንዲሁም የጊዜህ ተካፋይ ስላደረከን በራህማኑ ስም ላመሰግንህ እወዳለሁ። አህለን ራስህን በማስተዋወቅ ጀምርልን...
#ሪያድ እኔም እንግዳቹ አድርጋቹ ስለጋበዛቹኝ አመሰግናለሁ፤ አላህ ያክብርልኝ። ሙሉ ስሜ ሪያድ አብድልጀባር ይባላል። የተወለድኩት ሀረርጌ የሚባል ደዳር ቆቦ የምትባል አከባቢ ውስጥ ነው። ከዛ በኃላ በ3 አመቴ አዲስ አበባ መጥቼ ኑሮዬን ጀምሬ መስርቻለሁ አልልም ኑሮዬን አስመስርተውኛል ያው ቤተሰቦቼ። እንግዲህ ይሄን ይመስላል ዱኒያ ግን በጥሩ ሁኔታ ተቀብላኛለች አልሀምዱሊላህ።

#ሂባ: ሚዳድ የኑን ቁርአን መድረክ አዘጋጅ ነህ፤ እንዴት ነው ያልተለመደ ስራ ላይ መገኘት ውጣ ውረዶች ምን ይሁኑ? ትንሽ ስለ ፕሮግራሙ አላማ እንዱሁም ይዘት ብታብራራልን እንወዳለን
#ሪያድ: መልካም! ኑን የቁርአን መድረክ በርግጥ ያልተለመደ እና አዲስ ስራ ይዞ የመጣ ነው፤ ይሄ ደሞ ትንሽ ቻሌንጅ ነበረው። አሁንም ወደ ማህበረሰቡ ጉዳዩን ለማስረፅ በጣም አድካሚ እና አዳጋች ነገሮች ይኖሩታል፤ ቢሆንም ግን ሁሉንም ነገር ተቋቁመን ማሳለፍ መርጠናል፤ ምክንያቱም የያዝነው የቢዝነስ ነገር አደለም፤ የያዝነው ትልቅ አላማ ነው! ትውልድ መቅረፅ ነው የምንፈልገው እና በተለይ ማህበረሰባችን እንደማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዝቅ ያለበት ምክንያት ከቁርአን የመራቁ ችግር ነው። ስለዚህ ወደቁርአን መቅረብ ይኖርበታል፤ ማህበረሰቡ ከቁርአን ጋር ትውውቅ ማድረግ ይኖርበታል፤ ወደ ቁርአን የቀረበ ማህበረሰብ ደሞ ለድል ለታላቅነት የቀረበ ነው። ስለዚህ ኢንሻ አላህ በቁርአን የሚልቅ፣ በቁርአን የሚበረታ፣ በቁርአን ትልቅ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችል ትውልድ መፍጠርና በመላው አለም ላይ መደቆሳችን አብቅቶ ቀና ቀና የሚል ትውልድ እንዲፈጠር ነው። እንግዲህ ከወንድሞቼ ጋር በጋራ ሆነን ኑን የቁርአን መድረክን ማዘጋጀት ጀመርን፤ እንዳልኩሽ እንደዚህ አይነት አላማ ተይዞ መንገድ ሲገባ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነገሮች አሉ። በተለይ እንደኔ ያለ ወጣት ከፈይናንስም ከምንም አኳያ ብዙ ቤዝ የሌለው ሰው በጣም ይቸገርበታል። ቢሆን ሁሉ ነገር ተቋቁመን ፕሮግራሙን ለማስኬድ እየሞከርን ነው፤ እስካሁን የመጡልን አስተታየቶች ደግሞ እንድንበረታ ተግተን እንድንጥር የሚያበረታቱ ናቸው። እናም የተሻለ ደረጃ ላይ እንድንደርስ ደሞ ዱዐ እንዲደረግልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

#ሂባ: ለዱዐ እንኳን አናንስም ኢንሻአላህ!
በአሁኑ ሰአት ያንተ የስራ ድርሻ ምንድነው? እንዲሁም በስራህ ኢስላምን እያገለገልኩ ነው ትላለህ?
#ሪያድ: በአሁን ሰአት እየሰራሁ የምገኘው ሱና መልቲሚዲያ ወይም የዳዕዋ ቲቪ ፕሮዳክሽን ላይ ኤዴቲንግ እና ግራፊክስ ሶሻል ሚዲያ ማኔጂንግ እየሰራሁ ነው። ስለዚህ ኢስላምን እያገለገልኩ ነው ብሎ መናገር ለኔ በጣም ድፍረት ነው የሚሆንብኝ ምክንያቱም ኢስላም እኛን ያገለግለናል እንጂ እኛ ኢስላምን አናገለግልም። ስለዚህ ኢስላምን እያገለገልነው ሳይሆን በኢስላም እየተገለገልን ነው፤ ነብሳችንን ያያረጋጋል እንደዚህ አይነት ቦታ መዋል በእራሱ ለምሳሌ እኔ እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ ዳዕዋ ትምህርት ሳደርስ እኔም በዛው እየተማርኩ ነው ብዬ ነው ማስበው እንጂ ኢስላምን መካደም ደረጃ ላይ ደርሻለው ብዬ አላስብም... አላህ ግን ኢስላምን ከሚካድሙ እንዲያረገኝ ዱአ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ
#ሂባ: ሁላችንን ያድርገንማ! ባንተ ህይወት ውስጥ ስኬት፣ ደስታ፣ ህልም ምን ይሁኑ?
አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል አልያም ያበቃኛል ብለህ የምታስበው ካለ እንደው ብታወጋን
#ሪያድ: ስኬት፣ ደስታ ያው ሁሉም ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር የተያያዙ ናቸው። ለኔ ትልቁ ስኬት ብዬ የማስበው የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው፤ ትልቁ ነገር እሱ ነው እሱ ከተሳካልን ደስታውም ስኬቱም እሱ ውስጥ ነው፤ አልማለው የአላህን ውዴታ እና ከረሱልን ጎረቤት መሆን፣ ይሄ ህልሜ ይሳካል ብዬ አስባለው እሱ ከተሳካ ደስተኛ እሆናለው ብዬም አስባለው፤ ተያያዝነት አላቸው አንድ ሰው ያለመው ነገር ከተሳካለት ስኬታማ ሆነ ይባላል፤ የተሳካለት ነገር ሲያጣጥም ደሞ ደስተኛ ይሆናል ማለት ነው። የኔ ህልም የአላህ ውዴታ ማግኘት ነው፣ ስኬቴም የአላህን ውዴታ ሳገኝ ነው ማለት ነው። እሱን በማገኘት የማገኘው ደስታ ደሞ በምንም አይተመንም አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል። እ.. በነገራች ላይ በልጅነቴም በማንኛውም ስራ ላይ ኒያ .. ለምሳሌ እኔ ልጅ ሆኜ ፁሁፍ መፃፍ፣ ወደሚዲያ አካባቢ ያሉ ስራዎችን መስራት አልም ነበር። አሁን እያንዳንዱ ህልማችን ለምንድነው የታለመው የሚለው ነገር ይወስነዋል። እኔ አላህ ኢኽላሱን ይወፍቀኝና አንደኛው ህልሜ ኒያዬ ቢሆንልኝ አላህ ኒያህ እንደዛ ነው ብሎ ቢመዘግብልኝ ደስ የሚለኝ.. ለምሳሌ እኔ መፅሀፍ ስፅፍ አላህ ይወድልኛል አላህን አስደስታለው ብዬ የሱን ውዴታ አገኝበታለው ብዬ የምሰራው ስራ እንዲሆንልኝ እመኛለው።

#ሂባ: አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል አልያም ያበቃኛል ብለህ የምታስበው ካለ ብታወጋን...
#ሪያድ: ማንኛውም ስራ እንዳልኩሽ ትልቁ ግቤ የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው። በዚህ ውስጥ ጥቃቅን ያሳካሁት ስኬት አለ በ18 አመቴ መፅሀፍ ማሳተም ፈልግ ነበር አሳክቼዋለው፤ ምሩቅ ባልሆንበትም በትምህርት ገበታ ገብቼ ትምህርቱን ባልከታተልም ጋዜጠኝነት አከባቢ መስራት ፈልግ ነበር ወደዛም አከባቢ አላህ አቃርቦኛል። ስለዚህ ደራሲ መሆን ፈልግ ነበር፣ ደራሲነትም ሰጥቶኛል፤ ገጣሚ መሆን ፈልግ ነበር ገጣሚነቱን አላህ ሰጥቶኛል፤ እነዚህ በጣም በልጅነቴ በጣም ማስብባቸው የምተጋላቸው ነገሮች ናቸው። ከዛ ባሻገር ደግሞ ከኮንስትራክሽን ጋር በተያያዘ ህልም ነበረኝ እሱንም ቢሆን ተመርቄበታለው። ስለዚህ ትልቅ ተፅእኖ አለው፤ በልጅነታችን ምናስበው ዋጋ ምንከፍልበት ነገር አብቦ እንደምናየው ምንም አይነት ጥርጥር የለውም እና በተወሰነ ደረጃ ተሳክቷልኛል ብዬ አስባለው። ሌላው ደሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑን አለ ...ኑር የቁርአን መድረክ እሱም እንደዚሁ ነው የታቀደ የታለመ ነገር ነው። የተሳካም ይመስላል አልሀምዱሊላህ ረቢል አለሚን! ከዛ ባሻገር ሰፋ ብለን ከወንድሞቼ ጋር የምናስባቸው ነገሮች አሉ፤ እነሱም የጊዜ ጉዳይ ነው አንድ ጊዜ ይሳካሉ ብለን እናምናለን ኢንሻ አላህ!

#ሂባ: ኦውው ማሻአላህ ዘርፈ ብዙ ባለሙያ ነህ።
ወጣትነትህ በስራህ ና በዲንህ ላይ ምን ተፅዕኖ ፈጥሮብሃል?
161 views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:40:02 #ሪዛል:- <<ሱብሃነላህ ሁኔታው በምናብ ለመሳል እንኳን የሚከብድ አንጀት የሚያላውስ ነበር .... እኛስ ለራህማኑ ምን ያህል ታዛዥ ነን?>>
#ያስ:- <<ልክ ነሽ... የቅንጭቡ ማብቂያ ላይ ስለታዛዥነት የሰፈረው አገላለፅ ሁላችንንም ለታዘዝናቸው ቀላል ዒባዳዎች ያለንን ምላሽ የሚያስዛዝንብን ይመስለኛል ።....ኢላሂ ለሁላችንም ገደብ የሌለውን መውደድና ታዛዥነት ይስጠን ።>>
#ሪዛል:- <<አሚን ...

እንግዲ አንባቢያን ጥያቄው ያነበባቹትን ይመስላል.... ቀድሞ የተወሰደበትን መፅሃፍ ስም ለሚነግረን አንባቢ የአረፋ ሽልማታችንን የምናደርስ ይሆናል ማለት ነው።>>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★
#ነጃት:- <<እኔ መመለስ እችላለሁ? >>
#ረያን:- <<አትሸለሚም እንጂ አዎ >>

#ነጃት:- <<ተዉታ >>

#ሂባ:- <<ያስ >>
★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ያስ:- <<ሰደቃችንን ሳታወጣው ወደ ቀጣዩ መሰናዶአችን ብናልፍስ ሪዙ? >>
#ሪዛል:- <<ግድ ነው ....

ውድ አንባቢያን.... ቀጥሎ ከማስታወቂያው ጀምሮ ስትጠብቁት፣ ዝግጅቱ ከጀመረ ጀምሮ ደግሞ ስናስጠብቀው የቆየነውን እንግዳችንን ወደ መድረክ እንጋብዛለን ። ከሂባ የ"ከእንግዳ ጋር" ዝግጅት ጋር መልካም ቆይታ ተመኘን.... እስከምንመለስ አብራቹን ቆዩ... >>

@Re_ya_zan
171 views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:35:02 ከመፃህፍት መንደር
(በTeam huda)

አሰላሙ ዐለይኩም ውድ የሁዳ ቤተሰቦች ። ስለዓረፋ ሲነሳ ተያይዞ የማይረሳው የአባታችን ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ታዛዥነት ሁላችንም ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። በሰዓቱ አባት ልጁን ለማረድ ሲወስን የሁኔታው ከባድነት አያጠራጥርም። ነገር ግን የኢስማኢል (ዐ.ሰ) ምላሽስ ምን ሆኖ ይሆን? እርዱ እንደሚፈፀም እርግጠኛ በሆኑበት ቀፅበት የተናገሩት የመጨረሻ ንግግራቸው ምን ነበር? ዛሬ.... ታዛዥነትን ከሳቸው አንፃር እናየው ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ ጋበዝናቹ....

.........

{...... የኢስማኢል የመታረጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ አባታቸውን እንዲህ በማለት መከሩ።

"አባቴ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ:-

~እጆቼን ና እግሮቼን አጥብቀህ እሰራቸው። ስቃይ ሲበረታብኝ እንዳላስቸግርህና የጌታዬን መብት እንዳላጎድል ይረዳኛል።
~ደሜ እንዳይረጭብህ ልብሶችህን በደንብ ሰብስብ።
~ቢላዋው በደንብ ሳለው፤ ነብሴ ቶሎ እንድትወጣ አንተም ቶሎ እንድትገላገል።
~ልብሴን ይዘህ ወደ እናቴ ሂድ ለመፅናናት ይረዳት ይሆናል።"

ኢብራሂም(ዐ.ሰ) አነዚህን ቃላት ከልጃቸው አንደበት ሲሰሙ ዓይኖቻቸው በእንባ ተሞሉ።አብዝተው አለቀሱ። እንዲህ አሉ:-

"የአላህን ትዕዛዝ እንድፈፅም ምን ያህል አገዝከኝ?" ቀጥለው እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ዱዐ አደረጉ:-

"ጌታዬ ባለሁበት ሁኔታ ትዕግስትን አላብሰኝ! እንግዲህ ምንም አልቀረኝም። አርጅቻለሁና እዘንልኝ!"

ኢስማዒልም አሉ:-

"ጌታዬ ትዕግስትንና ፅናትን አላብሰኝ። አባቴ ሆይ የጀነት በሮች ተከፍተዋል።"

መላኢካዎች በነገሩ ግራ ተጋብተው ተደናግሯቸው ሱጁድ በመውረድ አላህን ይማፀናሉ። <<ጌታችን ሆይ! ነብይህ ያንተን ፍቃድ ሊሞላ ለመሰዋት ተጋድማል!... እዘንላቸው >>ይላሉ።

"አባቴ! ከፍቅር ማሳያዎች አንዱ አለመዘግየት ነው! በላ የታዘዝከውን ቶሎ ፈፅም!" }

ቅንጭቡን እንተመከራቹበትን እናምናለን። አያይዛቹ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክሩ...

........<<ከላይ የሰፈረልን ቅንጭብ ከየትኛው መፅሃፍ የተወሰደ ነው?>>

ቀድሞ ለመለሰ አንባቢ የዒድ ሽልማታችንን የምናደርስ ይሆናል....

መልካም እድል.....ዒዱኩም ሙባረክ

@Re_ya_zan
174 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:30:09 #ያስ:- <<ማሻአላህ ደስ የሚል ዝግጅት ነበር.... የራሳችንን ጉድለቶች ያንፀባተቀልን ይመስለኛል >>
#ሪዛል:- <<ሀቅ ነው.... ኢላሂ ባነበብነው የምንሰራ ያድርገን። የየቲሞችና የደካሞችን ሃቅ ከማጉደል ይጠብቀን.... >>
#ያስ:- <<አሚን .... የማንበብ ልምዳችንንም ያለምልመው! ከቴክኖሎጂው መራቀቅ ጋር ብዙ መፅሃፍትን የማንበብ ልምድ እየጠፋ ይመስላል... >>
#ሪዛል:- <<ሳህ ልክ ነሽ.... ኢስላማዊ መፅሃፎች በብዛት እየታተሙ ቢሆንም ተጠቃሚው ያን ያህል አይደለም ። ለምን በቀጣዩ ዝግጅታችን ይሄን እውነታ አንፈትሸውም?>>
#ያስ:- <<ኸይር ነበር.... ግን እህት ሂባ እንግዳዬን ብዙ አስቆማቹብኝ እያለች ነው.... >>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ሂባ:- <<እህእ¡ ኧረ በጣም... >>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ሪዛል:- <<ሃሃህ .... አንባቢያንም የእንግዳ ዝግጅታችንን በጉጉት እየጠበቁት መሆኑ አያጠራጥርም። ወደዛ ከማለፋችን በፊት ግን በመፃህፍት መንደር አጠር ያለ ጉዞ አድርገን ስለምንመለስ ትንሽ መታገስ ይኖርባችኋል... >>
#ያስ:- <<ሃሃህ መርሃባ .... ተመልካቾቻችን ቀጣዩ የመፅሃፍት መንደር መሰናዶአችን ነው፤ አብራቹን ቆዩ... >>

@Re_ya_zan
177 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:25:06 የዒድ ውሎ - [በእውነተኛ ታሪክ ተመርኩዞ የተፃፈ]
:
(ᴛᴇᴀᴍ ʜᴜᴅᴀ)
.
የአመቱ ምርጥ ቀን ኢድ ለመንጋቱ ማስረጃ የሱብሒ አዛን ከአቅራቢያችን መስጂድ ተሰማ። 'አስማ' ውድ ልጄንና ባለቤቴን ከቀሰቀስኩ በኋላ ወደመታጠቢያ ቤት ገባሁ። ተጣጥቤ ከሰገድኩ በኋላ የልጅነት ማስታወሻዬን ለአፍታ ስከፍት የያዘኝ ከሕፃንነቴ በአንዱ ያሳለፍኩት የአረፋ ውሎዬን የከተብኩበት ገፅ ነበር።

*
*
አርብ 16/02/2005

ቤቱ ውስጥ በሚሰማው ጫጫታ ብቻ የኢድ ቀንን የሚለይ ሰው ካለ እኔ ነኝ። ኢድ ለኔ የአዘቦት ቀን ነው። ከተራው ቀን የሚለየው በብዛት ፎቶ በመነሳቴ ብቻ ነው። ካለንበት የወንዶች ክፍል በተቃራኒ ያለው የሴቶች ማደሪያ ክፍል ከወትሮው በተለየ ይናወጣል።

<<ሒጃቤን የት አደረጋችሁት?>>
<<ጫማው አንድ እግሩ የለም!>>
<< ለእናት ሐፍሳ ነው የምናገረው የእጅ ጌጤን ሰበራችሁት።>>
ሁሉም ያለ መሰማማት ይጮሀል። ኢድ እስክንሰግድ እንጂ ከዛ በኋላ ቀና አሳቢ መሳዮች ሲዘይሩን በተራቸው እነሱ ያውኩያ እኛ ተመልካች እንሆናለን። እዚህ ማሳደጊያ አራት ወንዶች ና ሰባት ሴቶች አለን። እናት ሐፍሳ የሁላችንንም መሻት ለመሙላት ትጥራለች። እጅ አጥሯት ስታዝን ሳይ ምነው ኢድ ባልኖረ እላለሁ። ልጆቿም ለመመፃደቅ ካልሆነ ዞር ብለው አያዩንም እንዲያም ሆኖ እናታችን ናት።

የወንዶች መሔጃ ባስ ሲመጣ ከሴቶቻችን ጋ መለያየት ግድ ሆነ። እስከ መሐል ከተማ በባስ ሔደን ከዛ ተልቢያ እያልን በእግር ጉዞ ጀመርን። አትዋሽ አትበሉኝና ከኢድ ብቸኛው የሚስበኝ ቦታ ይሔ ነው። የሙት ልጅ ሳልባልና ከንፈር ሳይመጠጥልኝ ከሰው እኩል ተስተካክዬ 'አላሁ አክበር' የምልበት።
የኢድ ሰላትን ከሰገድን በኋላ ኹጥባ ለማድመጥ ዘግየት አልን። ዙሪያዬን ቃኘሁ እንደተለመደው ሁሉም ኹጥባውን ትቶ ወደቤቱ መሽቀዳደም ያዘ።
<<እርድ ስላለባቸው ነው ኮ ዩሱፌ>> ይለኛል ታላቅ ወንደሜ ሐሰን። የሚያርዱትም ባይኖር መሔዳቸው አልቀረ። ኹጥባውን አድምጠን ወደ ባሳችን ተመለስን።
<< እናት ሐፍሳ ደውላ ነበር። ቤት ደርሰው በዛው ከነፈትሑዲን(የእናት ሐፍሳ የመጨረሻ ልጇ ነው) ጋር ይመጣሉ።>> ሲል የሁላችንም ታላቅ የሆነው ሐምዛ ነገረን። እናት ሐፍሳና ቤተሰቦቿ እስኪመጡ ቤት(ማሳደጊያው ውስጥ) ያዘጋጀነውን ዳቦ አቅርበን አፈጠርን።

ግቢ ተንኳኳ። ቀኑን ሙሉ እንዴት አረፈዱ ስንል የጠበቅናቸው ዘያሪዎቻችን... ከፊት ያለው ሰልፊ ስቲኩን ይዞ ቀድሞ ገባ። ሌሎቹ ዳቦ ለስላሳና ሌሎች ነገሮችን ተሸክመዋል። ሴቶቹ በእናት ሐፍሳ በኩል ሲደረደሩ ወንዶቹ ያለችን አዳፋ ሶፋ ላይ ተደረደሩ። ከኛ ይልቅ እነሱ የተራቡ ይመስላሉ። ገና ከመግባታቸው ሱፍራ ዘርግተው ምግቡን በሰሐን ካቀራረቡ በኋላ መብላት ጀመሩ። የረሐብ ስካራቸው ሲበርድ ካመጡት ለስላሳ ያስቀሩትን በአይኔ ቃኘሁ። ሶስት ያልተከፈተ ና አንድ የተጀመረ ጠርሙስ። ግቢውን ከፍቼ ወጣሁ። በሩ ላይ የመመገቢያ አዳራሽ ይል እንደሁ ብዬ። የለም!
የእናት ሐፍሳ ማሳደጊያ እንደሆነ የሚገልፀው ወረቀት ከዝናብ ብዛት በስብሶ ቀለሙን ለቋል። ሌላ የለም!

ተመልሼ ስገባ በር ላይ ሐምዛን አገኘሁት።
<<የሆነ ነገር ፈልገህ ከሆነ ብዬ ነበር። ለምንድነው የወጣኸው ዩሱፍ?>>
<<ስማማ ወንድሜ ሐምዛ፣ የኛ ቤት ኢድ ኢድ ላይ ብቻ የመመገቢያ አዳራሽ ይሆናል እንዴ? ለምን ቤታቸው አይበሉም?>> አይኑን እያየሁ ጠየቅኩት። የሴቶቹ ሳቅ ሙሉ ግቢውን እያወከ ስለነበር ወደአንድ ጥግ ጎተት አድርጎኝ እንዲህ አለኝ
<<ስማ ዩሱፍ ገና የአስራሁለት አመት ልጅ ነህ። ይህን ሰዎች የሚያደርጉት መልካም አስበው እንደሆነ ብቻ እወቅ እሺ። ደሞ እንግዶቻችን ፊት እንዲህ ብትል...ዋ! እናት ሐፍሳ ታዝንብናለች። በል ና እንግባ።>> እጄን ይዞኝ ወደ ቤት ገባን። ስንገባ ግን ጭራሽ ቪዲዮ ላይ ናቸው፣ የስልኩ ፍላሽ (መብራት) አህላም ላይ እየበራ ስለነበር እንባዋ ይፈሳል። የsolar አለርጂኳ እንደተነሳ ስለገባኝ እንደምንም እያራመድኳት ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ። የዛሬ አመት በር ላይ ተጥላ ካገኘኋት ጀምሮ እየተባባሰ የመጣ የአይን ሕመም አለባት። በጠብታ እያስታገስን ነው እስካሁን ያቆየነው። እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርጋት ወደ ሳሎን ተመልሼ መጣሁ። ሊወጡ አካባቢ ነው መሰለኝ፣ የመጨረሻ ፎቶ ብለው ደረደሩንና አበሩብን። የባለካሜራውን እጅ ነክሼ ተመልሳችሁ አትምጡ ማለትን ወደድኩ። ተንኮሌ የገባው ሐሰን በአይኑ ጎሸም ባያረገኝ ኖሮ...!

እናት ሐፍሳ ልቧ ቀና ነው። እስከበር ድረስ የምስጋና ናዳ እያወረደች ከሸኘቻቸው በኋላ የበሉበትን የሰሐን ክምር ከሴቶቹ ጋር ለማጠብ ወደጓሮ ሔደች። ወንዶቹ ደሞ እንደ ፈረቃችን ቤቱን ስንጠርግ መግሪብ ደረሰ። ከሐሰን ጋ ወደ መስጂድ ወጥተን ስንመለስ እንዲህ አለኝ፦
<<ሰዎች ሶስት አይነት ናቸው። እንደ እናት ሐፍሳና እንደቅድሞቹ ወንድሞቻችን እና እንደሌሎቻችን። ሳይኖራቸው ግን የሚሰጡ፣ ቢኖራቸውም ለመስጠት ወደ ኋላ የማይሉ አሉ። ኖሯቸው ደሞ ሲሰጡ የሚሳሱ ና ለታይታ የሚቸሩም አሉ። ተራርፏቸው ግን አላህ በቀልባቸው የመስጠትን ኒእማ ስለነፈጋቸው ብቻ የማይሰጡም አሉ። አንተ ታዲያ አርአያ የምታደርገው አላህ የሚወደውን እንጂ ስላደረሱብህ ለመበቀል የሚያነሳሱህን አይደለም። ገብቶሀል አይደል?>>
<<አዎ እንደእናት ሐፍሳ እሆናለሁ። ትልቅ መኪና እገዛላትና እንደኛ አይነቶቹን ሰብስቤ እንደእናታችን እንዲሆኑ መክራቸዋለሁ።>> ከልቤ ደስ እያለኝ ነበር ያልኩት። ሊመፃደቁ እጃቸውን ሲዘረጉላቸው ላዘኑት መፅናኛ ሆናለሁ።
*
*
*
<<አልሐምዱሊላህ ለዚህ ላደረስከኝና ቃሌን ሞልቼ የእናት ሐፍሳን ማሳደጊያ እንዳስፋፋ ለረዳኸኝ>> ከማለቴ ባለቤቴ ወዳለሁበት ተጠግታ <<ዩሱፌ እናት ሐፍሳ አንተን በማሳደጓ አትርፋለች>> ስትል ግንባሬን ሳመችኝ።

ኢድ ሙባረክ በድጋሚ

@Re_ya_zan
198 views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ