Get Mystery Box with random crypto!

ከእንግዳ ጋ ( ሂባ ሁዳ) መወደድ የተወፈቃቸው ከላይ ሁኖ....ትዕዛዙን ሊፈፅሙ ...የራስ ስጋን | TEAM HUDA

ከእንግዳ ጋ
( ሂባ ሁዳ)

መወደድ የተወፈቃቸው ከላይ ሁኖ....ትዕዛዙን ሊፈፅሙ ...የራስ ስጋን ያኽል ነገር ሊያርዱ ስለት ማጅራቱ ላይ ሲያሳርፉ....ጀነት የደለበው በግ ምትክ ሁኖ ሲቀረብ! እኛም እቺን ክስተት እንዘክር ዘንዳ የዛሬዋ ቀን ላይ ላደረሰን ጌትዬ ሃምድ ይድረሰው። ገደብ...ስፍር.. ቁጥር የሌለው እዝነትና በረከት ለናንተ ውድ የሁዳ ቻናል ቤተሰቦቻችን ያውርድልን። አሚን እያልን

እነሆ ከተለመደው አጥር ያለ ቆይታ ወጣ ብለን፤ ሰፋ ያለ ጊዜን ወስደን፤ ለዛሬ ተመራጭ ካደረግነው እንገዳ ጋ የሰከነ ቆይታ እያደረግን፤ ከህይወት ባህሩ እየጨለፍን፤ የምንኮመኩምበት ሰአት ላይ ደርሰናል፤ እስከ ፕሮግራማችን ፍፃሜ አብራቹን እንድትቆዩ ግብዣዬ ነው። ወደ እንግዳዬ...

#ሂባ: ፕሮግራማችን ከመጀመሩ በፊት እንደ ህይወት ውድ ከሆነ ጊዜ ላይ ከእኛ ጋር ሰዐታትን ለማሳለፉ እንዲሁም የጊዜህ ተካፋይ ስላደረከን በራህማኑ ስም ላመሰግንህ እወዳለሁ። አህለን ራስህን በማስተዋወቅ ጀምርልን...
#ሪያድ እኔም እንግዳቹ አድርጋቹ ስለጋበዛቹኝ አመሰግናለሁ፤ አላህ ያክብርልኝ። ሙሉ ስሜ ሪያድ አብድልጀባር ይባላል። የተወለድኩት ሀረርጌ የሚባል ደዳር ቆቦ የምትባል አከባቢ ውስጥ ነው። ከዛ በኃላ በ3 አመቴ አዲስ አበባ መጥቼ ኑሮዬን ጀምሬ መስርቻለሁ አልልም ኑሮዬን አስመስርተውኛል ያው ቤተሰቦቼ። እንግዲህ ይሄን ይመስላል ዱኒያ ግን በጥሩ ሁኔታ ተቀብላኛለች አልሀምዱሊላህ።

#ሂባ: ሚዳድ የኑን ቁርአን መድረክ አዘጋጅ ነህ፤ እንዴት ነው ያልተለመደ ስራ ላይ መገኘት ውጣ ውረዶች ምን ይሁኑ? ትንሽ ስለ ፕሮግራሙ አላማ እንዱሁም ይዘት ብታብራራልን እንወዳለን
#ሪያድ: መልካም! ኑን የቁርአን መድረክ በርግጥ ያልተለመደ እና አዲስ ስራ ይዞ የመጣ ነው፤ ይሄ ደሞ ትንሽ ቻሌንጅ ነበረው። አሁንም ወደ ማህበረሰቡ ጉዳዩን ለማስረፅ በጣም አድካሚ እና አዳጋች ነገሮች ይኖሩታል፤ ቢሆንም ግን ሁሉንም ነገር ተቋቁመን ማሳለፍ መርጠናል፤ ምክንያቱም የያዝነው የቢዝነስ ነገር አደለም፤ የያዝነው ትልቅ አላማ ነው! ትውልድ መቅረፅ ነው የምንፈልገው እና በተለይ ማህበረሰባችን እንደማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዝቅ ያለበት ምክንያት ከቁርአን የመራቁ ችግር ነው። ስለዚህ ወደቁርአን መቅረብ ይኖርበታል፤ ማህበረሰቡ ከቁርአን ጋር ትውውቅ ማድረግ ይኖርበታል፤ ወደ ቁርአን የቀረበ ማህበረሰብ ደሞ ለድል ለታላቅነት የቀረበ ነው። ስለዚህ ኢንሻ አላህ በቁርአን የሚልቅ፣ በቁርአን የሚበረታ፣ በቁርአን ትልቅ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችል ትውልድ መፍጠርና በመላው አለም ላይ መደቆሳችን አብቅቶ ቀና ቀና የሚል ትውልድ እንዲፈጠር ነው። እንግዲህ ከወንድሞቼ ጋር በጋራ ሆነን ኑን የቁርአን መድረክን ማዘጋጀት ጀመርን፤ እንዳልኩሽ እንደዚህ አይነት አላማ ተይዞ መንገድ ሲገባ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነገሮች አሉ። በተለይ እንደኔ ያለ ወጣት ከፈይናንስም ከምንም አኳያ ብዙ ቤዝ የሌለው ሰው በጣም ይቸገርበታል። ቢሆን ሁሉ ነገር ተቋቁመን ፕሮግራሙን ለማስኬድ እየሞከርን ነው፤ እስካሁን የመጡልን አስተታየቶች ደግሞ እንድንበረታ ተግተን እንድንጥር የሚያበረታቱ ናቸው። እናም የተሻለ ደረጃ ላይ እንድንደርስ ደሞ ዱዐ እንዲደረግልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

#ሂባ: ለዱዐ እንኳን አናንስም ኢንሻአላህ!
በአሁኑ ሰአት ያንተ የስራ ድርሻ ምንድነው? እንዲሁም በስራህ ኢስላምን እያገለገልኩ ነው ትላለህ?
#ሪያድ: በአሁን ሰአት እየሰራሁ የምገኘው ሱና መልቲሚዲያ ወይም የዳዕዋ ቲቪ ፕሮዳክሽን ላይ ኤዴቲንግ እና ግራፊክስ ሶሻል ሚዲያ ማኔጂንግ እየሰራሁ ነው። ስለዚህ ኢስላምን እያገለገልኩ ነው ብሎ መናገር ለኔ በጣም ድፍረት ነው የሚሆንብኝ ምክንያቱም ኢስላም እኛን ያገለግለናል እንጂ እኛ ኢስላምን አናገለግልም። ስለዚህ ኢስላምን እያገለገልነው ሳይሆን በኢስላም እየተገለገልን ነው፤ ነብሳችንን ያያረጋጋል እንደዚህ አይነት ቦታ መዋል በእራሱ ለምሳሌ እኔ እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ ዳዕዋ ትምህርት ሳደርስ እኔም በዛው እየተማርኩ ነው ብዬ ነው ማስበው እንጂ ኢስላምን መካደም ደረጃ ላይ ደርሻለው ብዬ አላስብም... አላህ ግን ኢስላምን ከሚካድሙ እንዲያረገኝ ዱአ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ
#ሂባ: ሁላችንን ያድርገንማ! ባንተ ህይወት ውስጥ ስኬት፣ ደስታ፣ ህልም ምን ይሁኑ?
አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል አልያም ያበቃኛል ብለህ የምታስበው ካለ እንደው ብታወጋን
#ሪያድ: ስኬት፣ ደስታ ያው ሁሉም ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር የተያያዙ ናቸው። ለኔ ትልቁ ስኬት ብዬ የማስበው የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው፤ ትልቁ ነገር እሱ ነው እሱ ከተሳካልን ደስታውም ስኬቱም እሱ ውስጥ ነው፤ አልማለው የአላህን ውዴታ እና ከረሱልን ጎረቤት መሆን፣ ይሄ ህልሜ ይሳካል ብዬ አስባለው እሱ ከተሳካ ደስተኛ እሆናለው ብዬም አስባለው፤ ተያያዝነት አላቸው አንድ ሰው ያለመው ነገር ከተሳካለት ስኬታማ ሆነ ይባላል፤ የተሳካለት ነገር ሲያጣጥም ደሞ ደስተኛ ይሆናል ማለት ነው። የኔ ህልም የአላህ ውዴታ ማግኘት ነው፣ ስኬቴም የአላህን ውዴታ ሳገኝ ነው ማለት ነው። እሱን በማገኘት የማገኘው ደስታ ደሞ በምንም አይተመንም አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል። እ.. በነገራች ላይ በልጅነቴም በማንኛውም ስራ ላይ ኒያ .. ለምሳሌ እኔ ልጅ ሆኜ ፁሁፍ መፃፍ፣ ወደሚዲያ አካባቢ ያሉ ስራዎችን መስራት አልም ነበር። አሁን እያንዳንዱ ህልማችን ለምንድነው የታለመው የሚለው ነገር ይወስነዋል። እኔ አላህ ኢኽላሱን ይወፍቀኝና አንደኛው ህልሜ ኒያዬ ቢሆንልኝ አላህ ኒያህ እንደዛ ነው ብሎ ቢመዘግብልኝ ደስ የሚለኝ.. ለምሳሌ እኔ መፅሀፍ ስፅፍ አላህ ይወድልኛል አላህን አስደስታለው ብዬ የሱን ውዴታ አገኝበታለው ብዬ የምሰራው ስራ እንዲሆንልኝ እመኛለው።

#ሂባ: አሁን ላይ ለስኬት አብቅቶኛል አልያም ያበቃኛል ብለህ የምታስበው ካለ ብታወጋን...
#ሪያድ: ማንኛውም ስራ እንዳልኩሽ ትልቁ ግቤ የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው። በዚህ ውስጥ ጥቃቅን ያሳካሁት ስኬት አለ በ18 አመቴ መፅሀፍ ማሳተም ፈልግ ነበር አሳክቼዋለው፤ ምሩቅ ባልሆንበትም በትምህርት ገበታ ገብቼ ትምህርቱን ባልከታተልም ጋዜጠኝነት አከባቢ መስራት ፈልግ ነበር ወደዛም አከባቢ አላህ አቃርቦኛል። ስለዚህ ደራሲ መሆን ፈልግ ነበር፣ ደራሲነትም ሰጥቶኛል፤ ገጣሚ መሆን ፈልግ ነበር ገጣሚነቱን አላህ ሰጥቶኛል፤ እነዚህ በጣም በልጅነቴ በጣም ማስብባቸው የምተጋላቸው ነገሮች ናቸው። ከዛ ባሻገር ደግሞ ከኮንስትራክሽን ጋር በተያያዘ ህልም ነበረኝ እሱንም ቢሆን ተመርቄበታለው። ስለዚህ ትልቅ ተፅእኖ አለው፤ በልጅነታችን ምናስበው ዋጋ ምንከፍልበት ነገር አብቦ እንደምናየው ምንም አይነት ጥርጥር የለውም እና በተወሰነ ደረጃ ተሳክቷልኛል ብዬ አስባለው። ሌላው ደሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑን አለ ...ኑር የቁርአን መድረክ እሱም እንደዚሁ ነው የታቀደ የታለመ ነገር ነው። የተሳካም ይመስላል አልሀምዱሊላህ ረቢል አለሚን! ከዛ ባሻገር ሰፋ ብለን ከወንድሞቼ ጋር የምናስባቸው ነገሮች አሉ፤ እነሱም የጊዜ ጉዳይ ነው አንድ ጊዜ ይሳካሉ ብለን እናምናለን ኢንሻ አላህ!

#ሂባ: ኦውው ማሻአላህ ዘርፈ ብዙ ባለሙያ ነህ።
ወጣትነትህ በስራህ ና በዲንህ ላይ ምን ተፅዕኖ ፈጥሮብሃል?