Get Mystery Box with random crypto!

TEAM HUDA

የቴሌግራም ቻናል አርማ re_ya_zan — TEAM HUDA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ re_ya_zan — TEAM HUDA
የሰርጥ አድራሻ: @re_ya_zan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K
የሰርጥ መግለጫ

"أَفَلَا تَعْقِلُونَ"
"አታስተነትኑምን?"
አንብቡ! ራሳችሁን፣ በዙሪያችሁ ያሉትን ነገሮች፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ፅሁፎችን.... አንብቡ! አስተንትኑ! ጠይቁ!

Big thanks for joining!
All team huda!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 17:32:06
.
"እንባዎችም ጸሎቶች ናቸው...እኛ...መናገር በማንችልበት ጊዜ ወደ #አላህ ይጓዛሉ"
.
.
#መድ
@yeruh_weg
395 views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 21:23:33
....ከሰው ወደ ሰው የምትጋባን ፈገግታ የፈጠርክ ራህማን ጌታ.... ከሀሳብና ጭንቀት ነፃ የሆነችን ደስተኛ ነፍስን ወፍቀን

....ስለወደድኩት
....ውብዬ ምሽት...

መድ

@Yeruh_weg
1.5K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 12:07:33 #ካነበብኩት... - 4

የቢላል የጥንካሬ ምንጭ ምን ነበር?

ሚሥጥሩ ከአንዲት ሀሳብ የተቀዳ ነዉ፡፡ የሰዉ ልጅ እኩል ነዉ የሚለዉ የነብዩ ሙሃመድ (ሰዐወ) መልእክት ድንገት ሲወራ ሰምቶ ነዉ፡፡ ከመጤፍ የማይቆጠር ማንነቱ ክብር እንዳለዉ የሚናገር ሰዉ መልእክት ሲሰማ ወዲያዉ ከዉስጡ ተዋሃደ፡፡ ለአመታት በባርነት የገረደዉን ኡመያ ከልቡ ጠላ፡፡ በአረቢያ ስለሚሰማዉ አዲስ እምነት ጥበባትም ልቡ ተዘነበለ፡፡

"አስተዉል"

የተልፈሰፈሰ ወኔ ነበረዉ፡፡ ኡመያን ሲበዛ ይፈራዋል፤ ቁጣው ሁለመናዉን ነበር የሚያናጋበት፡፡ አሁን ግን እንደኡመያ የሚንቀዉ ሰዉ አልነበረም፡፡
ስለሰዎች እኩልነት የሚያዉጀዉን አዲስ አብዮት ከልቡ ተቀበለ፡፡ ስለመቀበሉም ዑመያ ሲሰማ እጅግ በንዴት ናረ፡፡ እንደወትሮዉ በፍርሃት ካባ ተጀቡኖ እየተንቀጠቀጠ ይጠብቀኛል ብሎ ቢያስብም ቢላል ልበ-ሙሉ እንደሆነ ቆመ፡፡ እንግዳ ነገር ያየዉ ዑመያም ተደናበረ፡፡

ትኩር ብሎ አየዉ፤ በቢላል ፊት ላይ ግን አንዳች ለዉጥ ሳይታይ ቀረ፡፡ ስለሰብዓዊ ዘሮች እኩልነት የሚያስተምረዉን የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጥበበ-ብርሃን መቀበሉን ሳያመነታ ነገረዉ፡፡ ቀና ብሎ ለማየት እጅግ ይንቀጠቀጥ የነበረዉ ቢላል ዑመያን ፊት ለፊት እያየ በዉስጡ ስለያዘዉ አዲስ ማንነት ሳይደብቅ ገለጠለት፡፡ ይህም እጅግ የከበደ ቅጣት አስከተለበት፡፡ ከ40 ዲግሪ ሙቀት በሚልቀዉ የአረቢያ አሸዋማ ሜዳ ላይ የገዘፈ አለት ሆዱ ላይ በመጫን ዑመያና ግብረ አብሮቹ ይገርፉት ጀመር፡፡ የግርፋቱ ምክንያት አዲስ የተቀበለዉን አስተሳሰብ (እምነት) እንዲተዉ ነዉ፡፡ ቢላል ግን ፍጹም አዲስ ሰዉ ሆነባቸዉ፡፡

ለብዙ ሆነዉ ከሚገፉት አለት በላይ የጠነከረ አቋም ያዘባቸዉ፡፡ የግርፋታቸዉ መጠን ሲጨምር የርሱም አቋም ይበልጥ እየጠነከረ መምጣቱ ግራ አጋባቸዉ፡፡ በመጨረሻም መግረፋቸዉ ሲያደክማቸዉ ከበረሃዉ ድንጋይ ሆዱ ላይ እንደጫኑበት ጥለዉት ሄዱ፡፡ ሲመለሱም ግን አቋሙን አልቀየረም፡፡

አዲስ በገነባዉ የዉስጥ ማንነቱ ጠነከረ፡፡ በየትኛዉም ዉጫዉ ተፅዕኖም ላይቀረይዉ ጸንቶ ቆየ፡፡ በመጨረሻ ከሞት ተርፎ ነጻ ወጣ፡፡ በዓለም የኢስላም ታሪክ ቀዳሚዉ የአፍሪካ ጥቁር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሙዓዚን በመሆን በወርቃማ ብዕር የታሪክ ቅጽ ላይ ሰፈረ፡፡

*

ዉጫዊ ማንነታችን ያድጋል ግን መሰረታዊ መልኩን አይለዉጥም፡፡ ከልጅነት ወደ እርጅና ጊዜ ጠብቀን እናዘግማለን፡፡ የመልካችን መሰረተ ምስል ግን ይታወቃል፡፡ በዚህ የአካላዊ (ባዮሎጂካዊ) ማንነታችን የምንፈጥረዉ ተፅዕኖ የለም፡፡ እንደተወለድን እናድጋለን፡፡ አንደግ ብንል ፈቃድ የለንም፤ ሞትም በመጣ ጊዜ አንሙት ብንል አንችልም፡፡ ሙሉ ነጻነት ያለን በዉስጣዊ ማንነታችን ላይ ነዉ፡፡

ደካማዉን ስብዕና ማጠንከር ይቻላል፡፡ ሰነፉን ማንነት ማጎበዝ ይቻላል፡፡ የሰዎች ስኬታማነት በዉጫዊ ገጽታቸዉ (አካላዊ ቅርጻቸዉ) አይወሰንም... በዉስጣቸዉ በሚገነቡት ጠንካራ መንፈስ እንጂ፡፡ ዉስጣችን እንዲጠነክር በፈተናዎች መከበብ አለበት። ምቾት ባለበት ሜዳ ጥንካሬ አይኖርም፡፡ ችግሮች ናቸዉ ወደ ምቾት ወይም የስኬት ከፍታ የሚያወጡን፡፡

____

በወንድም ሙሐ
መድ አሊ ቡርሐን ከተፃፈው የስኬት ፈለግ ቁጥር አንድ መፅሐፍ የተቀነጨበ

@Re_Ya_Zan
1.8K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 16:27:16 #ካነበብኩት -3

«እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በትእግስትና በሰላት ታገዙ።»
(አልበቀራህ:153)

ፍርሀትና መረበሽ ሲመጣብህ ወዲያውኑ ተነስና ስገድ፡፡ ነፍስህ ምቾትና እርጋታ ታገኛለች፡፡ ሶላትህን በተመስጦ እስከሰገድከው ድረስ ለውጥ እንደሚያመጣልህ ዋስትና ኣለው፡፡ ነቢዩ (ሲዐ.ወ) ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ “ቢላል ሆይ! አዛን አሰማና ገላግለን” ይሉ ነበር፡፡

ሶላት የአይናቸው ብርሃን፣ የደስታቸው ምንጭ ነበር፡፡ የብዙ ደጋግ ሰዎችን የህይወት ታሪክ አንብቤያለሁ፡፡ ችግርና መከራ በመጣባቸው ጊዜ ቁርጠኝነታቸውና መንፈሰ ጠንካራነታቸው እስኪመለስላቸው ድረስ ተነስተው ይሰግዱ ነበር፡፡

ጦርነት ላይ እጅና እግር ሲደክም፣ ጭንቅላቶች ሲበሩ፣ ነፍሶች ከስጋ ሲለያዩ የፍርሀት ሰላት ይታዘዛል፡፡ በዚህ ወቅት ጥንካሬ የሚመጣው ከልብ በመነጨ ሶላት ብቻ ነውና፡፡
ይህ በበርካታ ስነልቦናዊ በሽታዎች የተጠመደ ትውልድ ስግደት እንዲፈፅምና የአላህን ደስታ እንዲያገኝ ወደ መስጊድ መመለስ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኣይናችን በእንባ ይታጠባል፤ ልባችን በሀዘን ይቃጠላል፡፡

አምስት ወቅት ሶላቶችን በደንብ ከሰገድን ጌታችን ለሃጢያታችን ምህረቱን፣ ከጸጋዎች ሁሉ ትልቁን፣ ከደረጃዎች ሁሉ ከፍተኛውን ይሰጠናል፡፡ ሶላት ጥሩ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡ ምክንያቱም በልብ ውስጥ እምነትን ያንቆረቁራል፡፡ ከመስጊድና ከሶላት የራቁ ሰዎች ህይወታቸው በሀዘንና በምሬት የተሞላ ነው፡፡

“ለነሱ ጥፋት ተገባቸው፤ ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡” (47፡8)

“ለኛ በቂያችን አላህ ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ::” (3፡173)

ጉዳዮችህን ለአላህ ብትሰጥ፣ ወደሱ ብትጠጋ፣ ቃል የገባቸውን ነገሮች ብታምን፣ ባዘዘው ነገር ብትደሰት፣ እሱን ብትወድና እርዳታውን በትዕግስት ብትጠብቅ ትላልቅ የኢማን ፍሬዎችን ትቀጥፋለህ፤ የአማኞችን ደጋግ ባህሪያት ትይዛለህ፡፡ እነዚህን ጥሩ ነገሮች ወዳንተ ስታመጣ የወደፊቱን በተመለከተ ሰላም ታገኛለህ፡፡ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ለፈጣሪህ ትሰጣለህ፡፡ ውጤቱም እንክብካቤ፣ እገዛ ፣ ጥበቃና ድል ማግኘት ይሆንልሀል፡፡

ነቢዩ ኢብራሂም አለይሂ ሰላም እሳት ውስጥ በተደረጉ ጊዜ “ለኛ አላህ በቂያችን ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ' አሉ፡፡ ከዚየም አላህ እሳቷን ቀዝቃዛ፣ ምቹና ሰላማዊ እንድትሆን አደረገላቸው፡፡
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸው በጠላቶቻቸው አደገኛ ጥቃት በተቸገሩ ጊዜ ከዚህ አንቀፅ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቃላትን ነበር የተናገሩት፡፡

« በቂያችንም አላህ ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ። ከአላህም በሆነ ፀጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸው ሆነው ተመለሱ። የአላህንም ውዴታ ተከተሉ። አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።»
(አል ኢምራን:173-174)

የደረሰበትን ችግር በራሱ የመመለስ ችሎታ ያለው ሰው የለም። ምክንያቱም የሰው ልጅ የተፈጠረው ደካማና ልፍስፍስ ሆኖ ነው። ሆኖም በችግር ወቅት ሙዕሚን ሰው እምነቱንና መመካቱን በጌታው ላይ ይጥላል። ይህ ሲሆን ሁሉም ችግሮች ሊወገዱ እንደሚችሉ ያውቃልና፡፡

“ምዕመናን እንደሆናቹሁ በአሏህ ላይ ተመኩ::”
(5:23)

ለራሳችሁ ታማኝ ለመሆን የምትመኙ ሰዎች ሁሉ ከችግርና ከአደ ጋ ሊጠብቃችሁ በሚችለው በሀያሉ ጌታ ላይ ተመኩ፤ ህይወታችሁን በዚህ መርህ ኑሩ- ለኛ አላህ በቂያችን ነው፡፡ ምን ያምር መጠጊያ፡፡

_____

ተሕዘን ከሚለው የዶክተር ዓዒድ አልቀርኒ መፅሐፍ የተወሰደ! [በአማርኛው የምን ሐዘን በሚል በእህት ሐዲያ ሙሐመድ ተተርጉሟል!]

@Re_Ya_Zan
1.3K views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 10:25:18
አውስ ኢብኑ አውስ ረዲየላሁ አንሑ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም እንዲህ አሉ:-
«ከቀኖቻችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በኔ ላይ የምታወርዱት ሰለዋት ይቀርብልኛልና።»
:
አላሁመ ሰሊ አላ ሰይዲና ሙሐመዲን ወአላ አሊሒ ወሳህቢሂ ወሰለም!
:
ከእድፎቻችን ርቀን ከአላሁ የምንቀርብበት፣ ሐዘናችንን በሐሴት የምናፀዳበት የተዋበና ሰላም የሆነ ጁምዓ ለሁላችን ይሁን!

#ሸጋ_ጁምዓ!

@Re_Ya_Zan
1.1K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 06:00:24 ከሙሉነት ጥቂቱን...7
(Team Huda)
:
#ጀግንነት_ራሱኑ!!

ስለ እዝነትና ይቅር ባይነታቸው ስናወጋ ሌላኛው ጎናቸውሳ ማለታችን አይቀርም... ፍርሀት ማነው አይነት ጥያቄን የሚያስነሱ ጀግና መሆናቸውን በተለያየ የታሪክ ሁነት አንብበናል። ወደ መዲና ለመሰደድ ሲወጡ በራቸውን የከበቧቸውን ጎረምሶች በእንዴት ያለ ድፍረት ተሻገሩ? ያሲንን ቀርተው!! እዚህ ጋር ነው የምንተዛዘበው...ጀግንነት በጡንቻህ አለይለካም...በምላስሽ ስለፎከርሽ አይወለድም...በአካኪ ዘራፍ አይነቃነቅም...በርግጥም ጀግንነት ሙሉ የሆነ መወከልን በአሏህ ላይ በመወከል እንጂ ከዬት ይገኛል? ቃሉን በመያዝ እንጂ እኛ ላይ የተቃጣ ሸር ሁላ በምን ይከሽፋል?

የበድር ጦርነት ወቅት ጀግናችን የነበሩበትን ሀል ጀግናው ፈረሰኛ ዐሊይ ቢን አቡጧሊብ(ረዲየሏሁ አንሁ) ሲተርኩ፡
<የአሏህ መልእክተኛ ከሁላችንም ይበልጥ ለጠላት ቅርብ ነበሩ።ከሁላችንም በላቀ ጀግንነት ተፋልመዋል።እኛም ከጠላት ጥቃት በርሳቸው እንከለል ነበር።>
በራእ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) ሲለጥቁ
<በአላህ እምላለሁ አደጋ ሲበረታ በእርሳቸው እንከለል ነበር።ከመካከላችን በጣም ጀግናው ከእርሳቸው ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ነበር።>
ብለው ምስክርነታቸውን ሰደዋል...ጀግንነት በሳቸው በቃ!!


@Re_ya_zan
@Re_ya_zan
for any comment
@Teamhudabot
991 views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 06:01:57
ምስል#11
(Team Huda)

ለልጆቼ የማወርሰው ሃብት በዘመኔ አላከማቸሁም፤ ወጣትነቴን ለቤቴ ለኑሮዬ ማቃኛ የሚሆንልኝን ጥሪት አላከማቸሁም፤ ጀሊሌ መቼም ለባሮቹ ቅርብ ነውና እንደሰው የሚያስፈልገኝን አልነፈገኘም፤ የዕለት ሪዝቄን አያላሳጣኝም... "አልሃምዱሊላህ"
ለከርሞ መጠበቤ ያ አነበረም። ከልጆቼ አልፎ ለትውልዱ የማወርሰውን እውቀት በማሰባሰብ ላይ ቁዋውን ይችረኝ ዘንድ ነበር ሃሳብ ጭንቀቴ፤ ዱንያ መቼም ለዚህ ገር ባትሆንም ጀሊሉ ሰብሩን ሰጥቶኝ ከመንገዴ እንዳልፈናቀል በእዝነቱ ጠብቆኛል።
አሁን ስጋቴ በጭራሽ ያ አይደለም በእድሜ ማምሻ የሚደክሙ አይኖቼ ከዛሬ ነገ ኡማው ጋ ሳላደርስ እንዳላልፍ ነው... በኔ ላይ ያኖረውን ኢልም እንዴት ሳላወጣው ከኔው ጋ ይጠፋል..! ለዚህም ቀንከሌት አለይም...ምሽት አላውቅም..ንጋትን አልጠብቅም። እስካለሁ ከጠረቤዛዬ ተሰይሜ አደራዬን ለማውረስ እተጋለሁ ጀሊሌ ይቀበለኝ።

ባላደራ ሁኜ ሳለ እንዴት አደራዬን ሳላደርስ አይኖቼ ማንቀላፋት ይቻላቸዋል!

@Re_ya_zan
For any comment
@Teamhudabot
1.2K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 15:15:04 #ሪዛል:- <<ሰለዋቱ ሏሂ ወሰላሙሁ ዓለይህ ..... ኢንሻአላህ ሁላችንም የፍትህ አምባሳደሮች ሆነን ያስተማሩንን የምንተገብርበት ዒድ ይሆናል >>
#ያስ:- <<ኢንሻአላህ ...

ተመልካቾቻችን.... ለእለቱ ያሰናዳንላቹ የዒድ ዝግጅቶች ይሄን ይመስላሉ.... ወደ መሰነባበቻችን ተቃርበናል ...>>
#ሪዛል:- <<ከመለያየታችን በፊት ግን ውጤቶቹን ወደ ማሳወቁ እንለፍ ....>>
#ያስ:- <<መርሃባ.... እኔ ልቅደም አንቺ?....>>
#ሪዛል:- <<እንደጓጓሽለት አንቺው ጨርሺው... >>
#ያስ:- <<ኸይር እሺ....
ደረጃዎቹ ቅድም በከፊል እንደገለፅነው.... ሁሉንም ጥያቄዎች በመሳተፍ፣ በፍጥነት በመመለስና፣ ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብ ላይ መሰረት አድርገው የወጡ ናቸው።

ተሸላሚዎቻችን....
አንደኛ!... ከ 27ቱ 25 በማምጣት
BH

#ሪዛል:- <<ሁለተኛ!.... ከ 27ቱ 24 በማምጣት
Anayra ...>>

#ያስ:- <<ሶስተኛ!.... ከ27ቱ 21 በማምጣት
@Yenechereka

ናቸው ማለት ነው >>
#ሪዛል:- <<እንድናገኛቹ.... በ @teamhudabot ኣችን ላይ "አሰላሙ ዐለይኩም" ብላቹ በመላክ ሽልማቶቸችሁን መውሰድ ትችላላችሁ ። በዚሁ ወደ መለያያችን ደረስን ማለት ነው...>>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ሩሽዳ:- <<ወይ ሩጫ.... አስተያየቱን እንዳትረሱ >>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ያስ:- <<ከመውጣታችን በፊት.... በቻናላችን ላይ ቢሻሻል የምትሉትን፣ ይበልጥ አልተነካም በሱ ላይ ስሩበት ብላቹ የምታስቡትን፣ ከዛም ውጪ ያላቹን ማንኛውንም አስተያየት፣ ማሻሻያ እና ግሰፃ በ @teamhudabot እንድታደርሱን እንጠይቃለን። >>
#ሪዛል:- <<ኢንሻአላህ.... ደካማ ጎኖቻችንን አሻሽለን፤ ይበልጥ ተጠናክረን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደተለመደው በአዲስ መልክ ወደናንተ የምንመለስ ይሆናል። >>
#ያስ:- <<እስከዛ በዱዓችሁ አትርሱን >>
#ሪዛል:- <<ዒዳችን የፈካ ሆኖ እንዲቀጥል ተክቢራ ጋብዘናችሁ የምንለያይ ይሆናል። የመፅሃፍት መንደር ላይ የቀረበላቹን ጥያቄ በመመለስ መሳተፍ እንዳትረሱ ልናስታውሳቹ ወደድን

ለሁላችሁም ያማረና የተዋበ ዒድ እንዲሆን እንመኛለን ። ወሰላሙ ዐለይኩምወራህመቱላሂ ወበረካቱህ >>

◌◌ ◌◌ ◌ ◌ ◌◌ ◌◌

@Re_ya_zan
279 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 15:10:04 የሩሕ ጉዞ...
(Team Huda)

ፍትሕ እንደ አድማስ ከእጃችን ሲርቅ ይናፍቁኛል። ሕግ ይሉት የማይታይ መንና ሲሆንብኝ ይናፍቁኛል። ቁራሽ መሬት፡ ክቡዱን የሰው ልጅ መቆራረሻ ሰበብ ሲሆን ቢኖሩ እንዴት ይሆኑ እያልኩ በማሰብ ወስጥ ይናፍቁኛል። ምክንያት...እሳቸው ...የፍትሕ አምባ... የሐቅ ሚዛኑ ናቸውና። የእውነተኝነት አይነታው!!

ነብይ መሆናቸው ከመታወጁ በፊት ስለሆነው እናውጋ... ሀጀረል አስወድን ማን ነው ወደ ቦታው የሚመልሰው? የትኛው ጎሳ ነው የሚከበረው? በጎሳ በተቧደነ ...ደም ለመፋሰስና ሰይፉን ለመሳል ኢምንት ሰበብ የሚጠብቅ ማህበረሰብ ውስጥ ናቸውና ጉዳዩ እንደተፈታው ባይፈታ ኑሮ እንዴት እልቂት ሊመዝ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ጋር ነው የፍትሕ አይነታነት!
በጋቢ(ኩታቸው)ያስቀመጡትን ሀጀረል አስወድ የሁሉም ጎሳ ተወካዮች ጫፉን እንዲይዙ ተደረገ...የሑሉም ልብ በተካሽነት ረካች... ከጎሳዎቹ የተመረጠ አልነበረም... አሚኑ ሙሐመድ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያስቆሙት ለዘመናት ሊቋረጥ የማይችልን የሰው ልጅ ሞትን ነው። ከዛማ በበረካ እጆቻቸው አንስተው ወደ ቦታው መለሱት...ምን ያማረ ሕግ ፈፃሚነት!!
እንዲህ እንዲህ አይነት ሁነቶችን እየመዘዝን ብናወጋ የአሚኑን አሚንነት ሳናወላዳ እንረዳለን። ወቅታችን ይህን ወደ ሀያታችን ልናወርድበት የሚገባ ነውና ኢምንት በምንላት ነገር እንኳ ፍትሐዊነት እንለማመድ...እኩል መቁረስን...በእኩል አይን ማየትን...!!

በፍጡር ትንፋሹ
በአየር ነፋሹ
በአፍቃሪ ልቦች
በተንኮሻኮሹ
በገፈሉ ቀልቦች
በተረባበሹ
ከነሱም በላቁ
አውርድ ራህመትህን
በወደር የለሹ
በአሐመድ ሙሐመዱ
በናፍቆት ጨራሹ
በቤተሰቡም
ከኑር ተቀንጣሹ
በሰሃባው ሁላ
ሙሓባ ቀላሹ

ሰለዋቱ ረቢ ዓለይክ ያ ሀቢበ ሏህ!

@Re_ya_zan
206 views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ