Get Mystery Box with random crypto!

የዕለቱ መና

የቴሌግራም ቻናል አርማ menaabew — የዕለቱ መና
የቴሌግራም ቻናል አርማ menaabew — የዕለቱ መና
የሰርጥ አድራሻ: @menaabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የዕለቱ መና ተከታታዮች በቻናሉ ላይ ያላችሁን አስተያየት በዚህ @Teme30 ላኩልን

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-25 06:21:27
በጥንት ዘመን ይጓዙ የነበሩ መርከበኞችን ትክክለኛውን ወደብ ለማግኘት በወደቡ ላይ የሚያበራ መብራት ተራራ ወይም ከፍ ብሎ የሚታይ ምልክት ይጠቀሙ ነበር። ይህም ያንን እያዩ ወደባቸውን ለማግኘት እንዲያገለግላቸው ነው። የቅዱሳንን ገድልና ሕይወት ማወቁ እነርሱን እያየንና እየተከተልን ወደ ወደባችን /ወደ ክርስቶስ/ ለመድረስ ይረዳናል።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘ ኑሲስ
267 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:24:40
578 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:24:02 ጌታ ሆይ ና!

ጌታ ሆይ ወደ እኛ ና! ኢየሱስ ሆይ ጴጥሮስን እንዳትሰማው! ከታቦር ወርደህ ወደ ቤታችን ወደ ልባችን ግባ። እኛ መከራን ወደምንቀበልበት ለዕለት እንጀራችን ወደምንሰቃይበት ወደ ቤታችን ድኅነትን ይዘህልን ና! ጌታ ሆይ ጴጥሮስ መውረድን ማይሻ ከሆነ በዛው ተወው፣ አንተ ግን ወደኛ ወደልባችን ውረድ!

እንዴት መዳን እንደሚቻል ወርደህ አስተምረን፣ የጽናትን መንገድ ምራን! የሕይወታችንን መስቀል መሸከም አስተምረን። እባክህ ና ወደኛ! ና ስለኛ መካራን ተቀበል፣ በእኛ ፈንታ አንተ ተሰቀልልን። የሞትን ጽዋ አንተ ቀድመህ ቅመስልን። ጌታ ሆይ እባክህ ወደኛ ውረድ፣ በመከራ ውስጥ ምትገኘውን የድኅነት መንገድ አሳየን።

ከጴጥሮስ ጋር በታቦር ተራራ መቆየት ብንችል ምንኛ በወደድን! ነገር ግን የተሸከምነው የተሸከመን በዝሙት እና በፍቃደ ሥጋ የደቀቀ የጎሰቆለው አካላችን ከተራራው እንድንወጣ በዛም እንድንቆይ አያስችለንም።

ከጴጥሮስ ጋር አንተ ሙሴ እና ኤልያስ ያላችሁበትን ድንኳን ከበን መደሰትን ምንኛ በወደድን። ነገር ግን የከበበን የኃጢያት ጉም የአንተን ብርሃን እንዳናይ ፍጹም ደስታንም እንዳንደሰት ጋርዶናል። አቤቱ አትተወን! ኢየሱስ ሆይ ወደኛ በፈጣን ንፋስ ተጭነህ ውረድ፣ ወደ ተራራው ግርጌ ታድነን ዘንድ ና! በተራራው ግርጌ እኛ አንተን እንጠብቃለን። ከቶማስ እና ከእንድርያስ፣ ከያዕቆብ እና ማቴዎስ፣ ከበርተሎሜዎስ፣ ከስምዖን እና ከታዴዎስ ጋር እንጠብቅኻለን። ከርሁባን እና ከተራቆቱት፣ ቤት ከሌላቸው እና ከዕጓለ ምውታን ጋር፣ ከሕፃናት እና ከአረጋዊያኑ ጋር፣ ከባልቴቶች እና ከነዳያን ጋር፣ ከታመሙት እና በስቃይ ካሉት ጋር ሁላችን አንተን ተጠምተን በተራራው ግርጌ እንጠብቅኻለን። ሰላማችን ሆይ እባክህ ወደኛ ና!

መድኃኒታችን ሆይ ከታቦር ግርጌ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ውረድ። ሕይወት በባሕሩ ኃይል ከዚህ ወደዚያ ወደምትናጋበት ና! መርከቦች ከባሕር ድንጊያ(ድንጋይ) ጋር ተላትመው ተሰባብረው ወደ ባሕሩ ወለል ላለመስጠም ወደሚታገሉበት፣ ብዙ የጀልባ መቅዘፊያዎች ተሰባብረው ወደሚንሳፈፉበት፣ በዐመፀኛው ሞገድ ብዙዎች ነፍሳት ወደ ባሕሩ ወደሚጎተቱበት ና! ዝም ያለው ተራራ ለጸሎት እንደሚስብህ እናውቃለን ነገር ግን አቤቱ በባሕሩ እየሰጠምን ወዳለን ወደኛ በኅዘኔታ ተመልከት። በባሕሩ ላይ ከሞገድ፣ ከንፋስ እና ከድቅድቅ ጨለማ ጋር ሚታገሉትን በጀልባ የተመሰሉ ልጆችህን እባክህ አድን።

ወደ ጥልቁ የባሕር ስፍራ (ወደ ሰው ልጅ ልብ) እባክህን ውረድ! ብርሃን ከጨለ ጋር፣ ሕይወት ከሞት ጋር፣ ደስታ ከማቃተት፣ እውነት ከውሸት ጋር ማርም ከመርዝ ጋር፣ ፍቅር ከጥላቻ፣ ወይንም ከሆምጣጤ ጋር፣ መዋቲነት ከዘለዓለማዊነት ጋር ወደተደበላለቁበት ቦታ ና! ሰላማችን ሆይ ሰላምህን ስጠን! ባሕርን አረጋጋት የነፍሳችንን ሐሳብም ባንተ አንድ አድርገው።
534 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 07:08:17
692 views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 06:55:15
ያለውና የነበረው የሚመጣው

አንዲት በአረብ ሀገር የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረች ሴት ወደ አንድ የግብፅ ካህን ጋር በመሄድ አባቴ አጥምቁኝ አለቻቸው።

ካህኑም አንቺ የእስልምና እምነት ተከታይ ነሽ
እናም አስቀድመሽ ልትማሪ ልታምኚ ይገባል አሏት
እርሷም እኔ ክርስቲያን ነኝ ሁሉን ነገር ራሱ ክርስቶስ አስተምሮኛል አንድታጠምቁኝ እፈልጋለሁ አለቻቸው።

ካህኑም በመገረም ለመሆኑ በማን ስም ነው የምትጠመቂው አሏት?

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማናቸው?

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ልዩ ሦስትነት ያላቸው አንድ አምላክ ነው።
"አብ አምላክ ነው። ወልድ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው። ግን ሦስት አምላክ አይባልም አንድ ልዩ አምላክ ነው። አለች

"ይህን እንዴት አወቅሽ?

በራዕይ ዩሐንስ ላይ፦
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” ራእይ 1፥8

ይህ ስለ ጊዜ የተነገረ ነው፦

ትላንትም ጊዜ ነው። ዛሬም ጊዜ ነው። ነገም ጊዜ ነው። ነገር ግን ትላንት ዛሬ አይደለም። ዛሬም ትላንት ወይንም ነገ አይደለም። ነገም ትላንት ወይንም ዛሬ አይደለም። ሦስቱም ግን ጊዜ ናቸው። ነገር ግን በአንድ ላይ የተጨፈለቁ አይደሉም። ትላንት ለብቻ ነው፣ ዛሬ ለብቻው ነው።፣ነገም ለብቻው ነው።

እንዲሁም፦

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው።
ነገር ግን አብ፥ ወልድ አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም። ሦስቱም በህልውና አንድ አምላክ ሆነው ይኖራሉ እንጂ።

እንዲህ አድርጎ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮኛል አለቻቸው።

ካህኑም እጅግ በመደነቅ ከልብ ለሚፈልጉት ለልበ ንፁሐን ምሥጢርን የሚገለጥ ክርስቶስን እያደነቁ አጠመቋት።
1.6K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:00:24
"ተማርና ለራስህ የምትበቃ ሁን።"

ዓሣ በማጥመድ የምትተዳደር አንድ ትንሽ መንደር ነበረች። ወፎች እንኳን ሳይቀሩ የሚኖሩት ዓሣ አጥማጆቹ የሚተውላቸውን በመመገብ ነበር።

በድንገት ዓሣዎች በጣም እየቀነሱ ስለመጡ በዛ ያለ የዓሣ ምርት ፍለጋ ዓሣ አጥማጆች ያንን መንደር ትተው ወደ ሌላ ሰፈር ሄዱ ዓሣ አጥማጆች የሚተዉላቸው ዓሣዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ጥገኛ ሆነው ስለነበር ወፎቹ ምንም ዓይነት ምግብ ማግኘት አልቻሉም። ራሳቸውን እንዴት መመገብ እንዳለባቸው በፍፁም አልተማሩምና መጨረሻ ላይ ወፎቹ ሞቱ።

አንዳንድ ጊዜ የእኛ ሁኔታ ልክ እንደነዚህ ወፎች ነው። ከሌሎች ማግኘት በምንችለው ላይ ብቻ እንንጠለጠላለን እንጂ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር የተቆራኘ የራሳችን የሆነ ሕይወት የለንም። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ሕይወት ይልቅ በሌሎች ልምድ ላይ ጥገኛ እንሆናለን። ምንም እንዳልተማሩ ወፎች ወደ ሞት ራሳችንን የምንወስደው በዚህ መልኩ ነው።

ታድሮስ ያዕቆብ ማላቲ
1.1K views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 06:48:30
በሰው ፊት አንድ ሰው ቢቆምልህ ማንኛውም ነገር ታደርጋለህ በእጅጉ በማመስገን ትናገራለ። ካህን ግን በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልሃል። ውለታውን ግን አታስብም። እርሱ ለአንተ ይፀልያል በጥምቀት የሚገኘውን መንፈሳዊ ስጦታ እንድታገኝ በማድረግ ያገለግልሃል። ሆኖም እርሱ የአንተ መነጋገሪያ ርዕስ ከመሆን ውጪ ምንም ያገኘው ነገር የለም። እናም የአንተን አቁሳይ ንግግሮች ታግሦ ይኖራል።

ክርስቶስን የሚያፈቅር ቄሱን ምንም ይሁን ምን ያፈቅረዋል። ምክንያቱም አስፈሪውን ምሥጢራት ያገኘው በእርሱ በኩል ነውና። ዘላለማዊ ልደት የተወለድከው በእርሱ በኩል ነው።
ሁሉም ነገር የተከናወነው በእነርሱ እጆች ነው። ስለዚህም ስለ ሥራቸው በፍቅር ከመጠን ይልቅ አክብሯቸው። ክርስቶስን የምታፈቅሩት ከሆነ "ስለ ሥራቸው ስትሉ ከእነርሱ ጋር በሰላም ኹኑ።" /1ተሰ 5፤12/

[የዕለቱ መና - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።]
945 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 05:10:58
“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14
1.3K views02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 08:32:50
1.0K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ