Get Mystery Box with random crypto!

ሳሙኤል ተመስጌን ወ/ሃና

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsidq — ሳሙኤል ተመስጌን ወ/ሃና
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsidq — ሳሙኤል ተመስጌን ወ/ሃና
የሰርጥ አድራሻ: @tsidq
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-14 23:52:07 ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ኦሪት ዘፍጥረት 2 : 18
ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል።
ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፤ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።

ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል?
አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፤ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።
መጽሐፈ መክብብ 4 : 9 -12)

መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ ወንድሜ
72 viewsedited  20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 23:51:51
73 views20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 23:48:30
60 views20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 23:47:55 ነፍሰጡር ፦ የሥጋ ሕይወት የሚሆን ነፍስ ያለው ሕፃን የተሸከመች ሴት የምትጠራበት ስም ነው። ጹረት የሚለው የግእዙ ቃል መሸከም ማሸከም አሸካከም ሸከማን ይገልጣል። የአማርኛውም መጦር አጧጧር ጡረታ ከዚሁ ጋር የሚዛመድ ነው። ብእሲት እንተ ጾረት ነፍስ (ነፍሳ ያለው ፍጥረት የተሸከመች ሴት) ናትና ነፍሰጡር በማሕፀንዋ ነፍስ የምትጦር ፣ ሥላሴ አካል ዘየአክል (የሚበቃውን ሰውነት ሠጥተው የቀረጹትን ፍጥረት በማሕፀን ዓለም የያዘች ማለት ነው።

ለዛሬው የሚበቃ መሰለኝ በስሙ መታሰቢያ ቀን ስለአስማት እንድናወጋ የፈቀደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጋና ይድረሰው። ከመነሻዬ አንድ መልእክት ተውሼ የዛሬውን ከዚህ ልቋጭ

ዛሬ ጌታችን ከተወለደ ሳምኒት ዕለት (ስምንተኛው ቀን) ነው! ዕለተ ግዝረት ኢየሱስ የሚለው ስም በእናቱ በኩል የወጣለት ዛሬ ነው። ጥር ፮ የአስማት ቀን ነው መባሉም የእርሱ ስም መድኃኒትነት ለዲያቢሎስ መርዝ ማርከሻ በ፵ ቀኑም ለአረጋዊው ስምኦን መታደሻ ሆኖታል። ለእኛም «ለስምንተኛው ሺህ ጉዶች» ስምንተኛውን ቀን ከኃጢዓት ሸለፈት በንስሐ የምንገዘርበት ያድርግልን። በከበረው ስሙ መድኃኒት ይሁነንማ።

በቴዎድሮስ በለጠ ጥር ግዝረት ፳፻፲፫ ዓም ተፃፎ በማቅኛና ተጨማሪ ሐሳብ ጋር Яερôšтεδ today
. አዲስ አበባ
55 views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 23:47:55 ማሞ ፦ ይኽኛው ደግሞ ከቀደሙት በእጅጉ ይለያል በሰው ስም ከመታወቁ ውጪ «ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ» ፣ «ማሞ ቂሎ»… በሚሉት አገባቦች ስንሰማው የኖርን መጠሪያ ነው። ስለመነሻው ሳስስ ይህ መጠሪያ ሀገርኛ እንዳልሆነ ባውቅ የበለጠ ደንቆኛል። ታዲያ ከምን ተገኘ? አትሉም ፤ ማሞ ከልሳነ ጽርእ (ግሪኩ) ማሞን (μαμμωνᾶς) ከሚለው የተገኘ ነው፤ ለዚህ አስረጂዬ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ክርስቶስ ጌታችን ለሁለት ጌቶች መገዛት እንደማይቻላቸው በቃሉ ላፌዙት ገንዘብ ወዳጅ ፈሪሳውያን ሲያስተምር "ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም" ይላቸዋል ‘Ye cannot serve God and mammon.’ ወለንዋይ ባለው ወለማሞን ይላል የእኛም ግእዝ፡፡ ኪዳነ ወልድም በቃላቱ መዝገብ ሕፃናትን ማሞ ማሚት ማለት ከዚህ የወጣ ስም ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።

✧ አማርኛው አቻ ትርጉም ሴቷን ገንዘቤ (ማሚት) ወንዱን ንዋይ (ማሞ) ብሎ ይጠራዋል።

ምንዳዬ ፦ ይህን ደግሞ ቢዘገይም ባክልበት ነው።
ለዚህ መነሻው ነዲእ / ነዲኦት የሚለው ነው መንዳት መውሰድ መሸኘት ማጀብ መከተል ማድረስ ማለት ነው፤
አንድ ሰው ነዳኢ ነው ከተባለ የሚነዳ ነጂ እረኛ ሹም ነው የሚለውን ይገልጣል። ይህን ይዘን ምንዳእ ላይ ስንደርስ መንጃ ፣ መነጃ ፣ በትር ፣ ጅራፍ መንገድ ወደሚል ትርጉም ያደርሰናል። በቁሙ ደግሞ ምንዳ የእረኛ ዋጋ ደመወዝ ዐስበ ኖላዊ (ለገበሬም ይኾናል ሲያርስ በሮች እየነዳ ነውና) ማለት ይሆናል።
አሁን ምንዳዬ ላይ ደርሰናል። (ምንዳእየ⇨ ምንዳዬ) በአማርኛው ደሞዜ ገንዘቤ ዋጋዬ በትርየ ፍኖቴ ማለት ይሆናል የፍቺው አገባብ ከላይ ነሲቡ በሚል ከተገለጠው ጋር ይወራረሳል።

ተኰላ/ተኮላ ፦ በአጠራሩ ኒኮላ (ኒቆላዎስ) እንደሚለው የውጪ ስም ይመስላል። ተኰላ ማለት ግን ቀጥታ ተወለወለ፣ ተሰነገለ ፣ ጠራ ፣ ነጠረ ጥሩ ኾነ የሚለውን ይገልጣል።

ተምትም፦ አስማማ አጣጥም አስታርቅ አግባባ (መተምተም ማጣጣም… ቁራሽ በብትን ድቁስ ተምትሞ አጥቅሶ መብላት)

መርድ ፦ በሁለት መንገድ ሊታይ ይችላል (መርዕድ፣ መርድእ) ብሎ ፤ መርዕድ ካለ መራድ መፍራትን ይዞ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ባለ ግርማ ሞገስ የሚለውን ይገልጠል፣ መርድእ ካለ ደግሞ ረድእ የሚለውን መነሻው በማድረግ ተማሪ ደቀ መዝሙር የሚውን ይተካል።

አርማሕና ሐርቤ ፦ እነዚህ ከሀገራችን ነገሥታት ወገን የነበሩ ስሞች ናቸው፤ የሁለቱም መነሻ ሐርብ የሚለው ቃል ነው ጦርነት ውጊያ ሰልፍ ባለው የሚተካ ነው። ዐ(ሐ)ርበኛ የምንለው ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል

☞ አንዱ ንጉሥ በሙሐመድ ዘመን የነበረ ሰላማዊና ጀግና የኢትዮጵያ ንጉሥ መጠሪያ መሆኑን ታሪከ ነገሥት ይናገራል ፦ ንጉሥ አርማሕ ትርጉሙ ጦረኛ ሐርበኛ (አርበኛ) ማለት ነው።

☞ ሁለተኛው በላስታው ታሪክ ውስጥ በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ከተነሱ 11 ነገሥታት መካከል የሚጠራና ከከበሩ አራቱ ቅዱሳን ነገሥታት (ሐርቤ ፣ ላሊበላ ፣ ነአኩቶ ለአብ እና ይትባረክ ) መካከል የሚደመር የታላቅ ሰው ስም ነው [ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም)] ሐርቤ ማለት ሐርብየ አርበኛዬ ጀግናዬ ማለት ነው።

ሙና /ሙናዬ ፦ ሴት እናት እህቶቻችን በዚህ መጠርያ ሲሰየሙ አልፎ አልፎ እሰማለሁ። መነሻ መጠሪያው ሙናሕ/ሙናኅ የሚል ነው፤ ትርጉሙ ማረፊያ ምዕራፍ ማለት ነው፤ ነዊኅ፣ ኖኅ የሚለው የዚህ አቻ ነው። በፍትሐት ጸሎታችን አምላካችን የሚያሳርፍ የሚያረጋጋ ብሎ ሲማጸን «መናህይ ወመናዝዝ» ይላል። በመጽሐፈ ግንዘት ሃባ ናህየ ወዕረፍተ ላዛቲ ነፍስ እንዲል።

ከዚህም ጋር በተወዳጀ ስያሜ አንዳንድ ተመሳሳይ ትርጉም ያነገቡ ስሞችም በአንድ ቤት ለእህት ለወንድም ሲሰጡም አይቻለሁ ለምሳሌ ዕሌኒ እና ሔለን ፣ ሐመልማል እና ለምለም ፣ ኂሩት እና ቸርነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ስሞች ቢሆኑም ልዩነት ያላቸው መስለው ለተለያዩ ግለሰቦች ሲታደሉ ይታያል።

ይህን ይዘን እግረ መንገድ ጥቂት ለማለት ወደ ወል መጠሪያዎች ደግሞ እንለፍ።

አቶ ፦ ዛሬ አንድ ወጣት ወንድ እድሜው ሲገፋና ሕግ ሲገባ (ትዳር ሲይዝ) በክብር የሚጠራበት ስሙ ነው ይህ አቶ የሚለው። በቀድሞውስ ዝክረ ሊቃውንቱ እንደሚነግረን ‘የአዋቆች’ የሊቃውንቱ መጠሪያ ማዕረግ ሁሉ ነበር (ለዚህ ሊቁ አለቃ አስረስ የኔሰው አቶ አስረስ ስለመባላቸው የገለጹትን ማየት!) ለፍቺው መነሻ አተወ/አቶ ነው በፍቺው ገባ ተመለሰ መጣ ይላል፤ እትወት [አቶነት] መግባት መመለስ መምጣት ነውና (ዲያቆን በቅዳሴው ማብቂያ እትዉ በሰላም እንዲል) አቶ ማለት ባለ ሕግ ፣ ትዳር የያዘ ፣ ወደ ልቡ የተመለሰ ፣ ከሰው ቁጥር የገባ ፣ ከሚስት ከባልንጀራ አቻ ኾኖ የተካከለ ማለት ነው።

ወይዘሮ ፦ ይህም እንደቀድሞው ለሴት አንቀጽ ተቀጽላ ሆኖ ለሴት እመቤት ላገቡ የሚዛረፍ የባለትዳሮቹ የክብር መጠሪያ ነው። መርዓዊት (ሙሽሪትን) ሲያስጌጧት ሲሸልሟት ሲያንቆጠቁጧት አወየዘረ ወይዘሮ አደረገ አስወየዘረ ወይዘሮ አስደረገ ይላል። የተጌጤች የተሸለመች የተሞሸረች ናትና ወይዘሮ ትባላለት፤ ገና ያልተሞሸረችዋን ተወዛሪት ወይዘሪት ማለት በዚህ ልማድ ነው ገና የምትሞሸር ናትና።
በእርግጥ አወየዘረ ማለት ሾመ አከበረ ራስ ቢትወደድ አደረገ ማለትም ነው፤ ለሚስትነት የወደዳት ባል ያገኘችውን ሴት ሞገስና ባለሟልነት ያላት ናትና ክብርት ወይዘሮ ብሎ ይገልጣታል። (ዘረከበ ብእሲተ ኄርተ ረከበ ሞገሰ ወበረከተ)

እመጫት ፦ ይህ ደግሞ የጨቅላ እናት በክብር የምትጠራበት ስም ነው። በተረት «እመጫት ሆዷ ቅርጫት» ሲባልም እንሰማለን፤ ቃል በቃል እንፍታው ብለን ከታገልን የአደንዛዡ እጽ (የጫት) እናት ወደማለት ያወርደናል። (ለእናቴስ ላቲ ክብር) አማርኛችን ከእናቱ ግእዝ ቃላትን ሲዋስ እንደየ (አ)ከባቢው የሚለውጣቸው ሆሄያት አሉ፤ ከከባቢ ከባቢ (አካባቢ) እንኳ ቀ እና ኧ የሚተካኩበት (መኧነት፣ ባዔላ … መቀነት ባቄላ) መኖራቸውን በብዙ ምሳሌ ማስረዳት ይቻላል። በተጨማሪ ጸ/ፀ፣ ጠ እና ጨ ሲወራረሱ ይታያል።
ትልቅ ምሳሌ ለዚህ እንጥቀስማ "ጤናዳም" ሲባል የማያውቅ የለም "ጤና አዳም" በሚል ፍቺ ከገነት እጽዋትና ከአዳም ኑሮ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ ስለመኖሩ ማስረጃ አልተገኘለትም።

ይሁንና እንደነ ኪዳነ ወልድ ገለጻ ከሆነ ጤናዳም የሚለው " "ጼና አዳም" ባለበጎ ሽታ (ጼናሁ አዳም ሽታው መልካም) የሆነውን ቅጠል ይዞ የተሰጠ ስም መሆኑ ተጽፏል። በልሳነ ትግሪኛውም "ጨና አዳም" የሚለው የበለጠ ይህን ገላጭ ነው። በዚህ መነሻ ጸ/ፀ በጠ መተካቱን ልብ ይሏል። ጠሃይ እንዲል ፀሐይን፣ ንግሥት ጣይቱ ይላል የእምዬ ምኒሊክን እምዬ ፀሐይቱን!

ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ እመጫት የሚለውን የጨ፣ የፀ እና የጠ መተካካት ከእኛ ቢያርቀው ትርጉሙን ሳንይዘው ቀረን። ፃት ፦ ማለት ጣት ማለት ነው ፤ የእጅና የእግር ቅጥይ ነው። ሕፃን ጨቅላ ፣ ርጥብ ለጋ ፣ ቀንበጥ ዐራስ ወጣት ልጅ ጻጹት/ጫጩት ሁሉ ፃት ይባላል የተክል ጫፍ የዛፍ ቅርንጫፍ ፃት ተብሎ ይጠራል ዛሬ በእኛ ጣት እምንለውን ሁሉ ማለት ነው። ታዲያ እኛም በዚሁ እመ ፃት ያለውን ነው እመጫት ያልነው፤ ትርጉሙ የጨቅላ እናት፡፡ የዶሮ እመ ጫጩት/ጻጹት የዝንጀሮ እመጫት እያሉ መጥራት በዚህ አገባብ የተለመደ ነው።
54 views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 23:47:55 ጥር ፮ የአስማት ቀን ነው!
━━✦༒ ༒✦━━

ቸር አላችሁ? እንኳን አደረሳችሁ!

አስማት የሚለውን ቃል ስንሰማ ቀድሞ ወደ አእምሯችን ዓይኖች ምትሀት የሚለው ትርጉም ድቅን ይል ይሆናል።

በእርግጥ ስያሜው ከኅቡእ መለያዎች (magic spells) እየተጠጋ አስማት (incantation) የሚባለውንም ይገልጣል፤

በእኛም ዘንድ አንድ ሰው አስማታዊ/አስማታም ነው ከተባለ ባለኅቡእ ስም ፣ አስማት ያሚደግም ፣ የሚጥፍና የሚያነግት የሚያስነግት ፣ ስም የሚጠይቅ በስም የሚያሟርት ጠንቋይ መሠሪ ኮከብ ቈጣሪ ነው ማለትም ይሆናል። (ኪዳነ ወልድ እንዳመለከቱት)

"በሸንጎ ቢረታ ከቤት ሚስቱን መታ" ሆኖብን የውጪዎችንስ «ምናምን» ለእኛ ምሥጢር ማርከሻ እንዳናውል እየተጠነቀቅን አስማት የሚባለው ስም ለሚለው አብዢ ቁጥር ሆኖ የሚያገለግል ስያሜ ነው የሚለውን ለዛሬው እንያዝ። (የአምላካችንን በእጅጉ የከበሩ ስሞች ለመግለጥ አስማተ መለኮት እንዲል)

ከዕለቱ ጋር የሚገናኘውም ይህ ነው!

ዛሬ ጌታችን ከተወለደ ሳምኒት ዕለት (ስምንተኛው ቀን) ነው! ዕለተ ግዝረት ኢየሱስ የሚለው ስም በእናቱ በኩል የወጣለት ዛሬ ነው። አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው እንዳለ ዘማሪው። ነቢዩ "አማኑኤል ትለዋለች ሲል መልአኩ ኢየሱስ ትዪዋለሽ ብሏታልና)
ብርሃነ ብርሃናት ሠረቀ እማርያም ድንግል
ዘይነብር ቀትረ መልእልተ ጌልጌል
ሰመየቶ አማኑኤል
ጥር ፮ የአስማት ቀን ነው መባሉም የእርሱ ስም መድኃኒትነት ለዲያቢሎስ መርዝ ማርከሻ በ፵ ቀኑም ለአረጋዊው ስምኦን መታደሻ ሆኖታል። ለእኛም «ለስምንተኛው ሺህ ጉዶች» ስምንተኛውን ቀን ከኃጢዓት ሸለፈት በንስሐ የምንገዘርበት ያድርግልን። በከበረው ስሙ መድኃኒት ይሁነንማ።

“እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” (ማቴ ፩፥፳፩)

በግእዙ ስም “ሰመየ፤ ስም አወጣ፣ ጠራ፣ ለየ” ከሚለው ግስ ይወጣና መጠሪያ መለያ የሚለውን ይገልጣል፡፡ በልሳነ ዐረብ ኢስም ism (اسم) በእብራይስጡም ሼም shame (שֵׁם) ከሚለው ተቀራራቢ ቃል ጋር አቻ ፍቺ ያለው ነው።

በአጠቃላይ ስም ቦታነትና አካልነት ህላዌና ሕይወት ላለው ሁሉ መገለጫ ሆኖ የሚያገለግል መጠሪያ ነው።

የስም የትመጣነትን አጉልቶ የሚገልጠው ቅዱስ መጽሐፋችን በመጀመሪያው ሰው በአዳም በኩል ለገዛ አጋሩ ቀድሞ ሴት ኋላ ሔዋን የሚለውን መጠሪያ በመሰየም ጭምር ቀዳሚ ስም አውጪ እርሱ እንደነበር ተጽፎልናል።

መላእክቱ በሁለተኛው ሱባኤ በ፮ኛው ቀን በእግዚአብሔር ታዘን ፍጥረቱን በየወገኑና በየመልኩ ወደ አዳመቅ አመጣን "ወአምጻእነ በቃለ እግዚአብሔር ኀበ አዳም …" ይላሉ።

አዳምም እኒህን ፍጥረታት በየስማቸው ጠራቸው ስማቸውም እርሱ እንዳወጣላቸው ሆነ " ወሰመዮሙ አዳም ለኵሎሙ በበ አስማቲሆሙ ወበከመ ጸውዖሙ ከማሁ ኮነ ስሞሙ፡፡" [ኩፋ ፬፥፪ ]

ቅዱስ ቀሌምንጦስም ይህን ሲያጸና እንዲህ አለ “ወሰመዮሙ ለኵሎሙ በበአስማቲሆሙ ወተአዘዙ ሎቱ ኵሉ ፍጥረት ወዓቀቡ ቃሎ፤ አዳም ለሁሉም በየስማቸው ሰየማቸው፣ ስም አወጣላቸው፤ ፍጥረት ሁሉ ለአዳም ይታዘዝና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር” (ቀሌ ፩፥፵፪)

በዘልደት መጽሐፍም እንዲህ የሚል ይገኛል “እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ደግሞ ከምድር ፈጠረ፤በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደጠራው ስሙ ያው ሆነ፡፡ አዳምም ለእንስሳት ሁሉ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣለቸው” (ዘፍ፪፥፲፱-፳)

የሰዋስው ምሁራን የስም ዓይነቶችን ከአገልግሎታቸው አንጻር ስመ ባሕርይ ፣ ስመ ተቀብዖ ፣ ስመ ግብር ፣ ስመ ተጸውኦ፣ ስመ ተውላጥ (መራሕያን) እያሉ በአምሥት ከፍለው ያጠኑታል። (በመጽሐፈ ሰዋስው መጽሔተ አእምሮ እንደተብራራው)

መጠሪያ ስም (ስመ ተጸውዖ) አስቀድሞ ፍጥረቱ ኹሉ ከፈጣሪውና ከጌታው ከአዳም እንደ ተሰየመ እንዲሁ ደግሞ ከአባት ከእናት ከጌታ ከእመቤት ከካህናት ከቤተ ክርስቲያን ተሰይሞ የሚጠራበት መገለጫው ነው። በዚህ ላይ የሹመትና የማዕረግ ስሞችም አሉ ስመ ተቀብዖ ይባላል። ይህም ከተጸውዖ ስም በኋላ በሹመት ጊዜ ከቀቢ ከሿሚ የሚሰጥ የማዕርግ ስም ነው ጳጳስ ቄስ ንጉሥ ራስ ይህን የመሰለ፡፡

ዕለቱ ካገናኘን አይቀር አንዳንድ ሀገርኛ ስሞች ትርጉማቸውን ሳናውቅ ምንጫቸውንም ሳንጠይቅ በመጠሪያነት ስንጠቀማቸው ይስተዋላል (ተሸካሚና ተጠቃሚ ቢለያይም )

በግሌ ሰዎች ስማቸውን ሲነግሩኝ "ምን ማለት ነው?" ብዬ እጠይቃለሁ ካላወቁት እንኳ ትርጉሙን በማሰስ የደረስኩበት እንደሆነ አስታውሼ እንዲያውቁት ለማድረግ እጥራለሁ።

ለዛሬው «ሀገርኛ» መጠሪያ ይዘው ትርጉሙን ግን ሳይረዱ ከሚጠሩበት አንዳንድ ግለሰቦች ያገኘሁትን ስም በደረስኩበት ደረጃ በትርጉም ላመላክት እና ላጋራችሁ ወደድኩ።

#በጥቂቱ
☞ ነሲቡ፣ አባተ ፣ ዘበነ ፣ ማሞ ፣ ምንዳዬ፣ ተኮላ፣ ተምትም ፣ መርድ፣ አርማሕ፣ ሐርቤ ሙናዬ…
☞ አቶ ፣ ወይዘሮ ፣ እመጫት፣ ነፍሰጡር … የሚባሉቱ መጠርያዎች መነሻ ግንዳቸው የትርጉም ዐውዳቸው ምን ይሆን?

ነሲቡ፦ በዚህ ስም የሚጠሩ ጥቂት ግለሰቦች በግል አውቃለሁ። መነሻው ነሲብ ነው ይህም ግምት ድርሻ፣ እድል ፈንታው ማለት ነው፤ ዐንሰበ ይላል ገመተ ሲል። ከዚህ ስም ጀርባ አንድ አስደናቂ ክስተት ይነገራል፦
ወላጆች ልጅ ወልደው በተደጋጋሚ በሞት ሲነጠቁ "የሰጠ ቢነሳ የለበት ወቀሳ" ይሉና «እባክህ ይህንንስ ተውልኝ ለእኔ ድርሻ እድል ፈንታዬ ይሁነኝ» ብለው ብፅዐት ገብተው ይወልዱና ስሙን ነሲቡ ብለው ይሰይሙታል እንዳሉትም ይሆንላቸዋል፤ በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ግደይ እየተባሉ ከተጠሩ ሰዎች ጀርባ ይህ ሐቅ ይገኛል።

✧ ነሲቡ በአማርኛው ድርሻዬ ፣ በትግሪኛው ግደይ የሚለውን የሚተካ ነው።

ዘበነ ፦ ይህ እንኳን የበርካቶች መጠሪያ የሆነና ለብዙዎችም ከነ ትርጉሙ እንግዳ እንደማይሆን ባውቅም አንዱ ወንድሜ «መጠሪያው ጸያፍ ነው» ብሎ ሲነቅፍ ስላየሁ ለእርማት አካትቼዋለሁ። ዘበነ የዘባን መነሻ ግንድ ነው ፤ ዘባን ደግሞ ጀርባ ነው የደረትና የሆድ ጓሮ ጎረቤት ነው ፤ ጀርባ ደግሞ በዘይቤ መከታ ደጀን የሚለውን ያመለክታል። በዚህ መነሻ ዘበነ መከታ ሆነ፣ ጋሻ ሆነ፣ ደጀን ደራሽ ሆነ ማለት ነው፤

✧ በአማርኛው ደጀኔ (ደጀንየ) የሚለውን ይተካል።

አባተ፦ ይህም በማኅበረሰባችን ውስጥ የተለመደ ስም ይመስለኛል። አጠራሩ አብሐተ የሚል ሲሆን ከመነሻው ብሒት ማለት መሰልጠን፣ መሾም፣ ከበላይ መሆን የሚለውን ይይዛል። አባተ ማለት አሰለጠነ ሾመ (ባለስልጣን ፣ ሥዩም አደረገ) ማለት ነው።

✧ በአማርኛው አባተ ስዩም ፣ ተሾመ ፣ በላይ በሚለው ተተክቶ ሊነገር ይችላል።
በመባህተ መኑ ትገብር ዘንተ
አብሀነ በመንፈስ ንኪድ ኵሎ ኃይሎ ለጸላኢ
72 views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 15:52:11 +++ የማርታ ጸሎት +++

ማርያም: ትእዛዙን ሰሚ
ማርታ: የማይታዘዘውን አምላክ አዛዥ፣ "ንገራት" ባይ። (ሉቃ 10፥40)

እኛስ የእርሱን ትእዛዝ በትሕትና እንሰማለን ወይስ እንደ ማርታ "እንዲህ አድርግ? እንዲህ ተናገር?" ብለን የምንፈልገውን እናዘዋለን?

እስኪ ጸሎታችንን እናስተውል?!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
162 views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 07:42:12 ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡

አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/tsidq
443 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 10:38:33 ጾሙስ አበቃ.....?
(#በአባ_ገብረ_ኪዳን)

ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!

የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
https://t.me/tsidq
1.3K viewsedited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 19:41:55
ብዙ የተወለዱብን እና የተወለዱልን ሰዎች አሉ መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ሐይሌ ከተወለዱልን ሰዎች አንዱ ነው በተለይ ለእኔ መምህሬ ዲያቆን ሄኖክ ሐይሌ መልካም ልደት እግዚአብሔር አምላክ እረጅም እድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ይስጥልኝ
398 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ