Get Mystery Box with random crypto!

ነፍሰጡር ፦ የሥጋ ሕይወት የሚሆን ነፍስ ያለው ሕፃን የተሸከመች ሴት የምትጠራበት ስም ነው። ጹረት | ሳሙኤል ተመስጌን ወ/ሃና

ነፍሰጡር ፦ የሥጋ ሕይወት የሚሆን ነፍስ ያለው ሕፃን የተሸከመች ሴት የምትጠራበት ስም ነው። ጹረት የሚለው የግእዙ ቃል መሸከም ማሸከም አሸካከም ሸከማን ይገልጣል። የአማርኛውም መጦር አጧጧር ጡረታ ከዚሁ ጋር የሚዛመድ ነው። ብእሲት እንተ ጾረት ነፍስ (ነፍሳ ያለው ፍጥረት የተሸከመች ሴት) ናትና ነፍሰጡር በማሕፀንዋ ነፍስ የምትጦር ፣ ሥላሴ አካል ዘየአክል (የሚበቃውን ሰውነት ሠጥተው የቀረጹትን ፍጥረት በማሕፀን ዓለም የያዘች ማለት ነው።

ለዛሬው የሚበቃ መሰለኝ በስሙ መታሰቢያ ቀን ስለአስማት እንድናወጋ የፈቀደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጋና ይድረሰው። ከመነሻዬ አንድ መልእክት ተውሼ የዛሬውን ከዚህ ልቋጭ

ዛሬ ጌታችን ከተወለደ ሳምኒት ዕለት (ስምንተኛው ቀን) ነው! ዕለተ ግዝረት ኢየሱስ የሚለው ስም በእናቱ በኩል የወጣለት ዛሬ ነው። ጥር ፮ የአስማት ቀን ነው መባሉም የእርሱ ስም መድኃኒትነት ለዲያቢሎስ መርዝ ማርከሻ በ፵ ቀኑም ለአረጋዊው ስምኦን መታደሻ ሆኖታል። ለእኛም «ለስምንተኛው ሺህ ጉዶች» ስምንተኛውን ቀን ከኃጢዓት ሸለፈት በንስሐ የምንገዘርበት ያድርግልን። በከበረው ስሙ መድኃኒት ይሁነንማ።

በቴዎድሮስ በለጠ ጥር ግዝረት ፳፻፲፫ ዓም ተፃፎ በማቅኛና ተጨማሪ ሐሳብ ጋር Яερôšтεδ today
. አዲስ አበባ