Get Mystery Box with random crypto!

#ሪያድ: ቀላል የማይባል ተፅእኖ አለው። እሳት የሚባል ጊዜ ነው፤ በጣም አዳጋች፣ በጣም ፈታኝ የ | TEAM HUDA

#ሪያድ: ቀላል የማይባል ተፅእኖ አለው። እሳት የሚባል ጊዜ ነው፤ በጣም አዳጋች፣ በጣም ፈታኝ የሆነ ጊዜ። ይሄን ጊዜ ተቋቁሞ ማለፍ በጣም ፅናት ይፈልጋል፤ እኔ ተቋቁሜ አልፌዋለሁ። ወላሁ አዕለም አላህ ነው ሚዛኑን የሚለካው ግን በጣም እጥራለሁኝ ይሄ ጊዜ እንዳይፈትነኝ እራሴን ለመቋቋም በጣም እጥራለሁ፤ አንዳንድ ፈተናዎችን መውደቅ አይቀርም ከብዙ ነገር ከኢባዳም አኳያ ከብዙ ነገር መውደቄ አይቀርም፤ በዛው ልክ ደሞ አልሀምዱሊላህ። የሚጠበቅብኝን ያክል ሳይሆን የሆነ ነገር በዚህ እድሜዬ ለማሳረፍ ሞክሬአለው ከዚህ የተሻለ ነገር አልም ነበር ያ ያልሆነው ደሞ በራሴ ስንፍና ነው። አላህ ትንሿን ነገር በረካ ሞልቷባት እንደ ትልቅ ነገር እንዲቆጥርልኝ ዱዐ እንድታረጉልኝ... በዚህ አጋጣሚ የምጠይቃቹ ወጣትነት ላይ አንደኛ ጉልበቱ አለ፤ ለምሳሌ በዚህ ሰአት ያለኝ አቅም ከዚህ በፊት አልበረኝም፣ ወደፊትም አይኖረኝም። አሁን ላይ ትልቅ አቅም አለ፤ ያንን የመጠቀም እና ያለመጠቀም ጉዳይ ነው። ስለዚህ ወጣትነትን በአግባቡ እየተጠቀምኩ አይደለም፤ ግን ልጠቀም ካልኩ ወጣትነት የፈጠረብኝ እድል ቀላል የሚባል አይደለም። በዛው ልክ ደግሞ ያመጣብኝ እሳቱ ደሞ ቀላል አይደለም ሁለቱንም መቋቋም እንዲሰጠኝ ደሞ እንደተለመደው በዱአ

#ሂባ: እንደው እዝች ዱንያ ላይ ትልቁ ፊትና ምንድነው ባንተ እይታ?
#ሪያድ: እዚህ ዱኒያ ላይ ትልቁ ፈተና ረሱል የተናገሩት ንግግር አለ <<የገንዘብ እና የሴት ፈተና>>። እኔ አልሀምዱሊላህ ወደ ትዳር በጊዜ ገብቻለው፤ የሴት ፈተናን ከአሁኑ ወደ ጎን ያሸሸሁት ይመስለኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዱኒያ ፈተና ደሞ አላህ ይጠብቀን!

#ሂባ: ፋሊስጢም ሲነሳ ሪያድ አብሮ ይነሳል፤ ብዙዉን ጊዜ በፊሊስጢም ዙሪያ ስትፅፍ ትስተዋላለህ ከምን የተነሳ ነው?
#ሪያድ: በነገራችን ላይ ፁሁፍ ላይ ያለ ሰው፤ እነካካለው የሚል ሰው መሰረታዊ የሆኑ የፍትህ ጉዳዮች ላይ ስስ ነው ብዬ ነው የማስበው፤ አዛኝነት ይኖራል። አላህ ከአዛኞች ያድርገን!
ፀሀፊዎች ምናልባት እኔንም ሸንቆጥ ሳያደርገኝ አይቀርም ከልጅነቴ ጀምሮ አንዳንድ የምሰማቸው ዜናዎች የሚፈጥሩብኝ ነገሮች ነበሩ። በተለይ ነገሮች ካለፉ በኋላ፣ የሶሪያ ችግር ከተፈጠረ በኋላ መፅሀፌ ላይም ፅፌዋለው... የከንአን ናፍቆት ጋር፤ አላህ ካለ የሚወጣ ረጅም ልብ ወለድ ታሪክ ነው። አልጀዚራ ላይ ያየሁት ዜና ትልቅ ተፅእኖ ፈጥሮብኛል፤ አንድ ህፃን ሲናገር <<ምንበላው የለንም ተቸገርን>> ብሎ ሲያለቅስ አየሁት። ይሄ ህፃን ልጅ ነው... ቤተሰብ እንዳያጣ በተሰበረ አንደበት ሲያወራ አየሁት። ሶሪያዊ ነው እና የዚህ ሶርያዊ መበደል መነሻው እዛች ፊሊስጢን የምትባል ከተማ ውስጥ እንዳለ ተረዳሁ፤ ስለዚህ የኢትዮጲያ ሙስሊም ገዳይ አይደለም፣ በመላው አለም ያለ ችግር ሊፈታ የሚችለው እዛች ፊሊስጢን ላይ ያለ ችግር ሲፈታ ነው ብዬ ማመን ጀመርኩኝ። ስለዚህም ትግሌ ነገሬም ሁሉ ፍሊሲጢን ላይ ያለው ችግር ለመፍታት ነው። ኢንሻ አላህ አላህ ከፈቀደው የሚሳካ ይመስለኛል፣ በዛው አያይዤ እፅፋለሁ ያው መፃፍ ነው የምችለው። ከዛ ውጪ ሪያድ እንደሪያድ የተሰጠውን አቅም ተጠቅሜ እዛ ቦታ ላይ የተቻለኝን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ።

#ሂባ: ኢላህ በፊልስጢምና ህዝቦቸቿ ላይ እዝነቱን ያውርድልን

መነሻችን እንጂ መዳረሻችን ባልታወቀባት ዱንያ ላይ አሁን ላይ ከምትሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ ምን የተለየ ስራ ሰርተህ ማለፍን ትፈልጋለህ?
#ሪያድ: ምድር ላይ ፍትህን አስፍሬ ማለፍ ነው የምፈልገው። ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት አቅሳን መክፈት ይህን ስል ሙስሊሞች በእውቀትም በሁሉም ነገር የዳበሩ እንዲሆኑ የሙስሊሞች ጥናትና ምርምር ማዕከል ከወንድሞቼ ጋር እናቋቁማለን ብዬ አስባለሁ። ኢንሻላህ እውን ይሆናል በተለይ የሙስሊሞች ጥናትና ምርምር ማዕከል ሰፊ ፕሮጀክት ነው። እሱን አሳክተን በዛ ውስጥ የሚመጣው ትውልድ ስለ ፉልስጢን፣ ስለአለም እያሰበ ለህዝብ ፍትህ የሚጨነቅ ትውልድ እንደምናፈራ ምንም አይነት ጥርጥር አይኖረንም ኢንሻአላህ። አንዳንዴ ህልሞች ስናልማቸው እሩቅ ይመስላሉ ግን ሁሉንም ነገር ምድር ላይ ያደረጉት ሰዎች ናቸው። ያው ከአላህ በታች...በዚህ መንገድ ላይ ሳላሳካው እንኳን ብሞት እዳሳካሁት ሁሉ ይሰማኛል። ኢንሻአላህ ህልሜ ነው!

#ሂባ: ሪያድ ከረሱል ሲራ(ታሪክ)የትኛው ይበልጥ ይዐጅበዋል? የትኛውስ ይበልጥ ያሳዝነዋል?
#ሪያድ: ከረሱል ታሪክ ውስጤን የሚነካኝ ወላሂ የዳሩ ሰውር ታሪክ ነው። ዳሩሰውር ላይ የአቡበከር ፍቅር መስዋትነቱ ሁሉነገሩ ብቻ እዛ ውስጥ ያለው ታሪክ ለኔ የተለየ ነው... ወደ መዲና ሲሄዱ ሂጅራ ላይ ያለው ታሪክ ማለት ነው፣ ለኔ በጣም ትልቅ ቦታ አለው። ወደ ሃገራቸው የተመለሱበትን ሁኔታ ደግሞ ለኔ በጣም የሚያስደንቀኝ ታሪክ ነው። እንደ ድል ታሪክ ደግሞ ወደ መዲና ድል አድርገው ባለድል ተከታዮቻቸውን ይዘው ሲገቡ አንገታቸው ደፍተው የገቡበት ተናናሽነት ሁሌም በሁላችንም ዘንድ እንዲኖር እመኛለሁ።

#ሂባ: እንደው ከዝች ፈታኝ ዱንያ አንተን ከሁሉም በላይ ምን ያስፈራሃል?
#ሪያድ: እኔ ነገር አልወድም። ከሰው ጋር ብዙ መነካካት አይመቸኝም ከሁሉም ጋ በሚቻለው መልኩ ተግባብቶ ማለፍ ነው በምችለው መልኩ። እንዳልኩሽ ህልሜ ላይ ግን ምንም አይነት ፍርሃት የለብኝም በማይሆን ነገር ላይ ግን ራሴን መሰዋት ማድረግ አልፈልግም። መጎዳት አልፈልግም፣ በኢስላም መንገድ ላይ ከሆነ ምንም የሚያስፈራኝ የለም። ዱንያ ላይ ማጣትን አልወድም ትንሽ ይጨንቀኛል ሳጣ ኪሴ ባዶ ሲሆን ነፍሴ ትጨነቃለች መውጣት ሁላ ያስጠላኛል ምናምን... ሲኖረኝ ደግሞ ደስ ይለኛል። በቃ ረሃ መሆን ነው ይሄ ጭንቅ መተሳሰር ምናምን ሚባል ነገሮችን አልወድም ሁሌ ፍሪደም (ነፃ መሆን) ነው የምሻው ኢንሻአላህ! እንደዛ እንድንሆን

#ሂባ: ግጥም ላይ የዳበረ እውቀት እንዳለህ ይነገራል። ስነ ፁሁፍ ለሪያድ ምን የተለየ ነገር አለው? በዚሁ አጋጣሚ ከሰሞኑን መፀሃፉ የማሳተም ጭምጭምታ ደርሶኛል እውነት ነው?
#ሪያድ: የዳበረ እውቀት ይኑረኝ አይኑረኝ የግጥም አንባቢዎቼ ናቸው ይህን ነገር ሊፈርዱ የሚችሉት። እኔ መግጠም እወዳለሁ እሞክራለሁም። ስነፁሁፍ ለኔ የተለየ ነገር አለው። የህይወቴ ትልቅ ቦታ ነው፣ ህይወቴም ነው፣ ህይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ከጠያቂ በቀር የሚያውቀው ያለ አይመስለኝም። እና መፅሀፍ የማሳተም ጭምጭምታ ሳይሆን አንድ አሳትሜያለ፣ <ኢንቢያ> የተሰኘች የግጥሞችና የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነች 2007 የታተመች አለች። ከዛ ባሻገር አላህ ካለ በቅርቡ <የመራመድ እውነት> የተሰኝ ግጥም መደብልና የሃሳብ ማዕድ የያዘች መፀሃፍ ወደ ተደራሲያን የማደርስ ይመስለኛል። ከዛ ባሻገር ደግም <ኢክራም ናፍቆት> የተሰኘ በፊልስጢም ታሪክ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን የረዥም ልብወለድ ስራ የተሰራ ነው። መታረም ብቻ የሚቀራቸው ናቸው። <አድል ሰአት> የአጭር ልቦለድም... በተከታታይነት ይወጣሉ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው። የገንዘብ ምናምን ችግሮች ይኖራሉ እነሱ ነገሮች ተሟልተው ሁሉም ወደ አንባቢያን እነደሚደርሱ እምነቴ ነው።

#ሂባ: ጥበቃችንን ጉጉት ያዘለ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት በቶሎ እንድታደርሱልን ምኞታችን ነው እንደው ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት ካለ መድረኩን ልልቅቅልህ
#ሪያድ: ሂባ በጣም ነው የማመሰግነው።
ያው የተለየ ሃሳብ የለውም ግን ይጠቅማል ብላቹ ያላቹትን ትንሽም ብትሆን ውሰዱ ካልሆነ ተውት ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ!