Get Mystery Box with random crypto!

ከመፃህፍት መንደር (በTeam huda) አሰላሙ ዐለይኩም ውድ የሁዳ ቤተሰቦች ። ስለዓረፋ ሲነሳ | TEAM HUDA

ከመፃህፍት መንደር
(በTeam huda)

አሰላሙ ዐለይኩም ውድ የሁዳ ቤተሰቦች ። ስለዓረፋ ሲነሳ ተያይዞ የማይረሳው የአባታችን ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ታዛዥነት ሁላችንም ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። በሰዓቱ አባት ልጁን ለማረድ ሲወስን የሁኔታው ከባድነት አያጠራጥርም። ነገር ግን የኢስማኢል (ዐ.ሰ) ምላሽስ ምን ሆኖ ይሆን? እርዱ እንደሚፈፀም እርግጠኛ በሆኑበት ቀፅበት የተናገሩት የመጨረሻ ንግግራቸው ምን ነበር? ዛሬ.... ታዛዥነትን ከሳቸው አንፃር እናየው ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ ጋበዝናቹ....

.........

{...... የኢስማኢል የመታረጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ አባታቸውን እንዲህ በማለት መከሩ።

"አባቴ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ:-

~እጆቼን ና እግሮቼን አጥብቀህ እሰራቸው። ስቃይ ሲበረታብኝ እንዳላስቸግርህና የጌታዬን መብት እንዳላጎድል ይረዳኛል።
~ደሜ እንዳይረጭብህ ልብሶችህን በደንብ ሰብስብ።
~ቢላዋው በደንብ ሳለው፤ ነብሴ ቶሎ እንድትወጣ አንተም ቶሎ እንድትገላገል።
~ልብሴን ይዘህ ወደ እናቴ ሂድ ለመፅናናት ይረዳት ይሆናል።"

ኢብራሂም(ዐ.ሰ) አነዚህን ቃላት ከልጃቸው አንደበት ሲሰሙ ዓይኖቻቸው በእንባ ተሞሉ።አብዝተው አለቀሱ። እንዲህ አሉ:-

"የአላህን ትዕዛዝ እንድፈፅም ምን ያህል አገዝከኝ?" ቀጥለው እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ዱዐ አደረጉ:-

"ጌታዬ ባለሁበት ሁኔታ ትዕግስትን አላብሰኝ! እንግዲህ ምንም አልቀረኝም። አርጅቻለሁና እዘንልኝ!"

ኢስማዒልም አሉ:-

"ጌታዬ ትዕግስትንና ፅናትን አላብሰኝ። አባቴ ሆይ የጀነት በሮች ተከፍተዋል።"

መላኢካዎች በነገሩ ግራ ተጋብተው ተደናግሯቸው ሱጁድ በመውረድ አላህን ይማፀናሉ። <<ጌታችን ሆይ! ነብይህ ያንተን ፍቃድ ሊሞላ ለመሰዋት ተጋድማል!... እዘንላቸው >>ይላሉ።

"አባቴ! ከፍቅር ማሳያዎች አንዱ አለመዘግየት ነው! በላ የታዘዝከውን ቶሎ ፈፅም!" }

ቅንጭቡን እንተመከራቹበትን እናምናለን። አያይዛቹ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክሩ...

........<<ከላይ የሰፈረልን ቅንጭብ ከየትኛው መፅሃፍ የተወሰደ ነው?>>

ቀድሞ ለመለሰ አንባቢ የዒድ ሽልማታችንን የምናደርስ ይሆናል....

መልካም እድል.....ዒዱኩም ሙባረክ

@Re_ya_zan