Get Mystery Box with random crypto!

ቀለማት

የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የሰርጥ አድራሻ: @qelemaat
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.43K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ሀገርኛ ቀለም ያላቸው ስነ ልቦናዊ ረጢብ ስንቆች፣ ከህይወት ሰበዝ የተመዘዙ ጎምቱ ልምዶች፣ በአስተውሎት የጎለመሱ ሰብዓዊ ሃሳቦች፣ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ምክክሮች በድምፅ እና በጹሑፍ ወደ እናንተ የሚቀርቡበት የእናንተው ቀለመ-ብዙ ቻናል ነው !
Addis Ababa, Ethiopia

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-15 06:59:01 የሲግማ ደምብ - 11 - ከሴቶች መራቅ ሰላም ይሰጥሃል!

አልፋ ወንድ ሁሌም ቢሆን በሴቶች መደነቅ ፍላጎቱ ነው ፣ በመንጋው መሃል ሆኖ መጠበር ያስደስተዋል።ጋማ ወንድ ደግሞ ሴት በጣም ስለሚወድ ፣ አብሯቸው ሲሆን ውጤታማ ለመሆን ይነቃቃል ፣ ዴልታ ወንድ ሴትን ለግል ስሜቱ ማጭበርበር ደስ ይለዋል ፣ ኦሜጋ ወንድ ደግሞ የሴቶችን ስሜት መረዳት ትልቁ ፈተናው ነው ፣ሲግማ ወንድ ግን የሚፈልጋትን ሴት እንዴት በጁ ማስገባት እንዳለበት አብጠርጥሮ ያውቃል ፣ ሮማንቲክ ህይወት ላይ እንደ ፊልም አክተር የፍቅረኛውን ልብ መግዛት ይችላል ፣ ጎብዝ እና ታታሪ እንደሆነ ስለሚያውቅ ፣ ከሴቶች ተቀባይነትን ለማግኘት አይጥርም ፣ ከሴቶች መራቅ ሰላም እንደሚሰጠው ያውቃል! ሴቶች ሲግማ ወንድ ብቻውን ሆኖ ሲያዩት ፣ ሊያውቁት ይጓጓሉ ፣ የሲግማ ወንድን ለማውራት የሞክረች ሴት ፣ ስልክ ቁጥሯን ሳይቀበላት ይሸኛታል ፣ እንደምትፈልገው ያልሆነላት ይቺ ሴት ከሱ ጋር ማውራት ስለምትፈልግ በሆነ መንገድ አሳባ ስልክ እንዲለዋወጡ ታረጋለች።

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
800 viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:07:18
በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት - ስነ-ልቦናዊ የሆኑ የንባብ ስልቶችን በቀለማት የቲክቶክ አካውንት እንሆ:-

Study Tip 1 : ማንበብ ስታስቡ ድካም ለሚሰማችሁ ይሄ የንባብ ፍላጎታችሁን ያመጣዋል - Survey አድርጉ!

https://vm.tiktok.com/ZMYtEnVLc/
1.6K viewsቻLu, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 06:59:58 የሲግማ ደምብ - 10 - ከማንም ሰው በላይ ራስህን ታውቀዋለህ!

ቤታ ወንድ ለራሱ ያለው ግምት የወረደ ስለሆነ ፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ውድ እና ተዋቂ የሆኑ ብራንዶችን በመልበስ ክብር የሚገኝ ይመስለዋል ፣ ጋማ ወንድ ደግሞ እኔ ፍጹም የታመንኩ እና ጻድቅ ነኝ ብሎ ያስባል ፣ አልፋ ወንድ ስትሆን ሁል ጊዜ ሰዎች ጆሯቸውን ላንተ እንዲሰጡህ ታወራለህ ፣ ሲግማ ወንድ ከሆንክ ግን ከማንም በላይ ራስክን ታውቀዋለህ ፣ አዲስም ለበስክ አሮጌ ሁሌም አንተ አንተ ነህ ፣ ሁሌም ልደነቅ ባይ አትሆንም ፣ ሰዎች ሲያደንቁህ ግን በአክብሮት ታመሰግናለህ ። ወዴት መሄድ እንዳለብህ ስለምታውቅ ማንም ወደፈለገበት እንዲነዳህ አትፈልግም። ድክመቶችህን ስለምታውቅ ፣ ታነባለህ ሰዎችን ታማክራለህ ፣ Google ታረጋለህ ፣ ጠንካራ ጎኖችህን ሰለምታውቅ አውጥቶ መጠቀም አይከብድህም! እንዲህ አይነት ሰው ብዙ የለምና ሰዎች አንተ ብትመራቸው ደስ ይላቸዋል ፣ ትልቁ ችግር ግን አንተ ብቻህን መሆን ትፈልጋለህ! ያንን ሲያዩ ደግሞ የምትኮራ ይመስላቸውል! ይህንን ባህሪህን ለማሻሻል ሞክር!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership እጩ ባለሞያ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaa
1.0K viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 06:59:58 የሲግማ ደምብ - 9 - እናትህን እና አባትህን ታከብራለህ!

ዴልታ ወንድ የራሱን ችግር ቤተሰቦቹ ላይ ማላከክ ደስ ይለዋል !ሁል ጊዜ ሰበበኛ ነው ፣ ይህን ማረጉ ለለውጥ እንዳይነሳ ያረግዋል ፣ አልፋ ደግሞ ወንድ እናት እና አባቱን አይሰማም! ቤታ ወንድ በቤተሰቦቹ ቁጥጥር ስር ነው ፣ አድርግ የተባለውን ያረጋል ፣ አታርግ የተባለውን አያረግም ፣ ጋማ ወንድ ከዚህ በተለየ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚሆን ይልቅ ራሱን በሴት ጓደኞቹ መሃል ቢያገኝ ደስ ይለዋል፣ ሲግማ ወንድ ግን ቤተሰቦቹን ያከብራል ፣ ቤተሰቦቼ በተገቢው መንገድ አላሳደጉኝም ብሎ ቢያስብ እንኳ ይቅር ይላቸዋል ፣ ሲግማ ወንድ ያባቱን ምክር ይሰማል ፣እናቱን ደግሞ ይንከባከባታል ! ቤተሰቦቹ አርግ የሚሉትን ለማረግ ምክንያት ይፈልጋል ፣ ቤተሰቦቹ ያለፍቃዱ እጣፋንታውን ለመወሰን በሞከሩ ጊዜ አክብሮት ባለው መንገድ ተደራድሮ ሃሳባቸውን ያስቀይራቸዋል!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership እጩ ባለሞያ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
2.0K viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 00:02:10 ተግባር /Taking Action

ምኞት አያከብርም፤ ደመና አያበቅልም በቃ ጠንክሮ መስራት ነው። ስሩ

3ቱ የ “መ" ህጎች
መስራት
መስራት
አሁንም መስራት

ፈረስ ያደርሳል እንጅ አይዋጋም። ፈረሱ ካደረሰን ጦርና ጋሻውን ይዞ መዋጋት የኛ ፋንታ ነው

ቻLu lGech  - Upcoming Psychologist from Addis Ababa University

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
284 viewsGech, 21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:03:51 የምርም ያለንን አቅም/ልካችንን እናውቀዋለን ወይ
ከዶሮ መካከል የወደቅን ወፍ አንሁን
”መነሻችሁ የት ነው?" ተብላችሁ ብትጠየቁ መልስ አላችሁ። “መድረሻችሁ የት ነው?" ብትባሉስ። መልስ እርግጠኛ ነኝ የላችሁም። ለምን? የሰው ልጅ potential limited ቢሆንም ነገር ግን infinite'ም ነው።
ጠይቁት ራሳችሁን “Where is ur destination?"

አይቻልም ያልነውን ነገር እንደማይቻል ያመነው ሞክረነው ነው ወይስ ሰዎች እንደማይቻል ስለነገሩን?

ምሳሌ ከመጥቀስ ወጥተን ራሳችን ምሳሌ መሆን ይጠበቅብናል

አይተን እና ሰምተን ከመጣነው ነገር በላይ የኛ ልክ እና አቅም ከፍ ማለት ይችላል

Think out of the box
ቻLu lGech  - Upcoming Psychologist from Addis Ababa University

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
879 viewsGech, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:21:51 ሰላም ሰላም ምርጥ የተባሉ #channel ልጋብዛችሁ

minister of education 65k
minister of education 65k


ቀለሜ ለተማሪዎች
ቀለሜ ለተማሪዎች


Top students
Top students


A+ አካዳሚ
A+ አካዳሚ


English በቀላሉ ለመልመድ
English በቀላሉ ለመልመድ


ቀለማት psychology
ቀለማት psychology

Brilliant አካዳሚ
Brilliant አካዳሚ


ትምህርት news
ትምህርት news


ትምህርት of education
ትምህርት of education


G+ አካዳሚ
G+ አካዳሚ


የድሮ መፅሐፍ
የድሮ መፅሐፍ


English & mathematics learning
English & mathematics learning
1.1K viewsLij ãbďisă, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 06:59:58 የሲግማ ደምብ - 8 - ረጋ ብለህ ትራመዳለህ !

ሲግማ ወንድ ብቻውን ሲራመድ ረጋ ብሎ ነው ፣ ረጋ ብሎ መራመድ የአስተዋይነት ምልክት ነው ፣ የሲግማ ወንድ እያንዳንዱ እርምጃ በተመስጦ የተመላ ነው! ሲግማ ወንድ አካባቢውን እየቃኘ ፣ የፈጣሪን ስራ ሓልዎቱን እና መግቦቱን እያስተዋለ ተፈጥሮን እያደነቀ ፣በተመስጦ ይራመዳል! ቤታ ወንድ የበታችነት ስሜት ስለሚሰማው አንገቱን ደፍቶ መሬት ለመሬት አቅርቅሮ ይራመዳል ፣ አልፋ ወንድ ትኩረት ማግኘት ስለሚወድ እያኮበኮበ እንዳለ አውሮፕላን እጁን አወራጭቶ ደረቱን ገልብጦ ይራመዳል ፣ ሲግማ ጋር እንዲህ ብሎ ነገር የለም ፣ ሁሉም ነገር በእርጋታ ነው የሚከወነው ፣ሰዉነቱን አያስጨንቅም ዘና ብሎ ከባቢውን እየቃኘ ይሄዳል ፣ በዚህም መልኩ በስነ ልቦናው ዓለም (the positive hallo effect ) የሚባለውን ሞገስ ከባቢው ያገኛል! ምን ማለት መሰላችሁ ፣ ሰዎች ሁሉ እንዱሁ ሲያዩት ይገረማሉ ፣ እሱን ለማወቅ ያላቸው ጉጉት ከፍ ይላል! ሴቶች ጓደኛው መሆን ምኞታቸው ነው! ችግሩ ግን ሲግማ ወንድ ከማህበራዊ ህይወቱ ይልቅ ስራ እና ትምህርቱ ላይ ነው ማተኮር የሚፈልገው!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
2.0K viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:00:34 ራስን ማወቅ/Self Awareness _-_ ክፍል -2

እንዴት ራሳችንን ማወቅ እንችላለን
ወደኋላ ተመልሰን ልጅነታችንን ማሰስ
አሁን ላይ የት እንዳለን እና ምን እየሰራን እንደሆነ ማወቅ- በክፍል አንድ

ክፍል -2
ያለንን Personality ማወቅ
ማንነትን ማወቅ ማንችለውን ነገር እንድናውቅ ብቻ ሳይሆን ለመቻልም ይረዳል

Alfred Nobel - አሁን ላይ በየአመቱ የሚካሄደው የ Nobel Prize መስራች U-turn ወይም እጥፋት ምክንያት የሆነው “ሳይሞት ሞተ" የታሪክ አጋጣሚ

እስከመጨረሻው ስሙት

ቻLu lGech  - Upcoming Psychologist from Addis Ababa University

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
2.3K viewsቻLu, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 06:59:58 የሲግማ ደምብ - 7 - ትውፊት ፣ ስርዓት ፣ ዶግማ በሚባሉ ነገሮች መታጠር አትፈልግም!
(ማሳሰቢያ ስለ ሃይማኖታዊ ዶግማ አደለም እያወራን ያለነው)

አልፋ ወንድ በራስ መተማመን ቢኖረውም የማህበረሰቡን ትውፊት ፣ ስርዓት እና ዶግማ የሚባሉ ነገሮችን ይጠብቃል ፣ ሲግማ ወንድ ግን በእንደዚህ አይነት ነግሮች ተወስኖ መታጠር አይፈልግም ፣ እይታውን ያጠቡበታል። ሁልጊዜም ቢሆን አድማስ ተሻግሮ ነው ማሰብ የሚፈልገው ፣ እያንዳንዱ ስርዓት እያንዳንዱ ትውፊት የሚደረግበትን ምክንያት ማውቅ ይፈልጋል ፣ ካልሆነ ግን በራሱ አለም መኖር ደስታው ነው ፣ ይህ ማንነቱ ደግሞ ከሌሎች በተለየ የነጻነት ስሜት ይሰጠዋል፣ ጓደኛህ ሲግማ ወንድ ከሆነ እና ትውፊት፣ ዶግማ ፣ ስርዓት የሚባሉ ነገሮችን እንዲከተል ከፈለክ ፣ በምክንያት ይሄ እኮ እንዲህ ስለሆነ ነው የሚደረገው ብለህ አስረዳው! ሲግማ ወንድን እንዲህ አይደረግም ብሎ በስሜት መናገር ፣እልህ ወስጥ ይከተዋል! ሲግማ ከሆንክ በልማድ የሚደረጉ ነገሮችን መመርመርህ ከሰዎች አንድ እርምጃ እንድትቀድም ያረግሃል!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
2.5K viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ