Get Mystery Box with random crypto!

ቀለማት

የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የሰርጥ አድራሻ: @qelemaat
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.43K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ሀገርኛ ቀለም ያላቸው ስነ ልቦናዊ ረጢብ ስንቆች፣ ከህይወት ሰበዝ የተመዘዙ ጎምቱ ልምዶች፣ በአስተውሎት የጎለመሱ ሰብዓዊ ሃሳቦች፣ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ምክክሮች በድምፅ እና በጹሑፍ ወደ እናንተ የሚቀርቡበት የእናንተው ቀለመ-ብዙ ቻናል ነው !
Addis Ababa, Ethiopia

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-21 22:46:59
ከፖስቱ እውነቱ! ይህን ያውቃሉ

የጥላቻ እና የተሳሳተ መረጃ ያያዘ የማህበራዊ ሚዲያ መጣጥፍ ላይ የትችት ሃሳብ መስጠትዎ መረጃው ለብዙሃኑ እንዲደርስ የበኩልዎን እየተወጡ ነው!

የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም ደግሞ መልካም የመረጃ እና የእውቀት ምንጮችን ለማገዝ ፣ የሶሻል ሚዲያዎችን አልጎሪዝም እንወቅ!


#የሚዲያ_አሻራዬ #ከፖስቱእውነቱ #ነቄፖሳች #ያላማከርኩትንአለጥፍም #ሁሌምአጣርቼ #ያገባኛል #ሳታጣራአታብራራ #አርቆአሳቢ #ተሰሚ

መርሳ ሚዲያን ካሉበት ይከተሏቸው!

Facbook: facebook.com/Mersamedia
Twitter: twitter.com/mediamersa
Youtube: youtube.com/@mersamedia
Instagram: instagram.com/mersamedia
TikTok: Tiktok.com/@mersamediainstitute

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

JOIN US NOW :  @qelemaat |  @qelemaat
1.9K viewsቻLu, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 15:29:32 በኢትዮጰያ ላይ ላሉ የሳይኮሎጂ ተማሪዎች በሙሉ አዲስ ዜና


በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተከፈተ አዲስ Group

አላማው :-

በተለያየ ዩኒቨርስቲ  እና ኮሌጆች ያሉ ተማሪዎች አንድ ላይ በማምጣት ትውውቅን መፍጠር

የስራ እና የትምህርት ዕድል መረጃዎችን መለዋወጥ

የእውቀት ሽግግር እና የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ማረግ

በየ አመቱ ለሚሰጥ Exit Exam ዝግጅት ተማሪዎች እንዲተጋገዙ ማስቻል

በመጨረሻም ፣በሁሉም ክልሎች እና መስተዳደሮች ላይ ላሉ የሳይኮሎጂ ተማሪዎች መብት እና ጥቅምን የሚያስከብር ተቋም መፍጠር  !

ADD በማረገ ብርቱ ክንድ እንዲኖረን የበኩላችሁን አድርኩ!

https://t.me/Ethiopian_Psychology_Students
3.8K viewsቻLu, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 00:27:07 ክረምታችሁን እንዴት እያሳለፋችሁት ነው

ክረምት ላይ የእረፍት ጊዜዬን እንዴት ባሳልፈው ላተርፍበት እችላለው

Written by: ቻLu
Reviewed by: Getachew


ብዙዎቻችን እድሚያችን እየገፋ ሲሄድ እንደተሸወድን የሚገባን ፣ ክረምት ላይ ያኔ ብናረጋቸው ኖሮ የኑሯችን ስንቅ ይሆኑን የነበሩ ተግባራት ብለን ልናስባቸው የምንችላቸው አሁን ላይ ብናደርጋቸው ጥሩ ትዝታ ህይወታችን ላይ ደርበውልን የሚያልፉ ሰበዞች

ደስ ያላችሁን ምረጡ እና ወደ ተግባር ግቡ እመኑን፣ የኋላ ሗላ በምርጫችሁ ትኮራላችሁ!

የክረምት ወቅት ለብዙዎቻችን ያሳለፍነውን ዓመት ጊዜ ገዝተንና ትዝታ ተዝተን እንዴት እንዳለፈ እና እንዳሳለፍነው ወደኋላ መለስ ብለን የምንቃኝበት፣ የተለየ የእረፍት ጊዜ የምናሳልፍትበት፣ ሩጫና ውድድር ከበዛበት ዓለም ትንሽ ፋታ አግኝተን ከራሳችን ጋር የምንሆንበት፥ የምናወራበት፣ ለወደፊታችንም ወይም ለሚመጣው ዓመት የምንዘጋጅበት ደስ የሚል ወቅት ነው! ተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት ይማራሉ፤ መጽሐፍ ያነባሉ፣ ከጓደዶቻቸው ጋር ጊዜ ያሳልፉሉ (በተለይ የግቢ ተማሪዎች ሌላ ጊቢ ካሉ የቀድሞ የhigh school ጀለሶቻቸው ጋር ተገናኝተው የፈረደበትን አስተማሪ ሲጨፈጭፉ (F የጠጡበት ኮርስ ካለማ አይጣል ነው፤ አይምሩትም )፣ ግቢ ውስጥ ያለችውን crushቸውን ልክ ፍቅረኛቸው እንደሆነ/ች አድርገው ሳክሳቸውን ሲቶኩ )፣ ሰራተኞች የትምህርት ደርጃቸውን ከፍ ለማረግ የክረምት ትምህርት ይማራሉ ፣ ብዙዎች ዘመድ ጥየቃ ብለው ከተሜዎች ወደ ገጠር ፣ የገጠር ተወላጆች ደግሞ ወደ ከተሜዎች ይመጣሉ...... በጣም ብዙ
እናንተስ ዘንድሮ በዚህ ክረምት ምን አሰባችሁ? የሚቀጥሉት ዝርዝሮች ሊጠቅሟችሁ ከቻሉ ብለን አዘጋጀንላችሁ! መልካም ንባብ

መንፈሳዊ ትምህርቶችን መማር(ነገረ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ)

ለነፍስ ምግቧ የእግዜብሔር ቃል ነው እንዲል መጽሐፍ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናቶች መርሃ ግብር ውስጥ መሳተፍ፣ መዝሙር ማጥናት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች በክረምት የሚሰጧቸው ትምህርቶች ካሉ በየ ቤተ-ክርስቲያናችሁ አጥቢያ ፈልጋችሁ መመዝገብ እና የእግዚአብሔርን ቃል መማር አንዱ በክረምት ልታረጉት የምትችሉት ነገር ነው።


ልዩ ልዩ የኪነ- ጥበብ እና የግብረ ገብ ስልጠናዎችን መወሰድ


እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ለትምህርት እና ለሞያ ህይወታችሁ ላይጠቅሟችሁ ይችላሉ ፣ ነገር ግን ራሳችሁን በተለየ መንገድ የምተገልጹበትን እና በራስ መተማመናችሁን ልታሳድጉበት የምትችሉባቸው አማራጮች ናቸው። ደግሞም ሁሉም ለሞያችሁም ሊጠቅሟችሁ ይችላሉ። ለምሳሌ እንደ በገና ያሉ የዝማሬ መሳሪያዎችን መማር ፣ የምግብ አሰራር ሙያ መማር ፣ የጓሮ አትልክታችሁን እንዲሁም ግቢያችሁን ጋርደኒንግ ማስዋብ ፣ የግጥም ፣ የስነ ፅሁፍ ፣ የትወና እና ሌሎች መሰል ክህሎቶችን እንደየ ምርጫችሁ መማር እንዲሁም መሳተፍ እንደ ቆንጆ አማራጭ ልትወስዱት ትችላላችሁ።

ትምህርታዊ እና ሙያዊ ስልጠናዎችን መውሰድ


ይህንን ከ ግብረ ገብ ስልጠናዎች ለይቼ ያወጣሁት ከዛኛው የተለየ ዓላማ ያለው ይዘቱም የተለየ ነው ብዬ ስላሰብኩ ነው። በተለይ በሚቀጥለው ዓመት የትምህርት እና የስራ ህይወታችሁ ላይ መሻሻልን ማየት ከወደዳችሁ ፣ እንደያላችበት Department እና የትምህርት ደረጃ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ የአጭር ጊዜያት ስልጠናዎችን መውሰድ ፣ ክፍያ ያለውም የሌለውም Internship መስራት፣ ባላችሁበት የትምህርት field Volunteer ማድረግ፣ በጣም excel ማረግ የምትፈልጉትን የትምህርት በእውቀትም በልምድም እንድትበስሉበት በሙያው ዘርፍ ያሉ ሰዎችን በስልክም በአካልም ማውራት፣ እውቀታችሁ advanced እንዲሆን ከፈለጋችሁ ደግሞ ለፈተና ካጠናችሁበት መንገድ ወጥታችሁ ገጽ በገጽ ጊዜ ሰጥታችሁ ማንበብ ሌላኛው ክረምታችሁን ውብ የምታረጉበት አማራጭ ነው።


የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ማድረግ

ሰዎችን መርዳት እጅግ ከማስደቱም በላይ በእንዲህ አይነት የማህበረሰብ ግብረ ሰናይ ተሳትፎች ላይ መሳተፋችሁ ፣ ሰዎችን በማገልገል ውስጥ ያለውን በጎ የህይወት ትርጉም የምታጣጥሙበት ፣ ከተለያዩ አዳዲስ ሰዎች ጋር የምትተዋወቁበት ፣ ለተለየ የስራ እና የትምህርት እድል የምትታጩበት ፣ ከዚያም አልፎ ደግሞ ተገቢውን እውቅና እና ሽልማት ልታገኙበት የምትችሉበት መድረክ ነው። ልብ በሉ ፣ አሁን ላይ ያሉ የሰራ ዕድሎችን ለማግኘት ፣ ከውጭም ሆነ ከሃገር ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት ፣ የተለያዩ ተቋማት ላይ ለተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለመሾም እንዲህ አይነት ተሳትፎዎች ላይ መኖራችሁ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው። የበጎ አድራጎት ተሳትፎዎች ከማንም ምንም ሳትጠብቁ ለነፍሳችሁ ሃሴት የምተሰሩዋቸው መልካም ሰራዎች ቢሆኑም ፣ እንዲህም አይነት እድሎች እንዳሉ ማውቁ አይከፋም።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማረግ

የሰውነት ከብደታችሁን መጨመር አልያም መቀነስ የምትፈልጉ ፣ የሰውነት ቁመናችሁን በማስተካከል ሸንቀጥቀጥ ማለት ለምትፈለጉ ፣ ሰውነታችሁ በቂ እረፍት እየሰጣችሁ ፍርጥምጥም ለማለት ክረምት አመቺ ጊዜ ነው። በየ አካባቢያችሁ የጂም ፣ ካራቴ ፣ ቴክዋንዶ እና የስፖርት ቡድን ውስጥ በመግባት መስራት፣ ቤት ውስጥ ወይም በአካባቢያችሁ ባለ ነገር መስራት ትችላላችሁ። እንደየ ምርጫችሁ እና አቅማችሁ።

ቤተሰብ፣ ዘመድ ጥየቃ እና ሀገር መጎብኘት

እንዲሁ ሲታይ ቀላል ሊመስል ይችላል፤... የናፈቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ ጋር አብሮ ማሳለፍ፣ ዘመዶቻችሁን መጠየቅ ግንኙነታችሁንም ከማስቀጠል ባለፈ ሆቴል Book እንደማስደረግ በሉት ፣ ምንም ባልቸገራችሁ እና ባላጣችሁበት ጊዜ የጀመራችሁት ዝምድና ፣ ኋላ ላይ ከችግር ያወጣችኋል ፣ ድንገት ሩቅ አገር ለ ስራ ወይ ለትምህርት መሄድ ቢኖርባችሁ ፣ ለትንሽ ቀናት ሰፈር መቀየር ቢኖርባችሁ ፣ በቃ ዘና ብላችሁ የምትቆዩበት ፣የምታድሩበት ቦታ አገኛችሁ ማለት አደል ፣ ሊያውም ባይተዋር ሳትሆኑ ፣ ያ ብቻ አደለም ሃገሩን እና ሰፈሩን መውጫ መውረጃውንም ለማወቅ ይጠቅማችኋል።

ለስለስ ያሉ ሙዚቃዎችን መስማት፣ ከዚህ ቀደም እንሰማቸው፣ እንከታተላቸው የነበሩ የሬዲዮ ወይም የቲቪ ፕሮግራሞች ግቢ ከገባን በኋላ ግን ጊዜ በማጣት ወይም በሌላ ምክንያት መስማት፣ መከታተል አቋርጠን ከነበር እንደ አዲስ መከታተል፣ መስማት መጀመር ጥሩ ስሜት ሊፈጥርብን ይችላል። እንዲሁም እንደ አዲስ ሰምተን የእኛን ብስለት ልንለካበት እንችላለን። ይሄም ጥሩ የክረምት ጊዜ ማሳለፊያ አማራጭ ነው።

እናንተም ጨምሩበት፤ የተለየ ልምድ ካላችሁ ደግሞ አጋሩን። ክረምታችሁ የእረፍት ጊዜ የሆነላችሁ ተማሪዎች መልካም የክረምት ጊዜ እንድታሳልፉ ምኞታችን ነው

ቻLu | ጌታቸው- Upcoming Psychologist at AAU

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

JOIN US NOW : @qelemaat |  @qelemaat
5.5K viewsGech, edited  21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 19:59:59
ልዩ ቅናሽ 

ኦሪጅናል ኤርፖድ መግዛት ለፈለጋችሁ ሁሉ !


1200ብር   700 ብር ብቻ

     አምስት ቀን ሚቆይ ቻርጀር
      Touch ሴንሰር ያለዉ
       packed
       play suspended
       With charger

ለጊዜዉ 3 ደርዘን (36 ፍሬ ብቻ) ሰላስመጣን  ቶሎ ከማለቁ በፊት ይፍጠኑ

ግቢ ዉስጥ ያላችሁ ተማሪዎች ከ ግቢዉ ኤጀንቶቻችን መዉሰድ ትችላላችሁ።

  ከግቢ ዉጪ ላላችሁ ፈላጊዎች አዲስ አበባ ዉስጥ በነፃ ያሉበት አከባቢ ማድረስ ጀምረናል


መግዛት የፈለጋችሁ ደንበኞች ከታች በተቀመጠዉ የቴሌግራም አድራሻ ዉስጥ በመግባት
1. ስልክ ቁጥራችሁን፤
2. የት አከባቢ እንደምትገኙ እና
3 ለመቀበል የሚመቻችሁን ቀንና ሰዓት ፃፉልን።

የቴሌግራም አድራሻችን @AAU_Shop

አዳዲስ እቃዎች ስናስመጣ ለመመልከት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@AAU_Online_Shopping
4.3K viewsቻLu, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 08:31:50 ክፍል ሁለት

...... በአጠቃላይ ለስኬት አንዱ ቁልፍ ግብ ማስቀመጥ ሲሆን ግብ ስናስቀምጥም ከላይ የዘረዘርናቸውን 5 ነገሮች ማካተት አለበት፡፡ ግባችን እነዚህን ነገሮች ሲያሟላ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ግባችንን ከማሳካት ጋር ይሆናል፡፡

እነዚህ ማንኛውም ግብ ሊያሟላቸው የሚገቡ ነገሮች ቢሆኑም የበለጠ ስኬታማ ለመሆን ተጨማሪ በግብ ውስጥ መካተት እንዳለባቸውም የተለያዩ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የተወሠኑትን ለመጥቀስ ያህል ግብ በምናስቀምጥት ጊዜ ግባችን ሰፊ መሆን አለበት፡፡ ግባችን በጣም ትንሽ ከሆነች በቁርጠኝነት እንድንሠራ እያደረገንም፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥረን ለመስራት ብናቅድ ይህን እንዳሣካን ባለንበት ቀጥ ብለን ነው የምንቀረው፡፡ ስለዚህ ግባችን ሠፊ መሆን አለበት። ሌላው ግባችን ማካተት ያለበት ነገር ደግሞ ዉጣ ውረድ የሚጠይቅ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ስኬት የዉጣ ውረድ ውጤት ነው፡፡ ነገሮች አልጋ በአልጋ ከሆኑልን ብዙም ውጤታማ አንሆንም፡፡ የተወሳሰቡ ሰራዎችን የሚከተል ግብም ተመራጭ ነው፡፡ ሁሌ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ስንሠራ ብዙዎቻችን እንሰለቻለን፡፡ በመሆኑም የበለጠ ስኬታማ ለመሆን ግባችን ውስብስብ ስራዎች የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡

ሰዎች ለምን ግብ አያስቀምጡም?

ስኬታማ መሆንን የማይፈልግ ሰው ይኖራል ብሎ ማሠቡ ተገቢ ባይሆንም ግብ የማናስቀምጥ ግን ብዙዎቻችን ነን፡፡ ከስኬት ቁልፎች አንዱ ግብ ማስቀመጥ እደሆነም ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ነገር ግን ግብ ሳያስቀምጡ ስኬት “ላም አለኝ በሰማይ” ነው፡፡ ታዲያ ሰዎች ለምን ግብ አያስቀምጡም? ብለን መጠየቅ ያሥፈልገናል፡፡

ግብ ላለማስቀመጥ ዋናው ምክንያት የምንፈልገውን አለማወቅ ነው:: ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን ማወቅ ቀላል መስሎ ሊታየው ይችላል፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን በትክክል ማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነዉ::ምክንያቱም ፍላጎታችን በየጊዜዉ የሚቀያየር በመሆኑ ነዉ::ለዚህም ነው ያየነው ሁሉ የሚያምረን፡፡ የሚያዝናና ኳስ ስናይ እግር ኳስ ተጨዋች መሆን ያምረናል፣ የኦሊምፒክ ሰሞን ደግሞ ሯጭ መሆን ያምረናል፡፡ ፊልም ስናይ አርቲስት መሆን እንፈልጋለን፣ አንድ የፈጠራ ስራ ስናይ ጥሩ ኢንጂነር መሆን ያምረናል፣ የሲ አይ.ኤ ንና ሞሳድን ዝና ስንሰማ ሰላይ መሆን ይከጅለናል ::የተሳካ ቀዶ ጥገና ስንሰማ ደግሞ ዶክተር መሆን በእጅጉ እንመኛለን:: አሪፍ ህንፃ ስናይ ባለ ሐብት መሆን እንቋምጣለን፡፡ ኧረ ስንቱ…፡፡ ስለዚህ የእኛ ትክክለኛ ፍላጎት የትኛው ነው? ፍላጎታችንን በትክክል ካወቅን ግብ ማስቀመጥ አይከብደንም፡፡

“ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ” እንዲሉ አንድ ወጣት የስኬታማነትን ቁልፍ ለማወቅ ፈልጎ ዝነኛውን የግሪኩ ፈላስፋ ሶቅራጥስን የስኬትን ቁልፍ እንዲነግረው ጠየቀዉ ይባላል፡፡ ሶቅራጥስም ወጣቱን ና እየሄድን እነግርሃለሁ ብሎ በባህር ውስጥ እየተራመዱ መሄድ ጀመሩ ፡፡ እየሄዱ እያለም ሶቅራጥስ ወጣቱን ምን እንደሚፈልግ ዳድም ይጠይቀዋል፡፡ ወጣቱም የስኬት ምስጢርን እንድትነግረኝ ፈልጌ ነው ይለዋል፡፡ ባሕሩ መሀል እንደደረሱ ሶቅራጥስ ወጣቱን አንገቱን ይዞ አሰጠመው፡፡ ወጣቱም አየር ለማግኘት ይፈራገጥ ጀመር፡፡ ሶቅራጥስ ግን ሊለቀው አልቻለም፡፡ ወጣቱም ኧረ እባክህ ልቀቀኝ ልትገለኝ ነው እያለ ቢጮህም ሶቅራጥስ አለቀቀውም፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሶቅራጥስ ወጣቱን ከውሃው አወጣውና ለምን ይፈራገጥ እንደነበርና እንዲለቀው የጠቀበትን ምክንያት ይጠይቀዋል፡፡ ወጣቱም አየር ፈልጌ ነዉ ይለዋል፡፡ሶቅራጥስም ወጣቱን “አየህ አየር እንደሚያስፈልግሀ ስታውቅ እንደዚህ ከተፈረገጥክ ስኬታማ መሆን ከፈለግህም መጀመሪያ ምን እንደምትፈልግ እወቅ” ብሎ መለሰለት ይባላል፡፡

ስለዚህም ወደ እንቅስቃሴና ትጋት የምንገባው ውስጣችን እንድናገኘዉ የሚፈልገዉን ነገር ማወቅ ስንችል ነው፡፡ ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው በመጀመሪያ ፍላጐቱን ማወቅ ግድ ይለዋል፡፡ ነገሩን ስናጠቃልለው ሰዎች ግብ የማያስቀምጡበት ዋነኛው ምክንያት ፍላጐታቸውን ማወቅ አለመቻላቸው ነው፡፡ ግብ ከማስከመጣችን በፊት ፍላጐታችንን ጠንቅቀን ማወቅ ታላቅ የቤት ሥራ ይሆናል፡፡

2. የውስጥ መነሳሳት (Motivation)

ግብ ስላስቀመጥን ብቻ ስኬታማ እንሆናለን ማለት አይደለም፡፡ ግባችንን ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት ያስፈልገናል፡፡ በመሆኑም ሁለተኛው የስኬት ቁልፍ ውስጣዊ መነሳሳትን መፍጠር ነው፡፡ ይህን ውስጣዊ መነሳሳታችንን ለማምጣት ደግሞ ያቀድነውን እቅድ በተለያዩና ሊታዩን በሚችሉ ቦታዎች ማስቀመጥ ይመከራል፡፡ ያስቀመጥነው ግብ ሁልጊዜ ስናየው የበለጠ ለመስራት እንነሳሳለን፡፡ ሌላው ውስጣችንን ለማነሳሳት ልንጠቀምበት የምንችለው ነገር ግባችንን ካሳካን በኋላ ልናገኘው የምንችለውን ስሜት በማሰብ ነው፡፡ ግቤን ሳሳከ ምን አያለሁ፣ ምን እሰማለሁ፣ ምንአይነት ስሜት ይሰማኛል የሚሉትን ጥያቄዎች ሁል ጊዜ በማንሳት ውስጣዊ መነሳሳትን ልናመጣ እንችላለን፡፡

3. ፅናት (persistence)

ስኬት ጽናት ለሌላቸዉ ጀርበዋን የምትሰጥ ወይዘሮ ናት፡፡ከእያንዳንዱ ስኬታማ ሰዉ በስተጀርባ ጽናት ይኖራል፡፡ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሆነዉለት ስኬታማ የሆነ ማግኜት ይከብዳል፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት ያህልም ሁለት ዋሽንት የሚነፉ ሰዎች ነበሩ ይባላል፡፡አንደኛዉ ሲነፋ ሁሌም ዝናብ ይዘንባል ፡፡ሌላኛዉ ሲነፋ ግን አይዘንብም፡፡ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ በሚዘንብለት ሰዉ የሚያዩት ሁሉ ይገረሙበታል፡፡ ሁለቱም ግን ተመልካች አላቸዉ፡፡ከእለታት በአንድ ቀን ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ የማይዘንብለትን የሚመለከቱት ሰዎች ሲነፋ የሚዘንብለትን የሚመለከቱትን ሰዎች ዋሽንት ሊያሰሙዋቸዉ ጋበዙዋቸዉ፡፡ተጋባዦችም ዋሽንቱን ከሰሙ በሁዋላ ለጋበዙዋቸዉ ሰዎች እነርሱም በተራቸዉ ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ የሚዘንብለትን ሰዉ ያዩት ዘንድ ጋበዙዋቸዉ:: ተጋባዦች ሲያዩ ሰዉዬዉ ሲነፋ ከቆየ በሁዋላ ዝናብ ይዘንብ ጀመር:: በጣም ተገረሙ ::ዋሽንት የሚነፋዉንም ሰዉየ እርሱ ሲነፋ ለምን ዝናብ እንደሚዘንብ ይነግራቸዉ ዘንድ ጠየቁት::ሰዉዬዉም "አይ እኔ ስነፋ አይደለም ዝናብ የሚዘንበዉ ነገር ግን ዝናብ እስከሚዘንብ ነዉ የምነፋዉ"ብሎ መለሰላቸዉ ይባላል::አዎ እኛም ያቀድነዉ እስከሚዘንብልን ድረስ መጽናት ያስፈልገናል:: ይህ ካልሆነ ግን ስኬትን ማምጣት ከባድ ነዉ:: በመጨረሻም
CHANGE YOUR WAY BUT NOT YOUR GOAL" ብዬ ላብቃ።
መልካም የስኬት ጊዜ!!!

Via unknown source

ቀለማት - ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው።

Join us @qelemaat/@qelemaat
3.7K viewsGech, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 20:10:01
ልዩ ቅናሽ 

ኦሪጅናል ኤርፖድ መግዛት ለፈለጋችሁ ሁሉ !


1200ብር   700 ብር ብቻ

     አምስት ቀን ሚቆይ ቻርጀር
      Touch ሴንሰር ያለዉ
       packed
       play suspended
       With charger

ለጊዜዉ 3 ደርዘን (36 ፍሬ ብቻ) ሰላስመጣን  ቶሎ ከማለቁ በፊት ይፍጠኑ

ግቢ ዉስጥ ያላችሁ ተማሪዎች ከ ግቢዉ ኤጀንቶቻችን መዉሰድ ትችላላችሁ።

  ከግቢ ዉጪ ላላችሁ ፈላጊዎች አዲስ አበባ ዉስጥ በነፃ ያሉበት አከባቢ ማድረስ ጀምረናል


መግዛት የፈለጋችሁ ደንበኞች ከታች በተቀመጠዉ የቴሌግራም አድራሻ ዉስጥ በመግባት
1. ስልክ ቁጥራችሁን፤
2. የት አከባቢ እንደምትገኙ እና
3 ለመቀበል የሚመቻችሁን ቀንና ሰዓት ፃፉልን።

የቴሌግራም አድራሻችን @AAU_Shop

አዳዲስ እቃዎች ስናስመጣ ለመመልከት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@AAU_Online_Shopping
3.2K viewsቻLu, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 16:18:09 የስኬት ቁልፎች (The key to success)- ክፍል አንድ

ስኬት አንድ የታቀደ እቅድ(ግብ)በትክክል መፈፀም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ዐረፍተ ነገረ መረዳት የምችለው ነገር ቢኖር ከስኬት በፊት ምንጊዜም የታቀደ ግብ ሊኖር እንደሚገባ ነው፡፡ ስኬት ግብ ለሚያቀምጡ ብቻ የተሠጠች ነች ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው “ If you fail to plan, you are planning to fail’ የሚሉት ምሁራን፡፡ ከስኬት ቁልፎች መካከል አንዱ ግብ ማስቀመጥ(Goal setting) ሲሆን ሌሎች ደግሞ የዉስጥ መነሳሳት(Motivation) እና ጽናት (persistence) ናቸዉ::

1. ግብ ማስቀመጥ ( Goal setting)

ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው እቅድ ማቀድ እንዳለበት ከተስማማን እቅዱስ ምን ምን ማሟላት አለባቸው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ማንኛውም ዓይነት እቅድ “SMART ” መሆን አለበት:: ትርጓሜውም እንደሚከተለው ይተነተናል፡፡
S- Specific ( ግልጽና የተወሠነ)
M-Measurable (የሚለካ)
A- Achievable (ሊሳካ የሚችል)
R- Realistic (እውን ሊሆነ የሚችል)
T- Time framed ( በጊዜ የተወሰነ)

i). specific ( ግልጽና የተወሠነ)

እቅድ (ግብ) በግልፅ የሚታወቅ መሆን ይገባዋል፡፡ ግልጽነት የሚጎድለዉ እቅድ እንዴት እንደምናሳካዉ ለማወቅ ከባድ ነዉ::ብዙ ሰዎች ግባቸውን ሲጠየቁ “የተሻለ” የምትለዋን ቃል በማስቀደም ሌሎችን ፍላጎታቸውን ያስከትላሉ፡፡ የተሻለ ትምህርት፣ የተሻለ ቤት፣ የተሻለ ገቢ ፣የተሻለ የስልጣን ቦታ ወዘተ ይላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ግብ ግልጽነትና ዉሱንነት ይጎድለዋል፡፡ ለስኬታማነትም ሊያበቃን አይችልም፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜያቸው የሚያጠፉት ከአንዱ አንዱ በመንከራተትና በመወዛገብ ነው፡ የተረጋጋ ህይወት ለእነርሱ ተረት ነው፡፡ የተሻለ ገቢ ለማግኜት የሚያቅድ ሰውና የ3000 ብር ደመወዘኛ የ3200 ብር ደመወዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ከወጣ ያለ ጥርጥር ስራውን ይቀይራል፡፡ ምክንያቱም እቅዱ የተሻለ ማግኜት ነውና፡፡ ለዚህም ነው እንዳንድ ሰዎች ከእድሜያቸው በላይ መስሪያ ቤት ሲቀያይሩ የሚኖሩት፡፡ በተመሳሳይ የተሻለ ትምህርት የሚፈልግና ዲግሪ ያለዉ ሰው በአጋጣሚ መንገድ ጠፍቶበት በዩኒቨርሲቲ በር ሲያለፍ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ማስታወቂያ ቢያነብ ትምህርቱ ይጥቀመውም አይጥቀመውም ዘሎ ገብቶ ይመዘገባል፡፡ ተምሮ ሲወጣ ግን በህይወቱ ምንም ዋጋ ላይጨምር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብ በግልጽ ተወስኖ የተቀመጠ መሆን ይገባዋል፡፡ የተሻለ ገቢ በማለት ፈንታ በወር ማግኜት የሚፈልገውን የገንዘብ መጠን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ የተሻለ ትምህርት በማለት ፈንታም ዲግሪ፣ ማስተርስወይም ፒ.ኤች. ዲ እና የመሣሰሉትን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡

ii). Measurable (የሚለካ)

ሌላው ግብ ስናስቅምጥ ማስተዋል የሚገባን ነገር ግባችን የሚለካ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰዎችን የሚረዳ ድርጂት ለማቋቋም ያቀደ ሰው ምን ያህል ሰዎችን እንደሚረዳ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ቤት ለመሰራት ያቀደም ሰው ቢሆን የቤቱን ስፋት አይነት እና የመሳሰሉትን በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ አለበለዚያ አንድ ሰው ብቻ የምታሰገባ ቤት ቢሰራም ቤት ቤት ነውና እቅዱን እዳሳሣካ ሊቆጥረው ይችላል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግብ የሚያስቀምጥ ሰው ግቡ የሚለካ መሆን አለበት፡፡

iii). Achievable (ሊሳካ የሚችል)

አሁንም ግብ ስናስቀምጥ ግባችን ሊሳካ የሚል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህን በምሳሌ ለማስረዳትም አንድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ዛሬ ላይ ሆኖ የዛሬ 10 ዓመት ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪዉን እንደሚይዝ ቢያቅድ እቅዱ ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ስርዓተ-ትምህርቱ ከ7ኛ ክፍል ወደ ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ በ10 ዓመት ያጠናቅቅ ዘንድ አይፈቅድለትም፡፡ በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ7ኛ ክፍል ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ ለመያዝ ቢያንስ 14 ዓመታትን ይፈጃል፡፡ ስለሆነም ይህን እቅድ ያቀደ ሠው እቅዱን ሊያሳካ አይችልም፡፡ ስለዚህም ሁጊዜ ግብ ስናስቀምጥ ሊሳካ የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን ማሠብ ይኖርብናል፡፡

iv). Realistic (እውን ሊሆን የሚችል)

አራተኛው ግብ ሊያካትተው የሚባው መስፈርት ደግሞ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ቀጥታ ከተፈጥሮ ጋር የሚያያዝና ልንቀይራቸው የማንችላቸውን ነገሮች ማቀድ እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ “change the changeable, accept the unchangeable”
እንዲሉ ምሁራን በተፈጥሮ እውን ሊሆን የማይችልን ነገር ማቀድ ድካሙ ነው ትርፉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “የዛሬ ዓመት መልዓክ ለመሆን ቢያቅድ እቅዱ እቅድ መሆኑ ቀርቶ ቅዠት ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም ግባችን በገሃዱ አለም እውን ሊሆን የሚች መሆን አለበት፡

v). Time framed ( በጊዜ የተወሰነ)

የመጨረሻውና ግብ ስናስቀምጥ ማካተት ያለብን ነገር ግባችን በጊዜ-የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ችግር ከሌሎች ማሟላት ከሚገቡን ነገሮች የበለጠ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡ “መኪና ሳልገዛማ አልሞትም” ሲል የምንሠማው ሰው መኪና መቼ እንደሚገዛ ግን አያውቀውም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ይህንን ሲደግመው እናሠማለን፡፡ ግብ ስናስቀምጥ ምን ጊዜም በጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ነገ እሠረዋለሁ እያልን እድሜያችንን መፍጀታችን ነዉ፡፡

Via unknown source

ቀለማት - ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው።

Join us @qelemaat/ @qelemaat
3.3K viewsGech, 13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 16:42:06 " ባነበበ አይደለም በገባው ነው" ይባላል ፣ ግን የምር እንደዛ ነው ወይ?

ሲጀመር ማንበብ ምን ይጥቅማል እውነት እኮ ነው ፣ የተማረ የት ደረሰ በቃ ማወቅ ማለት ንድፈ ሃሳብን ማራቀቅ ማለት ነው

በእውነት የትምህርት ስርዓቱ አክትሞለታል በቃ የምንማረው ትምህርት ትርኪ ምርኪ ነው ማለት ነው?

ኢትዮጵያ ሃገራችን እውነትም ሙያችንን እና ክህሎታችንን እንዲናሳድግ የሚያስችል እድሎች የላትም ወይ? ያለን አማራጭ ሀገር ለቆ መጥፋት ነው?

አንዳንድ ሰዎች "ባነበበ አደለም ፣ በገባው ነው።" ሲሉ ሰማለሁ ግን ስናነብ የግድ ሊገባን ይጠበቃል ወይ ? ዶ/ር ዳንኤል የሚባሉ መምህሬ "ግራ ከገባችሁ አስተምሬያለሁ ማለት ነው" ሲሉ ትዝ ይለኛል። ለተከታታይ ዓመታት ባነበብን እና ባወቅን ቁጥር መጨረሻ ላይ የሚገባን ነገር ግራ መጋባታችን ነው ፣ ግራ መጋባታችንም ይመስለኛል ለተሻለ ነገ እንድንተጋ የሚያረገን ፣ የሆነ ያልፈታነው እንቆቅልሽ እንዳለ ማወቃችን ዘና ብለን የተደላደለ ህይወት እንድንኖር አያስችለንም ፣ አጋጣሚውን ሁሉ እየጠበቀ በአይምሯችንን ይመላለሳል ፣ ነገ ፈተና እንዳለ እያወቃችሁ ዛሬን ሰላማዊ እንቅልፍ እንደመተኛት ቁጠሩት ፣ በደንብ እስካልተዘጋጃችሁ ድረስ "አንዲት ወረቀት ህይወቴን አትወስንም " ብላችሁ ለሽ ለማለት ብትሞክሩ እራሱ የሆነ ቅር የሚላችሁ ስሜት አለ ፣ ሰላም የማይሰጥ ፣ በጣም የሚረብሽ። ታዲያ አኗኗራችንን ለማሻሻል የሚኖረን ተነስሽነት የሚጀመረውም ከዚህ ይመስለኛል።

ድንገት ስትባንኑ ፣ ብዙ ያለተፈቱ ችግሮች በኑሯችሁ ላይ ፣ በአካባቢያችሁ እና በአገራችሁ ላይ ታያላችሁ። መማር ማለት ችግር የማይመስሉ ግን ብዙ መፈታት ያለባቸው ተግዳሮቶች እንዳሉ ማውቅንም ያካትታል። ምክንያቱም ስትማሩ የትኛው ትክክል የትኛው ደግሞ ስህተት ነው የሚለውን ለማውቅ እድል ስለሚሰጣችሁ ፣ ከምታዩት እያንዳንዱ አጋጣሚ ጋር እየሄዳችሁ ትላተማላችሁ። ይሄ እንዲህ ቢሆን ፣ ያ እንዲያ ቢሆን ማለት ትጀምራላችሁ ፣ ይሄን እንዲህ ቢያስተካክሉት ያንን ደግሞ ቢያሻሽሉት ማለት ስትጀመሩ ፣ ወስጣችሁ በእምቅ ሃይል መሞላት ይጀምራል ፣ ክዚህ በኋላ ግን የሚትኖሩት ዓለም የተለየ ነው ፣ እንኳን ወደ ስራው ዓለም በሰላም መጣችሁ!

አሁን የሆነ ማስተካከል የምትፈልጉት ነገር እንዳለ አምናችሁ ፣ ወደ ተግባር ገብታችኋል ፣ ሊሰራ የማይወድ አይብላ እንደሚል ቃሉ ፣ እናንተም ማስተካል ለምትፈልጉት ነገር ሁሉ ለመልፋት ስትወስኑ የምርም እናንተ ማስተካክል የምትፈልጉትን ነገር በቅጡም ቢሆን ያስተካከሉ ፣ እናንተ መስራት የምትፈልጉትን የሰሩ ፣ እናንተ መፅሃፍ እንደምትፈልጉት የፃፉ ሰዎችን መምህራችሁ ማረግ ትጀምራላችሁ ፣ በአካል ካሉ በአካል ስታወሯቸው ፣ መፅሃፋቸውን ስታነቡ ፣ ታሪካቸውን ስትሰሙ ፣ ቀስ በቀስ ሁሉም እየገባችሁ ያለ ይመስላችሗል። እና "የህወቴን ትርጉም አገኘሁት " ማለት ስትጀምሩ አንድ ያልታሰበ ተራራ ከፊታችሁ መቶ ይደቀናል። ብዙ ሰዎች እስከዚህ ድረስ ብቻ ነው መንገዳቸውን የሚመጡት ፣ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ያለው ፣ እራስን ማስተማር ፣ ዝቅ ብሎ መጠየቅ ፣ ሞክሮ መሳሳት ፣ ከሚጠበቅብን በላይ መስራት፣ ክህሎትን ማሳደግ ፣ እያለ የሚቀጥል ለምውጣት እንኳን የሚከብድ አድካሚ ተራራ።

አሁን "ያልታሰብ እንጀራ ይስጥህ " ተብዬ የተመረኩት ምርቃት ምናለ ቢሰራልኝ ብላችሁ ትመኛላችሁ ፣ ምክንያቱም ነገሩን በሰከነ ልቦና ስታዩት የሆነ ትልቅ ነገር እስካላረጋችሁ ድረስ ያስባችሁት ለውጥ እይመጣም፣ እግዚአብሔር ያውቃል ብላችሁ ነገሩን ልትተውት ስትሉ ደግሞ ፣ የናንተ ፍቃድ እስከምን ድረስ እንደሆነ ጥያቄ ይሆንባችኋል ።

እየተማራችሁት ያላችሁት degree የሂደቱ አንድ አካል እንጂ ብቸኛ አካል እንዳልሆነ ስታውቁ ፣ የተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ተጨማሪ ወጪ ማውጣት እንዳለባችሁ ሲገባችሁ ፣ እድሎችን ለመፍጠር ከመስሪያ ቤት መስሪያ ቤት መንቃቃት ሊኖርባችሁ እንደሆነ ስትረዱ ፣ እንቅልፋችሁን ሰውታችሁ ተጨማሪ ሰዓት በስራ እና በንባብ ማሳለፍ እንዳለባችሁ ውስጣችሁ ሲያምንበት ፣ የተለያዩ እድሎችን እና ማስታወቂያዎችን አንፍንፋችሁ መፈለግ እንዳለባችሁ ስትረዱ ፣ የጀመራችሁት ጉዞ ከብዙ ብጥቂቱ እንደሆነ ይገባችኋል። ከዚህም በላይ ሌላ ትልቅ ነገር ማድረግ ይኖርብኝ ይሆን ብላችሁ ራሳችሁን በየቀኑ ትጠይቃላችሁ! ምክንያቱም አሁን Law of attraction በሚባል የሃሳብ ፈንጠዚያ ውስጥ አደለም ያላችሁት ፣ ከናንተ በሚከፈል ጥረት ፣ በፈጣሪም ፍቃድ ፣ ማድረግ ያለባችሁን ነገር ሁሉ በተሻላችሁ መጠን እያረጋችሁ እንደሆነ ስታስቡ ፣ ሁል ጊዜም ለለውጥ ቦታ ሰው መሆን ትጅምራላችሁ ፣ ምክንያቱም አሁን ከሃጋራችሁ መሰደድ ብቸኛ አማራጫችሁ አይሆንም ፣ ሃገራችሁ ላይ ያሉ እድሎችን በሙሉ ለማግኘት ተወዳዳሪ ሰው ሆናችኋል እና። ለእንዲህ እያረጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች በሙሉ አክብሮቴን እና አድናቆቴን ለመግለፅ ወዳለሁ።

ቻLu - በ ኢትዮጵያ የሳይኮሎጂ ባለሞያዎች ማህበር እና በ American Psychological Association በተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች Certified የሆነ እጩ የስነ- ልቦና ባለሙያ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

JJOIN US NOW : @qelemaat |  @qelemaat
3.5K viewsቻLu, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 06:05:13 ምን አይነት #channel ይፈልጋሉ

ምርጥ ምርጥ ቴክኖሎጂ
ምርጥ ምርጥ ቴክኖሎጂ

የኢትዮጵያ ትልቁ ዩንቨርስቲ channel
የኢትዮጵያ ትልቁ ዩንቨርስቲ channel

ቀለሜ ለተማሪዎች
ቀለሜ ለተማሪዎች

TOP STUDENTS
TOP STUDENTS

CONCISE EDUCATION
CONCISE EDUCATION

ቀለማት psychology
ቀለማት psychology

FRESHMEN EXAM
FRESHMEN EXAM

STUDENTS CHANNEL
STUDENTS CHANNEL

GOLDEN ACADEMY 2023
GOLDEN ACADEMY 2023
3.3K viewsLij ãbďisă+, 03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 15:21:37 የሙያ ምክክር ከቀለማት የሳይኮሎጂ አገልግሎት | በነፃ

ሙያን በተመለከተ Field በመምረጥ ላይ ያላችሁ አልያም ደግሞ ሞያችሁን ማሰዳግ የምትፈልጉ @AtoChalu ላይ አውሩኝ! በዚህ ሳምንት ቀደመው ለመጡ ቤተሰቦች Career Counseling Service የምንሰጥ ይሆናል!

| ቻLu  -Internationally Accredited Career Coach| Upcoming Psychologist |Certified Trainer

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
3.2K viewsቻLu, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ