2023-05-16 00:15:29
ይህ ፅሁፍ የበታችነት እና የተሸናፊነት ስሜት ለሚሰማን ይሁንልኝ!
ታውቃለህ ፣ መሸነፍ ደስ አይልም! በአባቢህ ያሉ ሰዎች አሸንፈው ስታይ የሆነ ሰውነትህን ውርር አርጎ የሚያበግንህ ነገር አለ!
አንዳንድ ጎበዝ ተማሪ አለ በቃ የሚያናድድ በእኩለ ለሊት ተነስቶ የዶርም መብራት አብርቶ የሚያነብ ፣ አንተ በውድቅት ለሊት ተኝተህ ጣፋጭ እንቅልፍ እያሳለፍክ እሱ ተነስቶ ያነባል እንዴ?ሲያናድድ በዚህ ጊዜ በስንፍናህ ብግን ትልና ፣ አንተ መብራቱን አጥፋው ፣ ካልሆነ ላይብረሪ አንበብ ብለህ ትጮህበታለህ! ካንተ ጋር መጨቃጨቅ ሲጀመር ከዛም ደግሞ ማንበቡን ሲያቆም ደስ የሚል ስሜት ይሰማሃል! አሁን አንድ እኩል ናችኋ!
አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አሉ በቃ ሁሌ በነጋ በጠባ ቤተ-ክርቲያን ነው ፣ ነጠላቸው ከጀርባቸው አይለያቸውም! አቤት እነሱ ሄደው አንተ ቀርተህ የሚሰማህ ስሜት ፣ ቅጥል እኮ ነው የምትለው ፣ በቃ በቅናት ያንጨረጭሩሃል! ከዛን ግን እንደ እድል ፣ ቀን አሳስቷቸው ከቀሩ ''እሺ መነኩሴው ፣ዛሬ ቤተክርስቲያን ተዘጋ እንዴ ?'' ብለህ ስትቀልድባቸው ስጋህ አንዳች ሃሴትን ያገኛል ፣ በራስህ መተማመንህን ወደቀድሞ ቦታው ትመልሳለህ ፣ ጓደኛህ የበታችነት ስሜት እንዲሰማው በማረግህ ፣ አንተ የበላይነት ስሜት ይሰማሃል!
እማ አንቺንም እረዳሻለሁ ፣ ከናንተ ክላስ የሆነች ልጅ አለች ራሷን የምትጠበቅ ፣ አለባበሷ ኩል ፣ ፀጉሯ ተሰርታ ገበያ የምቶጣ የሚባለው እንቆቅልሽ ለሷ ነበር እንደውም! እና ይቺን ሴት ስታያት የሚሰማሽ ስሜት አይጣል ነው ፣ እንደው ማማሯ ፣ መዋቧ እንዴት እንደሚያንጨረጭር እኮ ፣ ከዛን በአይምሮሽ የሆነ ምስል ትሰጫታለሽ ፣ ክብር እና ጨዋነት እንደሌላት ሴት ማሰብ ስትጀምሪ ፣ አይምሮሽ ረፍት ያገኛል ፣ እፎይ ትያለሽ ፣ ይበልጥ የበላይነት ስሜት እንድታገኚ ''ፈጣሪ በሰጣት ውበት ስለማትተማመን እኮ ነው እዩኝ እዩኝ የምትለው ''ብለሽ ማሰብ ትጀምሪያለሽ ያኔ አንጀትሽ ራስ ይላል! አቤት ያለው ደስታ!
''የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ '' ሲባል ሰምቻለሁ! እሺ ክፍለ ሀገር እያለሁ ቢሆን አረገው ነበር ፣ እዚህ እንዴትስ ይቻለኛል? ለነገሩ አንዳንዶቻችን ላይብረሪ ውስጥ 2nd floor የምናነበው ለዛ ነው አሉ! አየህ ካንተ በታች 1st floor ላይ ተማሪዎች እንዳሉ በራሱ ማወቅ መንፈስን ያድሳል!
እና ወደ ነገረ-ጨዋታችን ስንመለስ -የ Highschool ተማሪ እያለሁ እኔ የምለብሰው ልብስ ብቻ አሪፍ ይመስለኝ ነበር! ከኔ በበለጠ ውድ ልብስ እንኳን ጓደኞቼ ቢለብሱ ''አልሄደባቸውም ፤ ወይ እንዴት ያስጠላበታል'' ብዬ ነው የማስበው! አሁን ወደኋላ ሄጄ ሳስብ ከሁሉም ደባሪ አለባበስ የኔ ነበር ፣ ያንን ማሰቤ በራሱ ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነበር!" ማለትም ያንን ጊዜ እንደዛ ብዬ ሳስብ እያሰብኩት ያለሁት ነገር ትክክል ነው አደለም ብዬ አላስብም ነበር! ብዙዎቻችን ጋር ችግር ሆኖ ያለው ይሄ ይመስለኛል! የበላይነት ስሜት እንዲሰማን ብለን ስለጓደኞቻችን የበታችነት የምናስበው ሃሳብ ፣ የምንናገረው ንግግር ከቁጥጥራችን ውጪ ነው! በዛ መንገድ ያኔ ማሰቤ ምንም አለጠቀምኝም ፣ I was Nerd and ገልጃጃ ተማሪ !
ከዚህ በተቃራኒ ግን ከፊታችሁ የቀደሙ ሰዎችን ማድነቅ ብትጀምሩ ፣ ጠንካራ ጎናቸውን ማወቅ ብትጀምሩ ፣ ነገሮች ለናንተ መልካም መሆን ይጀምራሉ! ሰዎችን ስናደንቅ ከዛ ሰው ለኔ የሚሆን ምሳሌ መውሰድ አለብኝ ብለን ለአይምሯችን እየነገርነው ነው!
ቻLu - Certified Trainer |የ Psychology እና Leadership ተማሪ
ቀለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!
Join us @qelemaat | @qelemaat
2.1K viewsቻLu, 21:15