2023-06-03 23:48:22
ስራ እቀጠር ይሆን ብሎ ማሰብ ቀረ !
Master Track ምንድነው? ያልተበላበት ድንቅ ዘዴ
ይህ ካላችሁ በስራ ዓለሙ ላይ ተፈላጊነታችሁ ይጨምራል
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ስራ የተሰጠኝ ምክንያት
ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ Career Development Center ስራ ለማመልከት ሄጄ ነበር ፣ በማስታወቂያ የተነገረ ክፍት የስራ ቦታ አልነበረም ፣ እንደምታውቁት ገና ተመርቄም አልጨረስኩም! ካዲያ እንዴት ሊቀበሉኝ ቻሉ?
Master track በአይነቱ ከ Masters Degree አነስ ያለ የትምህርት Specialization ዘርፍ ነው ! እኚህ አይነት ትምህርቶች ተግባር ተኮር የሆኑ እና ወደ ስራው ዓለም ማስፈንጠሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው! አሁን ብዙ ጥያቄዎች አይምሯችሁ ላይ እየተፈጠሩ እንደሆነ ይገባኛል! አንድ በአንድ እንመልሳቸዋለን!
Master Track መማር ማለት Training መውሰድ ማለት ነው?
አይደለም! Training መውሰድ እውቀታችሁን እና ኮህሎታችሁን ሲያሳድግላችሁ Master Track ግን እውቀት ከመጨመር አልፎ ባለሞያ ያረጋችሗል! ለምሳሌ እኔ Career Development and Counselling ላይ የሶስት ቀን training ብወስድ ስለጉዳዩ የጠለቀ እውቀት ይኖረኛል እንጂ በዛ እውቀት ላይ Professional አያረገኝም! Career Development ላይ የአራት ወር የ Master Track ትምህርት ወስጃለሁ ፣ ግን ደግሞ ድንገት ራሴን Career Counseling Psychologist ብዬ ስጠራ ደግሞ አታዩኝም ፣ እንደዛ ማለት አይቻልም ያንን ለማረግ የጠለቀ እውቀት ያስፈልጋል ፣ ከ Masters ጀምሮ እስከ Phd ድረስ! ግን በ አራት ወሩ ስልጠና Career couch and Navigator ሆኛለሁ።
ስለዚህ Masters Degree እስክንሰራ ድረስ ይጠቅመናል ማለት ነው?
በትክክል! በተለይ ደግሞ Specialize ማረግ የምትፈልጉትን Sub-Field ከመመረቃችሁ በፊትም ሆነ በሗላ እየሰራችሁበት ገንዘብ እንድታገኙ ያስችላችሗል! ለመሳሌ IT Support Specialist የሚባል የ አንድ አመት professional certificate ያለው ትምህርት Coursera ላይ ሳይ ነበር ! የ Tech ተማሪዎች ማለትም SS |CS |IS masters degree እስኪሰሩ ድረስ ይህን Specialization ተምረው ለገበያው ራሳቸውን ያበቃሉ ማለት ነው!...ያው ይሄ ግን ብቸኛ አማራጫችሁ ነው እያልኩኝ አደለም!
ቆይ ለሁሉም Field ተማሪዎች ይሆናል?
አዎን! ሙያችሁን ማሰደግ የሚያቸል አማራጭ ከዚህም ከዚያም ብላችሁ ብታስሱ ፣ በእርግጥም አማራጭ አለ! ከወራት በፊት በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስራ እና የሙያ ድግስ ተዘጋጅቶ ነበር ! ትዝ ከሚሉኝ የትምህርት ዕድሎቾ የሚከተሉቶን እንደምሳሌ ማየት ይቻላል!
American Society of Clinical Pathology
የጤና ተማሪዎችን አለም አቀፍ ባለሞያ የሚያረግ የትምህርት እድል
Huawi Handshake Technology
ለ Programming ፣ ለ Electrical Engineering እና ለሌሎች መሰል ዘርፎች የሚሰጥ የ Profesional Certificate
.........እና ሌሎችም
ካዲያ የ Master Track Specialization ትምህርቶችን በነፃ ማግኘት ይቻላል?
በዙ ጊዜ እኝህን አይነት ትምህርቶችን የሚሰጡ ተቋማት የሚከተሉት አይነት አሰራር አላቸው።
በነፃ ታገለግላላችሁ ፣ በነፃ ያስተምሯችሗል!
እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያሉ ሌሎች የግል አልያም የመንግስት መሰል ተቋማት ላይ የትምህርት ዕድል ሊያዘጋጁ ይችላሉ!
እንደ Coursera ያሉ የሙያ ልህቀት ትምህርት ቤቶች ለእንዲህ አይነት Specialization የ Scholarship አማራጭ አላቸው !
መክፈል ሊጠበቅባችሁ ይችላል!ሁሌ በነፃ ብሎ ነገር የለም!
ጠቅሟችሁ ከነበር ተመርቀው ስራ በማፈላለግ ላይ ላሉ ፣ ለተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም ገና በመማር ላይ ላሉ ሁሉ አድርሱልን!
ቻLu -Career couch |Certified Trainer | የLeadership and Management እጩ ባለሙያ Join us ፦ @qelemaat | @qelemaat
1.8K viewsቻLu, 20:48