Get Mystery Box with random crypto!

ቀለማት

የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የቴሌግራም ቻናል አርማ qelemaat — ቀለማት
የሰርጥ አድራሻ: @qelemaat
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.43K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ሀገርኛ ቀለም ያላቸው ስነ ልቦናዊ ረጢብ ስንቆች፣ ከህይወት ሰበዝ የተመዘዙ ጎምቱ ልምዶች፣ በአስተውሎት የጎለመሱ ሰብዓዊ ሃሳቦች፣ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ምክክሮች በድምፅ እና በጹሑፍ ወደ እናንተ የሚቀርቡበት የእናንተው ቀለመ-ብዙ ቻናል ነው !
Addis Ababa, Ethiopia

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-07 19:16:36 ምርጥ ምርጥ የተባሉ telegram channel

የኢትዮጵያ ትልቁ ዩንቨርስቲ
የኢትዮጵያ ትልቁ ዩንቨርስቲ


ቀለሜ ለተማሪዎች
ቀለሜ ለተማሪዎች


Top students
Top students


A+ አካዳሚ
A+ አካዳሚ


ኢትዮጵያ education
ኢትዮጵያ education


ቀለማት psychology
ቀለማት psychology


ትምህርት news ትኩስ መረጃ
ትምህርት news ትኩስ መረጃ


ትምህርት of education
ትምህርት of education


Freshman exam
Freshman exam


ለሁሉም ተማሪዎች የሚሆን ገራሚ የሆነ channel 9-ዩንቨርስቲ
ለሁሉም ተማሪዎች የሚሆን ገራሚ የሆነ channel 9-ዩንቨርስቲ


የድሮ መፅሐፍ ለሚፈልግ
የድሮ መፅሐፍ ለሚፈልግ
197 viewsLij ãbďisă, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 06:59:58 የሲግማ ደምብ - 3 - የራስህ አለቃ ሁን

አልፋ ወንድ ሁል ጊዜ አለቃ መሆን ይፈልጋል ፣ ቤታ ወንድ ደግሞ ሁል ጊዜ አቅጣጫ የሚያሳየው አለቃ ይፈልጋል ፣ ጋማ ወንድ ደግሞ መሪ መሆን ደስ አይለውም ፣ ከመምራት ይልቅ የሚመራው ሰው ይፈልጋል ፣ ሲግማ ወንድ ግን የራሱ አለቃ ነው ፣ እጣፋንታውን በራሱ ይወስናል ፣ ፣ ለመሪነት ከተመረጠ ግን ከአልፋ ወንድ በተለየ ብቁ መሪ መሆን ይችላል ፣ ይህ ሁሉ የሆነው በራሱ ስለሚተማመን ነው ፣ መቀጠር አይፈልግም ፣ ያራሱን ስራ ፈጥሮ መስራት ያስደስተዋል። የሲግማ ወንድ አለቃ ወይም ጓደኛው ከሆንክ የሚያነሳቸውን ሃሳቦች ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል ፣ ይህ ካልሆነ ግን ሲግማ ወንድ ብቻውን መሆን ስለማይፈራ ካንተ ጋር ያለውን ህብረት ያቆማል፣ ሲግማ የራሱ አለቃ ነው !

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
1.4K viewsቻLu, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:00:40 የሲግማ ደምብ - ፪ - ግርማህ የሚያስፈራ ይሁን -አልፋ እና ሲግማ ወንድ የማይስማሙበት ምክንያት

አልፋ ወንድ በጣም ጉረኛ ከመሆኑ የተነሳ ፣ ሲግማ ወንድ ባጠገቡ ሲሆን ለመጎረር ስለማይመቸው ነፃነት አይሰማውም ፣ ሲግማ ወንድ ግን ከአልፋ ወንድ የሚበልጥ አቅም እንዳለው እያወቀ ፣ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትኩረት ስጡኝ አይልም! ሲግማ የማያወራው አይናፍር ሆኖ አይለም ፣ ስለራሱ መች ማውራት እንዳለበት እና እንደሌለበት በትክክል ስለሚያውቅ ነው። አልፋ ሰዎችን በማስፈራራት ለማሳመን ሲሞክር ሲግማ ወንድ ግን በምሳሌ እና በአምክንዮ ቡድኑን ይመራል! አልፋ ሁሌ መሪ ካልሆነ ደስ አይለውም ፣ ሲግማ ወንድ ግን እንኳን ለመምራት ይቅርና ቡድን ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለውም ፣ የመሪነት ቦታ ከተሰጠው ግን በብቃት ይወጣል ፣ ለዛም ነው ጨዋው መሪ የሚባለው። ብቻውን መሆን አይፈራም ፡ ብቻውን ያዩት የመንጋው አባላት ፣ ሞገሱ ያስፈራቸዋል ፣ ከሚመራቸው አልፋ ወንድ ይልቅ ሲግማ ወንድን መከተልን ይመርጣሉ!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
1.7K viewsቻLu, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 07:02:04 የሲግማ ደምብ - ፩ - ሁሌም በትኩረት አዳምጥ!

አልፋ ወንዶች ከራሳቸው ውጪ ሌላ ሰው አላስወራ ይላሉ! ኦሜጋ ወንዶች ደግሞ በአጠገባቸው ያሉ ሰዎች ምን እየተሰማቸው እንደሆነ አያውቁም። ሲግማ ወንድ ስትሆን ፣ ግን ከማውራት ይልቅ በትኩረት አዳማጭ ተሆናለህ ፣ ያንን ማረግህ ደግሞ የሰዎችን ሃሳብ እና ስሜት መረዳት ስለሚያስችልህ ፣ አይምሯቸውን መቆጣጠር ይቀልሃል! ተከራክሮ ማሳመን ላንተ ቀላል ነው ፣ ለምን? አድማጭ ነሃ!

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
2.7K viewsቻLu, edited  04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:40:30 ክፍል ሁለት የቀጠለ
6ቱ የወንድ አይነቶች | ሴቶች ፡ ከየትኛው ወንድ ጋር date እያረግሽ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብሻል

ከስድስቱ የወንድ አይነቶች አንተ የትኛው ነህ ?

5) Delta Male Personality

ይህ ደግሞ ባሳለፈው ህይወት በጣም የተጎዳ ፣ አሁን ላይ ላለበት መጥፎ ሁኔታ በሙሉ ሌሎችን ሰዎች ጥፋተኛ ለማረግ ይሞክራል ፣ ብቸኛ ነው አዲስ ሰዎች ወደ ህይወቱ እዲመጡ አይፈልግም ይጎዱኛል ብሎ ይጠራጠራል ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ ድብርት እና ስንፍና ያጠቁታል። ህይወቱን ለማሻሻል አይፈልግም ፣ አዳዲስ ዕድሎች በህይወቱ ውስጥ ስሚጡ ፣ ከሚጠቀምባቸው ይልቅ እዛው ስንፍና ውስጥ ቁጭ ብሎ ፣ ህይወት ምን ያክል አስከፊ እንደሆነች ነው ማሰብ የሚፈልገው ፣ ሁል ጊዜ ሰዎች ይጎዱኛል ብሎ ስለሚያስብ አስቀድሞ ሊጎዳቸው ይሞክራል ፣ ጥሩ እድል እንደሌለው ያስባል ፣ ነገሮች በተበላሹ ቁጥር ቁጥር ያርባ ቀን እድሌ ብሎ ቢያማርር ይቀናዋል ፣ መሪ መሆን አይፈልግም ፣ ፋና ወጊ ባለህልመኛም አደለም ፣ ሴቶች አልፋ እና ሲግማ ወንዶችን ሲያሳድዱ ፣ እሱ ግን አንድ ቀን ፍቅረኛ ይኖረኛል ፣ አንድ ቀን ሙሉ የምታረገኝ ሴት ትመጣለች ብሎ ይጠብቃል ፣ ዴልታ ወንድን የምታፈቅሪ ሴት አደራሽን ተጠንቀቂ ፣ለግል ፍላጎቱ እና ጥቅሙ አታሎ ሊያጭበረብርሽ ይችላል

6) Sigma Male Personality

በሰው ልጆች ስብዕና ሳይኮሎጂ አሁን ላይ ትኩረት እየተሰጠው ያለ የወንድ የስብዕና አይነት ነው ፣ ድሮ ድሮ ሴቶች የሚወዱት አልፋ ወንዶችን ነው ተብሎ ይታሰብ ነበር አሁን ግን አቅጣጫዎች በሙሉ ወድ ሲግማ ይጠቁማሉ ፣ ሲጋማ ወንድ ከአልፋ የወንድ ስብዕና ጋር እኩል ችሎታ ያለው ሲሆንእንደ አልፋ ከሰዎች ጋር መሆን አይፈልግም ፣ ብዙ ጊዜ ብቻውን መሆን ይፈልጋል ፣ የየትኛው መንጋ ቡድን አባል መሆን አይፈልግም ፣ ብቻውን ሲሆን አዳዲስ የስኬት እና የፈጠራ ሃሳብፕች ይመጡለታል ፣ ዶግማ ስርዓት እና ትውፊት ምክንያት እስካላወቅ ድረስ መቀበል አይፈልግም፣ ከጓደኞቹ ጋር ሲሆን ቡዙ አያወራም ፣ የማያወራው ማዉራት ስለማይችል አደለም ፣ ስለማይፈልግ እንጂ። ሲግማ ወንድ ከማውራት ይልቅ ማዳመጥን ስለሚያዘዎትር ፣ ሰዎችን የመረዳት እና የሰዎችን አይምሮ የመቆጣጠር አቅም አለው፣ ሲግማ ወንድ አልፋ ወንድ መሆን ቢፈልግ ይችላል ፣ ግን አይፈልግም ፣ ትሬንዱን አይከተልም ሁል ጊዜ የራሱ የሆነ ስታይል አለው ፣ ሲግማ ወንድ ስለራሱ ብዙ አያወራም ፣ አንቺን መርጦ ካወራሽ ፣ እድለኛ ነሽ ፣ ምክንያቱም ሲግማ ወንድ ለወደደው እና ላመነው ሰው ብቻ ነው እራሱን የሚያሳየው ፣ አልፋ ወንድ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከመንጋው ፊት ለፊት በመሆን ከያንዳንዱ ሰው ትኩረት ለማግኘት ሲሞክር ፣ ሲግማ ወንድ ግን ቡድን ውስጥ ተደብቆ ዝምታው የሚያስፈራ መሪ ይሆናል፣ ከ አልፋ ወንድ በበለጠ ሲግማ ወንድ ሰዎችን የማሳመን ብቃት ቢኖረው ፣ ሲግማ ወንድን ያፈቀረች ሴት ፣ ሁሌ ጭቅጭቋ ጊዜ ስጠኝ የሚል ነው ፣ ምክንይቱም ሲግማ ወንድ ከሚስቱ ይልቅ ለስራው ነው የሚሞተው። ጓደኞቹ ብዙ ጊዜ ብቻውን ሲያዩት ሊያዝኑለት ይፈልጋሉ ፣ ብቻውን ሲሆን ምን ያክል እንድሚረካ ስለማያውቁ ነው!


| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
637 viewsቻLu, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:38:39 6ቱ የወንድ አይነቶች | ሴቶች ፡ ከየትኛው ወንድ ጋር date እያረግሽ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብሻል

ከስድስቱ የወንድ አይነቶች አንተ የትኛው ነህ ?

በ Socio-sexual hierarchy መሰረት የተቀመጠ የወንዶች Personality ምድብ |ይህ ጥንቆላ አደለም ይህ የሳይኮሎጂ ሳይንስ ነው!

ማሳሰቢያ ፥ አንድ ወንድ አንድ እና ከዚያ በላይ የስብዕና ቅልቅል ሊኖረው ይችላል፣ ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ ሁለቱን ወይም ሶስቱን በአንድ ሰው ላይ ልታይ ትችያለሽ ፣ እንደዛ ሲሆን ገናና የሆነውን የpersonality ይዘሽ ሌሎቹን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አትርሽ ፣ ወንዶች ደግሞ ይሄን ልብ በሉ ፣ ራሳችንን ለማሻሻል ጊዜው ረፍዶ አያውቅም ፣ ከታች የተዘረዘሩት የወንድ የስብዕና አይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከአንዱ ወደ አንዱ መሻሻል የሚችሉ ናቸውና።

1) Alpha Male Personality

ይህ አይነቱ ወንድ ኩራት ይፈትነዋል! እጅግ በራስ መተማመን ስላለው ሴቶችም ወንዶችም ከሱ ጋር መሆን ይፈልጋሉ። አዳዲስ ሰዎችን ማዉራት ያስደስተዋል፣ የሚፈልጋትን ሴት ለማሳመን ጊዜ አይወስድበትም ጨዋታ አዋቂ ነው ፣ ጓደኞቹ ከሱ ጋር ከሆኑ መሳቅ ነው ስራቸው ፣ ላፍታም እንኳን ወሬ አያጣም ፣ ድብቅ ሰው አይደለም ላገኘው ሰው በሙሉ ስለራሱ ያወራል! ብዙ ጊዜ ጓደኞቹ እሱ የሚላቸውን ነገሮች ቀጥ ብለው ያረጋሉ ፣ መሪ መሆን ያስደስተዋል ፣ ትኩረት ካላገኘ ደስ አይለውም ፣ የበላይነቱን ለሰዎች ለማሳውቅ ስለሚፈልግ ፣ ሁሌም ከሚመራው መንጋ ጋር መሆን ያስደስተዋል! ሰዎችን በቀጭን ትዕዛዝ መምራት ይፈልጋል! መስሪያ ቤት ላይ በሰራርተኞቻቸው ላይ የሚጮሁ አለቆች እንዲህ አይነት ወንዶች ናቸው ማለት ይቻላል!የማህበረሰቡን ትውፊት እና ወግ የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው! አልፋ ወንድ ጋር ግንኙነት ጀመረሽ ከሆነ ስለታማኝነቱ ብታስቢ መልካም ነው!

2) Beta Male Personality

ይሄ ደግሞ ሁሉንም ሰው ለማስደስት የሚሞክር ወንድ ነው ፣ በራሱ ብዙ ስለማይተማመን ሌሎች ሰዎች እንዲያደንቁት እና እንዲያምኑበት ይፈልጋል። እኔ የማቀርበውን ሃሳብ ማንም አይወደውም ብሎ ስለሚያስብ ፣ ሃሳቡን በጓደኞቹ ፊት አይገልፅም። ሰዎች ሊያሳምኑት ሲሞክሩ ፣ በሃሳቡ አመነበትም አላመነበትም ይቀበላቸዋል! ሰዎች ሃሳባቸውን የሚቀበልላቸውን ሰዎች ስለሚወዱ ከብዙዎች ጋር የዘለቀ ጓደኝነት አለው ፣ ቤታ ወንድ ብዙ ጊዜ ከአልፋ ወንድ እግር ስር አይጠፋም ፣ አልፋ ወንድ የሚለብሰውን እያኮረጀ ነው ቤታ ወንድ የሚለብሰው ፣ ሴቶች ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ ከ አልፋ እና ከሲግማ ወንዶች ጋር ማሳለፍ ቢፈልጉም ለትዳር የሚመርጡት ግን ቤታ ወንድን ነው ፣ ለምን ቢባል በጣም ታማኝ እና አርግ የሚባለውን ነገር በቀጥታ የሚያረግ ስለሆነ ነው ፣ ስራ ቦታ ላይ ተቀጥረው ካለቃቸው በኩል ትዕዛዝ እየተቀበሉ የሚኖሩወንዶች የዚህ የወንድ አይነት ማሳያ ናቸው! ከቤታ ወንድ ጋር ዴት እያረግሽ ከሆነ ፣ የልጆችሽን ዳይፐር የሚቀይር ተንከባካቢ ባል አገኘሽ ማለት ነው!

3) Gamma Male Personality

በጣም ጎበዝ ነው ፣ በሃሳቦች ላይ መራቀቅ ያስደስተዋል ፣እጅግ ሲበዛ ቅን ነው ፣ለሰዎች በጣም አዛኝ ስለሆነ የብዙ ሰዎች ህይወት መቃናት ምክንያት ነው፣ ብዙ ጊዜ መሪ መሆን አይፈልግም ፣ ከመምራት ይልቅ መከተል ያስደስተዋል ፣ ሴቶች በጣም ስለሚወድ ፣ ከነሱ ጋር አብሮ በመሆን ጊዜውን ያባክናል። ባሏ Gamma male የሆነች ሴት በጣም እድለኛ ናት ፣ በቃ ሽርሽር መዝናናት ፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር በጣም ያስደስተዋል ፣ Gamma ወንድ ለራሱ ከፍተኛ ቦታ ከምስጠቱ የተነሳ ሁል ጊዜም ልክ ነኝ ብሎ ያስብል ፣እልኸኛ ነው ፣ ስህተቶቹን ለመመርመር አይፈልግም ፣ ብዙ ነገር መማር ብዙ ነገር ማየት ስለሚያስደስተው ፣ አንድ ነገር ላይ መርጋት ይከብደዋል ፣ አልፋ ወንድ ሰዎችን ለማስደሰት ብሎ ወሳኔዎችን ሲወስን ፣ Gamma ወንድ ግን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ይወስናል ፣ Gamma male ብቻውን መሆን ቢችልም በህይወቱ ወስጥ ባሉ ሰዎች መወደድን እና መደነቅን ይፈልጋል!

4) Omega Male Personality

ከራሱ ፍላጎት ይልቅ የሰው ፍላጎትን ያስቀድማል ፣ ልክ እንደ ጋማ ወንድ ለሰዎች በጣም ያዝናል ፣ ጋማ እና እሜጋ ወንድ የሚለያቸው ኦሜጋዎች አንድን ነገር እስኪጨርሱ ድረስ አያርፉም ፣ ሳይንስ ፊዚክስ ወይ ሌላ የሚያመራምር እወቀት ላይ ጊዜያቸውን ማሳለፍ ይፈልጋሉ ፣ ትምህርት ላይ እሳት ናቸው ፣ ሃላፊነታቸውን መወጣት ላይ አይታሙም ፣ ሰዓታቸውን በደምብ ይጠቀማሉ ፣ ሰው ምን ይለኛል ብለው ስለማይጨነቁ ፣ ከሌሎች በተለየ የነጻነት ስሜት ይሰማቸውል ፣ እዚህ ጋር ግን ትልቁ ችግር ኦሜጋ ወንድ የሌሎችን ስሜት መረዳት ላይ እምብዛም ነው ፣ መረዳት አይችልምም አይፈልግምም ፣ ያ ቢሆንም ቅሉ ፣ አዲስ ሃሳብ ሲነሳ open minded ነው ፣ ሰዎች እንዲወዱት ወይም ከሰዎች ተቀባይነት ለማግኘት አይጥርም ፣ ከልቡ በሚመነጭ ተነሳሽነት ነው ነገሮችን መስራት የሚወደው ፣ ኦሜጋ ወንድን ያፈቀረች ሴት ስሜቷን ስለማይረዳላት መጎዳቷ ነው !

| ቻLu የ Psychology እና Leadership ተማሪ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
676 viewsቻLu, edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 11:24:59
The DEADLINE is approaching!!!

Apply before April 14 to get full scholarship benefits.
JOIN OUR CHANNEL
https://t.me/+f1BRMl9qxWYxYjdk


TALK TO US AT
@Rasbitwededservices
@rasbitwededchatbot

Students who have their IELTS results can sign up and get 15% off.

Call us now at 0944442700

የማብቅያው ቀን (ዴድላይን ) እየደረሰ ነው!!!

ከሚያዚያ 6 በፊት ጀምረዉ የሙሉ ስኮላርሺፕ አድል ተጠቃሚ ይሁኑ::

የ IELTS ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ሲመዘገቡ የ 15 በመቶ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ

አሁኑኑ በ 0944442700 ደውለው ያናግሩን



@Rasbitwededservices
@rasbitwededchatbot
1.7K viewsቻLu, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 11:09:30 እኛ ወንዶች ግን ምን አይነት ሴት ነው የምነወደው?

በአንድ ወቅት የሳይኮሎጂ ክላሳችን ላይ መምህራችን ወንዶች ምን አይነት ሴት ነው የሚወዱት ብሎ ሲጠይቀን ኮራ ብዬ እጄን አወጣሁና "ቀጠን ያለች " ብዬ መለስኩኝ ፣ ከዛን መምህሩ "አሃ ፣ የየግል ምርጫችንን አንናገራ ..... " ብሎ አሳቀብኝ። ጥሎብኝ ቀጭን ሴት ወዳለሁ ፣ በቃ ትንሽ ረዘም ብላ ፣ ጭንቅጥቅጥ ያለች ፣ ሎጋ ሴት !

ብዙ ወንዶች እንደሚሏት አይነት ፣ ወገቧ እንዲህ ሆኖ ፣ እንትኗ እንዲህ ሆኖ ፣ በዚህ ወታ ፣ በዚህ ገብታ ፣የሚሉት መስፈርቶች የሚያስጨንቀኝ ሰው አደለሁም ፣ ግን እኮ ሚስቴ እንደዛ ብትሆን ደስ ይለኛል

ፍሬሽ ተማሪዎች እያለን ፣ የነበረ ታሪክ ትዝ አለኝ ፣ ጓደኛችን ጥሎበት ቀለሜ ሴት ይወዳል ፣ በቃ ምን ራሷን ብትጠብቅ ፣ ምን አማላይ ብትሆን ሰቃይ ካልሆነች መስፈርቱን አታልፍም ፣ ይቺ በጣም ምሁር ከመሆኗ የተነሳ መነፅር የምታረግ ሴት በቃ እሷን እኮ ካገኘህ Man ፣ ስታወሩ እንኳን እርስ ትግባባላችሁ! ቆይ ቆይ እኔ ያልገባኝ ነገር ግን? መነፅር የሚያረጉ ሴቶች በሙሉ ምሁራን ናቸው ማለት ነው?

ሰው እራሱን የሚመስለውን ሰው ይወዳል! ኢትዮጵያዊ ስትሆን ኢትዮጵያዊት ትማርክሃለች ፣ አንዲት ፈረንጅ ባጠገብህ ስታልፍ ትዘጋሃለች .......(ይቅርታ ለቃሉ ) አጭር ወንድ ስትሆን ረጅም ሴት ማግባት ላታስበው ሁላ ትችላለህ። እኔ ግን እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ አለኝ ፣ ራሷን የምትጠብቅ ሴት የምወደው ራሴን ስልምንከባከብ ይሆን እንዴ ? እስኪ እንደዚህ አጋጣሚዎችን እየተጠቀምኩ ስለራሴ ልጎርር ፣ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሴት ልጅ እራሷን ስትጥል ደስ አይለኝም ፣ dead skin ፊቷ እና ከንፈሯ ላይ ማየት ያማል ፣ እኛ ወንዶች ሴቶች ፀጉራቸውን ፏ አርገው ተሰርተው ማየት ነው ደስ የሚለን አይ የኔዋ ፀጉሯ ሻግቶ ሳይ ነው ደስ የሚለኝ የሚል ካለ እጁን አውጥቶ ማሳወቅ ይችላል

አንዳንድ ወንድ እናቱን የምትመስል ሴት ሲያይ በቃ ልቡ ትርክክ ይላል በቃ ነጠላ ለብሳ ሲያያት ፣ ቀሚስ ለብሳ ክልትው ክልትው ስትል ( ይቅርታ ለቃሉ ) ጎርደድ ጎርደድ ስትል ለማለት ፈልጌ ነው ፣ ብቻ ቃሉ ምንም ይሁን ምን እንደዛ አይነት ሴት ምርጫው ነች ፣ ምግብ ቤት እንጀራ ቀርቦ ሲበሉ ፣ የተጠቀለለውን እንጀራ እያነሳች እኩል ለማዳረስ ማዕዱን ስታበጃጀው ሲያይ ልቡን እፍን ያረገዋል ፣ ወዲያውኑ " አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ፣ ላገባሽ እንደምፈልግ አታውቂምን " ሊላት ነው የሚፈልገው !

ወንዶች ምን አይነት ሴት ነው የምኖደው የሚለው ጥያቄ ሊመለስልኝ ስላልቻለ You tube ላይ ያለች የሆነች ሴትዮ ፣ የሰራችውን video ለማየት ገባው ፣ በቃ ስሰማው "ልቤ በቁስል ደማ " ግን ልቤ በቁስል ደማ ይባላል እንዴ ? አዲስ አባባል ነው ለማንኛው ከተናገረቺው በሙሉ ሃሳቤ የገዛኝ ነገር ፡ "ወንዶች መንፈሳዊ ህይወቷ ጠንካራ የሆነች ሴት ይወዳሉ " ፀሃይም ወጣ ዶፍም ዘነበ በቃ ፣ ከ ፈጣሪዋ ደጅ የማትርቅ ፣ ልባም ሴት!

ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? እሷ ለመማር ሰንፋ አታውቅም ፣ ይልቁንስ ሌላ ተጨማሪ ድግሪ ትማራለች ፣ የንድፈ ሃሳብ ሰው ብቻ አደለችም ፣ Internship ትሰራለች ፣ በጠዋት ከመኝታዋ ትነሳለች ፣ እጆቿን ላፕቶፗ ላይ አረገች ፣ ለማወቅ ሰንፋ አታውቅም! ባሏ በግቢ ውስጥ ብቻውን በሆነ ጊዜ ፣ አብራው ሆነች አልተለየችውምም! መማሯ ለመልካም እንደሆነ ታዉቃለች ፣ የዶርሟ መብራት በለሊት አይጠፋም! ባሏ በስራ እና በንባብ ተጨናንቆ ሩቅ አገረ እንደቆየ ሰው በናፈቃትም ጊዜ ፣ ጊዜ ስጠኝ እያለች አትጨቀጭቀውም!

ተጻፈ | ቻLu ዘብሔረ Psychology እና Leadership

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us @qelemaat | @qelemaat
775 viewsቻLu, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 17:40:40 ስታነቡ ሃሳባችሁን መሰብሰብ ለከበዳችሁ ቀላል የሳይኮሎጂ መንገድ | ሳይውል ሳያድር ተጠቀሙበት


#study_tips #ethiopia #psychology

YouTube ላይ ይመለከቱ :




TikTok ላይ ይመለከቱ :
https://vm.tiktok.com/ZMYqqxBt6/
1.2K viewsቻLu, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:18:05
ህይወቱ እስከሚጀምር እድሜ ልኩን የሚጠብቅ ሰው አይታችሁ አታውቁም? (… እንዴታ! እናንተው ራሳችሁ ናችሁ!) … ህይወቱ የሚጀምረው የዶክትሬት ዲግሪውን ሲያገኝ እንደሆነ የሚያስብ፤ ህይወቱ የሚጀምረው ዲቪ ሲደርሰው የሚመስለው፣ ደስተኛና አመስጋኝ መሆን የሚችለው ያሰበውን ገና ወደፊት ሲያገኝ እንደሆነ የሚያስብ... ህልውና ግን ከጀመረ ቆይቷል፡፡ ትርጉሙም ያለው ዛሬ ላይ ነው፡፡ ትዝታና ተስፋ ላይ የተቀመጠ ትርጉም፣ ህይወትን እስኪጀምር የሚጠብቁ እና በህይወት ላይ እያሉ የሞተ ትርጉምን የሚያነቡ “ዞምቢዎችን” ይፈጥራል፡፡

ጥያቄው፡- መኖር ወይንም አለመኖር ሳይሆን to realy be or to be with out being real. ጥያቄው ይህ ነው፡፡

የጥበቃ ህይወት፤ ህይወት አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለ ህልውናቸው የሚሰጡት ትርጉም የለም፡፡ ከመጠበቅ ውጭ፡፡ የህልውናቸው ትርጉም ጥበቃ ቢመጣም አያውቁትም፤ የሚጠብቁት ምን አይነት ነገርን እንደሆነ ለእነሱም ግልፅ ስላይደለ፡፡ ጠባቂዎች የስቃይ ሰለባዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶች እድሚያቸው ይገፋል፡ ሌሎች ሲጠብቁ እንደኖሩ ያልፋሉ፡፡ ትርጉም የሌለው ጥያቄ እየደገሙ ይጠያየቃሉ፡፡ ትርጉም ያለው መልስ ሌላ ሰው አብስሎ ይዞልን ይመጣል ብለው ይጠብቃሉ።

ህይወት ጥበቃ አይደለም። ሙከራ ነው- ደግሞ ደጋግሞ መሞከር። ልምምድ ነው። መኖር ነው። የራስን ትርጉም ራስ ማብሰል። የራስን እድል መፍጠር። የተፈጠረውን እድል እንዳይባክን መጠበቅ። የውልደታችን ቀን የጀመረ በሞታችን ቀን የሚጠናቀቅ ኮንትራት ነው ህይወት። ገድሉም፣ ትግሉም ያለው እዚሁ ምድር ላይ ነው። ለሰማይ ቤት ዙፋን ትሩፋት የምንሰበስብብበት አጭር ህይወት ናት ያለችን።

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us  @qelemaat |  @qelemaat
169 viewsGech, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ