2022-08-29 15:11:07
ሴትን አላምንም
ክፍል 1
" አቅራቢ semir ami "
"ዓለም በአውንታዊና በአሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት። ከአንድ መልካም ነገር ጐን ሌላ መጥፎ ነገር አለ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥ ሌላ መልካም ነገር ይገኛል።" ማንበብ የጀመርኩት መፅሀፍ ውስጥ ያገኝሁት ቆንጆ አባባል ነው።
ምን ያደርጋል የህይወትም መፅሀፍ የማንበብ ጣእሙ ጠፍቶብኛል ሁሌም ከጐኔ ሚታዬኝ መልካም ነገር ሳይሆን ላይመለሱ የሄዱ ትውስታዎች ናቸው።
ለብቻዬ የሰራሁት አንድም ታሪክ የለም በታሪኬ ውስጥ ሁሉ እሷ አለች "አህላም" በማጣቴ ውስጥ እጄን ይዛ አልፋ ፣ በማግኝቴ ውስጥ ተደስታ ፣ የጐጆዬን ቀዳዳ በላቧ ጠብታ ሞልታ ፣ ውበቷን ገብራ ፣ ሴትነቷን አሲዛ ፣ ውጣ ውረዶችን አልፋ የሄደች መልካም ሚስት እሷ ነበረች ታሪኬን ተጋርታ ያለፈች ።
እሷን የነጠቀኝ ማጣት ሁሌም ሳማረው እኖራለው ማጣት ህልሜን ወስዷል ፣ ድህነት ለአደባባይ አጋልጦኛል፣ ሁሌም ስብከነከን እኖራለው በማን ይፈረዳል? ድህነት ማን ነው? የት ነው ያለው? መግደል ይቻላል? ገድሎ የጣለን ጠላት መበቀል ልዩ ስሜት አለው እስኪ አሳዩኝ እና የልቤን ላድርስ።
ይሄን ሁሉ ወሬ መንገድ ላይ ለብቻዬ ነው ማወራው ድምፄን ከፍ አድርጌ ስለነበር ብሶቴን ለራሴ ደግሜ ምተርከው መንገዱ ላይ ሰዎች መኖራቸው ልብ አላልኩም።
ልብ ያሉኝ ሰዎች ግን " ከመሞት መሰንበት " ብለው ከኔ በተቃራኒ መንገድ ላይ ጉዞዋቸውን ቀጥለዋለው።
መድረሻቸውን ያወቁ ተጓዦች በመንገዱ ላይ ይኖራሉ መሄጃውን ያላወቀ ተስፋ የቆረጠም በመንገዱ ላይ ይኖራል ሁለቱንም መለየት ምንችለው ግን ተከትለን መጨረሻቸውን ስናይ ነው።
ሰው መጨረሻውን ባለወቀው ነገር ለምን እንደሚፈርድ አይገባኝም እኔም እኮ ጅማሮው ያማረ ትዳር ነበረኝ ሁሉም በየመንገድ ያየን ሰው ስታስቀኑ ያላለን መች አለ ፣ የአብራህምና የሳራ ትዳራቹ ይሁን ብሎ ያልመረቀን አንድ ሰው ያለ አልመሰለኝም።
አብራሃም እና ሳራ በማጣት ተለያይተዋሉ እንዴ? ከዚህ የሃሳብ ምስጠት ውስጥ በመንገድ ላይ ያሉ የህፃናቶች የጩህት ድምፅ ከሃሳቤ አባነነኝ ።
ሴት አላምንም መጣ ሩጡ ፣ ሴት አላምንም መጣ ሩጡ እየተባባሉ ይሯሯጣሉ።
እድፍ ያጨቀየውን ልብስ የለበሰው "ሴት አላምንም" መሪ ቃሉ ይዞ በሰፈር በኩል ያልፋል።
" ሴት አላምንም ! አዎ ሴት አላምንም ይላል" ለምንድን ነው ሴት ማያምነው? ምንድን ነው ለዚህ ያበቃው? እያልኩኝ ሁሌ ታሪኩን ለማወቅ እጓጓለው። እኔስ አህላም ስለ ሄደች " ሴት አላምንም እያልኩኝ ከእሱ ጋር አብሬ ሰፈር ልረብሽ ልብሴን ላቆሽሽ? የኔና አህላም ታሪክ ለማን ልንገር ለሱ ልንገረው ይረዳኝ ይሆን ብዬ ከራሴ ሙግት ይዣለው። የኔና አህላም ታሪክ ምን ነበር?
:
:
ክፍል ሁለት ይቀጥላል.........
አስተያየት እንፈልጋለን
@yegetemkalat
@poem_merry
4.2K viewsSemir ايمي سمير, edited 12:11