Get Mystery Box with random crypto!

ሴትን አላምንም ክፍል 2 አቅራቢ semir ami አሰልቺውን የህይወት ጉዞዬ በብቸኝነት ውስጥ | እግር ኳስ Meme™

ሴትን አላምንም

ክፍል 2
አቅራቢ semir ami

አሰልቺውን የህይወት ጉዞዬ በብቸኝነት ውስጥ ማለፉ ሌላ አንድ ተግዳሮት ሁኖብኛል ሲከፋኝ ምታፅናናኝ እና ስቸገር አለሁ ሚለኝ እንደ አህላምዬ አይነት ሰው አልነበርም። ምክሮቿ ሁሌም ልቤ ላይ እንደ አለት ተጣብቀዋል። "የኔ ባል ችግር በመጣብህ ጊዜ የተለዬ ችግር እንደደረሰብህ አታስብ። ተመሳሳይ ችግርን ከአንተ በፊት በርካታ ሰዎች እንዳለፉበት እወቅ። ራስህን የችግር ማካማቻ አድርገህ አትቁጠር። ሁሉም ጋር ችግር አለ። አንዱ ፈትቶ ፣ ሌላው ደብቆት ነው። በችግር ውስጥ ብቸኛ የችግር ሰለባ እንደሆኑ አድርጎ እራስ ላይ መጥፎ ስሜት መፍጠር የችግሩ የመጀመሪያ ችግር ነው። ከምንም በላይ ደሞ እኔ አለሁልህ እኔ ሀዘኔን የምረሳው ፣ መከፋቴን በሳቅ የምቀይረው አንተን ሳገኝ አይደል? አንተን አግኝቻለው ያጋጠምን የህይወት ፈተና በትጋት እንወጣዋለን የትኛውም የህይወት ፈተና ባጋጠመኝ ጊዜ ባንተ መፈቀሬን ሳስብ ልበ ሙሉነት ይሰማኛል። ስለዚህ በርታ እኔ ሁሌም ከጐንህ ነኝ ካንተ ጋር ማሳልፈው እያንዳንዱ ቅፅበት ነብሴን በደስታ ትሞላለች።"

ድንገት ይህን ስትለኝ የደከመው መንፈሴ በአንዴ ይነቃቃል እቅፌ ውስጥ በስስት ትገባና… "ስትደክም እደክምብሃለው ፣ ተስፋ ስትቆርጥ ከአንተ በላይ እቆርጣለው እባክህ በርታና አብርታኝ። የቤተሰቦቼ ወሬና ለሰዎች አሉባልታ ቦታ አትስጠው ትለኛለች። "
ፊቴ በፈገግታ ይሞላል ፣ ባልራመድም እግሬን ጫማዬ ውስጥ አጠልቀዋለው ከፍቷት ሀዘኗን ማየት ባልፈልግም ግን ምን ላርግ? እንባ እየተናነቀኝ ከቤት እወጣለው ጥሪ ካስተናገደ ረዥም ጊዜ የሆነ ስልኬን ስከፍተው በድምቀት የተደገሰው የሰርጋችንን ፎቶ እኔን ለማናደድ ይሆን ሌላ ከነ ፈገግታችን ያሳየኛል። ይሄን ፈገግታችን መቼ ነው የምመልሰው? እያልኩኝ ከራሴ ጋር አወራለሁ ለሚወዱት ሰው ከለላ አለመሆን እንዴት ልብን ይሰብራል? ፈገግታዋን በእንባዋ ሳላሻርክ ፣ ሩጫዋን ወደ ኋላ ሳላስቀር ፣ ምቾቷን ሳልነጥቅ በደስታ አኖራታለው ብዬ ቃል የገባሁበት ቀን ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስብ የታለ ቃሉ ብዬ እራሴ ላይ እጮህበታለው። እሷ ቃሏን አክብራለች ቢያጣም ፣ ቢያገኝም ፣ ቢደህይም ከአጠገቡ ላርቅ ብላ የገባችው የህይወት ቃል ይህው እንደፈፀመች ነው መኪናዬ ውስጥ በገባችበት ፈገግታ ፣ ታክሲ ውስጥም እኩል ትገባለች። ደግሞ መጣ " ሴት አላምንም ፣ አዎ ሴት አላምንም ይላል" እኔም ከመልመዴ የተነሳ ማለቱን ሲጀምር እንደ ህፃናቶቹ እኩል " ሴት አላምንም ፣ ሴት አላምንም " ብዬ ሳቄን ለቀቅኩት ለምን ሴት አያምንም? አይመና እኔ ግን ስለ ማምናት ሴት ታሪክ ፈተና እና ህይወት ምነግረው ሰው እፈልጋለው ታሪካችንን ስሙን። አህላም ማነች ?

ክፍፍ ሶስት ይቀጥላል

ቻናላችንን ሼር
@yegetemkalt
@poem_merry
አስተያየት እንፈልጋለን