Get Mystery Box with random crypto!

እግር ኳስ Meme™

የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የሰርጥ አድራሻ: @poem_merry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 904
የሰርጥ መግለጫ

ጥበብ እንደ ጥጥ ነው ለጉድ ተፈልቃቂ
ሰው ጥሩ ፈታይ ነው ድር ማግ ግን አላቂ
ስለ ግጥም ብላቹ @buchula36 ላይ አዋዩኝ
የናንተ ድምፅ ነው ለኔ እውቀት የሆነኝ
.
.
.
@buchula36
@yegetemkalat
@ortodox_fkr

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-12 07:14:06 ምን ይባላል የለ አንደበት
ለሚሳለቅ በ'ግዜር ፍጥረት
ለሚያስነባ ትውልድ በገፍ
አይገልፀውም ቃል ቢሰለፍ
ብቻ ይንገስ ይለፍለት
ይደላደል ሁሉ ይሙላለት
ለሚረግፈው ቅጠል ዝንጣፍ
በሰው ሳይሆን በግዜር መዳፍ
ይከፍላታል ቀኑ ሲደርስ
ላረከሰው ዙፋን መቅደስ
ላፈሰሰው የደም ዥረት
ላስለቀሰው የ'ናት አንጀት
ወላዲቷን ቀን ይፈርዳል
በሰፈረው ይሰፈራል።

MaኅDeር

@yegetemkalat
@poem_merry
190 viewsMerry G, 04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 21:35:21
1.4K viewsባህራን, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 21:21:33 ሳይጀመር ለቀረ
ለባከነ ፍቅር
ጥንስሱን መተው ነው
ሁሉም እርግፍ ይበል
ሁሉም ነገር ይቅር
መ..ተ..ው ለለመዱ መተው ምንም ነው
የኔና አንቺ ፍቅር ሳይጀመር ያለቀው ምክንያቱ ምንድን ነው
ጀመሩ ስንባል
እፍ አሉ ስንባል ባንዴ ለተቋጨው
የኔና አንቺ ፍቅር ምን ነበረ ምርጫው

ሳታውቂኝ አወኩሽ
እያደረ በዝቶ ያንቺም ፍላጎትሽ
ተውሽኝና ተውኩሽ
ገና ከጅምሩ
ተራርቀው ቀሩ
ተብሎ ቢወራ ለመንደር ለሃገር
ምክንያቱን አያውቁት
ምክንያቱን አናውቀው የኔና አንቺን ነገር

ሳንጀምር ጀመርነው በደስአለኝ ዲስኩር
በደስአለኝ ምናብ
ለጊዜያዊ ምቾት ለጊዜያዊ ድባብ

ዮኒ
ኣታን @Yonny_Athan

@poem_merry
@yegetemkalat
1.7K viewsMerry G, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:04:02 የሚፈልጉትን መፅሀፍ መርጠው ያንብቡ
393 viewsMerry G, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 10:35:25 ህሊና
እኔ ተደንቄ በአእምሮ አፈጣጠር
ስጋ እንዴት ያስባል ብዬ በመጠርጠር
አእምሮ ስጋ ነው እንዴት ያስባል
ቀምሮ አስልቶ አውጥቶ ያወርዳል
አእምሮ ለብቻው ጋዝ አልባ ፋኖስ
ጋዙን ዶለንበት ከክሩ ሲደርስ
የብርሃን ዓለም መካነ መንፈስ
የህሊና ምግባር ልክ እንደጋዙ ነው
አእምሮ እንዲሰራ ምርኩዝ የሚሆነው
LISE DECH SOFI YE LASTAWA
@LISEDECHSOFI

@yegetemkalat
@poem_merry
558 viewsMerry G, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 09:47:59
#የቻናል_ጥቆማችን ....
እየተዝናኑ እያወቁ የሚያተርፉበት ድንቅ ቻናል

|| የሙሐዘ ጥበባ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሑፎች መገኛ ||
377 viewsMerry G, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 04:45:31 ትልቅ ለውጥ
ትልቅ ለውጥ በትንሽ አስተሳሰብ አይፈጠርም። በህይወትህ ላይ ምን እንዲለውጥ ትፈልጋለህ ? መጀመሪያ አንተ እንዲለወጥ በፈለከው ነገር ልክ መለወጥ አለብህ። ህይወትህ ላይ ነገሮች ምርጥ እንዲሆኑ ትፈልጋለህ አንተስ በዛ በፈለከው መጠን ምርጥ ነህ?
የብዙ ሰው ችግር ይሄ ነው። ህይወታቸው በአንድ ለሊት እንዲለወጥ ከመፈለግ ውጪ እነሡ ለለውጥ ዝግጁ አይደሉም። ሀብታም መሆን ፈልገህ ነገር ግን ሀብት የሚመጣበትን አማራጭ ካልፈለክ ሀብታም ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ ካልከፈልክ ትልቅ እሚባል ለውጥ እንዴት ታስተናግዳለህ?

ህይወት የምትለወጠው አልጋህ ላይ ተጋድመህ በምታልመው ህልም ሳይሆን ህልምህን ለማሳካት በወሰንከው ውሳኔ ልክ ነው። ለውጥ የሚመጣው አንተ ለመለወጥ ስትዘጋጅ ነው። ለለውጥ ዝግጁ የሆነ ሠው የትኛውንም ዋጋ ይከፍላል። ዋጋ መክፈል ካቃተህ ከልተዘጋጀህም በቃ እመን። ሰበብ አትፈልግለት ዋጋ ላለመክፈልህ።

አንድ ምግብ ቤት ገብተህ ለመመገብ እኮ ፍላጎት ብቻውን በቂ አይደለም የምትገለገልበትን የምግብ ዋጋ መያዝ አለብህ። የምር ምግቡን መብላት ከፈለክ የምግቡን ዋጋ መክፈል አለብህ። አበቃ ሰበብ አያስፈልገውም። የምር አንድን ነገር ከፈለከው የምር ዋጋ ትከፍልለታለህ። የምር ካልፈለከው ደግሞ ሰበብ ስትደረድር ትኖራለህ አብዛኛዎቻችሁ ሰበበኞች ናችሁ። አዎ ናችሁ። ከስኬት ከለውጥ ከስልጠና ለመራቃችሁ እናት ፣ አባት ፣ ጓደኛ ፣ የሀገር ሁኔታ ፣ የገንዘብ ማጣትን ሰበብ ታደርጋላችሁ። ይሄ ምንም ምክንያት አይሆንም። ምክንያቱም ዋጋ ያልከፈላችሁበት ነገር እጃችሁ ላይ ቢገባም ታቀሉታላችሁ እንጂ አታከብሩትም። ስለዚህ የትኛውም ትልቅ የሚባል ለውጥ ትልቅ የሚባል ዋጋን ያስከፍላል። በዘመኑ ዋጋ የማይከፍል ሰው ምንም እየሰራ እና እየተንቀሳቀሰ ያልሆነ ሰው ነው አበቃ። ስለዚህ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ሁኑ ከዛ ለውጥ ምን እንደሆነ በደንብ ታዩታላችሁ እውነት።

@buchula36

@yegetemkalat
@poem_merry
1.1K viewsMerry G, 01:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 19:10:35
#የቻናል_ጥቆማችን ....
እየተዝናኑ እያወቁ የሚያተርፉበት ድንቅ ቻናል

|| የሙሐዘ ጥበባ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሑፎች መገኛ ||
495 viewsMerry G, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 12:26:09 ባለህ ነገር መደሰትን ልመድ !

ስታማርር ያለህን በአግባቡ ሳታጣጥም ስትቀር ነገ ሌላ አዲስ የምታማርርበት ግዜ ይዞልህ ይመጣል የባስ የምትከፋበት የምታዝንበት ነገር ያመጣብሀል ትላንት ለካ ሁሉ ነገሬ ውብ ነበር ምነው በአግባቡ ብደሰትበት ምነው በጥሩ ባሳለፍኩት ኖሮ የሚያስብል ግዜ ይወጣል ስለዚህ ዛሬህን በደንብ ኑር ባለህ እየተደሰትህ የሚያስፈልግህን ጨምር ስታመሰግን ባለህ ደስታ ላይ ይበልጥ ትጨምርበታለህ !

መልካም ጊዜ ተመኘሁ!

@buchula36

@yegetemkalat
@poem_merry
1.7K viewsMerry G, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 09:09:16 ያሳየሽኝ ሁሉ
የነገርሺኝ ሁሉ አለም ነው ሚዳሰስ
ገመና የለውም እንደ ሚስጥር መንፈስ።
አንቺዬ
በቃል ችሎ መቆም
ለነብስ ውሎን መፆም እንዴት አወቅሺበት
ያደፈ ይነጣል አንቺ ካለፍሺበት።
አዎ
ብቻ እንደው......ግራ ቢገባኝ ውሉ
ነብስ ዘርቶ ታየኝ የቃልሽ ምስሉ
ታድያ
ካጠገቤም ሆነሽ ፍቅርሽን ናፈኩት
ከቃልሽ ቃል ይልቅ ልብሽን አመንኩት።
አንቺዬ
የነካውት........ ያስነካሺኝ
ያሸተትኩት........ የነገርሺኝ
ሁሉም እውነታ አለው..... በቃል ያዋየሺኝ።

በረከት(@berii34)

@yegetemkalat
@poem_merry
1.8K viewsMerry G, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ