Get Mystery Box with random crypto!

እግር ኳስ Meme™

የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የሰርጥ አድራሻ: @poem_merry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 904
የሰርጥ መግለጫ

ጥበብ እንደ ጥጥ ነው ለጉድ ተፈልቃቂ
ሰው ጥሩ ፈታይ ነው ድር ማግ ግን አላቂ
ስለ ግጥም ብላቹ @buchula36 ላይ አዋዩኝ
የናንተ ድምፅ ነው ለኔ እውቀት የሆነኝ
.
.
.
@buchula36
@yegetemkalat
@ortodox_fkr

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-10-28 21:46:25 ።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር ።።።።።።

ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር
እንዴት አትበሉ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ብታውቁ ምንም ላይጠቅማችሁ
አጠይቁኝ እኔን ትላንትስ ብላችሁ
ታሪኬን የዃሊት እያስታወሳችሁ
የት ነበርሽ አትበሉ አታብዙ ጥያቄ
የትስ እንደነበርኩ እኔ የት አውቄ
ምላሼን በመሻት ጥያቄ አታብዙ
ዃላ ብነግራችሁ ብዙ ነው መዘዙ
አታድሙት ቁስሌን በሾክ ወጋግታችሁ
የማያባራ ደም ጉድ እንዳይሰራችሁ
ዝምታዬ ጎልቶ  ስሜት ካልሰጣችሁ
አላደክምም ራሴን አንዱም ላይገባችሁ

ስለዚህ እባካችሁ።።።።።።።

አጠይቁኝ ይቅር የለኝም መልሳችሁ።
 
@yegetemkalat
@poem_merry
5.6K viewsMerry G, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:25:09 ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)

የሆነ ጊዜ ላይ የተወሰኑ ጓደኞቼን የምወዳት ልጅ ወላጆች ቤት ሽምግልና ላክሁዋቸው::
የፍቅረኛየ አባት “ልጁ ምናለው?” ብለው ጠየቁ ::
ከሽማግሌዎች አንዱ ትንሽ ሲያቅማማ ከቆየ በሁዋላ፥

“ ከሁለት መቶ ሺህ ያላነሰ ተከታይ አለው፤ ፌስቡክ ላይ “ ብሎ ተከዘ::
ቁሞ የመቅረት ታሪኬም በዛች ቀን ጀመረ፤

በቀደም ለታ፥ ፌስቡክ ፥ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ተከታዮቼ መካከል፥ ዘጠኝ ሺውን ብቻ አስቀርቶል ሌላውን አፈሰብኝ፤ የገንዘቡ ሳያንስ የተከታይ ግሽበት መታገስ የምችልበት ጫንቃ አልነበረኝም::

ከተከታዮቼ መሀል ፥ ጽፌ የምለጥፈውን አንብበው መውደዳቸውን የሚያሳዩኝ አስተያየቱን የሚለግሱኝ ከአስር ሺህ አይበልጡም፤ ከተከታዮቼ መሀል” ክንዴ ቢዝል፥ ምላሴን ቢያዳልጠው፥ ግጥሜ ልቦና ባይረታ፥ ቀልዴ ጥርስ ባይመታ፥ ልክ ልኬን ሊነግሩኝ መከትከቻውን እየሳሉ እሚጠብቁኝ እንዳሉ አውቃለሁ፤ዝም ብለው ደጃፍ ላይ ተቀምጠው ሳልፍ ሳገድም እሚያዩኝም ሞልተዋል::

ቢሆንም “
“ባይነዳ ባይረዳ ባይኖረውም ሀብት “
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል አባት “ ይላል እማ ሸንበቆ ጠላ ቤት ግድግዳ ላይ የተለጠፈ ጥቅስ!
እኔም እለላሁ፤
“ባይለይክ፤ ባይኮምንት ፤ አሻራው ባይታይ”
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል ተከታይ”

የፌስቡክ አለቃ ፥ በሁሉን አወቅነቱ፥ ይህንን ስሜቴን ተረድቶ ፥ በነበሩት ተከታዮቼ ላይ አንድ የቀበሌ አዳራሽ የሚሞሉ ተከታዮች ከራሱ ጨምሮ መለሰልኝ::

በባለፈው ዝግጅት ላይ ለታደሙ ወዳጆቼ የምስጋና ቃል ልጽፍ ሰንዳ ሰንዳ ስል መብራት እልም አለ:: እኛ ሰፈር ያለው ትራንስፎርመር በሚፈነዳበት መጠን የልደት ፊኛ አይፈነዳም ፤ አሁን አሁንማ፥ መብራት ሲጠፋ እንደ ድሮው መናደድ አቁሚያለሁ፤ በጨለማ ውስጥም ቢሆን ስራ እንዳልፈታ ምቾት እንዳላጣ አድርጌ ራሴን አላማምደዋለሁ፤ ሆመር ፥ ሀሰን አማኑ፥ እማሆይ ገላነሽ፥ ወዘተ፤ ውበት ፥ ሀሳብ እና ለዛ ለማፍለቅ የግድ ውጫዊ ብርሀን አስፈላጊ እንዳልሆነ ምስክር ናቸው፤ እንዲህ እያልሁ ዘና ብየ ጥቂት እንደቆየሁ አምፖሉ እንደ ነሀሴ ሰማይ ብልጭ ብሎ ድርግም ይላል፤ ጉዋደኛየ ምኡዝ አንድ የሚወዳት ልጅ ነበረች፤ የሆነ ቀን ሲጽፍላት አትመልስም፤ ሲደውልላት አታነሳም፤ ጭራሽ ለተወሰኑ ወራት መገኛዋን ሁሉ ትደመስሳለች፤ እሱም ያለ እሷ ለመኖር ራሱን ለማለማመድ ይፍጨረጨራል፤ ከዛ እፎይ ብሎ እየኖረ እያለ You miss me? '' የሚል ቴክስት ትልክለታለች፤ አምፖሌ ብልጭ ብሎ የተለማመድሁትን የጨለማ ደስታ ሲያደፈርስብኝ ትዝ የሚለኝ ይሄ ነው፤

ጥለት ሚድያ ባሰናዳው የሰኞ ዝግጅት ላይ የታደማችሁ ምስጋናየን ይድረሳችሁ፤ ገና ሁለተኛ ዝግጅታችን እንደመሆኑ መጠን ጉድለታችንን ለማሻሻል አጥብቀን እንሰራለን፤ ሐረር ባንድ ጀንበር አልተገነባችም፤ (በጊዜው በጉልህ የታየው የድምጽ ችግር ከመብራት መጥፋት ጋራ በተያያዘ በጄኔረተር ምክንያት የመጣ ነው፤ ለዚህ ይቅርታ እንጠይቃለን) ሌላ እንዲስተካከል እምትፈልጉትን ሳታስባንኑ ፥ በአካል አግኝታችሁ፥ ምሳ እየጋበዛችሁ፤ ትከሻየን እየቸበቸባችሁ ንገሩኝ፤ በማቱሳላ አቆጣጠር ገና ልጅ ነኝ፤ እታረማለሁ::

የዝግጅቱ ቀን ከጉዋደኛየ ጋራ ስደርስ ጥቂት አርፍጄ ነበር፤ ከብሄራዊ ትያትር ወዲህ ማዶ፥ ኢትዮጵያ ሆቴልን አለፍ ብሎ ሰው በረጅሙ ተሰልፎ ሳይ ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ፤ ልቤ ተነካ፤” ወንድ ልጅ ብቻውን ነው እሚያለቅሰው “ ይላል ባለቅኔ ጸጋየ ገብረመድህን:: እኔ ግን ወንድ ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ባያላቅስ ደስ ይለኛል፤ የዛን ቀን ግን አልቻልኩም፤ የደስታ እምባየ “ናፕኪን” ከደረት ኪሴ እስካወጣ እንኳን አልታገሰኝም

“ አሁን እኔ ይሄን የሚያህል ሰልፍ deserve አደርጋለሁ?”
አልሁት ጓደኛየን፥

“ ተረጋጋ! እነዚህ ወደ ሜክስኮ የሚሄደውን ምኒባስ ለመሳፈር የተሰለፉ ናቸው “

ከወደዱ ያጋሩ

@yegetemkalat
@poem_merry
8.1K viewsMerry G, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:49:58 ጥበበኛዋ ትል

አንዲት ትል ከአንድ ራጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያለውን ፍሬዎች በመመልከቷ ከፍሬው ለመመገብ ወደ ዛፉ ላይ የመውጣትን ጉዞ ጀመረች፡፡ በእሷ ፍጥነት (ዝግመት) ዛፉን ወጥታ ያሰበችበት ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈጅ ከተሞክሮ ብታውቀውም በጣም የምትወደውን ዜማ እያንጎራጎረችና ወደላይ በወጣች ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየታያት የመጣውን የአካባቢ ገጽታ እያየች በደስታ ዳገቱን ተያያዘችው፡፡

ብዙም ሳትርቅ ከዛፉ ላይ ወደታች የምትወርድ አንዲት ምንነቷ በውል ያልታወቀ እንስሳ ቆም ብላ፣ “ወደየት ነው እንደዚህ በደስታ እየተፍለቀለቅሽ የምትሄጂው አለቻት”፡፡ ትል፣ “ዛፉ ጫፍ ላይ ያለውን ፍሬ ልበላ” አለች፡፡ እንስሳዋም፣ “በቅድሚያ እኔ ከዚያ ነው የመጣሁት፣ ፍሬዎቹ ገና አልበሰሉምና አትልፊ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ አጉል ደስተኛነትና አዎንታዊነት አያጥቃሽ ጉዞው ቀላል እንዳይመስልሽ፣ ስለዚህ ብትመለሺ ይሻልሻል” አለቻት፡፡

ትሏም፣ ቆም ብላ እዚያ ለመድረስ የሚፈጅባትን ጊዜ ካሰላች በኋላ፣ “ችግር የለውም፣ እዚያ እስከምደርስ ድረስ ፍሬዎቹ ይበስላሉ” በማለት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ያሰብከው ከፍታ ለመድረስና የለፋህበትን ፍሬ ለማግኘት . . .

1. ዓላማህን ከጊዜ አጣጥመህ እቅድ አውጣ

ከሁሉ በፊት ለመድረስ የምትፈልግበትን የዓላማ ከፍታ ወስን፡፡ ከዚያም፣ እዚያ ዓላማህ ጋር ለመድረስ የሚፈጅብህን የጊዜ ሁኔታ አስላና ሁለ-ገብ እቅድ አውጣ፡፡ ሁለ-ገብ እቅድ ማለት፣ እንደ አንተ ሁኔታ ገንዘብን፣ ትምህርትን፣ እድሜን . . . ያካተተ ሊሆን ይችላል፡፡  

2. የሰዎችን ሃሳብ ማመዛዘን

ሁል ጊዜ ከፍ ያለ እቅድ ስታወጣና መንቀሳቀስ ስትጀምር ተቃራኒውን የሚነግሩህ ሰዎች እንደሚያጋጥሙህ አትርሳ፡፡ አንዳንዶች ለአንተ አስበው በቅንነት፣ ሌሎቹ ደግሞ በአንተ ላይ አስበው በምቀኝነት፡፡ በጭፍንነት ከሰማሃቸው ውጤቱ ው ስለሆነ ሁለቱንም ቢሆን በጥንቃቄ ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡

3. በጉዞው መደሰት
ወደ ዓላማህ በአንተ አቅምና ፍጥነት ስትጓዝ ፍጻሜው ላይ የመድረስን ደስታ እስከምታገኝ አትደበር፡፡ የጉዞ ደስታ የሚባልም ነገር እንዳለ አስብ፡፡ የመድረስ ደስታ ዓላማህ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ያስጠብቅሃል፡፡ የጉዞው ደስታ ደግሞ አሁኑኑ በመደሰት ለጉዞው ጉልበትን ይሰጥሃል፡፡ በማንኛውም ጉዞህ ውስጥ “የምታዜመውን ዜማ” ፈልግ፣ የምትስቅበትን ምክንያት ፍጠር፣ ዙሪያህን እየቃኘህ ተደሰት፡፡ ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ ነውና፡፡

ያሰብከው ደረጃ መድረስህና ፍሬህን መብላትህ አይቀርምና፣ በፍጹም እንዳትቆም!!!

ሀሳብ አስተያየት @buchula36

@yegetemkalat
@poem_merry
7.0K viewsMerry G, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 20:23:36 //ልጠብቃት\\
አንዲት ቆንጆ መልከ ቀና፤
    ቀና ብዬ አየሁና፤
 ባለማመን ሳለሁ ገና።
 ፊቴን ሳብስ በተደሞ፤
      በአለም ካለሁ
      ወይም ደግሞ።
እውነት ከሆንኩ ሳረጋግጥ፤
  እኔን ጥላ እሷ ጥፍት።
  እፉዬ ነች የኔ ገላ፤
ታይታ የጠፋች እንደ ጥላ።
ገነት ይሁን እኔ የሄድኩት፤
ሴት መላእክት ነው ያየሁት፤
 ግን እፆታ መች አላቸው፤
 መላእክትስ አንድ ናቸው።
   ብዬ ብዙ ስደናገር፤
   ሳላናግር ስግደረደር።
  ንፋስ መጥቶ አበነናት፤
  እፉዬ ነች በቃ አወኳት፤
ስትዞር ውላ የማይደክማት፤
  ንፋስ ወስዶ እንዳራቃት፤ 
   ማረፊያዋን ካላገኘች
     እየገፋ ከመለሳት፤
ተስፋ አልቆርጥም.........
..................ልጠብቃት።
 
@abela_black

@yegetemkalat
@poem_merry
6.6K viewsMerry G, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 20:20:19 ፡፡፡ የይሁዳ ደብዳቤ ፡፡፡
<< አለም ሑሉ ያልፋል >>
ቢሆንም የአምላክ ቃል ከህይወት ይፃፋል÷
የ ሰላሳዉ ዲናር የማይሻር ዳፋ የማን ነዉ ጥፋቱ?
ግሳንግሱን ትቶ ዘመን እያለፈ ቃል ካልሆነ ከንቱ÷
የቀደመዉ ቃልህ ከበደል ከፃፈኝ
ደህና ሁን ክርስቶስ
ስሞ ከመሸጥ ዉጭ አንዳች ምርጫም የለኝ፡፡


ያብስራ እዮብ (ደብተራዉ)፡፡

@yegetemkalat
@poem_merry
6.3K viewsMerry G, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:11:22 ጦሩ ፍቅርሽ
ልቤን ወጋው፤
እንዳልነግርሽ
በጣም ፈራሁ።
አያልቅብሽ ጦር ውርወራው፤
ስንቱን አዳም ልቡን ገዛው።
ልክ እንደንብ እኛ ሆነን፤
አበባ አንቺን፤
ልንቀስምሽ በጣም ጓጉተን።
በዙሪያሽ ስንዞር
ልንከብሽ ስንሞክር።
ገለል አርጎ የከለለሽ።
አንቺን ያዘ ብልጡ አፍቃሪሽ።
ላንቺ ብለን ንብ ስንሆን፤
በብልሁ በአትክልተኛው ተቀደምን።

@abela_black

@yegetemkalat
@poem_merry
8.8K viewsMerry G, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 19:04:57 አንቺ ጋር ምን አለ..?
----------
.
የሳቅ ጠባብ መንገድ ፣ የጎድን ር'ግፎ ፣
ሰው የሸሸው እንባ ፤ ፊቴ ተዘርግፎ ፣
የትዝታ ዘፈን
ልቅሶ ተሸክሞ ፤ ልቤን ይፈትሻል
የለሁም አትበይኝ
ከወዲያ ጥግ ዳር ፤ ምን ታሪክ አይተሻል?

የለሁም አትበይኝ

ይልቅ ልጠይቅሽ
ትዝታ ሚመስል
ትዝታ ያይደለ
እኔ ጋር ያለውን የተመሳሰለ
አንቺ ጋር ምን አለ?
ተስፋ አለ?
ቃል አለ?

የሃዘን ትብታብ ክር ፤ ዙር አንገቴን አቅፎት ፣
ያረጀ ማሲንቆ ፤ ባረጀ ቅላጼ ፤ ልቤን ተደግፎት ፣
.
.
አለፈ ያልኩት ቀን ፣ እያለኝ አላልፍም ፣
ጠፍቷል ያልኩት እንባ ፣ እያለኝ አልነጥፍም ፣

እኔ ጋር ተስፋ አለ ።
አንቺን የመሰለ

ይልቅ ልጠይቅሽ
ትዝታ ሚመስል
ትዝታ ያይደለ
እኔ ጋር ያለውን የተመሳሰለ
አንቺ ጋር ምን አለ?
.
.
አንድ ራሱን ጥሎ
ሌላ ሰው ፈለጋ ፣ ልብሽ ይሸፍታል ?
ሳቅሽ እንዴት ሆነ ፣ ወይስ ሃዘን በልቷል ?
በትዝታሽ ድንኩን ፣ ሙዚቃ ተከፍቷል ?

በነገራችን ላይ

ትዝታ ውብ መልኩን ፣ ዘንበል እንዳረገው ፣
ፍቅር ውብ ታሪኩን ፣ ሸብለል እንዳረገው ፣
ያለፈ ሙዚቃ ፣ ምን አፈላለገው ?

ተስፋ አላት ማለት ነው ?
ቃል አላት ማለት ነው ?

የለኝም ካልች ግን ...?

ህይወት ሁሉን ትቶ
ያልነበረን ትናንት
ይኖራል እያለ ፣ ለምን ይፈልጋል?
ሁለት ተጉዥ እና
ምንም ቁሚ መሃል ፣ ዘፈን ምን ያደርጋል?

ያለፍ ሙዚቃ
ትዝታ 'ሚመስል
በ'በበዛወርቅ ድምጽ
ከወደ እሷ በኩል ፣ ለምን ይከፈታል ?
የለሁም ያለችን ፣ ትኖራለች ብለው ፣ እንዴት ያፈቅሯታል ?

ተስፋ አላት ማለት ነው ..?
ቃል አላት ማለት ነው..?

ቢኖራት ነው እንጅ ።

ሃገሬው ቃል ገብቶት
በእንጉርጉሮው መሃል
የምርቃቱን ደንብ ፣ የሚል ይሁን ይሁን ፣
ቢኖራት ነው እንጅ
የመንደሩ ዘፈን
እሷ ጋር አንተ አለህ ፣ ትመጣለች አሁን ፣

ቢኖራት ነው እንጅ ።

ግን
አሁን ማለት መች ነው ?

አሁን ማለት ማለት
አሁን ማለት እንዴት
ቃል በላች እያለኝ ፣ እልህ'ና ንዴት ።

አሁን ማለት መች ነው ?

ብቻ ልጠይቅሽ
ትዝታ ሚመስል
ትዝታ ያይደለ
እኔ ጋር ያለውን የተመሳሰለ
ንገሪኝ ምን አለ?

ዘመን እንደ ቅጠል ፣ እረግፎል ከፊትሽ?
የለሁም ይልሻል ፣ የኖርሽው ትላንትሽ?
ንገረኝ ምን አለ ? የቀን ግት የተፋው ?
ንገሪኝ ንገሪኝ ፣ እግርሽ መንገድ ጠፋው?
ንገሪኝ እባክሽ
ትዝታን እንደ እህል ፣ ማመንዥኬን ልተው
ተስፋዬን ከበላ ፣ አንቺ ለኔ ማምጣት ፣ ህይወት አያቅተው ።

ንገሪኝ ተስፋ አለ?
ንገሪኝ ቃል አለ?
.
ነገሩን አልኩ እንጅ

አንቺ ጋር ምን አለ
የሚል ተራ ግጥም
የሚል ተራ ቅኔ ፣ ለምን አስፈለገኝ ፣
ብቻየን ትተሽኝ
ካንቺ ለይተሽኝ
እኔ ጋር የሌለ ፣ አንቺ ጋር ምን ሊገኝ ?

--------------
ሶሎሞን ሽፈራው

@yegetemkalat
@poem_merry
9.2K viewsMerry G, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 13:39:39 ➽ ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል፡፡ ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ከመስኮት አጠገብ ነው።

➽ ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

➽ ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው:ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ " በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ...

➽ በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው!

➽ ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ። ወሰዱለት። ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

➨ "ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ።

➽ "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት።

➨ "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር" ስትል በመገረም መለሰችለት፡፡

➽ ልብ የሚነካ ነገር.. ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው። ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ የተጨነቀ አምሮአቸውን እረፍት እንስጠው::

@yegetemkalat
@yegetemkalat
8.8K viewsMerry G, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 20:52:17
7.5K viewsባህራን, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 13:05:53 #እንዳትረሺኝ_ብዬ
:
:
እንድታስታውሺኝ ሁሌም እንዳትረሺኝ ብዙ ለፍቻለሁ፤
ግን ይህ ድካሜ ፍሬ እንዳላፈራ በርግጥ አይቻለሁ።
:
:
ብዙ ቀልድ አውርቼሽ ብዙ ሳቅ ስቀሻል፤
ደግሞም በማግስቱ ሁሉን ረስተሻል።
ስጦታም ስሰጥሽ ወስደሻል በደስታ፤
ይረሳሻል እንጂ ያኖርሽበት ቦታ።
ናፍቀሺኛል ብዬ « አንቺስ?» ያልኩሽ እንደው፤
መልስሽ «ምንም» ነው እንደተለመደው።
:
:
ታዲያ እንደው ምን ላድርግ እስኪ እንደው ምን በጀኝ፤
በሷ መረሳቴ ውስጤን እኮ ፈጀኝ፤
እያልኩኝ ስጨነቅ ስንት ቀን አለፈ፤
ተመስገን ነው ዛሬስ ዕድሜ «ለአበው» ተረት ገልግሎኝ አረፈ።
:
:
አዎ...
ክብሩ ለአበው ይሁን አበው ይሰንብቱ፤
«የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም»ብለው ለተረቱ።
:
:
እናምልሽ ፍቅሬ...
ከዛሬ ጀምሮ ቀልድም አልነግርሽም፤
ስጦታ አልሰጥሽም፤
ናፈኩሽ ወይ ብዬም ከቶ አልጠይቅሽም።
:
:
ይልቅ በዚ ፈንታ...
ጤና ለተረቱ ማድረግ ያለበትን ውስጤ ስለነቃ፤
ከሰሞኑን ውዴ እንዳትረሺኝ ብዬ ልወጋሽ ነው በቃ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ


@yegetemkalat
@poem_merry
9.4K viewsMerry G, edited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ