2022-09-05 22:52:18
"ሴትን አላምንም"
ክፍል 6
አቅራቢ semir ami
ዛሬ ቀኑ ተለወጠብኝ እንደዚ አይነት ቀን ገጥሞኝ አያውቅም ጠዋት ት/ቤት ከገባውበት ሰአት አንስቶ ብዙ አዲስ ነገሮችን ተከሰቱ ፤ በአንድ ቀን እንደዚ ሰው መቅረቤን እያሰብኩ ገረመኝ፡፡ ብዙ ሀሳብ በውስጤ እየተመላለሰ ከአህላምዬ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ . . .አህላምዬ ገላ ላይ ያለው ያልደረቀው ቁስል አስቀናኝ ፤ ሰው እንዴት በቁስል ይቀናል? የኔን ቦታ የሚጋፋ አንድ ጎረምሳ ጉልበቷ ላይ የተኛ ያህል ተሰማኝ። የላዳውን ሹፌር እየተመለከትኩኝ በምድር ላይ ውቧን ሴት ማሳፈሩን ቢያውቅ "የደስታ ጮቤ" ይረግጥ ነበር አልኩኝ በልቤ። መንገዱ በዝናብ ምክንያ የተጨናነቅ የመኪና ፍሰት ይታያል። ቢሆንም እኛን ማስቀደም አለባቸው መኪናው ውስጥ ከአምቡላንስ በላይ ለቤተሰቦቿ አስፈላጊ፣እንደ ኦክስጂን የሚቆጡሯትን ልጃቸውን አዘግይተንባቸዋል የመኪናው ፍስት ብዙም ቦርጭ ባለወጣ ትራፊክ ተቃለል። ቦርጫም ትራፊኮች መሀል መንገድ ላይ ሲቆሙ ሌላ መጨናነቅ ይፈጥራሉ የዚህ ከሲታ ትራፊክ መኖር በፈጣን ትራፊካዊ አመራር መንገዱ አቀለለልን።
እስካሁን ትካሻዬ ላይ ተኝታለች? ማነች? እንዴት ትከሻዬ ላይ እስካሁን? ብቻ አላውቅም ወድጃታለው ትከሻ ላይ መተኛት የማመን ስሜት አይደል? ብዙ አመት ካወቅኳቸው ሰዎች በተለየ ሙሉ ለሙሉ ተማምኜብሃለው ነው? በዚህ ሃሳብ ውስጤ ሁኜ ቤታቸው በር ላይ በአህላምዬ አመላካችነት ደረስን። ከመኪና ወርዳ ልባዊ ምስጋናዋን ከፈገግታዋ ጋር ቸረችኝ እኔም በፈገግታ ተቀብያት መሄዷ ባያስደስተኝም የመጨረሻ ቃል ይመስል ሰላም መሆንሽን በምን አቃለው ሁለት ቀን ሙሉ አንገናኝም ስልክሽን ስጪኝ ብዬ በሙሉ ልብ ጠየቅኳት። ለመወሰን ጊዜ አልወሰደባትም የት/ት ቤታችን ህግ በትምህርት ሰዓት ስልክ መያዝ ስለማይቻል በወረቀት ፅፋ ሰጠችኝ ፤የነበረኝን ደስታ ላየ ስልኳን ሳይሆን ህይወቴን ሊቀይር የሚችል ቼክ ነበር ሚመስለው።
ቤቷ እስክገባ በዓይኔ ሸኝሗት ቤቷ በር ላይ ስትደርስ ወደኛ ዙራ በእጇ ሰላምታን ሰጠችን። ደህና ሁን ምትለኝ መሰለኝ ፣ ከአሁን በኋላ አንገናኝም ቸር ሰንብት ይመስላል። አህላም ገባች ድንገት ጨለመብኝ ፀሀይ ጠለቀች አጠላለቋ ደሞ አስፈሪ ነው አሁን ደምቃ በርታ እልም ብላ እንደ ጠፋች ፀሀይ መፍዘዜን ያወቅኩት ባለ ላዳው እንሂድ አለቃ ሲለኝ ነው።
እሷን ከሸኝሁኝ በሗላ ለቀጣይ ሁለት ቀናት እንደማላገኛት ሳስብ ልቤ ተረበሸ ፤ ትምህርት ሊጀመር የቀረው ሁለት ቀን ወይስ ሁለት አመት? ቀኑ አልመሽ አለኝ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ የግድግዳውን ሰአት ደጋግሜ እመለከለታው ቀኖቹ ረዘሙብኝ እንኳን ሊመሽ የምሳ ሰዓት አልደርስ ብሎኛል "የተረገመ ቀን" ምንም የምቀይረው ነገር እንደሌለ ቢገባኝም አልጋዬ ላይ በጭንቀት እገላበጣለው። አንዳንድ መፅሀፍትን ለማንበብ እየገለጥኩኝ መልሼ አስቀምጣለው የማደርገው ግራ ገባኝ አህላምዬ ናፈቃኛለች። በአንድ ቀን እንዲ ያደረገኝ" ፍቅር" ወይስ ስሜት? አላቅም ብቻ ሰኞ ምላትን ማሰብ ጀምርያለው ደፋር ከሆንኩኝ።
የፍቅር ማዕረግን ባንቺ ለብሽያለሁ..በምድር ላይ የማቱሳላ እድሜን ያክል ብኖር ወይም ደግሞ የቀረኝ እድሜ ዛሬን ብቻ ቢሆን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ይጨምረዋል እንጂ አይቀንሰውም ልበላት ወይስ?
" ደስታሽን ደስታዬ ላደርግ፤ መጥፎ የሚባል ሁኔታ ውስጥ ብትገቢም እንኳ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ ብዬ ቃል ልግባና ተንበርክኬ አብረሺኝ ሁኚ ልበል? የሰው ልጅ በቃሉ እንጂ በእንብርክኩ መቆም አላቃተውም ብትለኝስ።"ይህማ አይሆንም ምንም ስሜቷን ላላወቅኩት ሴት ተንበርክኬ ብዋረድስ? በቃ እንዲ ልበላት።
(ጁምአ) አርብ እለት ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሽ ውስጤ ለዘመናት ሲፈልግሽ የነበርሽው ሃዋዬ አንቺ ነሽ ብዬ ለራሴ ነገርኩት አዳምሽ ልሁን ልበላት? አቅሙን ካገኝሁኝ ሁሉንም እላታለው።
ቅዳሜ ማታ ስልኳን ብቀበልም መደወል አልፈልግኩም ፤ ወንድሜ አለ ስላለች ስደወልላት አይቶ ቢናገራትስ መደወሉን ትቼ አጭር ቴክስት ላኩኝ። "እንዴት ነሽ አህላም ሰኢድ ነኝ ተሻለሸ? ያልደወልኩት እቤት ከሰው ጋ ከሆንሽ ብዬ ነው አሁን እንዴት ነሽ?"
ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ስልኬ መልእክት ገባ ተጣድፌ ስክፈተው ያየሁት ነገር አላስደሰተኝም ጓደኛዬ መሀመድ ነው "የት ነህ"? የሚል ቴክስት የላከልኝ ። ማሜን ድንገት ጠላሁት አህላምዬን የተጋፋኝ መስሎ ታየኝ እቤት ነኝ አንተ "የት ነህ" ብዬ ከመፃፌ የአህላምዬ ቴክስት ገባ " ደህና ነኝ በጣም ቁስሌም ደርቋል ግን ለወንድሜ አንድ የትምህርት ቤት ልጅ ገፍቶ ነው የጣለኝ ብዬ ልነግረው አስብያለው" እንዳልነግረው ከፈለክ እኔን በደንብ ይቅርታ መጠየቅ አለብህ ብላ ይህን( ) አክላ ላከችልኝ። የቴክስቷ መልስ ፈገግ አስባለኝ ፈታ ያለችና ለመግባባት ምትመች ልጅ ሁና ታየችኝ እኔም " ምን ልቀጣ "? ግጥም እችላለው ልጋብዝሽ ብዬ አልኳት? ደስ ይለኛል ብላ መለሰች ፤ እድሉን አግኝቻለው በግጥም ስሜቴን መግለፅ አለብኝ ።
" እኔ ምን አጥፍቼ" poem semir ami
እኔ ምን አጥፍቼ ጥፋቱስ የአባትሽ
አንቺን መሳይ ልእልት
ያለምንም ረዳት አምነው መላካቸው
......
እኔን የሚገርሙኝ ወላጆችሽ ናቸው
አንቺን መሳይ ልዕልት
ያለማንም ረዳት እዚህ መላካቸው
በመንገድ ስትሄጂ....
ስንቱን ጎበዝ ጀግና
ባይንሽ ማርበድበድሽ ማን በነገራቸው ...............
...................
አህላምዬ አብረን ስንሳፈር አንቺን እያየሁኝ
ምናለ ላንድ ቀን አባትሽ በሆንኩኝ
ብዬ ተመኘሁኝ
ከስምሽ ቀጥሎ ስሜን ባስጠራሽኝ
እኔ አባትሽ ብሆን....
እንደ ዶሮ ዕንቁላል ታቅፌ ባኖርኩሽ
በስስት በፍቅር ነይ የኔ ልጅ ባልኩሽ
እኔ አባትሽ ብሆን.....
እንዳሁኑ ያንቺ አባት
በጠራራ ፀሐይ ያለምንም ረዳት
መች እልክሽ ነበር?
..... ...........................
እኔ አባትሽ ብሆን....
ይሄ ሁሉ ጀግና
ባንቺ ልዩ ውበት ውስጡ ባልታወቀ
ደፋሩ ባልፈራ አገር ባላለቀ ...............
.................
ተመልሼ ደሞ ነገሩን ሳስበው
እንኳንም አባትሽን ያንቺ አባት አረገው
እንኳንም የላከሽ ብቻሽን ያለሰው
እንዲያ ባይሆንማ....
እኔም ባልተመኘሁ እኔም ባልተቀኘሁ
ባንቺ ባልተገረምኩ ላገር ባልነገርኩኝ
ብዕሬን አንስቼ ግጥምም ባልፃፍኩኝ
እንዲሀ ተደስቼ አንቺን ባላገኝሁኝ።
ለረዥም ደቂቃ ቴክስት ሳትመለስ በመቆየቷ ልቤን ፍርሃት አራደው። ፍርሃቴ ብዙ ሳይቆይ በአንዲት የ text ድምፅ ተወገደ። ዘለግ ያሉ ኢሞጆችን ላከች ከልብ አመሰግናለው አንድም ሰው እንደዚ ብሎኝ አያውቅም የምር ልቤን ደስ አሰኝተሃዋል አመስግናለው ስላወኩ ደስ ብሎኛል መልካም እረፍት ፣ ሰኞን ናፍቅያለው "ግጥም ታነብልኛለህ" አለችኝ የትኛውን ሰኞ? የዛሬ አመቱ ወይስ የዛሬ ሁለት አመቱን? ሰኞ ስንት አመት ቀረው? የዚን ያህል እንዴት ቀርባ አወራችኝ? ሴት አይደለች ሴት እኮ እስክትግባባ ትቆያለች የሷ ግን ፈጠነ ምን አይነት ልዩ ባህሪ ነው ያላት? ሰኞም ትከሻዬ ላይ ትተኛ ይሆን?
ክፍል ሰባት ይቀጥላል ………
@yegetemkalat
@poem_merry
2.1K viewsSemir ايمي سمير, edited 19:52