2022-09-23 06:45:15
# ከጠቃሚ_ምክሮች_የተወሰዱ_ጠቃሚዎች
☞ በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ካጣኸው በኃላ ይቆጭሀል እና
☞ ባጣኸው ነገር አትበሳጭ የተሻለውን ፈጣሪ ይሰጥሀል እና
☞ የበደለህን ይቅር በል አምላክ ይቅር ባዮችን ይወዳል እና
☞ ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ጌታህን እርሱ አመስጋኞችን ይወዳል እና
☞ ባለህ ነገር አመስግን ፈጣሪን ይጨምርልሀል እና
☞ በወንድምህ ውድቀት አትደሰት ነገ ሌላ ቀን ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና
☞ የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ እርሱ ካንተ ጋር ነው እና
☞ድሆችን እርዳ ሰደቃ/ምፅዋት ወንጀልን ታብሳለች እና
☞ ሰወችን አትመቀኝ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለች እና
☞ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነው እና
☞ አምላክህን አፍቅረው እሱ የእውነተኛ ፍቅር ባለቤት ነው እና
☞ ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ ነው እና
☞ ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም ውሳኔው የፈጣሪ ነው እና
☞ በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አምላክ ከታጋሾች ጋር ነው እና
☞ ለሁሉም ነገር አትቸኩል ችኮላ የሸይጧን ነው እና
☞ አትበሳጭ ብስጭት የሸይጧንን በር ትከፍታለች እና
☞ የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ ያስታውስሀል እና።
እነኝህን ምክሮች ሼር አድርግ ያወቁትን ማካፈል ጥበብ ነውና።
መልካም አዳር ባይሆን ሳትፀልዩ አትተኙ እሺ !!
@poem_merry
@yegetemkalat
2.3K viewsMerry G, 03:45