Get Mystery Box with random crypto!

እግር ኳስ Meme™

የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የቴሌግራም ቻናል አርማ poem_merry — እግር ኳስ Meme™
የሰርጥ አድራሻ: @poem_merry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 904
የሰርጥ መግለጫ

ጥበብ እንደ ጥጥ ነው ለጉድ ተፈልቃቂ
ሰው ጥሩ ፈታይ ነው ድር ማግ ግን አላቂ
ስለ ግጥም ብላቹ @buchula36 ላይ አዋዩኝ
የናንተ ድምፅ ነው ለኔ እውቀት የሆነኝ
.
.
.
@buchula36
@yegetemkalat
@ortodox_fkr

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-09-21 06:08:58 "በስማም በወልድ በመፈስ ቅዱስ አዱአምላክ አሜን"
እግዚያብሔር ከናተ ጋር ይሁን(መዝ 2:3)
መርጌታ ዮሐኒስየ ምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
35 ጥይት የማያስመታ አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
ለጥያቄወ መልስ
0912999705ይደውሉ ማሳሰቢያ በካል መምጣት ለማትችሉ ሰርተን እንልካለን።
3.1K viewsMerry G, 03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 20:15:50
3.0K viewsባህራን, 17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 11:30:42 ​​​​​


                  ሴትን አላምንም

ክፍል 9

Semir ami

እልፍ አእላፍ ሰዎች በድንኳኑ ዙሪያ ላይ ቁመዋል በሀዘን ልባቸው የተሰበረ ፣ ለእንባቸው ገደብ አላበጅ ያሉ ሴቶች ይታዩኛል። የማየው ነገር ህልም እንጂ እውን አይመስልም "እኔን ልጄ" የሚሉ የሲቃ ድምፆች ከትላልቅ እናቶች  ይሰማል። ውሃ ሆንኩኝ ፤ እየተርበተበትኩኝም ቢሆን ወደ ድንኳን ውስጥ ገባሁኝ ክፍት ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ ማንን ልጠይቅ? አህላም የት ሄደች? ማንስ ነው የሞተው? መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎቼ የኔን የነገን ተስፋ በጉልህ የሚያሳዩ ወሳኝ ነጥቦች። ………" ልጇ ደህና ነው ሙቀት ክፍል ገብቷል ሚስኪን በወጣትነቷ ተቀጨች እስከ መቼ ድረስ ነው ግን በወሊድ ምክንያት የሚከሰት ሞት የሚያበቃው"የሚል ድምፅ ከወደ ጆሮዬ ዘልቆ ገባ … ልሳቅ ፣ ወይስ እልል ብዬ ድንኳኑን የሰርግ አዳራሽ ላስመስለው? የጐመዘዝው ህይወቴ ወደ ጣፋጭነት ሲቀየር ታየኝ ፣ የጠፋው ብርሃኔ ደምቆ ሲበራ ታየኝ። አህላም አልሞተችም እነሱ ጋር ግን የሆነ ሰው ሞትዋል ፤ ሞት ደሞ ለማንም አይቀርም መቅረት ያለበት ደግሞ ለአህላም ብቻ ነው አህላም አልሞተችም።


ልቤ ተረጋጋ ፤ ሰው እንዴት ለቅሶ ላይ ሟችን ያማርጣል የዚህች ልጅ መሞት ህልሙን የሚያጨልምበት ስንት ሰው አለ ? ጨካኝ! አልኩት እራሴን… ለራሴ ደስታ ስል በሰዎች ሞት ላይ ምሳለቅ ፍቅር ወይስ እራስ ወዳድነት ብቻ አላውቅም የማውቀው አህላም አለመሞቷን ነው። …… ድንኳኑን ለቅቄ ስወጣ በአይን የማውቀው የግቢያችንን ተማሪ አየሁት ጠጋ ብዬ ሰላም እንዴት ነህ? የሚለው ጥያቄዬ አስቀደምኩኝ እሱም ሞቅ ያለ ሰላምታውን ከሰጠኝ በሗላ ማን ሞቶ ነው? አልኩት የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ የክላሳችን ተማሪ እህት ነች ድንገት በወሊድ ምክንያት ነው የሞተችው አለኝ። oh የአህላም እህት አላህ "የጀነት" ይበላት አመሰግናለው ሰላም ሁን ብዬው አልፍኩኝ ማታ ደግሜ ስለመምጣ  ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረብኝ ላዳው ውስጥ ገብቼ ወደ ትምህርት ቤት አቀናሁኝ ፤ አነዛን አስጠሊታ እና አስቀያሚ ምሽቶችን አልፌ ዛሬን ደርሻለው።  አይ ፍቅር እስረኛ አድርጐኛል ያውም በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ የሚያሳዝነው ያሰረችኝ መታሰሬን ፣ በእስሩ ውስጥ የሚደርስብኝን ስቃይ ምንም አታውቅም እሷም  ዛሬ የሀዘን እስር ቤት ላይ ነች። እኔም ጋር ድንኳን አልተደኮነም እንጂ የምወዳትን ልጅ ሳላይ 2 ቀን ሞልቶኛል ታድያ ከዚ በላይ ለእኔ ምን ዱብዳ አለ።

 ምሽቱን እነ አህላምዬ ጋር ላሳልፍ ብዬ ከትምህርት ቤት መልስ መኪና አስፈቅጄ ለቅሶ ቤት ሄድኩኝ። ከቀኑ ቀለል ያለ ሰው ቢኖርም አሁንም ሰዎች ይታያሉ አህላምን ማግኝት አለብኝ ግን እንዴት? የቤተሰቡ አባል የሚመስል ሰው ውሃ ይዞልኝ መጣ እኔም "ይቅርታ" ወንድም አህላምን  ማግኝት እችላለው?  ከተረጋጋች አልኩት? ትኩር ብሎ አይቶኝ ይቻላል ማን ብዬ ልንገራት? ማን ይበላት?

በመከራ ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ የሚያስበው  ፣ ጦርነትም ውስጥ ሆነ ስለ አንቺ ሰላም በብዙ የሚጨነቀው ፣ በመሞት ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ  በህይወት መኖር የሚያሳስበው፣ ወንጀለኛ ሆኖ ስለ አንቺ ፅድቅ ከእራሱ በላይ የሚያስጨንቀው  ሰኢድ ይበላት? ሰኢድ... ሰኢድ በላት አልኩት ከሃሳቤ መለስ ብዬ። …… ብዙ ሳይቆይ አህላምን ይዟት መጣ… ልጁንም  የመልካም ሰው መገለጫ አድርጌ አሰብኩት ፣ የፈረሰውን የፍቅር ድልድይ ገንቢ መሃንዲስ ነው ብዬ መሰከርኩለት ፣ የፍቅር ጥም ቆራጭ መልካም ሰው ከቶ ከሱ ውጪ እንዴት ይኖራል?


አህላምዬ አዝናለች ቢሆንም ግን በመምጣቴ ደስ ሳትሰኝ አልቀረችም ያንን ከውሃ እና ከምግብ በላይ አስፈላጊ መስሎ የሚታየኝ ፈገግታዋን ቸረችኝ። ወደ መንገዱ እየተራመድን

አህላምዬ?
አቤት…
እንዴት ነሽ በረታሽ?
አልሃምዱሊላህ ምን ማድረግ ይቻላል አላህ ያመጣውን አምኖ መቀበል ግድ ይላል።

"አብሽሪ አላህ ሶብር ይስጣቹ ከህይወት አስቀያሚ ነገር  ውስጥ የሚወዱትን ሰው ማጣት ነው። ሀዘንሽ ከልብ ይገባኛል ግን ሁሉም ወደ ማይቀረው ሀገር ተጓዥ ነው ፤ ሁሉም እንደ ታክሲ ሰልፍ በሞት መስመር ላይ ተሰልፎ ተራውን እየተጠባበቀ ነው ህይወቱን እየገፋ ያለው ፣ ተረኛ ሟችም በሰልፉ መስመር እስከቆመ ድረስ ጊዜው ሲደርስ መሞቱ አይቀርም። ዋናው ቁም ነገሩ መሞት አይደለም ከሞት በሗላ ያለ ህይወት ነው ሞትማ ለማን ይቀራል? ለዚህ አይደል የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይሸኛል የሚባለው።  በርታ በይ ፤ በርትትሽ ቤተሰቦችሽን አበርቺ " ሰው ከሰው ሲለያይ አይደለም ወረቀትም ከወረቀት ላይ ሲቀደድ የስቃይ ድምፅ አለው" ሀዘንሽን እረዳለው እኔም አባቴን አጥቼ  በብዙ ተሰቃይቻለው። ግን መመለስ በማይቻል ነገር ላይ ቆዝሞ ማሳለፍ ትርፉ ሌላ ህመም ነው ትእግስት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው ታገሺ።………

የገፋትን ሃይል ባላቅም እንባ እየተናነቃት እቅፌ ውስጥ ገባች  …… ከልብ አመሰግናለው  አውቃለው ለህይወትህ ትርጉም የነበረውን ሰው ካጣህ በኃላ የህይወትን
ጠአም ማግኘት ከባድ ነው ። ግን ዛሬ አንተን በማወቄ እድለኛ እንደሆንኩኝ ተሰምቶኛል ፤ ብዙ ሰው ያቃተው በደስታህ ጊዜ አብሮ መኖርና ማሳለፍ ሳይሆን በችግርና በመከራ ጊዜ ከወዳጁ ጎን ሆኖ ሀዘኑንና ስቃዩን አብሮ መካፈል ነው ዋናዉ ይህ ነዉ ሰኢዲዬ በሀዘኔ በህመሜ ሰዐት ከጎኔ በመሆን እና ብርታትና  ጥንካሬ እንዳገኝ ስለመከርከኝ የዛሬዋን ምክር አልረሳም ብላኝ አይንዋ ላይ የቀረውን እንባ አፈሰሰችው። እኔ እንባ የለኝም ትላንት ማታ ስለ እርሷ እያሰብኩኝ እያለው አንዲት የእንባ ዘለላ ቁልቁል በጉንጮቼ ኮለል ብላ ወረዳለች። እኔም "ወዴት ነው የምትሄጂው?"  በማለት ስጠይቃት በአይንህ ውስጥ የምትወዳት ሴት አለች "ለእኔ የሚሆን ቦታ አላገኘውም"  ብላኝ ከሄደች ቆይታለች ታድያ አይኔ ውስጥ አህላም ገብታ ለቅሶዬ ኬት ይምጣ።… … አህላምዬ እራስሽን ጠብቂ ነገ እመጣለው ብዬ ተሰናብቻት ሄድኩኝ ፤ ባትሄድ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ሰምቼ ቆምኩ ሰውነቴ አንዳች የፍቅር እና የመፈለግ ስሜት ወረረኝ እኮ አህላም እኔን እንዲ አለችኝ?  ፊቴን አዙሬ…  ልመለሳ? አልኳት…  አይ መሽቷል ቤት ማሚ ትጠብቅሃለች ስገባ ደውልልኝ አለችኝ።

ልቤ ፈነደቀ አህላምን ያገኝሗት መሰለኝ።  መኪና ወዳቆምኩበት ስፍራ እየተራመድኩኝ አንዳች ስሜት ዙር አለኝ ፊቴን አዙሬ ስመለከት አህላም ቁማለች  ደነገጥኩኝ…  ቀድማኝ እጇን አንስታ ቻው አለችኝ እኔም ቻው ብዬ በእጄ እንድትገባ ምልክት ሰጠዋት።  በፍጥነት መኪናዋን አስነስቼ ወደ ቤት ገሰገስኩኝ ልቤ ሀሴት አርድጓል አዲስ እድል አዲስ ቀን አዲስ ህይወት … ድንገት አንድ ነገር ታወሰኝ እና ፈገግ አልኩኝ ማሚ ሁሌም አንድ የሚያስቃት ግጥም አለ እሱን ትልና ትስቃለች።

ሚስቴና ሰበቧ
·
·
ለስጋዋ ስትኖር ነፍሴን አሞኝታ
አገኘኋትና ወንድ ጋር ተኝታ
ምነው ምን በደልኩኝ? ብዬ ስጠይቃት
እግሯ ስር ወድቄ በእንባ ስማፀናት
እንደለመደችው ሰበብ አዘጋጅታ
አንተ መስለኸኝ ነው አለችኝ ተነስታ።።

ስልኬ ጮኸ የቴክስት ድምፅ ነው መኪናውን ዳር አቁሜ ሳየው አህላም ነች።


            ክፍል አስር ይቀጥላል….......
3.3K viewsSemir ايمي سمير, 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 11:29:56 ​​​​​​




                 "ሴትን አላምንም"

ክፍል 8

Semir ami

                ……አህላምዬ ዛሬ አልመጣችም ማንን ልጠይቅ ለማን አቤት ልበል? አህላም ከሌለች መንገዱስ የት አለ? እረ እግሬስ እንዴት እሺ ብሎ ይራመድልኛል? … ስልኬን ስላልያዝኩኝ ያለኝ አማራጭ በፍጥነት እቤት ደርሼ መደወል ነው።

ጥያት መሄዱ ቢያስከፋኝም አማራጭ አልነበረኝም። በአቅራብያዬ ባለ ታክሲ ገብቼ ተሰፋርኩኝ ታክሲው ሲንቀሳቀስ  ቅር ፣ ቅር ይለኝ ጀመር። ከት/ቤት እየራቅኩኝ ስመጣ በመስኮት ዞሬ ተመለከትኩኝ ለብዙ ደቂቃዎች ስፈልጋት የነበረችው አህላምዬ በር ላይ ቆማ ማያት መሰለኝ…… የለችም ባር ባር አለኝ ሳላየት ላድር ነው ላለፉት ቀናቶች አስለምዳኝ የሄደችውን ጨዋታና ሳቅ ዛሬ የለም መንገዱ ላይ ያሉ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ ፣ የንዴት እና የብስጭት ፊት የሚታይባቸው ሰዎች መንገዱ ላይ ቁመዋል ለምን ተቆጡ እነሱም  አህላምዬን ስላላዩ ይሆን?

ታክሲ ውስጥ የተከፈተው ለስለስ ያለው ሙዚቃ ከሃሳቤ አባነነኝ…  የአህላምዬ ፈገግታ ፊቴ ድቅን   እያለ ያስቸግረኛል ምን አለ ሰዎች "የሳቅን ስልት" ከሷ ቢማሩ ሰው ለስልኩ ጥሪ ከሚቀያይር እያደር አዲስ ሚሆነውን የአህላምዬን ፈገግታ አንዴ ጥሪ ቢያደርግስ?  ታክሲው ጉዞውን ቀጥሎአል። እኔም ሙዚቃውን እየሰማሁኝ በሃሳቤ ገስግሻለው…  ለእኔ ከአህላምዬ ጋር ያሳለፍኳቸው አጭር ቀናቶች የራሳቸው ገፅ አላቸው ዛሬ ግን አህላም የለችም።  ትዝታዋ ግን አለ የረዥም ጊዜ ሳይሆን ሰሞኑ የሆነ ዛሬ ላይ ግን ትዝታ የሆነ እኔ በትዝታ ወደ ሁዋላ ተመልሻለው ፤ ታክሲው ግን ወደፊት ይገሰግሳል።

አህላምዬ ከመጀመርያው እለት ጀምሮ በተፈቀደላት መሠረት ልቤ ውስጥ ገብታ ፤ እግሮቿን አኮራምታ ቁጢጥ አለች ፣ ውላ ስታድር ተንፈራጣ ተቀመጠች ፣ በቆይታዋ ደግሞ በጀርባዋ ጋደም አለች ስትከርም ጭራሹን ጓዟን ጠቅልላ ይሄ መከረኛው ልቤ ላይ ተኛችበት።

እቤት ስገባ እናቴ የተለመደውን ፈገግታዋን አሳየችኝ ሳያት ድካሜ ይጠፋል የመኖር ፍላጐቴ ያይላል ፣ አንድ ልጇ ነኝ ለእኔ ብዙ ሁናለች። ከት/ቤት ስመጣ ውጊያ ሂጄ እንጂ ተምሬ የመጣሁኝ አይመስላትም ራበህ? ደከመህ? ምን አዲስ ነገር አለ? የዘወትር ጥያቄዎቿ ናቸው ማሚ ዛሬ እነዚህን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ፍቃደኛ አይደለሁም በልቤ አልኩኝ። ዛሬ ፀሀይ መች ወጣች ፣ ዛሬ ከተማው ላይስ መች ሴት ነበር ፣ ዛሬ ከተማው ላይ ማን የሳቀ አለ? ሴትም ፣ ሳቅም ፣ ፀሀይ አልነበሩም ስለዚህ ስለየትኛው ልንገራት ስልኬ ጋር ለመድረስ ጓግቼ ማሚን በቅጡም ሰላም ሳልላት ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ምን ያረጋል አህላምዬ አልደወለችም። ጨካኝ ደህና ነኝ ፤ በሰላም ነው ያልመጣሁት አትልም?  ይጨነቃል ያስባል ብላ አታስብም?  ደህና ባትሆንስ? የሆነ ነገር አጋጥሟት ቢሆንስ? "የመኝታ ቤቴ በር ተከፈተ እናቴ ናት ማሚ የድሮ አራዳ ነች ቀለል ሲላት ከትዝታዎቿ ማህደር ታገራኛለች ዛሬ ግን አንድ የፈለገችው ነገር እንዳለ ያስታውቅባታል።

ሰኢዲዬ ስትጨርስ ሳሎን ና እየበላን ማወራህ ነገር አለህ አለችኝ  እሺ ብዬ ወደ ስልኬ ተመልሼ አህላም ጋር ደውልኩኝ ስልኳ አይነሳም ከአንድም ሶስቴ ደውዬ አታነሳውም።  ድንገት አንድ ነገር ትዝ አለኝ ወንድሟ ቀጣይ ለሶስት ሳምንት ከሄደበት በያዝነው ሳምንት ይመጣል ብላኝ ነበር ቁርጥ ቀነኑን ባትነግረኝም። ወንድሟ መጥቶ ይሆናል ብዬ እኔም ተረጋጋሁኝ ልብሴን ቀይሬ ሳሎን ገባሁኝ።

ማሚ ሳሎን ላይ ባለው መጅሊስ እንደ ልእልት ተቀምጣለች፤ ዝምታዋን ለመስበር ማሚ" አንዳንዴ ትኩር ብዬ አይሽና ምን ያህል እድለኛ ብሆን ነዉ
አንቺን እናቴ አርጐ የሰጠኝ ብዬ አስባለሁ " ብዬ ግንባሯን ሳምኳት። እናቴ ምንም ከመናገሯ በፊት ከጥያቄ ነው ምትነሳው ትምህርት እንዴት ነው? እና ተያያዥ ጥያቄዎች ? በተርታ ከመለስኩኝ በሗላ ። ሁሌም ስለ አባቴ ስታነሳ  እንደምትሆነው አንገቷን አቅርቅራ።

ሰኢዲዬ?
ወዬ ማማ ጠጋ ብዬ ታፋዋ ላይ ተኛው እሷም  ፤ ባባ ከሞተ በሗላ የስራው ሁኔታ መስመር ለማስያዝ ሞክርያለው አሁን እየደከመኝ ነው። ሃላፊነቱን እንድትረከበኝ እፈልጋለው ይህ የሚሆነው አሁን ሳይሆን የዚህን አመት ትምህርትን ስታጠናቅቅ ነው ፤ የኮሌጅ ትምህርቱንም በማታው ክፍለ ጊዜ ትቀጥላለህ ለዚህም እስከ ክረምቱ ረዥም የማሰብያ ጊዜ አለህ  እስከዛው ድረስ ግን ቅዳሜና እሁድ አብረን እንወጣለን አለችኝ። ባባ ጠንካራ ነጋዴ ነበር 9ኛ ክፍል እያለሁኝ ነበር ድንገት በተከሰተበት የልብ ህመም ነው ያረፈው  ። ባባ ተቆፍሮ የማይደርስበት ጥልቅ የሃሳብ ሃብት ፣ከሰማይ የራቀ ምልከታ የነበረው ነበር።  አላህ የጀነት ይበለውና ሁሌም ምክሩ እናትህን አደራ ነበር አደራዬን ማስቀየም አልፈልግም ዩንቨርስቲ ገብቼ መማር ብፈልግም የእርሷ ፍላጐት ከሆነ ከእሷ የሚበልጥ ነገር የለምና ሃሳቧን እንደምቀበል ነገረኳትና ግንባሯ ስሜ ወደ ክፍሌ አመራው።

ፀሀይ ጠልቃለች ቢሆንም አሁንም አህላም ስልክ አታነሳም ልቤ ፍርሃት ፍርሃት አለው፣ ውጣና ብረር እቤታቸው ሂድ ሂድ አለኝ። የወጣችልኝ የህይወት ፀሃይ በደንብ ሳላያት የጠለቀችብኝ መሰለኝ ፤ ነገ ጠዋት የመጀመርያ ስራዬ ሰፈሯ ሂዶ መውጫዋ ጋር መከታተል ነው ቢያንስ ደህንነቷን አረጋግጬ እመለሳለው ብዬ ጋደም አልኩኝ በዛችው ቅፅበት ኬት መጣ የማይባል እንቅልፍ ጭልጥ አርጐኝ ይዞኝ  ሄደ አይነጋ የለ ነጋ የመጀመርያ ስራዬ ወደ አህላም ስልክ መደወል ነበር።

ስልኳ ጥሪ አይቀበልም ፍርሃቴ ይበልጡኑ ጨመረ፣  ማታ አይነሳም አሁን ደግሞ ዝግ ነው ምን ሆና ይሆን? የዚህን ጥያቄ መልሱ ያለው እቤቷ ደጃፍ ስደርስ ነው።  ደህንነቷን አረጋግጬ ወደ ክላስ እገባለው ብዬ 1፡00 ከቤት ወጥቼ ላዳ ይዜ  ወደ ሰፈራቸው አቀናው። ወደ መንደራቸው መግቢያ ጋር የመኪና መጨናነቅ አለ እዛ ስደርሰወ 2:00 ሰዓት ሆኖዋል በዚህ ሰአት የመኪናው ግርግር ስላልገባኝ ባለላዳውን እዚህ ጋር አቁመውና እኔ ደርሼ ልምጣ ብዬው ወደ ሰፈራቸው ገባሁኝ። …… ድንኳን እግሬ ተንቀጠቀጠ ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ፣ እይታዬ ተጋረደብኝ። ጥቁር ዩኒፎርም የለበሱ ሴት ተማሪዎች ከሩቅ ይታዩኛል አዎ ድንኳኑ እነ አህላም በር ላይ ነው ዙሪያውን ደግሞ የትምህርት ቤታችን ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች አሉ እየፈራሁኝ ወደ ድንኳኑ ተራመድኩኝ……



        ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል………

#,yegetem kalate

የወደዳችሁት በላይክ አሳዩን ፈጥነን እናደርሳለን
2.8K viewsSemir ايمي سمير, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:38:27 ልማልብሽ

ለማንም የማልሰንፍ ለአንቺ እጄን ምሠጥ
ለሌላው ኮስታራ ለአንቺ ምቁነጠነጥ
በጉልበት በሀይሉ የለም ከሡ በላይ
.......................ተብሎ እየተወራ
በአንቺ ሲመጡ ግን ልቤ የሚፈራ
የሳምሶንን ጉልበት የሚያስንቀው ክንዴ
ነገር ግን ደሊላ ሁነሺብኝ አንዴ
እንዴት አልቸገር አልጨነቅ ውዴ ።
ነገር ማበላሸት ከሄዋን ቢሆንም
ታላቁ ዳዊትም ለአቢጊያ ብሎ
አሽከሩን ቢገልም,ኦርዮን ቢሞትም
የኔ ግን ከነሱ በምንም አያንስም
እንደውም የኔ ውብ ሳይበልጥ እንዳልቀረ አንቺን ልጠይቅሽ።
ነው! እንደ ውሻ እግርሽ ስር ልንሞሽሞሽ
እንደ ሠለሞን ክጄ ጣኦቴ ላድርግሽ
የሷ ነኝ እያልኩኝ በአንቺ ልማልብሽ።

ፍፁም ለማፈቅርሽ ግን ለማላገኝሽ

ባር
3.5K viewsባርሙራ ፡ጣሰዉ, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:28:20 ።።።።።የፍቅርሽ ሃያልነትሽ።።።።።

~~~~~~~~~~~~~

ያኔ ስንገናኝ በጓደኝነታችን፤
ድንገት ሳናስበው በፍቅር መጥለቃችን፣
ወደታች እንደሚሠምጥ የባህር ድምፅ እንጉርጉሮ፤
የፍቅርሽ ሃያል በደሜ ውስጥ ገብቶ ልቤን ጎርጉሮ፤
መተንፈስ እስኪያቅተኝ መናገር ተቸግሬ፤
ለመናገር የፈራሁት አንቺን አፍቅሬ፤

-------ሁሌም እልሻለው-------
--------እወድሻለው------

እና እምልሽ አንቺን ካገኘው ከወደድኩሽ በኅላ፤
ያለኝን ሁሉ አየው ተመልሼ ወደኅላ፤
አለም አንቺን ሰጠችኝ፤
ደስተኛ እንድሆን አደረገችኝ፤

ጥይት እንኳን ቢተኮስ የማይበሳውን ልቤ፤
በአንቺ ፍቅር ብቻ በአንቺ ፍቅር ተከፈተ ልቤ፤

--------ሁሌም እልሻለው----------
ባር
3.1K viewsባርሙራ ፡ጣሰዉ, 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:23:24 . . . #ፍቅር_ማለት . . .

ፍፃሜው የሚያምር ቅርብ ማንነት ግልፅነት ሚያስተምር .. .. .. ርህራሄ እና ለሰው ማዘንን በልብ የሚያኖር ከፈጣሪ የሚገኝ ፀጋ ነው።

ፍቅር የሚመሠረተው . . . አንድ ነፍስ በሁለት. . . አካል ሲኖር ነው፡፡

ምንጊዜም በቂ ነገር አሟጠን የማናገኝበት ነገር ፍቅር ነው፡፡

እውነተኛ ፍቅርን አግኝተህ ከተንከባከበው . . . እራስህን በምድር ላይ ካሉ ጥቂት እድለኞች መሀል አንዱ ነህ፡፡

ፍቅር የተለየ ቀን ልዩ ቦታና ድርጊት አይፈልግም . . . በድንገት ሳይጠበቅ ይከሠታል፡፡

#መልካም_ምሽት

ባርሙራ
2.9K viewsባርሙራ ፡ጣሰዉ, 19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:21:07 ፍቅር ተገፋ
ሊሞትለት እያለ እራሱ ለፍቅር
እራሱ አጥፍቶ ፍቅርን ለማኖር
ስም ሰጡት ያለ ስሙ
አብጠለጠሉት እያሙ
አደሙበት አወሩ ገዳይ ነህ እያሉ
የሚታየዉ ፍቅር ግደለዉ ቅበር አሉ
ቢመርህም ዋጠዉ ብለዉ ተማማሉ
ወረት የሌለዉ ምክንንያት የማያሻዉ
ኮትኩቶ አሳድጎ ፍሬዉን ሊያይ የጓጓዉ
      አትየዉ ፍቅርን አትቅረበዉ ከቶ
      ሊኖር የተመኛዉ ታየዋለህ ሞቶ
ተገፋ ፍቅር በአጀንዳ አሉ ባልታ
እዴት ይርቀዋል ልቡ የማይረታ
ቅኔዉም ሚስጥር ነዉ በማነዉሚፈታ
ማበል ነዉ ወጀቡ ቀኑም ምሽቱ
መኖር ግራ ገባዉ ወይስ ይምረጠዉ ሞቱ
       ፍቅር ከተገፋ ከተደረገ በደለኛ
       ቢኖር ምን ይጠቅመዋል ሆኖ ብቸኛ
       ሣይን አሸበሪ ሰንቴ ተሰለ
      እሺ ምን አጠፋ እሱ ምን አለ
ይቅር መኖሩም መሞቱ ይምረጠዉ
ፍቅር ለኖረለት እደዉ ምን ሊዉጠዉ
ቆይ ምን አጠፋ ምንድነዉ ክፋቱ
ለምንስ ትገሉታለቹ ፍቅራች 12 አመቱ
ሮጬ ስመጣ ልክ እደ ቤቴ
ውዴ እያየኻት ልክ እን እናቴ
ጋሼም አየዉ ነበር ልክ እንደ አባቴ
ዛሬ ግን በፊት ገፋቹት ህይወቴ
ቃላት ብዛት ጠላሁት ማንነቴ
ዉዴ ብትታመሚም አልደርስልሽም ሮጬ
ያኔማ ልሞት ነበር ቆርጬ
ልኑር ለፍቅሬ እየገፋኝም አምልጬ
ሁሉም ለመርሳት ቆርጬ


ባርሙራ
3.0K viewsባርሙራ ፡ጣሰዉ, 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:41:53
እንኳን ለ አዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ

አዲሱ አመት የሰላም የጤና የብልፅግና ዘመን ይሁንላችሁ። ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት ደስታችሁ ሁሉ ሙሉ የሚሆንበት ከትላንት ዛሬ የምትሻሉበት ዘመን እንዲሆን በቻናላችን ስም እመኛለሁ መልካም የዘመን መለወጫ በዓል ይሁንልን።

@poem_merry
1.5K viewsMiky, 20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:17:28 የአብርሃም እና ሣራ

Miky / @mikotad2

@poem_merry
1.9K viewsMiky, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ