2022-08-30 19:19:27
ሴትን አላምንም
ክፍል 3
አቅራቢ semir ami
ያጋጠሙን ቁስሎች ሁሉ በጊዜ ሂደት ይሽራሉ ፣ ጠባሳው ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ ቢሆንም ሁሉም ይታለፋል። ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ናት እያንዳንዱ ስኬት እና መልካም ውጤት ከባድ ሸክምን አሳልፎ ነው ሚመጣው የኔ ስኬት መነሻ ከባዱ የሸክም ወቅት ነበር።
ጊዜው 2001 አመት ልደት በየቀኑ ሚነሳው የራስ ምታት ህመሜን በመማር ሂደት ውስጥ ተፅእኖ ፈጥሮብኛል። ባስ ሲል ከክፍል እየወጣሁኝ መታጠቢያ ቦታ ዘለግ ላለ ጊዜ ማሳለፉን ልምድ ካደረግኩት ሰነባብቻለው የዛሬው ትንሽ ለየት ይላል ጉልበት እያነሰኝ መጥትዋል ። ኪኒን መውሰዱ አድክሞኛል። ህመምህ ማይግሪን ነው። ሙሉ ለሙሉ ባይድንም ጠንካራ ፀሃይን መሸሽ ፣ ራስን አለማጨናነቅ ፣ ንዴትን መቆጣጠር ፣ እንቅልፍ አለማጣት ህመሙ ቶሎ እንዳይከሰት ይረዳሀል ብሎ ሀኪሙ የነገረኝን አልረሳም።
መታጠቢያው ጋር ሆኜ የዛሬው ህመም መነሻ ምክንያት በፀሃዪ አሳብቤ ከራሴ ጋር ወጉን ይዥዋለው።
ወንድም አፍንጫህ እየደማ ነው ቀና በል የሚል አንዳች ድምፅ ወደ ጆሮዬ ሰርፆ ገባ ለኔ እንደሆነ የገባኝ ከጥቂት ሰከንዶች በሗላ ነው። ወደ መሬት የወረደውን ደም ስመለከት
ከአፍንጫዬ ቀና ብዬ ሚወርደውን ደም በሶፍት ጠርጌ ፀጉሬን መታጠብ ስጀምር የሸሚዜን ኮሌታ ወደ ኋላ ተሳበ ዝቅ በልና ታጠብ ልብስህን ውሃ እንዳይነካው እኔ ይዤልሃለው። ደም መፍሰስ ከጀመረ እኮ ቆየ እንዴት ልብ አላልከውም? ሚል ድምፅ ዳግም ወደ ጆሮዬ ገባ ይህ ከድካም ስሜት አስፈንጥሮ ሚያሶጣ ፣ ከሙዚቃ ቃና በላይ ልቆ የሚሰማ ፣ ሳይቀኝ የተቃኝ ሚመሰል የሙዚቃ ዜማ ያለው የሴት ድምፅ ነው። የሰማሁት ድምፇ ቢሳል የሞናሊዛን ውበት እስኪመስል ድረስ ፣ ድምፇ ቢገነባ የቡርጅ ኸሊፋን ህንፃን ውብት ያክል ያምር ነበር ድምፅ ብቻ ወይስ ሌላ አንዳች ውበት?
ቀና ብዬ እስካያት ጓጉቻለው። ከአንገቴ ቀና እያልኩኝ ከልብ አመሰግናለው የኔ እህት ሚለውን ሀበሻዊ ቃል አስከተልኩኝ።
ፊቷን ለማየት የቆየሁባት ደቂቃዎች ርዝመታቸው ከእድሜ ልክ እስር በላይ ሆኑብኝ ፣ ጐንበስ ያልኩት ልታጠብ ሳይሆን በርበሬ ልታጠን እስኪመስል ድረስ ቀና ማለቴን ናፈቅኩት ።
ቀና ስል ተዓምረ ውበት ከፊቴ መቆሟን አስተዋልኩኝ ፣ የውበት ናሙና ሳይሆን እራሱ ውበት ፊቴ ቆሞ ሚያወጋኝ መሰለኝ ከመደሰት ይልቅ ንዴቴ ገዘፈ። ደም ቢፈሰስ በደም ይተካል ደም ቢጐድል የሚሪንዳ ስራ ምንድን ነው? ይህ ውበት ሳላየው ቢያልፈኝስ? እስካሁን ቀና አለማለቴን ረገምኩት እንዴት ይህ ውበት ለአንድ ደቂቃ ያመልጠኛል እራሴን በመውቀስ ያገኝሁትን እድል ማሳለፍ አልፈለግኩም። እዚ ግቢ ውስጥ እንደዚህ አይነት ውበት መኖሩን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? እስካሁን ያላየናት ብቻዋን እያሰተማርዋት ወይስ የቆንጆዎች ሌላ ክፍል አለ?
"አንድ አንድ ጊዜ ፣ ደስታን ለማወቅ በሀዘን ፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት ፣ የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው ሚለው አስተምህሮ ውበትን ለማወቅ በአስቀያሚዎች መከበብ ግድ ይል ይሆን እንዴ?
እኛ ክፍል ያሉ ሴት ተማሪዎች የእሷ ምርቃት መስለው ታዩኝ ኧረ እንደውም አይባልም እንጂ የእሷ አግልጋይነትም ባገኙ ብዬ ተመኝሁኝ ። ምን ሆኜ ነበር ያገኝሗት? ፈዝዤ ቀረሁኝ ምን ብዬ ላናግራት ነበር?
ክፍል አራት ይቀጥላል.........
Share and join
@yegetemkalat
@poem_merry
3.6K viewsSemir ايمي سمير, edited 16:19