2023-05-13 13:20:51
ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአበበ በለው ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ
ንሥር ብሮድካስት
ግንቦት 5/2015
ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል።
አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት።
የአማራ ህዝብ ህግ ያለ እንዳይመስለው ህግ የለም እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት።
የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። የሚያስከብረው ሀይል ብቻ ነው የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው።
አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል።
የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል
የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው።
አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሄር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ሀይል ነው።
ሌላው ጠላት ይበቃናል ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም።
የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው መገደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው።
እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው።
የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው።
ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos
FaceBook Page 1 : https://www.facebook.com/Nisirbroadcast
FaceBook Page 2: https://www.facebook.com/Nisirmereja
Telegram: https://t.me/nisirbroadcasting
Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter: https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram: https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
396 views10:20