Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.01K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On Utube sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-12-23 22:32:56 ወንጌላዊው ክርስትና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል!

ፈር - ቀዳጁ የወንጌል መልዕክተኛ

ወንጌላዊ ማሄ ጮራሞ ያገኘሁት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የአገር ውስጥ ሚሲዮናዊ ነው፡፡ ያገኘሁት ታስሮ ነበር። ጠዋት ከ26ዐዐ ሜትር ከፍታ ላይ ወዳለችው የቡልቂ ከተማ ስገባ ቅዝቃዜው አይጣል ነበር፡፡ እስረኞቹ በቡድን ሆነው በቀርከሃው አጥር ሥር በመቀመጥ ፀሀይ ይሞቃሉ፡፡ ወታደር ከአጠገባቸው ሆኖ ይጠብቃቸዋል፡፡

ማሄ በእጆቹና በቁርጭምጭሚቱ ላይ በሰንሰለት ታስሮ ነበር፡፡ በሚራመድበት ወቅት ሰንሰለቱ ያቃጭል ነበር፡፡ ልብሶቹ በደም ተጨማልቀዋል። ማታ በጭካኔ ድብደባ ስለደረሠበት ፊቱ አባብጧል፡፡ ከንፈሮቹ ተሰንጥቀዋል፡፡ ከተፈነካከተው ጭንቅላቱ የፈሰሰው ደም ከትከሻው ላይ ክብ ሠርቷል። መላ ሰውነቱ ቆሳስሎ ስለነበር ከፍተኛ ህመም እየተሰማው እንደሆነ የሚያጠራጥር አልነበረም፡፡

ማሄ እኔን ሲያይ ፈገግ ለማለት ሞከረ፡፡ ሚሲዮናዊ መሆኔን ጠርጥሮ ነበር፡፡ ድንገት መንፈሳችን ኅብረት፣ ጓደኝነትና ለዕድሜ ልክ የሚዘልቅ አገልግሎት ለማካሄድ ተጣመረ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ሊከሰት የሚችለው የክርስቶስ መንፈስ ባላቸው ሰዎች መካከል ብቻ ነው፡፡ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወንጌላዊያን ማሄ ስደትንና መከራን የአገልግሎቱ አካል አድርጎ ተቀብሎታል። በመሆኑም የሚደርሰበትን መነጠል፣ በደል፣ ግርፋትና እሥራት የሚቀበለው በደስታ ነበር ።

መጀመሪያ ከተገናኘንበት ከጥቂት ዓመታት በኋላ ማሄና እኔ በቡልቂ ፍርድ ቤት ተከሰን ቀረብን፡፡ ሦስት ቁጡ ዳኞች፣ ከዳኞቹ በላይ የተበሳጨ አንድ የኦርቶዶክስ ቄስ፣ አያሌ የችሎት ባለሥልጣናትና ከሳሹ ፖሊስ በአንድ ላይ ጮሁብን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ችሎት በሥራ ላይ ሆኖ አየሁት፡፡ በክርስቲያኖች ላይ የተለያዩ ውሸቶች ሲነገሩ በፀጥታ ቆሜ ሰማሁ። አብዛኞቹ ክሶች "መንግስትን ተቃውመዋል፣ ግብር አይከፍሉም፣ የህዝቡን ሰላማዊ ባህሎች ለውጠዋል" የሚሉ የውሸት ክሶች ነበሩ፡፡ እውነቱን ለሚያውቅ ሰው ግን ይህ አስቂኝ ነበር፡፡

ለሦስቱ ዳኞች መመሪያ የሚሰጠው ቄስ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በአንክሮ ለመመልከት ቻልኩ፡፡ ከሳሹ ፖሊስ ለእስረኞቹ የረዥም ዓመታት እሥራት እንዲበየን በተደጋጋሚ ይጠይቃል። ክርስቲያኖቹ የኦርቶዶክስ ጾሞችን አለመጾማቸው ዳኞቹን በተለይ አበሳጫቸው፡፡ ዋናው ዳኛ "አዎ እኛ ኦርቶዶክሶች እንጾማለን እናንተ ግን አትጾሙም" ሲል ጮኸ፡፡ ያኔም ድንገት አጠገቤ የነበረው ማሄ መናገር ጀመረ።

"እኛ ግን እንጾማን!" አለ።

"ምን? ምን? ማነው ይህን ያለው?" ሲል ጮኸ ዳኛው። ማሄ ወደፊት ወጣ፡፡ "እናንተ ትጾማላችሁ? እውነት ትጾማላችሁ? ከምንድነው የምትጾሙት? ከወተት? ከእንቁላል? ከቅቤ?" ሲል ዳኛው ጮኸ፡፡ ማሄ ሁሉም ሰው እንዲሰማው ስለፈለገ ድምጹን ከፍ አድርጎ ይናገር ጀመር።

"ከኃጢያት እንጾማለን!"

በህዝቡ መሃል ሁካታ ሆነ። ሁኔታውን ለመከታተል የቆሙት ሰዎች ይሳሳቁና ይጨባበጡ ጀመር። 53ቱ እስረኞችም እየተሳሳቁ እጆቻቸው የታሰሩባቸውን ሰንሰለቶች አቃጨሉ፡፡

"አዎን እንጾማለን! ከኃጢያት እንጾማለን! " አሉ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ይህ ታሪክ "ኢትዮጵያውያን የወንጌል ጀግኖች" ከተሰኘው መጽሐፍ ምዕራፍ 27 የተወሰደ ነው። ሰሞኑን "በመጻሐፍት ዳሰሳ" ሰበብ የሕግ ተጠያቂነት ጉዳይ ሲነሳ ነው ትዝ ያለኝ። መጽሐፉን የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ በባልንጀራዬ ዳዊት ፀጋዬ ጥቆማ ገዝቼ እያነበብኩ በነበረበት ምሽት፣ ውድቅት ሌሊት እዚህ ምዕራፍ ላይ ስደርስ ጎረቤት ሊሰማ በሚችል ድምጽ ያወጣ ለቅሶ እሪሪ ብዬ ጮኬ አልቅሻለሁ። ዛሬ ላይ እንዲህ የሚቀለድበት ወንጌላዊው ክርስትና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል።

ሽመልስ ይፍሩ
@nazrawi_tube
715 viewsΒενιαμίν, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 13:17:36 በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያላችሁን እውቀት ለማሳደግ ቃሉን ከማጥናት ጎን ለጎን ብትከታተሏቸው የምመክራችሁ 40 የዪትዩብ ቻናሎች ናቸው እያንዳንዱን ገብታችሁ SUBSCRIBE አድርጉ።

የግለሰቦች፦
ዶክተር ማሙሻ ፈንታ፦ https://youtube.com/@equipmedia2577

ፓስተር አስፋው በቀለ፦ https://youtube.com/@asfawBekelepastor

ፓስተር ተስፋዬ ሀይሌ፦ https://youtube.com/@pastortesfayehaile6927

ዶክተር መለሰ ወጉ፦ https://youtube.com/@ethiopianoutreachministry-5165

ጳውሎስ ፈቃዱ፦ https://youtube.com/@PaulosFekadu

ሳምሶን ጥላሁን፦ https://youtube.com/@Samsontblog

ዘላለም መንግሥቱ፦ https://youtube.com/@zelalemmengistu6889

ሄኖክ ጌታቸው፦ https://youtube.com/@henokget

ወንጌላዊው ያሬድ ጥላሁን፦ https://youtube.com/@EvangelistYaredTilahun

ፓስተር እንዳልካቸው ተፈራ /አሹ/፦ https://youtube.com/@AshuTefera

ዳዊት ፋሲል፦ https://youtube.com/@dawitfassilministries

ተስፋዬ ሮበሌ፦ https://youtube.com/@tesfayerobeletesfaye2480

ስሜ ታደሰ፦ https://youtube.com/@SimeTadesse

ፓስተር ግርማ በቀለ፦ https://youtube.com/@GospelofGraceChannel1 ,,,,or,,,,
https://youtube.com/@girmabekele2963

አላዛር ታምራት፦ https://youtube.com/@alazartamiratministry1134

ቄስ ፍቃዱ ቦረና፦ https://youtube.com/@fikethelutheran5492

ሜሎስ፦ https://youtube.com/@melos8013

ወ/ዊ ኤርሚያስ፦ https://youtube.com/@ADIRTUBE

የክብር ዶ/ር አድያምሰገድ ወ/ማ፦ https://youtube.com/@globalhealinginloveandunit4682

amanuel dubale፦ https://youtube.com/@AmanMediaOfficial

ሚዲያዎች፦
እውነት ለሁሉ፦ https://youtube.com/@truthforalltube

ሕንጸት፦ https://youtube.com/@HintseTube

Bible project Amharic፦ https://youtube.com/@BibleProjectAmharic

የክርስቲያን ድምጽ፦ https://youtube.com/@voiceofchristian3089

ማዶ ቲዩብ፦ https://youtube.com/@madotube

ወንጌል ቲዩብ፦ https://youtube.com/@wengeltube


ፌሎሺፕ፦
ኢቫሱ፦ https://youtube.com/@EvaSUE

ትሪኒቲ ፌሎሺፕ፦ https://youtube.com/@trinityfellowshipaddisabab9716

AASTU ፦ https://youtube.com/@aastuecsf3055


ሚኒስትሪዎች፦
ሆም በየዕለቱ፦ https://youtube.com/@ho-medaily4876

ግሬት ኮምሽን ሚንስትሪ፦ https://youtube.com/@greatcommissionministryeth1008


የቤተክርስቲያን ሚዲያዎች፦
አዲስ ኪዳን ቤ/ክ ካናዳ ቶሮንቶ፦ https://youtube.com/@addiskidanchurchtoronto8789

ሀልዎት አማኑኤል ቤ/ክ፦ https://youtube.com/@halwotemmanuelchurch6433

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤ/ክ፦ https://youtube.com/@yhbctube1749

ECFUK፦ https://youtube.com/@ECFCUK

ECFCHouston፦ https://youtube.com/@ECFCHouston

አዲስ አበባ አማኑኤል ህብረት ቤ/ክ፦ https://youtube.com/@ADDISABABAEMMANUELUNITEDCHURCH

ሕያው መንገድ ቤ/ክ፦ https://youtube.com/@-livingwaychurch2411

living gosple church፦ https://youtube.com/@lgcwinnipeg

የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤ/ክ፦ https://youtube.com/@theanointedwordofgodchurch6205


ሌሎችም ይኖራሉ ለእኔ ግን የቻልኩትን ያህል ጥሩ ጥሩ ቻናሎች ናቸው ብዬ ያሰብኩትን ነው የሰበሰብኩላችሁ። አንዳንድ ተራ ቀልድ እያያችሁ ጊዜ ከማቃጠል እነዚህን ቻናሎች ብትጠቀሙ ትባረካላችሁ።
315 viewsΒενιαμίν, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 11:28:57

527 viewsΒενιαμίν, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 15:40:00 “የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን።” (የሐዋ. 21፥14)

ይሄን ጥቅስ ታክሲ ላይ ወይም ቤት ውስጥ ተለጥፎ ማየት ብርቅ አይደለም። የሰርግ ካርድ ላይ ተጽፎ ማንበቤን ግን መቼም የምረሳው አይመስለኝም። የሰርጉ ጠሪዎች የሙሽሪት ወላጆች ናቸው፤ በባል ምርጫዋ እንዳልተስማሙ በጨዋ መንገድ እየነገሩን ነበር።

ይህ ጥቅስ፣ ከሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሩሳሌም ጉዞ ጋር የተገናኘ ነው። አንዳንዶች ጳውሎስ ለእስር የተዳረገው የመንፈስ ቅዱስን ምሪት አልቀበል ብሎ፣ የወዳጆቹን ምክር ንቆ፣ መከራ ናፍቆ ወይም በጀብደኛነት ይመስላቸዋል። እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው፦

ቅዱስ ጳውሎስ በዐለ አምሳን በኢየሩሳሌም ለማሳለፍ ጥድፊያ ላይ ነበር (የሐዋ. 20፥16)። በዚህ ጥድፍያው ላይ ሳለ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ለስንብት አስጠራቸው። በስንብት ንግግሩ ውስጥ፣ “አሁንም፣ እነሆ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ፦ እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል” የሚል ሐሳብ ነበረበት (20፥22-23)። በዚህ ስፍራ፣ “በመንፈስ ታስሬ” የሚለውን ሌሎች የአማርኛ ትርጉሞች፣ “በመንፈስ ቅዱስ ታዝዤ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዴ ነው” (አት)፤ “መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው” (አ.መ.ት) ብለውታል።

ከዚህ እንደምንረዳው፣ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ እየጎተጎተው ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው። በኢየሩሳሌም ምን እንደሚገጥመው ርግጠኛ ባይሆንም፣ እስራትና እንግልት እንደሚጠብቀው በሄደባቸው ከተሞች ሁሉ ወገኖች ሲነግሩት ነበር። ከዚህ በመነሣት ጳውሎስ ከእስራትም በላይ ሞትም ሊገጥመው እንደሚችል ያስብ እንደ ነበር የምንገነዘበው ለስንብት የጠራቸውን ሽማግሌዎች፣ ከዚህ በኋላ ፊት ለፊት እንደማይተያዩ ሲነግራቸው ነው (ቁ. 25)።

ከዚህ ሁለት ነገሮችን እንወስዳለን። በመጀመሪያ፣ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ መንፈስ ቅዱስ ግድ ብሎታል። ከዚያም፣ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ በሚያልፍባቸው ከተሞች የሚያገኛቸው ወገኖች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው እስራትና መከራ እንደሚጠብቀው ይነግሩት ነበር። (ነቢዩ ኤልያስ እንደሚነጠቅ በየከተማው ያሉ የነቢያት ልጆች ያውቁ እንደ ነበር፣ ስለ ጳውሎስ እስር አይቀሬነት በየከተማው ያሉ ወገኖች በመንፈስ ተረድተው ነበር!) ሐዋርያው ጳውሎስ በሁለት ከተሞች የገጠሙት ተመሳሳይ ጉዳዮች በሚቀጥለው ምዕራፍ ተጠቅሰዋል።

የመጀመሪያው፣ በጢሮስ ከተማ የገጠመው ነው። በዚያ ያገኛቸው ወገኖች፣ “ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በመንፈስ አሉት” (21፥4)። ማለትም፣ “በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ጳውሎስን ‘ወደ ኢየሩሳሌም አትሂድ!’ ብለው ነገሩት (አት)። “በመንፈስ ሆነው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ነገሩት” (አመት)። እዚህ ጋ ያለው ሐሳብ ለትርጉም አስቸጋሪ ቢሆንም፣ እንደሚከተለው ብንቀበለው ተገቢ ይሆናል፤ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ምን እንደሚገጥመው መንፈስ ቅዱስ ለእነዚህ ወገኖች ገልጦላቸዋል። ጳውሎስ ወደዚያ እንዳይሄድ የሰጡት ምክር ግን የወዳጅነት ምክር እንጂ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ አልነበረም። ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ ግድ ያለው መንፈስ፣ በእነርሱ በኩል ደግሞ “አትሂድ” ሊለው አይችልምና። ምክራቸው ጥሩ ምክር ነበር፤ ጥሩ ምክር ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ላይሆን ይችላል!

ሐዋርያው ጳውሎስ እነርሱን ተለይቶ ከተጓዘ በኋላ ወደ ቂሳርያ ደረሰ። በቂሳርያ ደግሞ አጋቦስ የሚባል ነቢይ፣ ጳውሎስ በአይሁድ ተይዞ በአሕዛብ (በሮማውያን) እንደሚታሰር በድራማዊ መንገድ ለሁሉ ገለጠ (21፥10-11)። አጋቦስ ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበለውን ትንቢት ተናገረ እንጂ፣ “ወደ ኢየሩሳሌም አትሂድ” የሚል ምክር ለጳውሎስ አላቀረበም። ይህ ብስለት ነው! የአጋቦስን ትንቢት የሰሙ ወገኖች ግን፣ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ በልቅሶ ለመኑት። ከመካሪዎቹ መካከል ወንጌላዊ ወዳጁ ሉቃስም ነበረበት። ጳውሎስ ግን እንኳን እስራት ሞትም ቢጠብቀው ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድ እንደማይታቀብ ቁርጡን ነገራቸው (ቁ. 12-14)። ያኔ፣ “የጌታ ፈቃድ ይሁን” በማለት ዝም አሉ፤ በቅሬታ። የሆነውም ይኸው ነው!

ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው መከራን ስለ ናፈቀ ወይም የሰዎችን ምክር ስለማይቀበል አልነበረም። ምክንያቱም ወደ ኢየሩሳሌም ከደረሰ በኋላ፣ ከአይሁድ የሚቀርብበትን ተቃውሞ የሚያለዝብበት ምክር በቅዱስ ያዕቆብና በኢየሩሳሌም የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሲቀርብለት ተቀብሎ ተግብሯልና (የሐዋ. 21፥17-26)። ስለዚህ ነገሩ እንዳይከር ይፈልግ ነበር ማለት ነው፤ የሰዎችን ምክርም ይቀበል ነበር። ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ መንፈስ ቅዱስ የሰጠውን ምሪት ግን ከመቀበል ወደ ኋላ የሚል ሰው አልነበረም!

በአገልግሎት መንገዳችን ላይ ችግር እንደሚገጥመን እግዚአብሔር አስቀድሞ የሚናገረው ከስፍራው እንድንሸሽ ሳይሆን፣ ችግሩን አስበንና ተዘጋጅተን እንድንጋፈጠውም ሊሆን ይችላል።

አንዳንዴ ይህንም ማሰብ ያስፈልገናል!

@PaulosFekadu
@nazrawi_tube
371 viewsΒενιαμίν, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 20:08:33
በተከታታይ #9 ክፍሎች የተከታተላችሁት የቴዲ ታሪክ ዛሬ ተጠናቋል።
ይሄ የቴዲ እና ቤተሰቦቹ ፎቶ ነው። እስቲ ታሪኩ የተመቻችሁ ቴዲን እና ቤተሰቡን ባርኳቸው

የቴዲ fb ገጽ https://www.facebook.com/profile.php?id=100005920535746&mibextid=ZbWKwL
816 viewsΒενιαμίν, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 20:05:47
በተከታታይ #9 ክፍሎች የተከታተላችሁት የቴዲ ታሪክ ዛሬ ተጠናቋል።
ይሄ ይ ቴዲ እና ቤተሰቦቹ ፎቶ ነው። እስቲ በታሪኩ የተመቻችሁ ቴዲን እና ቤተሰቡን ባርኳቸው

የቴዲ fb ገጽ https://www.facebook.com/profile.php?id=100005920535746&mibextid=ZbWKwL
26 viewsΒενιαμίν, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 19:01:01 ላለፉት 14 ዓመታትም እግዚአብሔር ያስተማረኝን መስማት ለሚወዱ ሁሉ በማስተማር እና ቅዱሳንን ከስህተት ትምህርቶችና ልምምዶች እንዲጠበቁ ባገኘሁት መንገድ ሁሉ እያሳሰብሁ፣ እገኛለሁ። ቢሆንም ግን ያለፉት 14 ዓመታት በጣም ፈታኝ ነበሩ።

ከእኔም ልምድ ማጣት፥ ከትውልዱም (በርካቶቹን ለማለት ነው) ቁስ ተኮርነት እንዲሁም ለአገልግሎት ከሚያስፈልገው የገንዘብ እጥረት ጋር ተያይዞ በጣም ፈታኝ መንገድ ነበር ያሳለፍሁት። በ2002 ዓም ከጄሪ ጋር ትዳር ልንመሰርት ጥቂት ወራት ሲቀረን በጎተራ ኮንዶሚኒየም የደረሰኝን ባለሁለት መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት እስከመሸጥ ድረስ የሆነ ዋጋ አስከፍሎናል። በጌታ ፀጋ።

ያው በሐዋርያት ስራ ላይ የተመሰረተችው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ቤታቸውን እና መሬታቸውን ሸጠው ገንዘባቸውን በሰጡ ሰዎች አልነበር የተቋቋመችው? እኔም ያንን መንገድ ተከትዬ እግዚአብሔር የሰጠኝን ራዕይ ለመፈፀም ጥረት አደረግሁ። ጌታን እወደዋለሁና። ለሚወዱት የሚከፈል ዋጋ ደግሞ አይቆጭም። እግዚአብሔር ረድቶኝ በአገልግሎቴ ጥቂቶችም ቢሆኑ የክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት ሆነዋል።

እግዚአብሔርም ታማኝ ስለሆነ ራዕዬን የምትረዳ ጌታን የምትወድ እየሩሳሌም ነጋሽን የመሰለች (እኔ ባርኮት ነው የምላት) የትዳር አጋር ሰጠኝ። ሶስት ልጆችንም ኢዮሲያስና ዮሐና እና ሩትን (በእርግጥ ሩት ሳናያት ወደ ጌታ ብትሔድም) ወልደን እግዚአብሔርን በተሰጠን ፀጋ እና ራዕይ እያገለገልን እንገኛለን። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

አሁን 43 ዓመቴ ነው። ጌታ ቢፈቅድ እና ብኖር በቀጣይ 30 ዓመታት በሶስት አቅጣጫዎች ላይ አተኩሬ በመስራትና ለወንጌል ባለ ዐደራ የሆነ ትውልድ በማዘጋጀት የበኩሌን ላደርግ ተዘጋጅቻለሁ (እስከዚያ ጌታ ካልመጣ)።

የመጀመሪያው በቀጣይ ሰላሳ ዓመታት “አርባ” የባላደራ ትውልድ ቤተክርስቲያን “አጥቢያዎችን” በመላ ሃገሪቱ ብሎም ከሃገር ወጪ መትከል። ሁለተኛው አገልጋዮች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ተግዳሮት ሆነው በሚመጡ አስተምህሮዎች እና እንቅስቃሴዎች ላይ እውቀት የሚያገኙበት ወንጌልን ለመጪው ትውልድ ለማሻገር የሚታጠቁበት “የስልጠና ማዕከል” (ነህምያ የስልጠና ማዕከል) ማቋቋም። ሶስተኛው ተሃድሶዊ ትምህርቶች እና መርሃ ግብሮች ላይ የሚያተኩር “የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል” (ባለአዳራ ቲቪ ቻናል) ማቋቋም። ይህንን አድርጌ ማለፍ ከቻልኩ ለቀጣዩ ትውልድ በረከት እሆናለሁ እግዚአብሔርም ይከብራል ለእኔም ዘላለማዊ ብድራት ይሆንልኛል።

በመጨረሻም፦በእኔ በታናሹ ሰው እግዚአብሔር የሰራውን የህይወት ምስክርነቴን በዘጠኝ ተከታታይ ክፍሎች ሳቀርብ አንዳች ነገር ይገኝበታል ብላችሁ በትጋት ስለተከታተላችሁኝ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ለማለት እወዳለሁ። ቅዱሳን ሁላችሁ በፀሎታችሁ አስቡኝ ብዬ እጠይቃለሁ። ተባረኩ!!

እነሆ ምስክርነቱ ተፈፀመ። የእግዚያብሔር ማዳንና በጎነት ይታወቅ ዘንድ ተፃፈ።

ክብር ለእግዚያብሔር ብቻ ይሁን!!

ቴዎድሮስ ተጫን
@nazrawi_tube
190 viewsΒενιαμίν, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 19:00:41 የዛሬ 21 ዓመት#9
(ከሳውዲ ከመጣሁ ጀምሮ እስከ አሁን ያለውን በወፍ በረር ላካፍላችሁ)

አዲስ አበባ እንደደረስሁ የተቀበሉኝ ቤተሰቦቼ ነበሩ። በተለይ አንድ የተወደደ አጎታችን ገና ሰላም ሳይለኝ “አይ ቴድሮስ እንዲያው ምን ሆነህ ነው?” ብሎ በጣም እንዳዘነብኝ በሚገልጥ ቃል ነበር የተቀበለኝ (ያው እንግዲህ እናትህን ማገዝ ሲገባህ ምን ሆነህ ነው የመጣኸው ማለቱ ነበር)። እንደ ነገሩ ሰላም አሉኝና ወደ አክስታችን ቤት ሄድን። ከቤተሰቦቼ ጋር ብዙም የቀረበ ነገር ባይኖረኝም ሁሉም ግን በአንድ ልብ ጥፋተኛ መሆኔን በተለያየ መንገድ ሊያሳዩኝ ሞከሩ። መገፋት እንግዲህ የክርስቲያን ወጉ ነውና ብዙም አላሳሰበኝም። ከአክስቴም ጋር ብዙውን ጊዜ እኔ ወንጌል ስነግራት እርሷ ለእናቴ የማላስብ ጨካኝ መሆኔን ስታስረዳኝ በክርክር ነበር የምናሳልፈው።

አክስቴ ቤት ጥቂት ቀናት ካረፍኩ በኋላ ቤቱ ለመቆየት ምቹ ስላልነበር አፈር በአፈር የሆነች ጠባብ ቤት ተከራይቼ ወጣሁ። ከሪያድ ቋጥሬ ካመጣኋት ብር ላይ ፍራሽና ጥቂት ማብሰያ እቃዎች ገዝቼ አዲሱን ኑሮ አንድ ብዬ ጀመርሁት። እናቴም ያው እናት ነችና ከሳውዲ ሁሉን ትቼ በመምጣቴ ብታዝንም ከነጭራሹ ከምተወው ብላ በወር 300 ብር ትልክልኝ ጀመር። አኗኗሬንም ለሶስት መቶ ብር በሚሆን ልክ ክርክም አደረግኋት። ከዚያች 300 ብር ላይ 30 ብር አስራት እከፍልና 110 ብሯን ደግሞ ለቤት ኪራይ እከፍላለሁ። እንግዲህ የቀረችውን ቆጥቤ ወር ድረስ ለመጠቀም እሞክራለሁ። በእርግጥ የኑሮው ሁኔታ እንደ ዛሬው ውድ አልነበረም። ቢሆንም ግን በጣም ከባድ ነበር።

ገንዘቡ ወር እስከ ወር ስለማያደርሰኝ አመጋገቤ ላይ ዘዴ መፍጠር ነበረብኝ። ለምሳሌ ወፍጮ ቤት እሄድና አስር ኪሎ በቆሎ እና አምስት ኪሎ ስንዴ እንድ ላይ አስፈጫለሁ። አስራ አምስት ኪሎ እህል ወደ ቤቴ ገባ ማለት አይደል? ዘይት ደግሞ ለወር የሚበቃ እገዛለሁ። ከዚያማ ቁርሴን ገንፎ ሰርቼ እበላለሁ፥ ምሳዬን ደግሞ ለወጥ አድርጌ ጨጨብሳ እበላለሁ። እራቴን ከፈለከግሁ ቂጣ በሻይ አድርጌ በሌላ መልክ እመገባለሁ። አለፍ አልፍ እያልኩ ሽሮ እሰራና በእንጀራ ልኩን አሳየዋለሁ። በወር ውስጥ ግን በጣም በአብዛኛው ገንፎና ቂጣ ጋር የተያያዘ አመጋገብ ነበር የምጠቀመው። ለዚህ ምግቤም “መና” የሚል ስም ሰጠሁትና በጥቅስ አጅቤ በምስጋና እበላለሁ። መቼም ከዘላለም ሞት የዳነ ሰው በምግብ ምክንያት ከአምላኩ አይጣላም!

አዲስ አበባ እንደ መጣሁ መጀመሪያ መፅሐፍ ቅዱስ እና አጀንዳ ነበር የገዛሁት። ከዚያ በየቸርቹ እየዞርሁ መርሃ ግብሮችን እካፈላለሁ የሚያስተምሩ ሲገኙ እማራለሁ። በየ አውቶብስ መቆሚያውና በየመንገዱ ወንጌል እሰብካለሁ። በቤቴ እፀልያለሁ ቃሉን አነባለሁ። በሂደትም ወንጌል ብረሃን ቤተክርስቲያን (አዋሬ) በቋሚነት መካፈል ጀመርሁ። የአባልነት ጥያቄ ሳቀርብም እንደ አዲስ ደህንነት መማር እንዳለብኝ ተነገረኝ። ተማርሁ እና እንደገና ተጠመቅሁ። የደቀ መዝሙርነት ትምህርቱንም ቀጠልሁ። ወንድማችን አማኑኤል በቀለን በዚህ አጋጣሚ አመሰግናለሁ በትጋት ነበር ያስተማረን።

ከሳወዲ ከመጣሁ በሶስተኛ ዓመቴ ወደ አገልግሎት ገባሁ። የድነት (የደህንነት) ትምህርት ለማስተማር የትምህርት ክፍሉን ተቀላቀልሁ። ለአራት ዓመታትም ያክል በዚህ አገልግሎት ላይ ቆየሁ። በርካቶችን አስተማርሁ እና አስጠመቅሁ። ደህንነት ማስተማር ስጀምር ከአንዲት እህት ጋር ነበር የጀመርሁት ከእርሷ ጋር አብረን ካስተማርናቸው መካከል አንዱ ወንድሜ መላከ ሰላም ነው። በአሁን ወቅት የወንጌል ብርሃን ቤተክርስቲያን አዋሬ አጥቢያ መጋቢ ሆኖ ያገለግላል። በእርግጥ መሌ እራሱን ለማሳደግ የሚተጋ እና የሚጋደል ብርቱ ወንድም ነው። የአገልግሎት ቆይታዬም ደስ የሚያሰኝ ነበረ።

ነገር ግን ከሳውዲ ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት መካከል የሚታየው እኔ ቀድሞ በቃሉ ውስጥ ካነበብሁት የራቀ አስተምህሮ እና እረኝነት (አመራር) እንዲሁም በአብዛኛው ምዕመናን ዘንድ የሚታየው ቁስ ተኮር አኗኗር ፈፅሞ ምቾት ሊሰጠኝ አልቻለም። ምክንያቱም እኔ ሳውዲ እያለሁ ከቃለ እግዚአብሔር ያነበብሁት “ከሃገርህ ከወገንህ ተለይተህ ውጣ” ሚለውን አምላካዊ ጥሪ ሰምቶ ሃያ አምስት ዓመታት ሙሉ በሰው ሀገር የተንከራተተውን እግዚአብሔርን በእግዚአብሔርነቱ ብቻ የተከተለውን አብረሃምን ነው።

እኔ የማውቀው በፈርዖን ቤተ መንግስት ያገኘው ሹመት ለእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ እንደሆነ አውቆ የሚተጋውን የዮሴፍን ነው። እኔ ማውቀው የፈርዖን ቤተ መንግስት በረከት ባፍንጫዬ ይውጣ ብሎ ወደ ምድረበዳ የተሰደደውንና የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለማገልገል ዘመኑን የሰጠውን ሙሴን ነው። እኔ የማውቀው ስለ ክርስቶስ የተሰዋውን ያዕቆብን ነው የተወገረውን እስጢፋኖስን ነው።

እኔ ያነበብሁት ስለ ወንጌል እና ስለ ክርስቶስ የሚጠቅመኝን ሁሉ እጥላለሁ፥ ነፍሴንም በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራታለሁ ያለውን ጳውሎስን ነው። ከምንም በላይ ራሱን አዋርዶ ነፍሱን ለሞት ሰጥቶ፥ መስቀል ላይ ተሰቅሎ እኔን ተከተሉ ብሎ ፈለጉን እንድንከተል የጠራንን ክርሰቶስን ነው።

ኢትዮጵያ ከመጣሁ በኋላ ግን አብዝቶ ግራ የገባኝ በየመድረኮቹ ላይ በስፋት የሚሰጠው ትምህርት ነበር። ያነበብሁትና እዚህ የምሰማው ተራራቀብኝ። ለብዙ ጊዜ እኔ በጣም ፅንፈኛ ስለሆንኩ ወይም አንድ ወንድም እንዳለኝ እግዚአብሔርን በአንድ ጎኑ ብቻ ስላየሁት ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ የማየው “የጥቅም አደር” እረኞች እና ቁስ ተኮር ስብከታቸው ጉዳይ እረፍት ይነሳኝ ያዘ።

በተለይ ወንጌልን ለሚቀጥለው ትውልድ የመሻገሩ ጉዳይ በጣም ያሳስበኝ ጀመር። ስለ ምዕራባውያን አብያተክርስቲያናት መንፈሳዊ ውድቀት እያወቅሁ ስመጣ ደግሞ፤ ያለነው ገደል አፋፍ ላይ እንደሆነ በደንብ ገባኝ። ልክ እንደ እኔ ከሚሰማቸው ወገኖች ጋርም ስለ ሁኔታው እንጫወታለን እንፀልያለንም።

በሂደትም ለመጪው ትውልድ የወንጌልን እውነት የሚያሻግር ትውልድ ለማዘጋጀት የበኩሌን ማድረግ እንዳለብኝ አመንሁ። ይህ ስራ ቀላል እንዳልሆነ ቢገባኝም በቀረልኝ ዘመን ይህንን ለማድረግ መጣር አለብኝ ብዬ ወሰንሁ። ምናልባት እግዚአብሔርም በሳውዲ ምድር እንዳልሞት እና ወደዚህች ምድር ተመልሼ እንድመጣ የፈለገው ለዚህ ይሆናል የሚል ሃሳብ አደረብኝ።

በዚህ ጉዳይ ለአንድ ዓመት ያህል ከጥቂት ወገኖች ጋር በፀሎት አሳለፍን። በእርግጥ እግዚአብሔር ከዚያ የሞት ድግስ ያዳናኝ ለዚህ እነደሆነና እርሱን እንዳገለግለው እንደሚፈልግ በሚገባኝ መንገድ አስረዳኝ። የሚያስከፍለኝ ዋጋ ምንም ቢሆን የወንጌልን ንፅህና ለመጠበቅና ለመጪው ትውልድ ለማሻገር በዚህ ስራ ከሚተጉ ወገኖች ጎን የበኩሌን ለማድረግ ወሰንሁ።

ይህ ጉዳይ የእግዚአብሔር ሃሳብ እንደሆነ ከተረዳሁ በኋላ፤ 2ጢሞ 2፡2 ላይ “ከእኔ የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ” ያለውን ቃል መሰረት በማድረግ መስከረም 7/2000 ዓ ም “ለወንጌል ባለ አደራ የሆነ ትውልድ ተነስቶ ማየት” በሚል ራዕይ “ባለአደራ ትውልድ የተሃድሶ ቤተክርስቲኣንን ከጥቂት ወገኖች ጋር በመሆን መሰረትሁ። በዚያው በ2000 ዓ ም ሐምሌ 30 ከመንግስት ፈቃድ አወጣን።
181 viewsΒενιαμίν, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 20:03:05 የዛሬ 21 ዓመት #8 አህመድ ከሳዌ ከሰራተኞች ሁሉ ሽማግሌው ነው። ሱዳናዊ ነው። ቅጭጭ ያለ ሰውነት ያለው የሚለብሰውም ጀለቢያ (ነጩ) ሁልጊዜ አሮጌና እንደነገሩ ነው። የታችኛው ከንፈሩ እና ጥርሱ መካከል የትንባሆ ቅጠል ወሸቅ ሳያደርግ አይንቀሳቀስም። ለብዙ ነገር ብዙም ግድ የለውም። እድሜውን የጨረሰው እዚሁ ግቢ ሽማግሌውን ዓሚር ሲያገለግል ነው። ከዚህ የተነሳ ታማኝነት የሚፈልገውን የዕቃ ግዢ ጉዳይ…
660 viewsΒενιαμίν, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 19:01:30 የዛሬ 21 ዓመት #8

አህመድ ከሳዌ ከሰራተኞች ሁሉ ሽማግሌው ነው። ሱዳናዊ ነው። ቅጭጭ ያለ ሰውነት ያለው የሚለብሰውም ጀለቢያ (ነጩ) ሁልጊዜ አሮጌና እንደነገሩ ነው። የታችኛው ከንፈሩ እና ጥርሱ መካከል የትንባሆ ቅጠል ወሸቅ ሳያደርግ አይንቀሳቀስም። ለብዙ ነገር ብዙም ግድ የለውም። እድሜውን የጨረሰው እዚሁ ግቢ ሽማግሌውን ዓሚር ሲያገለግል ነው። ከዚህ የተነሳ ታማኝነት የሚፈልገውን የዕቃ ግዢ ጉዳይ ዓሚሮቹ ለእርሱ ነው የሰጡት። ለግቢው የሚያስፈልገውንም ዕቃ ሁሉ የሚገዛው እርሱ ነው። አንዲት ፒክ አፕ አለችው በእርሷ ሲሮጥ ይውላል።

በተለይ ሴት ሰራተኞች መውጣት ስለማይፈቀድላቸው እርሱ ነው የሚፈልጉትን እየተላከ የሚያመጣላቸው። ጨዋታ ወዳጅም ዓይነት ነው። አህመድ ከሳዌ ካለ ጨዋታ አለ። ሳቅ አለ፤ አንዳንድ ግዜም ብሽሽቅ (ለቀልድ) አለ። በሁሉ ተወዳጅ ነው በተለይ በሽማግሌው ዓሚር። ከእኔም ጋር ጥሩ ቅርበት አለን። በተለይ ከእናቴ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው።

ይህ ሰው በጓዳ የተደገሰውን ነገር አይቶ ዝም ማለት አላስቻለውም። እናቴም ጋር ሄደና “ልጅሽን በእነኚህ ቀናት ውስጥ የመንግስት ሰዎች በለሊት መጥተው እንዲወስዱትና እንዲገድሉት ተወስኗልና በቶሎ ከዚህ ግቢ እንዲጠፋ አድርጊ” ይላታል። ይህን ስትሰማ እናቴ እርሷ ወዳለችበት አስጠራችኝ ሃበሾቹም ጓደኞቿ አሉ። በአጭሩ ቤቱ ለቅሶ ቤት ሆነ።

እናቴና ጓደኞቿ ከዚያ ግቢ ለጊዜውም ቢሆን ዘወር በል ብለው በብዙ እንባ ለመኑኝ። እሺ አልኳቸውና የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ጋር ደወልኩላቸው። “መምጣት ትችላለህ” አሉኝ። ቢጃማዬን በፌስታል ይዤ ወጣሁ። እዚያች ፀሎት ቤትም ማደር ጀመርኩ። ወንድሞችና እህቶች በብርቱ ፀለዩልኝ፥ አፅናኑኝም።

በተለይ መጋቢው የተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እያነሳ ብዙ አበረታታኝ። አቢሜሌክ የተባለው ንጉስ የአብረሃምን ሚስት በወሰደበት ጊዜ እግዚአብሔር በለሊት እንዴት እንደገሰፀው፤ አምላካችን እስራኤላዊያንን ከፈርዖን ቀንበር እንዴት እንደታደጋቸው እየጠቀሰ ብዙ አበረታታኝ። ሁኔታውንም ለእግዚአብሔር አሳልፈን ሰጠን። ነገር ግን ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ማሳወቅ እንደሚገባ አንዳንድ ወንድሞች ሃሳብ አቅርበው ነበርና ወደ ኤምባሲ ሄጄ እንዳመለክት መከሩኝ።

ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ሄድኩኝ። መግቢያው በር አካባቢ ባለው መረጃ ክፍል ለሚሰራው ሰራተኛ ጉዳዬን በአጭሩ ስነግረው ወደሚመለከተው ቢሮ ይዞኝ ሄደ። የኢትዮጵያውንን መሰል አቤቱታዎች እንዲሰማ የተሰየመው ሰው ታሪኬን ከመጀመሪያው ጀምሮ በትዕግስት አደመጠኝ።

ስጨርስ ጠበቀና “ምን መሰለህ፤ አሁን አንተ የነገርከኝ ጉዳይ በጣም ከባድ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እኛ በሃይማኖታቸው ጉዳይ መግባት አንችልም። ምናልባት እንዲያውም ሃሽሽ ተገኝቶብህ ቢሆን ወይም ደግሞ ሰርቀህ ብትያዝ ልንረዳህ የምንችልበት ዕድል አይጠፋም ነበር። በዚህ ጉዳይ 'ምንም' ማድረግ አንችልም። ምናልባት ከተቻለ ልንሞክር የምንችለው በነጭ ወረቀት (በድብቅ ማለቱ ነው) ከዚህ ሀገር የምትወጣበትን መንገድ መፈለግ ብቻ ነው። እርሱም ከተቻለ ነው” አለና ቁርጥ ያለውን ነገር ባዘነ ፊት ሆኖ ነገረኝ።

ምንም አላልኩም። አመስግኜው ወጣሁ። የተወሰነ መንገድ እያሰላሰልኩ በእግሬ ሄድኩና ሜትር ታክሲ ይዤ ወደ ፀሎት ቤታችን አቀናሁ። በዚያም ይጠብቁኝ ለነበሩ ወገኖች ኤምባሲ ያሉኝን ሁሉ ነገርኳቸው። ከዚህ በኋላ ያለው አንድ ሁላችን ተስፋ ያደረግነው ነገር “ፀሎት” ብቻ ነው! በፀሎትም ተጋን። እኔም እዚያው ስለምውል ረጅም ሰዓት በፆምና በፀሎት ነበር የማሳልፈው። ምሽቱን ወገኖች ሰብሰብ ሲሉ አብረን እንፀልያለን። እዚያ በነበርኩበት ጊዜ አንድ ጎይቶም የሚባል ጌታን በጣም የሚወድ ስራ ያልነበረው ኤርትራዊም ነበርና አብረን እንፀልያለን። ታዲያ ፀሎታችን ብዙ ጊዜ “ጌታ ሆይ ራስህን ግለጥልን” የሚል ነበር።

እንዲህ ባለ ሁኔታ የተወሰኑ ቀናት ቆየሁ። ፀሎት ቤት ማደር በጀመርሁኝ በአራተኛው ቀን ስልክ ተደወለ። ከእናቴ ጋር አብራ የምትሰራ ጓደኛዋ ነች (ለእናቴ የፀሎት ቤቱን ስልክ ሰጥቻት ስለነበር ያውቁታል)። ዓሚሮቹ “ወደ ቤት ይመለስ አይገደልም!” ብለዋልና እንድትመጣ አለችኝ። ለወንድሞችም ነገርኳቸው። እነርሱም ፀለዩልኝና ተነስቼ ሄድኩ። በርግጥ የሄድኩት አምኛቸው ሳይሆን እግዚአብሔር የፈቀደውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የሚሆን ምንም ሌላ ተስፋ ስላልነበረኝ ነው።

ግቢ ስደርስ አህመድ አደምን (የዓሚር ስዑድን ሹፌር) አገኘሁት። “ያ ቲድሩስ” ና አለኝና ቡና የሚፈላበት አንድ ክፍል አለ እዚያ ይዞኝ ገባ። “አሊ” ብሎ ሊጠራኝ አልፈለገም። እኔም ደስ አለኝ (ስሜን አስመለሰኩ ማለት ነው አልኩ በልቤ)።

“ያ ቲድሩስ ዓሚር ስዑድ ሃሳቡን ቀይሮ ወደ እስልምና የሚመለስ ከሆነ ይቆይ ካልፈለገ ግን ወደ ሃገሩ ይመለስ” ብሏል አለኝ። የሰማሁትን ማመን አቃተኝ። በጣም ደስ አለኝ። በእርግጥ እግዚአብሔር በስራ ላይ እንደሆነ ተረዳሁ።

የዚህን ክስተት ዝርዝር ጉዳይ እናቴ እንደ ነገረችኝ ልንገራችሁ፦ እኔ ከግቢው መጥፋቴ ከታወቀ በኋላ በዚህ ጉዳይ ሁሉም የግቢው ማህበረሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ይነጋገራል። ዓሚሮቹ በአንድ በኩል፥ ወንዶች ሰራተኞችም በሌላ ወገን እንዲሁም ሴቶቹም ሰራተኞች በፊናቸው ይነጋገራሉ። እኔ “አልሰግድም፤ ሚያድነውም ኢየሱስ ነው” ብዬ ከተናገርኩ በኋላ ግቢው ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ አልነበረውም።

ጉደዩን የበለጠ ከባድ ያደረገው ደግሞ፦ ከሳምንት በፊት የሞገትኋቸው አራቱ ሰዎችም “ለእኛ የመለሰልን መልስ አደገኛ ነውና መገደል አለበት!” የሚል ሪፖርት ማቅረባቸውና፤ በተለይ አህመድ አደም (የአሚር ስዑድ ሹፌር) ደግሞ ያላልኩትን ነገር “ቴድሮስ ድንጋይ ነው የምታመልኩት ብሎናል” ብሎ ለዓሚር ስዑድ በውሸት መናገሩ ነበር።

ይህ በተለይ የበለጠ ቁጣ ፈጥሮም ነበር።
ነገር ግን አሚሮቹም ሰራተኞቹም በዚህ ጉዳይ ለሁለት ተከፍለዋል። ዓሚር ስዑድ እና አብዛኛዎቹ “ሸሪዓው መፈፀም አለበት”!ብለው ወሰኑ። በተለይ የዓሚር ስዑድ የታላቅ ወንድሙ ሚስት በጉዳዩ ላይ ገብታ “የዚህች የምስኪን ልጅ መገደል የለበትም” ብላ መከራከር ጀመረች። በዚህ መካከል አህመድ ከሳዌ (ከላይ የነገርኳችሁ ሱዳናዊ) ሽማግሌው ዓሚር ጋር ገብቶ “እናቱ በስንት መከራ ያሳደገችውን ልጇን ለምን ትገሉባታላችሁ? በቃ ወደ ሀገሩ ይሂድ ሸኙት” ብሎ ስለ እኔ ተከራከረ።

እንደነገርኳችሁ አህመድ ከሳዌ ብዙ ዓመት ያገለገለ ታማኝና ተወዳጅ ሰራተኛ ነው። ሸማግሌው ዓሚርም በአህመድ ከሳዌ ሃሳብ ተስማማ። ከብዙ ክርክር በኋላ የሽማግሌው ዓሚር ትዕዛዝ መቋጫ ሆነ “እንዳትገድሉት ነገር ግን ወደ ሀገሩ መልሱት ትኬት ወጪውንም እኔ እከፍላለሁ” ብሎ አዘዘ። የእግዚያብሔር ሃሳብ እንዲህ ነበርና!! እግዚአብሔር በመካከላቸው የቋንቋ መደበላለቅን አደረገ።

ይህ ለእኔ ትልቅ ተዓምር ነበር። እግዚአብሔር የእኔንም ሆነ የቅዱሳን ወገኖችን ልመና ሰምቶ ደግሞም በእኔ ሊሰራ ያሰበው ዓላማ አለውና የማይሆነው ሆነ፣ የማይቻለው ተቻለ፣ የተከፈተውም የሞት አፍ ተዘጋ!! ኢትዮጵያ ከመጣሁ በኋላ ብዙ ሰምቻለሁ። ሳውዲ ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ይዘው ስለተገኙና እምነታቸውን ለሌሎች ስላካፈሉ ብቻ ሞት የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው።
704 viewsΒενιαμίν, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ