2022-11-16 22:15:07
<<ክርስቲያን ንቅሳት ሊያሰራ ይችላልን?>>
መጋቢ ጆን ፓይፐር በ desiringod.org ላይ የሰጠው ምላሽ ወንድም አማኑኤል እንዳለ እንደተረጎመው
በየቀኑ ልንል በምንችልበት መንገድ ስለ ንቅሳት ከአድማጮቻችን ጥያቄዎች በኢሜይል ይደርሱናል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት ምን ይላል?
መጋቢ ዮሐንስ ፓይፐር (Pastor. John Piper)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ንቅሳት የሚናገር አንድ ግልጽ ምንባብ እናገኛለን ዘሌዋዊያን 19፡28። ጥቅሱም እንዲህ ይላል <<ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።>> (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) አሁን ይህንን ምንባብ ስናስብና ቀጥሎ ለመወሰን ጥቂት ደቂቃዎች ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል። ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን አቅርበን ይህንን ምንባብ ለምን ለምን ቆም ብለን ማሰብ እንደሚገባን እንመልከት።
“ሕግ እና ባሕል”
አንደኛው ምክንያት እኛ ከሙሴ ሕግ ሥር አለመሆናችን ነው። “ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እናንተም በክርስቶስ ኢየሱስ ሥጋ ለሕግ ሞታችኋል ይህም ከሙታን ለተነሳው ለእርሱ ለሌላው ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው። (ሮሜ 7፡4 አመት) ስለዚህ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመጽደቅ ወይንም በእግዚአብሔር ተቀባይነት ለማግኘት እንደ ሕግ አሰራር ከሙሴ ሕግ በታች አይደለንም። አሁን ከክርስቶስ ጋር ወዳለ ሕብረት መጥተናል የዚህም ሕብረት መገለጫ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጅረት የሚፈሰው የጽድቅ ፍሬያችን ነው። “አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን ከሕግ ነጻ ወጥተናል ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው። (ሮሜ 7፡6 አመት) ስለዚህ በዚህ ምክንያት ዘሌዋዊያን 19ን የምንረዳበትን መንገድ በቀጥታ ከእኛ ጋር አያይዘን መሆን እንደሌለበት ያመለክታል።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በዚህ ምንባብ (ዘሌ 19) በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስለሞቱ ሰዎች ተብሎ ቆዳን መቁረጥ ሆነ ንቅሳት ማድረግ እጅግ አደጋ የሚያደርስ ስለሆነ እየከለከለ ነው ማለት የሚቻል አይምስለኝም ወይም ደግሞ ከንፈርን ሊፒስቲክ መቀባትንም የኒከለክል ነው ማለት ይሆናል። ነገር ግን ከዚህ ይልቅ እነዚህን ምልክቶች ለሞቱ ሰዎች ብለው እስራኤላዊያን ሰውነታቸውን እንዳይነጩ የሚከለክለው በዙሪያቸው ያለው እውነተኛ የሆነውን አንድ አምላክ የማያውቁና የማያመልኩ ማዕበረሰቦች የሚያደርጉት በመሆኑ ምክንያት ነው። ይህንን በማድረግ ውስጥ አንድ እስራኤላዊ ለእግዚአብሔር ከገባው ቃል ኪዳን ይህም ለእግዚአብሐኢር ራሳቸውን የለዩ ሕዝቦች መሆናቸውን በመተው ርህጽስብ ግስር መመሳሰላቸውን የሚያሳዩበት ነው። ይህም ቆዳ ላይ የሚደረግ ንቅሳት ብቻ ሳይሆን በልብ ውስጥ ያለኝ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ቁርጠኝነት ማጉደልን የሚያሳይ ነው።
ስለዚህ ከእንግዲህ ዘሌዋዊያንን በመጥቀስ ማንንም ንቅሳት እንዳያደርግ ልከለክል አልችልም። ይህንንም አይነት ትዕዛዝ እጅግ በጥእም ከባድ ነው። ከእነዚያ ከላይ ካስቀመጥኩት ሁለት ምክንያቶች ውስጥ ስለ ክርስቲያናዊ መርሆች (Christians principles) ልንመሰርት እንችላለን።ለዚህም ሮሜ ምዕራፍ 7 መነሻ ከሆነን በመርህ ደረጃ ልንጠይቅ የሚገባን ነገር በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ፍሬ ማፍራት እችላለሁ? የሚለው መሆን አለበት። አሁን ይህንን የማደርገው ለእግዚአብሔር ባለኝ ታማኝነትና ፍቅር እንዲሁም በመድሐኒቴ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብደሙ በዋጀኝና በዓለም ክብሩን እገልጥ ዘንድ ነው? የሚለው ጥያቄ ዋና የክርስቲያን መርሕ ሊሆን ይገባል።
“ለእግዚአብሔር ፍሬ ማፍራት”
ለመነቀስ ስትሄድ ልትጠይቅ የሚገባህ ጥያቄ ከላይ ያለውን ይሁን። ይህንን በማድረግ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራቴ ነው? ይህንን የማደርገው እውነተኛውን አምላክ የማያውቁ አህዛብን ለመምሰል ነው የማደርገው? ይህንን በቁም ነገር መጠየቅ ይገባናል። ለምን ይህንን አደርጋለሁ? እግዚአብሔር የማይመስሉ ሕዝቦችን ለመምሰል ነው? ወይስ እኔ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በእውነተኛው ወንጌል መነፈስ ሳይሆን በባዕድ መንፈስ እየመራሁ ነው?
ቀጥሎ የምናደርገው ስለ ጌጣጌጥ አዲስ ኪዳን የሚሰጠው ትምህርት ጥቂት መመልከት ይሆናል። ጳሎውስ የሰጣቸው ትምህርቶች ውስጥ የክርስቶስ ተከታይ መሆን ከአለባበስ፣ከመዋብና ጸጉር አሰራር ጋር በተገናኘ በአማኙ ላይ ለውጥ የሚያመጣ እንደሆነ አስባለሁ። አዎ በትክክል አዲስ ኪዳን በግልጽ ይናገራል።እንዲያውም ከብሉይ ኪዳንም ይልቅ ግልጽ ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር እስራኤልን ያስውባታል። ይህም በትንቢተ ሕዝቄል ላይ በግልጽ ተቀምጦልናል “በጌጣጌጥ አንቆጠቆጠሁሽ በእጅሽ አንባር በዐንገትሽም ድሪ አጠለቁሁልሽ………….በወርቅና በብር አጌጥሽ ልብስሽም ያማረ በፍታ ሐርና ወርቅ ዘቦ ነበር …” (ሕዝ 16፡11,13 አመት) ይህ እግዚአብሔር ለሙሺራዋ እስራኤል ምን ያህል እንክብካቤና ውበት እንዳረገላት ያሳያል። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሆሴዕ ሁለት ላይ ትዕቢቷንና አለማመኗን ሲገልጽ “ለበኣል አማልክት ዕጣን ሰላጠነባቸው ቀናት እቀጣታለሁ በጌጣ ጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች እኔን ግን ረስታለች” ይላል እግዚአብሔር። (ሆሴዕ 2፡13) በአንድ ጽሁፍ ውስጥ አዎንታዊ የነበረው ተመሳሳይ ጌጣጌጥ በሌላኛው ላይ አሉታዊ ወይንም የክፋትና የኩራት ምልክት ሆኗል። ስለዚህ ቀድሞውኑ በብሉይ ኪዳይ ማስጠንቀቂያው እግዚአብሔርን መከተል በልብስህና በጸጉርህ በምትሰራው ለውጥ ያመጣል። ስለዚህ እዚህ ላይ በ1ኛ ጢሞቲዮስ ላይ ያለውን ለመረዳት ዕድል እናገኝእለን “እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ።” (1ጢሞ 2፡9 አመት) ወይም ደግሞ “ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።” (1ጴጥ 3፡3-4 አመት)
ጥያቄው ለሴቶችና ለወንዶች እንድምታው ተመሳሳይ ነው። ወንዶች በሚለብሱት ልብስና በሚጠቀሙት ጌጣጌጥ እና በጸጉር ውስጥ ለማስዋብ በሚያስገቧቸው ነገሮች እና ሁሉንም አይነት መዋቢያ ነገሮች በተመለከተ ለሁሉም ተመሳሳይ መመሪያ አለው። ይህ ሁሉ ለሴቶችና ለወንዶች ሁሉ ነው። ምክንያቱም ለሁለቱም አንድ አይነት መርህ መሆኑ ነው። ይህ ንቅሳት የእነዚያ መልካም ስራዎች መገለጫ ነው? ከልብ በመነጨ፣ እግዚአብሔርን መምሰል ነው? እግዚአብሔር ለእሷ ወይም ለእሱ ባለው ቸርነት የሚረካ የዋህ እና ከተረጋጋ መንፈስ አካል የመነጨ ነው?
ስለዚህ ይህ ሁሉ የእኔ አስተሳሰብ ነው። እኔ እንደማስበው ኃላፊነት የሚሰማው ክርስቲያን ለመነቀስ ሲያስብ ማለት ያለበትን ገልጫለሁ። ይህንን ሁሉ ካልኩ በኋል አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ መነቀስ እንዳለበት አስቦ ምክሬን ቢጠይቅ እንዳይነቀስ ለማሳመን እሞክራለሁ።
መጋቢ ጆን ፓይፐር (https://www.desiringgod.org/interviews/tattoos-in-biblical-perspective)
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
778 viewsΒενιαμίν, edited 19:15