Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85.03K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-04-21 22:09:56 «የሰበ ደለከ ፥ ቢያንዙይ ከፈቴ፣
ስረም ለልነበሪ ፥ ተሰብ ተላፈቴ!»

ዎገሬት ሂንደሩ!
16.0K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 22:07:50
ኢማሙ አሕመድ ያኔ በርሳቸው ዘመን አንድ ሰው ሐራም ላይ ወድቆ ሥራው እንዳይበላሽ ትዳር መያዝ እንዳለበት መክረዋል። "በዚህ ዘመን" ብለው!
የኛን ዘመን ቢመለከቱት ምን ሊሉን ይችላል?

ኧረ! ተፍ ተፍ በሉና በሐላሉ አግቡ ወንድምና እህቶች! በዚህ ዘመን መሰተርን ያክል ትልቅ ነገር የለም።
16.5K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 21:25:42
በኢቲቪ እየቀረበ ባለው "ነጋድራስ" በተሰኘው የሥራ ፈጠራ ውድድር ላይ ዛሬ ከነበሩ ተወዳዳሪዎች መካከል አንድ ሰልማን ዓሊ የተባለ ወንድማችን ያቀረበውን ሃሳብ እዚሁ ፌስቡክ ላይ በኢቲቪ ገፅ ተለቆ እያየሁት ነበር። በግሌ እስካሁን ካየኋቸው ሃሳቦች በሃሳብ ደረጃ የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ሃሳቡ አብዛሃኛው የሃገራችን ህዝብ ኑሮውን እየገፋ ያለበትን የግብርና ሥራን በቴክሎጂ (AI, IoT, GIS, Remote…
15.8K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 18:14:56
ኧረ! My Silte people!
ምነው የባድ ወልድ¿ ከምን ፈታችሁ ለቀቃችሁብን¿

የጎጃም ተረተኞችን የሚያስንቅ ቀደዳ¡

ወይ አዜጋን ፊርዓውን!
ሰው ግን ፈጣጥሮ የሚያወራውን ነገር ሲያወራ ኮስተር ብሎ ስሪየስ ሁኖ በቀም ነገር ማውራት መቻሉ¡
እኔ እየዋሸሁ መሆኔን ውስጤ ስለሚያውቅ ሳቄን አልችለውም¡

ለምንኛውም ሌላ ሳይጨመር ፈታችሁ የለቀቃችሁትን ያዙልን¡
13.0K viewsedited  15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 17:32:15
ኢትዮጵያ ውስጥ «ሰብዓዊ መብት» በሚል ስም ገለልተኛ ነኝ ብሎ ተቋቁሞ በተደጋጋሚ ሙስሊሞች ላይ ለሚፈጸም ጥቃት ደንታ የሌለው ተቋም አይቼ አላውቅም። ዳንዔል በቀለ (ዶ/ር) የሚመራው ኢሰመኮ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን "ኢትዮጵያዊ" መሆናቸውን አምኖ መቀበል የተሳነው፤ በአጼው ዘመን ላይ ተከንችሮ የቀረ ተቋም ይመስለኛል። ይህ መርጦ አልቃሽ የሆነ ተቋም ለአንድ እምነትና ለአንድ ብሄር ብቻ እንጂ ለሙስሊሙ እንደማይጨነቅ በተደጋጋሚ ታዝቢያለሁ። ወይ ይፍረስ፣ ወይ አመራር ተቀይሮ ኃላፊነቱን ይወጣ።

It's disheartening to witness the continued silence of the Ethiopian Human Rights Commission in the face of repeated violence and discrimination against Muslims. Despite our polite appeals for action, they have failed to address the systemic biases that perpetuate injustice. This selective silence speaks volumes about their priorities and raises serious questions about their commitment to human rights for all.

Is protecting ALL Ethiopians, regardless of religion, not their core function? Where is the outrage? Where is the investigation? The EHRC's continued silence is a betrayal of its mandate and a slap in the face to the victims and their families.
#EndBias #JusticeForAll
||
t.me/MuradTadesse
13.3K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 15:21:03
ከይፍ ? እንደት እንዲህ ሊሆን ይችላል¿

ሚስጥር¡ ትቀሰፋለህ¡
14.2K viewsedited  12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 14:31:44
ታሪክ ለማወቅም ይጠቅማችኋል፤ አንብቡት።


ሚያዝያ 12፣ 1966 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን ታላቁ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ለመዘከር፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል።

: Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
||
t.me/MuradTadesse
14.4K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 14:08:31
የጥንቃቄ መልዕክት =============== (በአሁኑ ዘመን የተቸገረን መርዳት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል!) || በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎችን መታመም ሰበብ በማድረግ እርዳታ በማሰባሰብ ሽፋን በተለያዬ መልኩ የሚያጭበረብሩ ሰዎች መብዛታቸው ትክክለኛ ተረጂዎች እንዳይረዱ መሰናክል ሆኗል። ለናሙና ያክል፦ ①) መኪና ተከራይተውና ሐሰተኛ የሕክምና ማስረጃ ይዘው «ወንድማችን ታሞብን ነው!» በማለት…
13.6K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 14:08:20 የጥንቃቄ መልዕክት
===============
(በአሁኑ ዘመን የተቸገረን መርዳት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል!)
||
በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎችን መታመም ሰበብ በማድረግ እርዳታ በማሰባሰብ ሽፋን በተለያዬ መልኩ የሚያጭበረብሩ ሰዎች መብዛታቸው ትክክለኛ ተረጂዎች እንዳይረዱ መሰናክል ሆኗል።

ለናሙና ያክል፦
①) መኪና ተከራይተውና ሐሰተኛ የሕክምና ማስረጃ ይዘው «ወንድማችን ታሞብን ነው!» በማለት በተለያዩ ወረዳዎች እየተዟዟሩ ከማኅበረሰቡ ከታች በፎቶው የምትመለከቱትን ብር ያጭበረበሩ ሰዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

አሁን የነዚህ ሰዎች ድርጊት በትክክል ሰው ታሞባቸው በመኪና ተዟዙረው ድጋፍ የሚያሰባስቡ ሰዎች በሙሉ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ ነው።

*
②) ከቅብር ጊዜ ወዲህ የቴክኖሎጂውን መሻሻል ተከትሎ ሌላኛው የማጭበርበሪያ መድረክ የሆነው ማኅበራዊ ሚዲያ ነው። በውሸት ውስወሳና ጅንጀና የተሻለ ገንዘብና ሥራ ታገኛላችሁ በሚል የሚያጭበረብሩ ዘርፈ ብዙ ስካመሮች እንዳሉ ሆነው፤ በተቸገሩ ሰዎች ሽፋን ኪሳቸውን የሚያደልቡም የትየለሌ ናቸው።

እነዚህን በሦስት ከፍለን እንያቸው፦
ሀ) የሆነ ወቅት ላይ የታመመን ህፃን ወይም ሰው ሆስፒታል ተኝቶ የሚያሳይ ወይም ህመሙን አሳዛኝ በሆነ መልኩ የሚገልፅ ፎቶ አያይዘው፤ ከስር የግላቸውን የባንክ አካውንት አያይዘው በሶሻል ሚዲያ በማሰራጨት የሚሸቅሉ አሉ። ምናልባትም ያ የለጠፉት ፎቶ የሆነ ወቅት ላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተፖስቶ ገንዘብ የተሰባሰበበት ይሆናል። ግን የተሰባሰበለት ሰው ብሩ ሞልቶለት ታክሞ ድኖ ይሆናል ወይም አላህ ከወሰነም ሞቶ ይሆናል። እነርሱ ግን ያንን እንደ አዲስ ፖስተው በነርሱ አካውንት እንድገባ ያደርጋሉ። ሰውም የተፖሰተውን አሳዛኝ ፎቶ ተመልክቶ ውስጡ ስለሚያዝን ሳያጣራ ይሰድቃል።
*
ለ) የተፖሰተው ፎቶ ወይም ቪድዮ እውነተኛ ይሆናል። በተለይም ቲክቶከሮችና ዩ ቲዩበሮች እዚያ ታማሚ ዘንድ ይሄዱና ቀርፀውት በፖስትና በቀጥታ ስርጭት ገቢ ያሰባስቡለታል። ግን የሚሰባሰብበት አካውንት የራሳቸው አካውንት ነው። ወይም እዛው ተመካክረው የሚተዋወቁት አጭቤዎች በግሩፕ የከፈቱት አካውንት ነው። በኋላ ለታማሚ ትንሽ ነገር ጣል ያደርጉለታል። ምክንያቱም ምን ያክል እንደተሰባሰበ መረጃው ስለሌለው የሰጡትን አምኖ ይቀበላል፤ ያንኑስ ማን አየበት በሚል መንፈስ!

አንዳንዶች ግን በተለይም አሁን ከትናንት በፊት ቲክቶክ ላይ የተከሰተው፤ «ያሰባሰብንለት ልጅ አይድንም ብዬ ብሩን አጥፍቼዋለሁ!» ብሎ በአደባባይ ሲናገር የተቀዳውን ቪድዮ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። አለፍ ሲልም ብሩ 350 ሺህ ብር እንደሆነና "ወጣት ነኝ፣ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው፣ አካውንቴን ሽጬ እከፍላለሁ!» ብሏል። ውርደት ከነ ግርማ ሞገሱ!
*
ሐ) ለአላህ ብለው ሳይሆን ጉዳዩን እንደ ቢዝነስ አድርገውት በኮሚሽን የሚያሰባስቡ አሉ። ማለትም በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ወይም በቲክቶክ ወይም በዩ ቲዩብ… በርካታ ተከታታይ ያላቸው ግለሰቦች ሰው የታመመበት ሰው ወይም ራሱ የታመመው ሰው ለሕክምና ተቸግሮ አሰባስቡልኝ ሲላቸው «እሺ! ግን ከሚሰባሰበው ገንዘብ ላይ 20%ቱን ልትሰጠን ትስማማለህ ወይ?» ይሉታል። ከዚያ አማራጭ ስለሌለው እሺ ይላል። ህዝቡ በዚህ መልክ እንደሚሠሩ ስለማያውቅ ዝም ብሎ ይሰጣል። ግን ከፊሉ ገንዘብ ለአሰባሳቢው ነው። ይህ ሥራ 100% ሐራም ነው ለማለት ባልደፍርም ግን ብልግና ነው። ወይ በዛ መልኩ እንደምትሠሩ ማሳወቅ አለባችሁ። የተጨነቀን ሰው ከኪሳችሁ አውጥታችሁ መርዳት ባትችሉ እንኳ በነፃ ብታስተባብሩለት ምን ትጎዳላችሁ? ከአላህ አጅር ማግኘት አትሹም?
አላህ ቢጠይቃችሁስ? ወጣት ናችሁ፤ የሶሻል ሚዲያ ጡረተኛ ከመሆን ሠርታችሁ አትበሉም?


ለካ ለዛ ነው ብዙዎች ሰው ታሞባቸው እንዳሰባስብላቸው ሲጠይቁኝ ወይም ሰውም ሆነ መኪና ጠፍቶባቸው አፋልጉኝ እንድለጥፍላቸው ሲጠይቁኝ፤ «የሚያስፈልግ ነገር ካለ እናሟላለን!» ይላሉ። ለካ በሌሎች ስለሚጠየቁ እኔም የምጠይቃቸው መስሏቸው ነው።



መፍትሄ፦
①) በማይታወቅ ሰው ለተፖሰተ አፋልጉኝ ሳታጣሩ አትሰድቁ። የሚታወቅ ቢሆንም በደንብ የሚታመን መሆኑን እወቁ። በተለይ ኮሚሽን ባልኳችሁ ዘዴ በርካታ የምታውቋቸው ሰዎች ጭምር ይሠራሉ። ወላሂ! ብነግራችሁ ታፍራላችሁ። የማትጠብቁት ሰው ሁላ ተዘፍቆበታል።

*
②) በቀጥታ የታመመውን ሰው በብረት ዓይናችሁ ካላያችሁ ወይም ያዬ የምታምኑት ሰው ካልነገራችሁ በመኪና ለሚዞሩትም ቢሆን አትስጡ። የሆነ ፎቶ ስለተለጠፈ ወይም ታማሚ ተብሎ የሆነ ሰው መኪናው ውስጥ ስለተኛ ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም። አንዳንዱ እግሩን በጀሶ ጠግኖ በውሸት የታመመ መስሎ ተኝቶ የተጋለጠ አለ።
በዚህ መልኩ ለሕክምና ከሚያስፈልገው በላይም የሚያሰባስብ አለ። እንዳውም የሆነ ቀልድ ላይ «መኪናህን መታከሚያ ገንዘብ ላሰባስብበት አከራየኝ ያለህ ሰው፤ በሳምንቱ "ስንት ትሸጠዋለህ?" ሲልህ…!» የሚል አይቻለሁ። ሁሉንም አይመከትም።

በነዚህ አጭበርባሪዎች የተነሳ በትክክል መረዳት ያለባቸው እንዳይጎዱና መተማመን ጠፍቶ መጨካከን እንዳይመጣ፤ እያጣራን እንርዳ እላለሁ። ውስጣቸውን ሳይሰቀጥጠው የአሳዛኝ ታማሚ ሰውነ ገንዘብ የሚያጭበረብሩና በሐሰት የሚለምኑ ሰዎችንም አላህ ልቦናቸውን ለሐቅ ይክፍትላቸው።


ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
========
ኦገስት 20, 2024 G.C.
ሚያዚያ 12, 2016 E.C.
||
t.me/MuradTadesse
13.6K viewsedited  11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 13:32:15
ሐላል ሪዝቅ ፍለጋ ወገብህን ይሰብረው ይሆናል፤ ግን ራስህን ቀና አድርገህ እንድትኖር ያደርግሃል።
13.8K viewsedited  10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ