Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 84.99K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-23 21:55:59
ይነበብ ======== በተለይም ነጋዴው ማኅበረሰብ አንብብ! * «የገቢና የወጪ ንግድን ጨምሮ በጅምላና በችርቻሮ የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች የሚያሟሉት የካፒታል መጠን ይፋ ተደረገ!» ይላል ከትናንት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ ይዞት የወጣው ዜና! ባይሆን በዋናነት ተጎጂ የሚሆኑት እነዚያ ከቻይና፣ ከዱባይ፣ ከቱርክ በርካሽ ዋጋ ያመጡትን እቃ በሁለትና ሦስት እጥፍ አትረፍው በብቸኝነት ሲሾፍሩን የነበሩ በጣት…
17.9K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 17:52:55 አንዱ ሙነሺድ «ያ ረሱለላሊ ባንቱ ነው ማማሬ፣ ባንቱ ነው መዋቤ!» አለ።
ሰውዬውም ቀበል አደረጉና «እንዴት አያምርብህ፣ መተዳደሪያ አድርገሃቸው!»


ኧረ! ተው ክፉ አታናግሩን! 5 ኪሎ ቦርጭ ተሸክሞ "በአንቱ ናፍቆት ከሳሁ ገረጣሁ!" ይላል! ቢያንስ በሚመስል ነገር እንኳ ዋሹን!
15.8K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 11:55:43 ② ምክሮች ለ② ሰዎች
==================
①) በቢዝነስ ጉዳይ፦
አንተ ማሻ አላህ ጎበዝ ተማሪ ነገር ነህ፣ ጥሩ ትሠራለህ። ዩኒቨርስቲ ገብረህ ድግሪህን ጨርሰሃል፣ ከዚያም ማስተርስና ፒኤችዲ እያልክ ሂደሃል፣ ወይም ስፔሻላይዝ ካደረግክ በኋላ ሰብ ስፔሻሊስት ሆነሃል። ግን ይህን ሁሉ አድርገህ ስትመለስ የምትቀጠረው ያኔ 10ኛ ክፍል ላይ ማትሪክ ወድቆ ውጤት ሳይመጣለት ሲቀር ሙያና ቴክኒክ ገብቶ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ ባቋቋመው ተቋም ውስጥ ነው። ሰብ ስፔሻሊስት ሆነህ ወጥተህ ተቀጥረህ የምትሠራው ጭራሽ ሜዲስን እንኳ ሳይገባ ገና ከድፕሎማ ጀምሮ ተምሮ ራሱን አስተዳድጎ በከፈተው የGP ክሊኒክ ውስጥ ነው። ዕውቀትህ ከርሱ በላይ፤ ግን ገቢህ ከርሱ በታች! የግሌ ልክፈት ብትል እንኳ ሁሉም ቦታ ቦታውን ስለተያዘ መግቢያ ቀዳዳ የለም፤ በዛ ላይ ያለው የዋጋ ንረት በቀላሉ አስፈላጊውን ነገር አሟልቶ መጀመር አያስችልም። ያኔ ከመቀጠር ውጭ አማራጭ የለህም፤ በተለይ ደመወዟ አሪፍ ከሆነች ስለምታዘናጋህ በቅጥርህ ትሞታለህ። የተማርከው አካዳሚ ለአኺራህ ጥያቄ መልስ የሚሆን ሸሪዓዊ ነገር ሳይሆን ዱንያህን በአግባቡ ልትጠቀምበትና በርሱም አኺራህን ልትሻበት ነው። ስለዚህ የልፋትህን ማግኘት አለብህ።

መፍትሄ፦ ቢያንስ ድግሪህን እንደያዝክ በፊልድህ የሚሄድ ቢዝነስ ጀምር። የተወሰኑ አመታት እርሱን ቢዝነስ አጠናክረኸው በሁለት እግሩ ሲቆምና ከአንተ ትከሻ ሲወርድ ሌላ ባለሙያ ቀጥረህ አንተ ትምህርትህን ቀጥል፤ በጎድንም በፓርት ታይም ሥራ። ያኔ እየተማርከው ያለው ዕውቀት ተቋምህንም ያጠናክረዋል፤ ትምህርቱም ቢዝበሱም አልቀረም። ተመርቀህ ጸጉርህን መልጠህ ስትመጣ መግቢያ አታጣም፤ ቀድመህ የሰራኸው ቤት ስላለ። አንዳንዱ ሰው ከመማር ውጭ አዕምሮ ለቢዝነስ ክፍት አይደለም፤ ሪስክ ይፈራል፣ እና ይሄን መሰናክል ማሳለፍ ካላስቻለህ መማርህ ምኑጋ ነው? ለዱንያ የሚሆን እንጂ ለአኺራ የሚሆን ሒፍዝ የገባህ መሰለህ እንደ¿

*
②) በትዳር ጉዳይ፦
ገና ሃይስኩልና ካምፓስ ተማሪ እያለሽ የትዳር ጥያቄ ሲቀርብልሽ «ቆይ ትምህርቴን ልጨርስ!» እያልሽ ስትመልሺ ነበር። ወላጆችም ልጃችሁን ስትጠየቁ «ገንዘብ (ቤትና መኪና) የሌለው መናጢ ድሃ ነው!» ከሚለው ባሻገር እነዚህን ያሟላ ቢመጣ እንኳ «ቆይ! ተምራ ትጨርስ!» እያላችሁ ስንትና ስንት ሰዎችን ስትመልሱ ነበር።

ድግሪዋን ስትጨርስ 23ና 24 አመት አካባቢ ይሆናታል። ሥራ ፍለጋ ይባልና በትንሹ አንድ አመት ጫማዋ እስኪገረጣ ልትሯሯጥ ትችላለች። ሥራው ከተገኘ በኋላ አንድ ሦስት አመታት ያልፋል። እነዚያ ለትዳር የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ እየቀነሱ ይመጣሉ። እንዲህ እንዲህ ይልና 30ዎቹ መግባት ይጀምራሉ። ያኔ ጭራሽ ጠያቂም ይጠፋል። ከማንም በላይ መከረኛዋ እናት በሯን ዘግታ ማልቀስ ትጀምራለች። ልጅም ወላጅም ያኔ ከእንቅልፋቸው መንቃት ይጀምራሉ፤ ግን ምን ዋጋ አለው! ብዙውን ነገር አሳልፈውታል። ያኔ ለሁለተኛም ሆነ ለሦስተኛ ብቻ በተገኘ ወደሚል ስሜት ይመጣል። አለፍ ሲልም የማይመጥን ወንድም ቢሆን ችግር የለም ወደሚል ተናዙል ይወረዳል። እነዚያ ከአንድ ገፅ በላይ የሚሆኑ የሚደረደሩ መስፈርቶች ወደ አንድ ሃረግ ይወርዳሉ። 40 ሲገባ አንድ ቃል ብቻ መሆናቸው አልቀረም።

ምን የመሰለ መልክና ቁንጅና፣ ምን የመሰለ ዲንና ጥንካሬ፣ ምን የመሰለ ውብ ቤተሰብና ዘር እያለ፤ ምን የመሰለችዋን ልጅ ጊዜዋን አሳለፉባት። አይበለውና ተስፋ መቁረጥ ከተደረሰ ወደ በቀላሉ ወደ ሐራም ግንኙነቶች፣ አላህ ይጠብቀንና ከካ'ፊ'ርም ጋር ቢሆን መጃጃል ይመጣል።

መፍትሄ፥ ገና ሃይስኩል እያለሽም ይሁን ግቢ ላይ እያለሽ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ የሚሆንሽ የትዳር አጋር ከተገኘ በጊዜ ተሰተሪ። በዚህ ወቅት አማርጠሽ የማግባት ሰፊ እድል አለሽ። ማግባት ትምህርትን አያስቋርጥም። ካገባሽ በኋላ ያስተምርሽ። ካላስተማረሽ ንገሪኝ! ወላጆችም ኋላ ከመጨነቅ በዚህ ወቅት ብዙም ሳታካብዱ በሐላሉ ሰትሯቸው። ኋላ ለናንተም ስቃይና ጭንቀት ነው።

በመጨረሻም፦ ምንም ይሁን ምን፤ ያለነው በጠፊዋ ዓለም በዱንያ ላይ ነውና ለሁሉም ነገር በሐላሉ ሰበብ ማድረስ፣ አላህን መፍራትና እርሱን መለመን፣ ጉዳይን ወደርሱ ማስጠጋትና በርን ዘግቶ ከርሱ ጋር ማንሾካሾክ መረሳት የለበትም። ያኔ አይሆንም ብለን ያሰብነውን ሁሉ አድርጎት እናገኘዋለን። ሆኖም ግን መዳረሻችን አኺራህ ነውና ለሁሉም ነገር ሶብር ማድረግ፣ ለሙእሚን ከዱንያ ይልቅ አኺራህ የተሻለ መኖሪያው መሆኑን ማሰብ፣ ዱንያ ሁሉ ነገሯ ፈተና የሆነች መሆኗን ማወቅ ያስፈልጋል።

አላህ በሪዝቁም ይሁን በትዳር በኩል መልካሙን ይወፍቃችሁ።



ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ሸዋል 13, 1445 H.C.
ሚያዚያ 14, 2016 E.C
አፕሪል 22, 2024 G.C.

||
t.me/MuradTadesse
18.4K viewsedited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 11:00:29 «ዚና ሲቀል → ኒካሕ ይከብዳል »
ወሏሁ-ል-ሙስተዓን!
17.3K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 10:54:55
﴿ثلاثةٌ حقٌّ على اللهِ عونُهم: المجاهِدُ في سَبيلِ اللهِ، والمكاتَبُ الَّذي يريدُ الأداءَ، والنّاكِحُ الَّذي يُريدُ العفافَ﴾
17.3K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 10:39:22 እስኪ ይህን ጽሑፍ አንብቡት፦

«ዛሬ ልጄን ለማሳከም ወደ አንድ ሀኪም ቤት አመራሁኝ ። የላብራቶሪ ውጤት እስኪደርስ ድረስ ዶክተሩ አንድ የማወያይህ ነገር አለ ብሎኝ ቁጭ አልኩኝ ። አንዲህም አለኝ አንድ የሚያሳስበኝ ነገር አለ ይኸውም የሙስሊም ሴት እህቶቻችን ጉዳይ ነው አለኝ ። በመቀጠልም እኔ ከሞያዪ አንፃር በተለያዮ ሀኪም ቤቶች ላይ እሰራለው በየቦታው የሚያጋጥመኝ አንድ ችግር አለ ይኸውም የሴቶች ውርጃ ነው አለኝ ። የተለያዮ ሴቶች ለማስወረድ ይመጣሉ ለምን የሚል ጥያቄ ሳነሳ አብዛኛው መልሳቸው ቤተሰብ አላወቀም የሚል ነው ይህ ማለት ደግሞ ያለ ኒካህ የተረገዘ የዝሙት ልጅ በመሆኑ ነው ። እኛ ጉዳዮ ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን የተቻለንን ምክር እንለግሳቸዋለን ነገር ግን በዚህ ዙሪያ የሚሰጥ ትምህርት አሊሞች ፣ ዱአቶች ዘንድ አናሳ ነው ለምን በዚህ ላይ አትሰሩም ፣ ለምን እህቶቻችንን አታነቁም ፣ …  ወቀሳውን ጠበቅ እያደረገው መጣ ።
  ከመፍቴዎቹ መሀከል አንዱ ሁለት ሶስት አራት ማግባት ነው ስለዚህም የሚሰጥ ትምህርት የለም ቆይ ግን ለምንድን ነው?  እያለ ወላሂ ብዙ ወሳኝ ነጥቦችንና ገጠሞቹን አወራኝ
  በበኩሌ ያለንበት ደካማ ጎኖቹን እያነሳ እያወራኝ ስለነበር እውነት ነው እያልኩኝ ተቀበልኩኝ እላችኃለው ከዚህ በፊትም አንድ ዶክተር ይህን ጉዳይ ቦታውን ሁሉ እየጠቀሰ ነግሮኛል አንዳንዶች እንደውም ይህን ተግባር/ማስወረድን/ ከቢዝነስ አንፃር ብቻ በመመልከት የተለያዮ ክሊኒኮችን በቦታው እንደሚከፍቱ ነግሮኛል
ስለዚህ ወንድሞቼ እንዲሁም ኡስታዞች በዚህ ዙሪያ ለየት ያለ ትኩረት ተሰጥቶት በዚህ ርዕስ ላይ ዘመቻ ቢደረግ መልካም ነው።»
: ኡስታዝ ዳውድ ያሲን
16.1K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 06:04:22
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ

[Part: ⓵⑤⑧③]


#ቁርኣን
16.8K views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 22:27:35
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ

[Part: ⓵⑤⑧②]


#ቁርኣን
17.3K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 22:18:55
ሐቀን!
16.6K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ