Get Mystery Box with random crypto!

እስኪ ይህን ጽሑፍ አንብቡት፦ «ዛሬ ልጄን ለማሳከም ወደ አንድ ሀኪም ቤት አመራሁኝ ። የላብራቶሪ | Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

እስኪ ይህን ጽሑፍ አንብቡት፦

«ዛሬ ልጄን ለማሳከም ወደ አንድ ሀኪም ቤት አመራሁኝ ። የላብራቶሪ ውጤት እስኪደርስ ድረስ ዶክተሩ አንድ የማወያይህ ነገር አለ ብሎኝ ቁጭ አልኩኝ ። አንዲህም አለኝ አንድ የሚያሳስበኝ ነገር አለ ይኸውም የሙስሊም ሴት እህቶቻችን ጉዳይ ነው አለኝ ። በመቀጠልም እኔ ከሞያዪ አንፃር በተለያዮ ሀኪም ቤቶች ላይ እሰራለው በየቦታው የሚያጋጥመኝ አንድ ችግር አለ ይኸውም የሴቶች ውርጃ ነው አለኝ ። የተለያዮ ሴቶች ለማስወረድ ይመጣሉ ለምን የሚል ጥያቄ ሳነሳ አብዛኛው መልሳቸው ቤተሰብ አላወቀም የሚል ነው ይህ ማለት ደግሞ ያለ ኒካህ የተረገዘ የዝሙት ልጅ በመሆኑ ነው ። እኛ ጉዳዮ ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን የተቻለንን ምክር እንለግሳቸዋለን ነገር ግን በዚህ ዙሪያ የሚሰጥ ትምህርት አሊሞች ፣ ዱአቶች ዘንድ አናሳ ነው ለምን በዚህ ላይ አትሰሩም ፣ ለምን እህቶቻችንን አታነቁም ፣ …  ወቀሳውን ጠበቅ እያደረገው መጣ ።
  ከመፍቴዎቹ መሀከል አንዱ ሁለት ሶስት አራት ማግባት ነው ስለዚህም የሚሰጥ ትምህርት የለም ቆይ ግን ለምንድን ነው?  እያለ ወላሂ ብዙ ወሳኝ ነጥቦችንና ገጠሞቹን አወራኝ
  በበኩሌ ያለንበት ደካማ ጎኖቹን እያነሳ እያወራኝ ስለነበር እውነት ነው እያልኩኝ ተቀበልኩኝ እላችኃለው ከዚህ በፊትም አንድ ዶክተር ይህን ጉዳይ ቦታውን ሁሉ እየጠቀሰ ነግሮኛል አንዳንዶች እንደውም ይህን ተግባር/ማስወረድን/ ከቢዝነስ አንፃር ብቻ በመመልከት የተለያዮ ክሊኒኮችን በቦታው እንደሚከፍቱ ነግሮኛል
ስለዚህ ወንድሞቼ እንዲሁም ኡስታዞች በዚህ ዙሪያ ለየት ያለ ትኩረት ተሰጥቶት በዚህ ርዕስ ላይ ዘመቻ ቢደረግ መልካም ነው።»
: ኡስታዝ ዳውድ ያሲን