Get Mystery Box with random crypto!

Meserete Ge'ez

የቴሌግራም ቻናል አርማ meseretegeez — Meserete Ge'ez M
የቴሌግራም ቻናል አርማ meseretegeez — Meserete Ge'ez
የሰርጥ አድራሻ: @meseretegeez
ምድቦች: ቋንቋዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.99K
የሰርጥ መግለጫ

“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅
📜 የሀገራችን ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ ነው። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ።
ለጥያቄና አስተያየት
- @Geez202-
ስልክ ፦ 0977682046

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-11 21:14:51
መዝገበ ቃላት ፍቺ

ከብካብ ➧ሰርግ - (ተጣይ)

ምሳሌ ፦ ልብሰ ከብካብ /የሰርግ ልብስ/ (ተናባቢ)

ሠርግ ➧ መስኖ

#መዝገበቃላት_ፍቺ #ስም
@meseretegeez
1.3K viewsedited  18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 21:29:30 ቃለ ምልልስ


ትሕትና
ሰላምለኪእኅትየ?
ሰላም ላንቺ ይሁን እኅቴ

ሐና
ወሰላምለኪእኅትየ
ሰላም ላንቺም ይሁን እኅቴ

ትሕትና
እስፍንቱሰዓትውእቱናሁ?
አሁን ስንት ሰዓት ነው

ሐና
ናሁሠለስቱሰዓትውእቱ
አሁን ሦስት ሰዓት ነው

ትሕትና
ሠናይእፎሕይወት፡ውእቱ?
ጥሩ። ሕይወት እንዴት ነው

ሐና
እግዚአብሔርይሴባሕጥቀሠናይ ውእቱ
በጣም ጥሩ ነው እግዚአብሔር ይመስገን

ትሕትና
ሠናይ
ጥሩ

ሐና
ግብርእፎውእቱምስሌኪ?
ሥራ እንዴት ነው ከአንቺ ጋር

ትሕትና
ሠናይውእቱ።
መልካም ነው

ሐና
ኦሆእኅትየሠናይመዓልት።
እሺ እኅቴ። መልካም ቀን

ትሕትና
አሜን ለኲልነ።
ለሁላችን ይሁንልን


#ቃለ_ምልልስ
መ ሠ ረ ተግ እ ዝ
@MesereteGeez
1.1K viewsedited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 08:55:13
እንቋዕ አብጽሐነ ለብርሃነ ልደቱ

ሠናይ በዓል

መሠረተ ፡ ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
1.5K views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:02:30
ሰላም ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ፤ እነሆ "ግእዝን በአንድ ወር" በ፬ኛ ዙር የኦንላይን ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለጀማሪዎች ለመስጠት ምዝገባ በመጀመራችን ቦታ ሳይሞላብዎት አሁኑኑ በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን ዕንወቅ።

የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት
የሚሰጥበት መንገድ፦ በቴሌግራም


የመመዝገቢያና ማብራሪያ ቦታ [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link]

+ ሞልተው እንደጨረሱ @MGeez24 በዚህ ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ። ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

መሠረተ ፡ ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
517 views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 16:46:24
በዴንማርክ የነበሩ ጥንታዊ የግዕዝ የጸሎት መጽሐፍት ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ1950-1960 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ይኖሩ ከነበሩ ስውዲናውያን ቤተሰቦች ሁለት ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ የብራና የጽሑፍ ቅርሶች በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ይኖሩ ከነበሩ ስውዲናውያን ቤተሰቦች አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ክርስትል ዌስትላንድ ሃርቡ ባለቤታቸው ከኢትዮጵያ ወደ ዴንማርክ ይዘውት የወጡትን፣ በጽሑፍ አጣጣሉ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ አንድ የግዕዝ መዝሙረ ዳዊት እና አንድ የግዕዝ መልክዓ-ማርያም የግል የጸሎት መጽሐፍ በራሳቸው ተነሣሽነት ለስውዲሽ የወዳጅነት ማኅበር አስረክበዋል።

የስውዲናውያን የወዳጅነት ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑት ኢትዮ-ስውዲናዊው ዶ/ር ቢንያም ወንድሙ ቅርሱን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ለቅርስ ባለሥልጣን አስረክበዋል።

በዕለቱ በቅርሱ መመለስ በየደረጃው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት የእውቅና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

@MesereteGeez
https://www.youtube.com/channel/UCA_P-T7Z1UcP-1kdEKjld-g
1.5K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 11:38:05 አውሥኦተ ቃል (ቃለ ምልልስ)
(Dialougue)

ዜናዊ
እፎ ወአልኪ እኅትየ?
(እንዴት ዋልሽ እኅቴ)

ሠናይት
እግዚአብሔር ይትባረክ ፤ እፎ ወአልከ?
(እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት ዋልክ)

ዜናዊ
እግዚአብሔር ይሰባሕ
(እግዚአብሔር ይመስገን)

ዜናዊ
ዳዊት ሀሎ?
(ዳዊት አለ)

ሠናይት
ናሁ ወጽአ።
(አሁን ወጣ)

ዜናዊ
አይቴ ዘሖረ ይመስለኪ?
(የት የሄደ ይስልሻል)

ሠናይት
ኀበ ቤተ ትምህርት ውእቱ ዘሖረ ።
(ወደ ትምህርት ቤት ነው የሄደው)

ዜናዊ
ሠናይ ፤ እስፍንቱ ሰዓት ይትመየጥ?
(ጥሩ ስንት ሰዓት ይመለሳል)

ሠናይት
በዐሠርቱ ሰዓት ይመጽእ።
(በአሥር ሰዓት ይመጣል)

ዜናዊ
ኦሆ እኅትየ አስከ ይመጽእ እምዝንቱ እነብር
(እሺ እኅቴ እስከሚመጣ ከዚህ እቀመጣለው)

ሠናይት
➾ኦሆ ንበር ዜናዊ ! በጊዜ ውእቱ ዘይበውእ ውስተ ቤቱ ።
(እሺ ተቀመጥ ዜናዊ በጊዜ ነው ቤቱ የሚገባው ፡፡ )

ዜናዊ
ምንት ነሲኦ ውእቱ ዘሖረ?
(ምን ይዞ ነው የሄደው )

ሠናይት
መጽሐፈ

ዜናዊ
ኦሆ እኅትየ እሴብሕ
(እሺ እኅቴ አመሰግናለሁ ፡፡)


መሠረተ፡ግእዝ
295 viewsedited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 15:18:23
ሰላም ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ፤ እነሆ "ግእዝን በአንድ ወር" በ፬ኛ ዙር የኦንላይን ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለጀማሪዎች ለመስጠት ምዝገባ በመጀመራችን ቦታ ሳይሞላብዎት አሁኑኑ በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን ዕንወቅ።

የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት
የሚሰጥበት መንገድ፦ በቴሌግራም


የመመዝገቢያና ማብራሪያ ቦታ [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link]

+ ሞልተው እንደጨረሱ @MGeez24 በዚህ ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ። ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

መሠረተ ፡ ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
1.2K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 18:59:42 የተለያዩ ተቋማት መጠሪያ ስሞችና የሌላ ሀገር ቋንቋ የሆኑ ቃላት ነገር ግን የእኛ የሚመስሉ የተቋማት ስሞች ትክክለኛውን የእኛ የሆነውን የግእዝ ቃል እንመልከት።


College (ኮሌጅ)
መካነ ትምህርት

University (ዩኒቨርስቲ)
መካነ አዕምሮ

Lecture (ሌክቸር)
ትምህርተ ጉባዔ

Lecturer (ሌክተቸረር)
መምህረ ጉባዔ

Dean (ዲን)
• ሊቀ ጉባዔ

Bureau (ቢሮ)
• መሥሪያ ቤት

Bank (ባንክ)
• ቤተ ንዋይ

Civil Service (ሲቪል ሰርቪስ)
• ሰላማዊ አገልግሎት


#ስሞች
- - - መሠረተ ግእዝ - - -
@MesereteGeez
▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣
1.1K viewsedited  15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 08:24:48
ዓርብ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም
አድራሻ ፦ ቦሌ ጃፓን ኢምባሲ ገባ ብሎ /ቀበሌ 20 ሜዳ/

@MesereteGeez
@MesereteGeez
938 viewsedited  05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 21:46:45
ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ  የግእዝ ቋንቋ መምህራንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አወጣ!

ሕዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ )

በሀገረ አሜሪካ ኒው ጀርሲ ግዛት የሚገኘው  ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ  የግእዝ ቋንቋ መምህራንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፋዊና ሀገር አቀፋዊ ጥናት ኢንስቲትዩት በሙሉ ሰዓት እንዲሁም በትርፍ ጊዜ የሚያስተምሩ የግእዝ መምህራንን መቅጠር እንደሚፈልግ በማኅበራዊ ድህረ ገጹ አስነብቧል።

አመልካቾች  የግእዝና የእንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገርን፣ የግእዝ ቋንቋን በዩኒቨርስቲ ደረጃ ማስተማርን ጨምሮ የተለያዩ መስፈርቶችን ያስቀመጠ ሲሆን ሙሉ መረጃውን ከሥር ባለው መስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል።


https://puwebp.princeton.edu/AcadHire/apply/application.xhtml?listingId=28521
1.4K viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ