Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-23 19:52:12 ሴተኛ አዳሪ ነኝ


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል ዘጠኝ▬▬▬ 


ሰከንድ ሰከንድ ላይ ደቂቃ ደቂቃ ላይ ተድርቦ ሰአት ሁለት ሰአት አለፈ እናም በሩ ተከፍቶ ካሽ ከቤ አባቴ እናቴ ቤዛ ተከታትለው እኔ ወዳለውበት መምጣት ጀመሩ። የልብ ምቴ ጨመረ መጀመሪያ አይኔ ውስጥ የገባው አባቴ ነበር። በዚ ጥቂት አመታትውስጥ በጣም ብዙ ለውጥ ይታይበት ነበር ፀጉሩ ሸብቶ ፊቱን ያረጀ ሰው ያስመስለዋል ያ ግርማሞገስ የሞላው ሰውነቱ አሁን ጠፍቶ ሄዷል አባቴን ሳየው  ከየት መጣ ሳልለው እንባዪር ከአይኖቼ መፍሰስ ጀመረ። ከዛም ከባጃጅ ውስት ወጣውና እንደምንም  ሄጄ አባቴ እግር ስር  ተደፋው። እርጉዝ መሆኔን ረስቼው ነበር እግሩ ላይ ወድቄም ማልቀሴን አላቆምኩም ነበር። አባቴም አብሮኝ ማልቀስ ጀመረ ቶሎ ብሎ ከወደኩበት አንስቶ አቀፈኝ ሁላችንም ተላቀስን።
እንኩን ቤተሰብ የሆነ ቆሞ የሚመለከት መንገደኛ  እራሱ ጉዳዩን ሳያቅ ከኛ ያለቅስ ነበር። ከዛ እናቴን ቤዛን የናፍቆቴን አቀፍኳቸው ።
፨ በቃ ለቅሶው በቅቶ ቤት ገብተን እንነጋገር አሉ ጋሽ ከቤ ሊያመልጣቸው የነበረውን እንባ እየሸፈኑ
ከዛም ሁላችንም ወደ ቤት ገባን። ቤቱ በብዙ ነገሮች ተለውጧል በፊት የነበሩ እቃዎች በአዲስ ተተክተዋል ብቻ ሰዉኡ ቤቱ እቃው ከተማው ለኔ አዲስ ሆኑብኝ።
፨ ግቢ የዛሬን አያርገውና የቦረቅሽበት የተጫወትሽበት ቤት ነበር  አለች እናቴ ግራመጋባቴን ተመልክታ።
፨ አንቺ ደሞ ገና ከመምጣቷ የምን ነገር ነው ምታወሪ። አለ አባቴ ከተል አርጎ
ከዛ ሁላችንም ከተቀመጥን ቡሀላ አባቴ ማውራት ጀምረ
፨ ያው ሁላችንም እንደምናውቀው የት ትደርሳለች የተባለችው ልጄ አላማዋን ስታ ቤቷን ለቃ ጠፍታ ይህን ቅድም አቶ ከበደ የነገርንን ስቃይ አሳልፋለች በእውነት ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት ልጄ........... ሲል ያሳለፈችው ሁሉንም ማለት ስራዬንም እንዳይሆን አያረጉትም ጋሽ ከቤማ አይነግሯቸውም እያልኩ ከራሴ ጋር ማውራት ጀምርኩ  ከዛ ቡሀላ የአባቴን ንግግር ብዙ አልሰማውም ግን ስላሳለፈው ነገር በተደጋጋሚ ሲያወራ እንባዬ ሲወርድ አስታውሳለው በኔ ምክንያት በሽተኛ እንደሆነ ራሱን ለማጥፋት ሁሉ አስቦ እንዳልተሳካለት አወራን እናቴም ቀጠል አርጋ ሰፈር ውስጥ የደረሰባቸውን ውርደት አንገት መድፋት አወራች።
፨ግን ያሁሉ አልፏል አሁን ላይ ሆነን ብንጮህ ብንቆጣ የምንለውጠው ነገር የለም ጣት ሸተተ ብለን እንደማን ቆርጠው ልጅም ተበላሸ ፀባዩ ተለወጠ ብለን ሜዳ ላይ አንጥለውም አለ።
ከዛም ብዙ ካወራን ከተጨዋወትን ቡሀላ በመሀል፨ ውይ ውይ ሞት ይርሳኝ ብለው ተነሱ ካሽ ከቤ
፨ምነው አሊ ሁሉን በህምረት
፨ጨዋታው ደርቶ የልጅ ልጃችሁን ረሳነው
አሉ።  እኔም  ረስቼው ነበር።
ያለውን ነገር እስክናስተካክል ብለን ሚኪን ይዘነው አልመጣንም ነበር ከዛም በቃ እንሂድ ብዬ ተነሳው አብሬ።
፨እንዴ አንቺማ እዚ ሁኚ እኔ ነገ በጠዋት ይዤው መጣለው አሉ።
አባቴም እናቴም እንዳልሄድ ጠየቁኝ እና ቀረው ከዛም።
፨በቃ ልሸኛቸው ብዬ ከካሽ ከቤ ጋር እስከ በር ድረስ ወጣንና እስከዛች ሰአት ሲያስጨንቀኝ የነበረውን ጥያቄ ጠየኳቸው።
ካሼ ቅድም ስለኔ ስራ ሁሉንም ነው የነገሯቸው ማለቴ ሰተኛ አዳሪ እንደሆንኩ አልኳቸው ድምፄን ቀንሼ።
፨ምን ሆነሻል እንዴት እንደዛ አረጋለው እኔቤት ተቀጥራ ነው የምትሰራው ነው ያልኩት አሉኝ።
ኡፍፍፍፍፍ አሁን ተረጋጋው።እሳቸውን እስከ በር ሸኝቼ ብዙ አመት ወደተለየውት ቤት ተመለስኩ ወደ ቤተሰቤ ከዛም ቤዚ ነይ እስቴ እኔ እናንቺ ደሞ እናውራ ብላኝ ወደ መኝታቤት ወሰደችኝ.......

አሁን ላይ ሆኜ ትናንትን መውቀስ አልፈልግም ምክንያቱም ያኔም ልክ ነበረኩ ያኔም ደስተኛ ነበርኩ ግን እንደአሁን አይሆንም ደሞ ደስታው የኔ ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ሁሉ ነው።
፨ ወይኔ ቤቲዬ እንደዚ ተለውጠሽ አይሻለው ብዬ አስቤ አላቅም አለችኝ ወደ ድሮ ክፍላችን ይዛኝ እየገባች
፨እኔም እንደዛው አልኳት ክፍሉን እያየው ብዙ ነገሩ ተለውጧል ግን መጀመሪያ አይኔን የሳበው ተደራራቢ አልጋችኝ በሌላ በአንድ አልጋ መተካቱ ነው። ትንድ ቅር አለኝ ይሄን ያሀል ከልባቸው ወጥቼ ነበር አልኩኝ ለራሴ።
፨እና አስኮብላይሽስ የት ገባ ተጣላቹ ወይስ.....
፨ሞተ አልኩኝ ከአፏ ነጥቄ በህመም ምክንያት ሞተ
፨ኦኦኦ በጣም ያሳዝናል  እና ብቻሽን ነው ልጅሽን ያሳደግሽው።እና አዲስ የተረገዘውስ የማን ልጅ ነው አለችኝ
፨ውይ ቤዛ ደሞ እሱ ረጅም ታሪክ ነው ሌላ ቀን እናወራለን ባይሆን ስላንቺ እናውራ ትምርት እንዴት ነው አልኩ ጨዋታ ለመቀየር
፨ካልሽ እሺ። ትምርት ሀሪፍ ነው አዳማ ዩንቨርስቲ ዶክት፨ካልሽ እሺ። ትምርት ሀሪፍ ነው አዳማ ዩንቨርስቲ ዶክትሬት እያጠናው ነው። አሁን ብሬክ ስለሆነነው የመጣውት አለችኝ።
ለሷ ደስ አለኝ እኔ ያንን ትልቅ ውሳኔ ባልወስን ኖሮ አሁን እኔም እንደሷ ነበር የምሆነው እያልኩ ማሰብ ስጀምር
፨ምነው ተከዝሽ ብላ ከሀሳቤ አነቃችኝ
፨አይ አሁን ላይ እኔ ያለውበትንና አንቺ ያለሽበትን እያሰብኩ ነው። ህይወት ግን አይገርምም ዛሬ ላይ እንዲ ይሆናል ብሎ ማን ገመት
፨እሱስ ልክ ነሽ ያኔ አንቺ ጠፋሽ ሲባል ማን ያመነ አለ ትምርት ቤትና ቤት እኛን ለማፅናናት የሚመጣአ ሁሉ ማመን አለመቻሉን ነበር የሚያወራው።
አባባም ራሱን መሆን አቅቶት ሆስፒታል ገብቶ ነበር ። በያንዳዱ ንግግሯ ውስጥ እያነባው ነበር የምሰማው ብዙ ነገሮችን አወራቺኝ እና ቤቲ ከዚ ቡሀላ አባባ ማዘንም ሆነ መደንገጥ የለበትም ይሞታል አሁንም ቢሆን በመድሀኒት ነው ያለው እውነት ለመናገር አንቺ ከሄድሽባት ቀን ጀምሮ ዛሬነው የእውነት ሳቅ ሲስቅ ያየውት እና እባክሽን ድጋሜ እሱን አታሳዝኚብን አለችኝ።
፨እረ ቤዛ ከዚቡሀላማ ያንን ሁሉ ስቃይ ካሳለፍኩ ቡሀላማ እንዴት ያንን ለማረግ አስባለው አልኩ እውነቴን ነው ማነው ወደዛ ችግር መመለስን የሚፈልግ ማነው ከዛ ህይወት ላውጣክ ሲባል መውጣት የማይፈልግ በኔ አስተሳሰብ ማንም የለም ይህን እያሰብኩ ነበር በመሀል እናቴ ቤራችንን አንኳኩታ የገባችው ።
፨ውይ ልጆች የናንተ ወሬ መቼም አያልቅ ኑ አሁን ራት ደርሷል አለችና ትርያይዘን ሳሊን ገባን።

,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

እናም የመጀመርያው የቤተሰብ ምሽቴ ደስ በሚል ሁኔታ አለፈ። በነጋታው ካሽ ከቤ ልጄን ይዘውት መጡ ያለነው የሴምስተሩ አጋማሽ ላይ ስለነበር ደብረዘይት ውስት ለማስመዝገብ ብዙም አልተቸገርንም ትምርትቤቱም እኔ እማርበት የነበረው የድሮ ት.ቤቴ።
ላስመዘግበው ስሄድ የድሮ ፊዚክስ መምህሬን ሚስ የሺን አግኘኋት ስታየኝ በጣም ነበር ደስ ያላር እና ትምርቴን መቀጠል እንዳለብኝ በተደጋጋሚ ስነግረኝ ነበር። እኔግን ያ ሀሳብ ብዙም አይምሮዬ ውስጥ የለም ግን ታድያ ዝም ብዬ የቤተሰብ ሸክምማ አልሆንም ይሄን ልጅ ልውለድ እንጂ አንድ ስራማ መሀመር አለብኝ.....

ይቀጥላል....


✎ ክፍል  አስር ከ 200 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11
28.0K views亗🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 12:15:41 ሳመና ረገጣት


ስራ ጥሎ ወጣ በጣም ተቅለብልቦ
ስለናፈቀችው ሊያገኛት አስቦ

ከዚያም እንዳገኛት
ከንፈሯ እስኪቀለ በከንፈሩ ሳማት
በሁለት ጣቱ ይዞ አሳሯን አሳያት

በመሳሙ ብዛት ቁመቷ አጠረ
ለሱ ያላት ፍቅር እጅጉን ጨመረ
እሱም ይህን ግዜ...

ባፍ የያዘውን ጭስ ወደ ውጭ ብሎ
ሳመና ረገጣት እመሬት ላይ ጥሎ

ስመው ይጥሉሻል ሁሉም በየተራ
.
.
ታሳዝኚኛለሽ ምስኪኗ ሲጋራ


       ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
21.6K views亗🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:49:39 ♡+:。.。 ደስታና ሀዘኔ 。.。:+♡


ደቂቃዎች አልፈው ሰሀታቶች ሄዱ
ልቤ አላቆመም ወደ
#እሷ መሄዱ
የፈገግታዋ ፍካት ሀዘኔን ያርቃል
ልቤ ያንን ለምዶ ሁሌ ይናፍቃታል
ራቡኝ አይኖቿ
#ናፈቀኝ ጠረኗ
ደስታዋን ማየቴ ሲያየኝ ያ
#አይኗ
እሷን የማይበት ጊዜው ቢሆንም ገና
#እጠብቅሻለው ለኔም ቀን አለና

       ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
22.4K views 𝙿𝙾𝙿 𝙼𝚄𝙱𝙰❦, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:46:38 በርግጥ ናፍቀኸኛል
..............................

ግን ግን አንተን ማግኘት ማለት፡
በጠራራ ፀሀይ እሳት እንደማንደድ፡
ከሙሽሮች መሀል ሙሾ እንደመውረድ።

እየሄድኩ በመታኝ እንቅፋት መደገም፡
ከመስጊድ ደጃፍ ላይ አማትቦ መሳለም።

የኔ መንገድ ካንተ  እንዲህ  ነው ተቃርኖ፡
በናፍቆት መዳፍ ላይ  መኖር ንፋስ ዘግኖ።

       ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
21.1K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:27:29 ለአንቺ ያለኝ ስሜት በቀናቶች ልዩነት አይቀንስም በነገሮች መለዋወጥ አይቀየርም ::
#ሁሌም በማይቀንስ ፍቅር አፈቃቅርሻለው።

   ፈ
      ቅ
         ር
            ሻ
               ለ
                  ሁ ሌ ም
* የልቤ ንግስት *
* የኔ ልዩ ስጦታ
* የኔ ዉድ ሚስት *
* የኔ የፍቅር *
* የኔ አዝግ
* የደስታዬ ምንጭ *
* የመኖሬ ትርጉም *
* የፈጣሪዬ ስጦታ *
* የአምላኬ ማመስገኛ *

       ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
21.6K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 21:47:55 ሴተኛ አዳሪ ነኝ


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል ስምንት▬▬▬       

ዶክተሩ ከመረመረው ቡሀላ ውጤቱን ነገረኝ ምን ውጤቱን መርዶዬን እንጂ ሳሚ የኤች አቪ ኤድስ ታማሚ ነው  እናም ብሎ ህመሙ በተጓዳኝ ያመጣበትን ሌሎች በሽታዎች ማውራት ጀመረ  እኔግንመስማት ያቆምቁት የኤች አቪ ኤድስ ሲለኝ ነው ።
፨ ያው አንቺም ባለቤቱ ከሆንሽ መመርመር ያለብሽ ይመስለኛል ያው መዳኒቱን በቶሎ እንድጀምሪ አለኝ እኔም ረጅም ሰአት በዝምታ ከተዋአኩ ቡሃላ ለመመርመር ወሰንኩ ከዛም ሳሚ ወደተኛበት ክፍል ሄድኩ።
ንዴት እልህ ሀዘን ብቻ ሁሉም መጥፎ ስሜቶች ይሰሙኛል ገና ክፍሉ ውስጥ እንደገባው ነበር እሱላይ መጮህ የጀመርኩት
፨ለዚ ነበር  የመጣከው ለሁለተኛ ጊዜ ህይወቴን ልበጠብጥ ምን ልሁን ቆይ አልሞት አልኩክ ድሮም እኔነኝ ጥፋተኛ ልቤን ብቻ የምከተል የማረባ ከንቱ........ሌላም ሌላም አሁን የማላስታውሳቸውን ብዙ ነገር ተናግሬዋለው ይህን ሁሉ ድናገር ዝም ብሎ እያለቀሰ ይሰማኛል።
ትንሽ ንዴቴ በረድ ሲልልኝ አንድ ጥያቄ ጠየኩት ታውቅ ነበር በሽታው እንዳለብካ ታድያ ለምን መጣክ።
፨ ቤቲዬ የምነግርሽን ነገር ማመንም አለማመንም ያንቺ ምርጫ ነው እኔግን ሞት አፋፍ ላይ ቆሜ አልዋሽም።
ያኔ ሻሸመኔ ውስጥ የምሰራው የቀን ስራ ሳይሆን...
፨ታድያ ምንድነው አልኩ በመገረም
፨የቀን ስራ ሳይሆን አለ ደገመና ማለት ስራያ ተርበተበተ ግን እንደምንም አወጣው በቃ ስራዬ ከተለያዩ ሀብታሞች ጋር ማደር ነው ጥሩ ስለሚከፍሉ ለዛ ነው አድሬም አምሽቼም እመጣ የነበረው የምሰራው የቀን ስራ አንቺና ልጄን ማኖር ስለማይችል አንቺም ቤተሰቦችሽ ጋር የለመድሽው እንዳይቀርብሽ ብዬነው። ግን ፀፀት ሁሌም ያሳምመኝ ነበር ለዛ ነው እጠጣ የነበረው።
፨ አሁን እሱን ተውና በሽታው እንዳለብክ ታውቅ ነበር ወይ አልኩ እየጮኩ።
የሚያወራልኝ ታሪክ በጣም ቢያሳዝነኝም ያን ሰአት ግን ማዘኔን ማሳየት አልፈለኩም
፨ በሽታው እንዳለብኝ በምርመራ አላረጋገኝኩም ግን እጠረጥር ነበር አለኝ በመተከዝ አይነት ።
፨ታድያ እየጠረጠርክ ነው እኔን ለመበቀል ያለውበትን ፈልገክ መተክ እንዲ የተጫወትክብኝ
፨ ይህን ለማረግ አልነበረም የመጣውት ግን ባልጠበኩት ሁኔታ ይቅር አልሽኝ እንደድሮ ቀረብሽኝ ቤቲ እኔ እኮ አፈቅርሻለው በቃ እንደዛ ስትሆኚ ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ ደሞ ያንቀን አብረን ማደራችንን እኔም አላውቅም ነበር አጋጣሚ ነው አለና ዝም አለ።
በጭቅጭቃችን መሀል ውጤቴ መድረሱን አንዲት ነርስ ነገረችቺኝ እና ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄድኩ።
፨ እሺ ዶክተር ውጤቴ ምን ሆነ አልኩት ለውጥ ያለ መስሎኝ  በተስፋ
፨ አዝናለው ቤቲ ፖዘቲፍ ነሽ አለና መርዶዬን ነገረኝ ነገርግን አለ ቀጠል አርጎ ደስ የሚል ዜና አለኝ የሶስት ወር ነብሰጡር ነሽ ብሎ ለሱ ደስታ የመሰለውን ለኔ ደሞ የሀዘን ሀዘን ሀዘን የሆነ ውን ትልቅ መርዶ ነገረኝ በጣም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ ግን ማረግ የምችለው ነገር አልነበረኝም።
፨ ቤተልሄም መደንገጥ የለብሽም በሽታው እኮ መድሀኒቱን እየተከታተልሽ ከወሰድሽ ራስሽን በሰንብ መጠበቅ ከቻልሽ ብዙም አይጎዳሽም........... ዶክተሩ ያወራል እኔግን እሱን የማዳምጥበት ምንም ጆሮ አልነበረኝም ጭንቀት ብቻ።

ቀናት ቀናትን ሳምንታት ሳምንታትን ወራት ወራትን እየወለዱ ያ ክስተት ከተፈፀመ ዛሬ አራተኛ ወር ተቆጠረ አራት ከባድ እና አስከፊ ወራትን አሳለፍኩ አሁን የርግዝና ስድስተኛ ወሬ ገባ።
የመጀመሪያውን ጥቂት ሳምንታት ወደስራ መመለስ ከብዶኝ ነበር ሳሚን ማስታመምና የራሴን ቁስል ማከም በጣም ይከብድ ነበር ነገር ግን ሳሚ ብዙም አልቆየም ከወር ቡሀላ አረፈ  ብቻዬን ቀበርኩት በሰው ሀገር ብቻዬን ሀዘን ተቀመጥኩ። እሱ ካረፈ ቡሀላ ልጄን እና እኔን ማኖር ስለነበረብኝ ወደ ስራ ተመለስኩ ቢሆንም እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ ግን መስራት አልቻልኩም ማንም የሚፈልገኝ ስለሌለ መቆም ብቻ ሆነ ስራዬ የሶስት ወር የቤት ክራይ  አልከፈልኩም አሁን አሁንማ የምንበላው እያጣን ነው።
አንድ ቀን ጠዋት አከራዬ በሬን አንኳኩ ፊታቸው ላይ ጥሩ ስሜት አላይም።
ማነሽ ቤተልሄም ላናግርሽ ፈልጋለው ነይ በረንዳው ላይ ጠብቅሻለው ብለውኝ ወጡ ምን ሊሉ ይሆን እያልኩ ፊቴን ታጥቤ ሄድኩ..

፨ተቀመጭ ቤተልሄም ማውራት አለብን አሉኝ ገና እንደደረስኩ
፨ምነው ጋሽ ከቤ ችግር አለ አልኩኝ ለማወቅ ጓጉቼ
፨ ያው ቤቲዬ እንደምታውቂው እኔና ባለቤቴ ጡረታ የወጣን ሰዎች ነን ግን ምስጋና ለልጄ ይግባውና ይህን የመሰለ ቤት ገዝቶ መተዳደሪያ ሰጠን እናም ከዚቤት ከምናገኘው ገንዘብ ነው ምንተዳደረው።
፨ ማለት ጋሼ ወደ ነጥቡ ይግቡልኝ አልኩ መጨረሻውን የማውቀውን ንግግር ከሳቸው ልስማው ብዬ
፨አንቺ ግን ለተከታታይ ወራት ክራይ አልከፈልሽም ወይዘሮ ጥሩ ባለውለታዬ ስለነበሩ ብዬ እስካሁን ታገስኩ አንቺ ግን ሰሞኑን ወደስራ ስቴጂም አላይም ጭራሽ አርግዘሻል ።
፨ እና ቤቱን ልቀቂ እያሉኝ ነው አልኩ ንግግራቸውን ሳላስጨርስ
፨እንደሱ ሳይሆን ወላጆችሽ ጋር ልውሰድሽ ነው የምልሽ
፨ወላጆቼን ያውቋቸዋል እንዴ አልኩኝ ትንሽ ደንግጫለው
፨ማነሽ ቤተልሄም ስላንቺ ሁሉንም ባይሆን በጥቂቱ ወይዘሮ ጥሩ አጫውታኛለች ለዚህም ነው ከነሱጋር ላስታርቅሽና ከዚ አሳዛኝ ህይወት ውጪ ልጄ እኔ አንቺን እንዲ የምጨቀጭቅሽ ከክራይ ለማገኘው ገንዘብ ብዬ ሳይሆን ደስ ብሎሽ እንድትኖሪ ነው አስቢበት ።
ብለውኝ ጥለውን ገቡ። ከባድ ጥያቄ ነበር የጠየቁኝ አሁን ላይ ሁለትችምርጫዎች የኔን የወደፊት እጣፈንታ ይወስናሉ። እንደዛ ያሰቃየሁት አባቴ እንደዛ ያስለቀስኳት እናቴ ጋር መሄድ ወይም ልጆቼ በረሀብ ሲሰቃዩ ምስየት ለኔ ሁለቱም ከባድ ናቸው።
ካሽ ከቤ ይህን ካሉኝ ከሳምንት ቡሀላ ውሳኔዬን ወሰንኩ ወደ ደብረዘይት መመለስ።

ውሳኔዬን ካሳወኳቸው ቡሀላ ወደ አባቴ ጋር ደወልን ወይኔ ድምፁን ስሰማ ደስ አለኝ ካሽ ከቤም በአሪፍ ሁኔታ ካናገሯቸው ቡሀላ ለእሁድ ቀጠሮ ያዙ አባቴ የኔን ስም ሲሰማ የደነገጠው ድንጋጤ ከድምፁ ውስጥ ያስታውቅ ነበር። የማይደርስ ቀን የለምና እሁድ ደርሶ ጉዞ ወደ ደብረዘይት አረግን።
ደብረዘይት እንደተለመደው እጇን ከፍታ ነበር የተቀበለችኝ ሁሌም መግቢያዋ ላይ የሚታዩት ችግኞቿ ከብዙ መታወቂያዎቿ ውስጥ አንዱ ነው በዚ ስድስት አመት ውስጥ ብዙ ነገሯ ተለውጧል። ትቻቸው የሄድኩት ጅምር ፎቆቿ አልቀዋል የህዝብ ቁጥሩና ግርግሩም እንዲሁ ጨምሯል ደብረዘይት ከገባን ጊዜ ጀምሮ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው። መንሀሪያ አካባቢ ወርደን እዛው አካባቢ የሚገኝ ምግብቤት ምሳ በልተን ትንሽ አረፍ ካልን ቡሀላ ካሽ ከቤ አንድ ጥሩ ሀሳብ አመጡ፨ለምን እኔ መጀመሪያ ሄጄ አላናግራቸውም አሉኝ
ለኔም ጭንቀቴን ስለሚያቀልልኝ ተቀበልኩት ከዛ በባጃጅ አብረን ሄደን አሳየዋቸውና እኔ ማንም እንዳያየኝ ባጃጅ ውስጥ ተደበኩ ግን የሚከናወነው ነገር ከርቀት ይታየኛል።
በሩን የከፈተችው ቤዛ ነበረች ወይኔ እሷን ሳይ እንዴት ደስ እንዳለኝ ደሞ አድጋለች ትንሽ በር ላይ ካወሩ ቡሀላ ወደውስጥ ገቡ አሁን በሩ ተዘግቷል።
ምን ዜና ይዘው ይመጡልኝ ይሆን ጨነቀኝ ተነሽና ገቢ የሚል ሀሳብ ጭንቅላቴን ወረረው ግን አልቻልኩም። ሰከንድ ሰከንድ ላይ ደቂቃ ደቂቃ ላይ ተድርቦ ሰአት ሁለት ሰአት አለፈ

✎ ክፍል  ዘጠኝ ይቀጥላ
24.5K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 20:44:29 ተጣልተን ሰነበትን ከናፈቀኝ ቆየው
ቀናትም አለፋ አይንህን ሳላያው
እወነት ወድካለው አፌ ነው ቃላባይ
ንገረኝ በሞቴ ጨክነህ ቀረህ ወይ?


      ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
21.4K views 𝙿𝙾𝙿 𝙼𝚄𝙱𝙰❦, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 09:51:43 ያቺ ልጅ ያቺ ደስተኛ የምታደርገኝ ልጅ ናፈቀችኝ
የሆነች ልጅ ሳቂታዋ አኩራፊ ቁምነገረኛ ቀበጧ
ከሁሉም ሴቶች ልዩ የሆነችው ሁሌ የማስባት ልጅ ናፈቀችኝ በጣም ናፈቀችኝ


የእውነት የሌለ

      ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
22.7K views 𝙿𝙾𝙿 𝙼𝚄𝙱𝙰❦, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 18:05:18 ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿» ‌✽‌┉┉┄┄        
                  " ያፍቃሪው ጸሎት"
  ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿» ‌✽‌┉┉┄┄    

ጧፌን ይዤ የጸለይኩት
ለፈጣሪ ያማከርኩት
....የነገርኩት....
      የኔ ጸጸሎት
እሱአን ፍቅሬን ቤት አሳጣት
ጎጆ ስታጣ ወደኔ ነው የምትመጣው
.....  አልዋሽሽም........
እንዲህ ብየ አማላጅዋን ለምኛለሁ
ከጠየከኝ ሌላም ሌላም ጸልያለሁ
አይን አሳጣት ብርሀን ንሳት
እኔን አይታለች አይን ሲኖራት
... ደግሞ ሌላ እንዳያምራት
ከልቤ ነው ስመኝልሽ
ጆሮ ንሳት ያልኩልሸ
እሄንንም ተስያለሁ
እውነት እውነት እልሻለሁ
ከኔ ሌላ እንዳትሰሚ
ማንም መቶ
ስለ ፍቅሬ እንዳያማ
አስቤ ነው ይሄን ስለው
ከጠየክሽኝ ሌላም ብዙ ብየዋለሁ
   ሙች ሙች ስልሽ
ተንበርክኬ ተማጽኜ ለምኛለሁ
   ...  ግና.....
ልብ ከነሳሽ እንዳትረሽኝ ስለፈራሁ
   .........................   ስለሰጋሁ
ልቧን ስጣት ብየ
እንዳይቀማሽ አልቅሻለሁ
አኔ ላንቺ ፀልያለሁ
..... ምክንያቱም....
ከዚያም በላይ ወድሻለው
 
  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
558 views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 21:38:07 የተያዘ ለታ

አይ ሰው ከንቱ፣
መስራት ሲችል ማማቱ፣
መውደድ ሲችል መጥላቱ።
     ሰው ተገዶ፣
      እሱ ማንን ወዶ፣
        ገባላት ተራምዶ።
ማፍቀሩ ደግ ሆኖ፣
መች ይሄን አምኖ።
       እየቀባጠረ፣
        ፍቅሩን አማረረ።
መቼ ደግ ሆነና፣
ገባ ከጋቢና፣
እራሱን ሊያዝናና።
     እሷን ትቶ ሌላ፣
      መርጦ ሌላ ገላ፣
      መች መታና መላ።
አቤት እዳው በዛ፣
ያ አዳም ፈዛዛ።
      ወይ ለ እሷ አልሆነ፣
       እሷ መች አመነ፣
      ወይ ለነፍሱ አላዘነ።
ዝም ብሎ ይዘላል፣
ይነሳል ይፈርጣል።
      ለነፍሱ  መች ፈርቶ፣
       ሄዋንን ከድቶ።
አንዷን ቀርቦ፣
ሌላዋን ተርቦ።
      እዳውን ያበዛል ፣
      መች በቃኝ ይላል።
አቤት አቤት፣
የላኛው ፍርድ ቤት።
       የተያዘ ለታ ፣
    አውጣኝ  የኔ ጌታ።

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
4.7K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ