Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-26 07:37:40 አንተ ምን አረከኝ?
~~~

ለቅፅበታት  ራሴን  ሆኜ ፣
ልረሳህ እልና ልቤን አጀግኜ፣
ወላዋይዋን ነፍሴን ላንዳፍታ ለምኜ፣
#የሌላ መሆንህን ውስጤን አሳምኜ
.
ልተውህ እልና አይኔን ረግሜ
ውብ ሳቅህን እንዳላይ ደግሜ
እንድረሳህ  ብዬ  ካንጀቴ  እጥራለሁ
ካይንህ #ተደብቄ ቀናት ቆጥራለሁ

ሞክራለሁ እንጂ መች ረሳሀለሁ
.
በወሬዬ  መሀል  ሁሌ  አነሳሀለሁ

አየህ
ያንን  ሁሉ  ጊዜ  ላመታት  ስርቅህ
#በይመጣል  ተስፋ ሁሌ ምጠብቅህ

የሚባክንልህ  ልቤ  ሚስኪኑ፤
ልክ እንደ ድራማ ሁሌ በየቀኑ፤
አንተን  እያሳየ  እኔን  ያከሰረኝ፤
እንዳልተውህ አርጎ አጥብቆ ያሰረኝ፤

የመልክህ ሰአሊ ለመላ አካላቴ
አንተ ምን አረከኝ ህልሜ ነው ጠላቴ።

ሼር  @melkam_lboch11

#ሼርር አደራ
2.9K viewsERMI , 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 21:18:31 ምን ሰርቼ እንደደከመኝ
ለማን ሰጥቼው ልቤ እንደተሰበረ
ምን ግዜ ኖሬ ትዝታ እንደተረፈኝ
..............አላቅም
ብቻ ግን ይደክመኛል
ብቻ ግን አዝናለው
ብቻ ግን እቆዝማለው።

share
@Melkam_lboch11
8.9K views▂▃▄▅▆▇█▓▒░𝙱𝚒𝚗𝚒𝚊𝚖░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 21:00:31 ‍ ‍‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል ሀያ▬▬▬         

#የመጨረሻው_ክፍል
ከተጓዘበት አለም የመለሰችዉ ኤዲ ናት፡፡
..."ምን ሆንክ የኔ ፍቅር?" አለችዉ፡፡ 'የኔ ፍቅር' የምትለዋን ብቻ ነዉ የሰማት
..."ወዬ ኤዲዬ" አላት እንደመደንገጥ እያለ... "እ..." ፡፡ እሷም ጥያቄዋን እንዳልሰማት ስላወቀች
..."ምን ሆነክብኝ ነዉ እንደዚህ የምታስበዉ?" አለችና ጥያቄዋን ደገመችለት፡፡ እንዳለፈዉ ጊዜ ሊደብቃት አልፈለገም፡፡ ሁሉንም ነገር ከኤዲ ጋር ተነጋግሮ መወሰን እንዳለበት አምኗል፡፡
..."ምን... የረድኤት ጉዳይ ትንሽ አሳስቦኝ ነዉ" አላት ፈራ ተባ እያለ
..."የረዲ ጉዳይ ምን? የሷ ጉዳይ ምን ያስጨንቀሃል?" ብላ እየጠየቀችዉ ወደሱ ቀረብ
አለችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡
..."ኤዲዬ ... አሁን እንዴት ብዬ ነዉ መጋባት እንደማንችል የምነግራት?" አላት፡፡
..."የኔ ፍቅር ረዲንማ ማግባት አለብህ" አለችዉ፡፡
..."ለልጅ ብዬ አልነበር የማገባት ያዉ አሁን ደግሞ ዉዷ ሚስቴ በሆዷ ያብራኬን ክፋይ ይዛልኛለች!"
."አየህ ውዴ...(በትኩረት እየተመለከተችዉ ነበር) መጀመሪያም ተሳስተን እንደነበር አሁን
ነዉ የገባኝ" አለችዉ፡፡
..."እንዴት ዉዴ? ምንድን ነዉ የተሳሳትነዉ?" አላት
እሱም ወደሷ ዞወር እያለ፡፡ ኤዲ ደግሞ
ይበልጥ ወደሱ እየተጠጋች እጆቿን ትከሻዉ ላይ ጣል እያረገች...
..."መጀመሪያም እሄን ያህል ዓመት ታግሰን በችኮላ መወሰን አልነበረብንም ትንሽ መታገስ ነበረብን" አለችው፡፡
...መጥፎ እንዳልሆንክ አዉቃለሁ፤ ስለ ጥሩነትህ
የማወራልህ፤ ስለ መልካምነትህ የምመሰክርልህ ሚስትህ ነኝ ስለዚህ ረዲን አግባት!!!!
እሺ ፍቅሬ....!!!" አለችዉ፡፡ በቃ የኔ ፍቅር ሁሉንም ነገር ነገ እናወራለን ብሏት ዛሬ የደስታችን ቀን ናት በቃ አሁን እንተኛ አላትና ተኙ፡፡

..." ረድኤት እንቅልፍ እንቢ ብሏት ስትገላበጥ ተነስታ ቁጭ ስትል ምንም እንቅልፍ በዓይኗ ሳይዞር ሊነጋ ነው፡፡ሊነጋጋ አከባቢ አንድ ነገር አሰበች፡፡ለምን?የሰው ትዳር ውስጥ ገብቼ ፍቅራቸውን ለምን?አቀዘቅዘዋለው ግን ለምን?ለኔ ያለውን ፈጣሪ ልክ እንደ ቢኒ ዓይነት አፍቃሪ እንዲሰጠኝ መለመን ስችል፡፡  እያለች ብዙ አሰበች መንጋቱ አይቀርምና ነጋ ልክ እንደነጋ ብዙም ሳትቆይ ረድኤት ለቢኒያም ደወለች፡፡ ስልኩን አንስቶ ረድኤትን ማዋራት ጀመረ
..."ሄሎ ረዲ...."
..."ቢኒ ሰላም ነው"አለችው፡፡
..."ደህና ነኝ..."ማታ እኔና ፈቲ ስላንቺ" ብሎ ሳይጨርስ" ረዲ... "ሄውልህ ቢኒ ምንም እንኳን ባንተ ፍቅር ብከንፍም ግን ያ እንደዛ ምትሳሱለትን የሞቀ ፍቅር በመሃላችሁ ገብቼ ማቀዝቀዝ በጭራሽ አልፈልግም እኔ ባንተና በኤዲ ፍቅር በጣም ነው የምቀናው ባይሆን ለኔም እንዳንተ አይነት ባል ፈጣሪ እንዲሰጠኝ ለምኑልኝ"አለችው፡፡
..."ረዲ ምንም ሆነሻል ቤቲስ እነ እማማ ና አባባስ ምን ይሉኛል፡፡አላት
..."አይ ቢኒ አታስብ ለእማዬም ለአባዬም እኔ አስረዳቸዋለው እዚህ ጊቢ ውስጥ ከአንዱ ጋር ፍቅር ይዞኛል ብዬ እነግራቸዋለው፡፡
ደሞ እነሱም የሚፈልጉት እሄንኑ ነው በጣም ነው ደስ ሚላቸው አታስብ አለችውና ኤዲን ሰላም በልልኝ ብላ ስልኩ ዘጋችው። ቀናት በቀናት ወራት በወራት እየተተኩ የኤዲ መውለጃ ጊዜም ደረሰ ኤዲም ቆንጂዬ በጣም የሚያምር ልጅ ወለደች<< በፀሎት>> አለው ስሙን ቢኒ። ቢኒና ኤዲ በጣም ደስተኞች ናቸው።


ከ 4 አመት ቡኃላ...


...ረድኤት ተመርቃ ምን የመሰለ ለአይን እንኳን የሚያሳሳ ባል አግብታ በፍቅር ኑሮዋን ጀምራለች።
  ፈጣሪ ሁሌም ከምትወዱት አይለያቹ።
                   
                    ተፈፀመ
ምኞትቴ የተሰኘው የፍቅር ታሪክ ዛሬ በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ለሰጣችሁኝ አስተያየት ከልብ አመሰግናለሁ ።


          ተ ፈ ፀ መ

ታሪኩን እንደወደዳችሁት እና እንደ ተማራችሁበት እምነታችን ነው።
በቅርቡ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን አሳብ አስተያየት ማድረስ ትችላላችሁ እናመሰግናለን።
8.8K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 21:41:38 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ዘጠኝ▬▬▬


አለቻት እሺ እደውልልሻለው ኤዲዬ ደህና ሁኝ ብላ ረዲ ስልኩን ዘጋችው።

...ቢኒያም ከስራ መጥቶ ወደ ቤቱ ሲገባ ኤዲ ቤት የለችም፡፡ "ኤዲ...ኤዲዬ!" እያለ ተጣራ
ምናልባት ወደ ጓዳ ዉስጥ እንደሆነች ብሎ ኤዲ ግን የለችም ነበር፡፡ ወደ ዉጭ ወጣና
እማማ በለጡን ተጣራና...
..."ኤዲ የት ሄዳ ነዉ?" አላቸዉ፡፡  እማማ በለጡም
..."እ...ሐኪም ቤት ሄዳ ነዉ፡፡" አሉት፡፡ ቢኒ ድንግጥ አለ፡፡
..."መቼ? ምን ሆና? ምን አገኛት? እና አትከተሏትም ነበር ወይም አደዉሉልኝ?" እያለ ጥያቄ
በጥያቄ ላይ እየደራረበ እማማ በለጡን የጠየቃቸዉን ጥያቄ የመመለሻ አፍታ አሳጣቸዉ፡፡
ይሄን ከማለቱ ወዲያዉ የግቢዉ በር ተከፈተና ኤዲ መጣች፡፡ በጣም አምሮባት፤ ከደስታ
ብዛት ፊቷ ላይ ፀሐይ የወጣች እስኪመስል ድረስ አብርታለች፡፡ በረዶ የሚመስሉት ነጫጭ
ጥርሶቿ ይፍለቀለቃሉ፡፡ ቢኒያም እንዳያት በጣም ደስ አለዉ፡፡ አሟት ነበር የመሰለዉ እሷ
ግን እንደጨረቃ ፈክታ፤ ከፀሐይ አብርታ ብቅ አለች፡፡ ገና የነጋ መሰለዉ፡፡ ለሱ ንጋቱ ኤዲ ነች፡፡ ያለ ኤዲ ሁሌም ጨለማ ነዉ የሚሆንበት፡፡ ወደነሱ ቀረበችና..."ቢኒ ና ወደ ቤት እንግባ" ብላዉ እጁን ይዛ ሳበችዉ፡፡ ሰላምታ እንኳን አልሰጠቻቸዉም ነበር፡፡ ደስታ አስክሯታል፡፡ ቢኒም ምንም አልተናገረም ዝም እንዳለ ተከተላት፡፡ እማማ በለጡ ..."ኤዲዬ ደህና መጣሽ?" ፊቷን ሳታዞር ወደ ቤቷ እያመራች "አዎ እማማ" አለቻቸዉ፡፡ ዉስጧ የሆነ ነገር አለ፡፡
ለቢኒያም እስከምትነግረዉ ቸኩላለች፡፡ ቤት ከገቡ ቡኋላ እየተፍለቀለቀች በደንብ ሳቀች፡፡
..."ኤዲዬ ምን ተገኝቶ ነዉ? ሆስፒታል አይደለም እንዴ የሄድሽዉ" አላት ቢኒ
..."አዎ ሆስፒታል ነበር የሄድኩት" አለችዉ
..."ምንሽን አሞሽ ነዉ?"
..."ሆዴን"
..."ወይኔ በፈጣሪ እንዴት አደረገሽ የኔ ፍቅር"  ብሎ እጆቹን ሆዷ ላይ አድርጎ አይን አይኗን
ያያታል፡፡ ኤዲ አሁንም ጥርስ በጥርስ እንደሆነች ናት፡፡ የምትስቀዉ እሱን ላለማስጨነቅ
እንደሆነ አድርጎ ነዉ ያሰበዉ - ቢኒ፡፡
..."የኔ ፍቅር" አለችዉ ድምፅዋን ለስለስ አድርጋ
..."ወዬ የኔ ቆንጆ"
..."የሆነ ነገር ልንገርህ?"
..."አዎ ንገሪኝ ፍቅሬ...ምንድን ነዉ እሱ?" እያለ ይመለከታታል፡፡
..."የ ሶስት ወር እርጉዝ ነኝ!" አለችዉ፡፡ ቢኒ የሰማዉን ማመን አቃተዉ፡፡ አራት አመት
እምቢ ብሏት እንዴት አሁን??
..."እዉነትሽን ነዉ ኤዲዬ? ለማረጋገጥ ያክል ጠየቃት፡፡ ኤዲ ለአዎንታ እራሷን ነቀነቀች፡፡
ቢኒ ምድር ጠበበችዉ፡፡ ኤዲን እቅፍፍፍ አደረጋት፡፡ ሰዉነቷ ላይ ጥምጥም ብሎባት ይስማት ጀመር፤ ግንባሯን...፤ አይኗን...፤ ጉንጯን...፤ አፍንጫዋን...፤ ከንፈሯን...የቀረዉ የለም፡፡ በየመሃሉ እየጮኸ 'ፈጣሪ ሆይ ተመስገን' ይላል።ኤዲም ትፈለቀለቃለች፡፡ ደስታ ቢገድል ኑሮ ከቢኒ ቀድማ ትሞት ነበር፡፡ ከምንም በላይ ያስደሰታት መፀነሷ ሳይሆን ቢኒያም እንደዚህ ሲደሰት ማየቷ ነዉ፡፡ በርግጥ የደስታዉ
ምንጭ ማርገዟ ቢሆንም...፡፡ቢኒ አሁንም እየጮኸ ጌታዉን ማመስገኑን አላቋረጠም፡፡ 'ጌታ ሆይ አመሰግንሀለው' እያለ ላንቃዉ እስኪበጠስ ድረስ ይጮሃል፡፡ እንደገና ቀጥ ብሎ ፈቲን በመሳም
ያጣድፋታል፡፡ ደስታቸዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡...
.
...ኤዲና ቢኒ ከዚያ ሁሉ ፈንጠዝያ ቡኃላ አብረዉ ቁጭ ብለዉ ራት እየበሉ ረዲ ደወለች፡፡
ቢኒም ስልኩን በኤዲ ሊያስነሳዉ አለና ..."ሆ ሆ ነገሩ እናንተ ወሬ ከጀመራችሁ ስለማታበቁ
እኔ ካዋራኃት በኃላ እሰጥሻለሁ" ብሏት ስልኩን አንስቶት ረድኤትን ማወራት ጀመረ፡፡ እያወሩ
እያለ ኤዲ አላስወራም አለችዉ፡፡ በትክክል እንዳያወራ ታጎርሰዋለች፡፡ በመሃል ትስመዋለች
ቅብጥ ቅብጥብጥ አለችበትና ረበሸችዉ፡፡ ቢኒም "ዉይ እንቺ እስኪ አዉሪያት" ብሎ
ስልኩን ሰጣት፡፡
... ኤዲና ረዲ ማዉራት ጀመሩ፡፡
..."ረዲዬ ራት እየበላን ነዉ፡፡ እንብላ አለቻት ኤዲዬ የተባረከ ይሁን ብሉ እሄ ቢኒ ሽሮ እንኳን መስራት አይችልም ስትላት ሁለቱም ተሳሳቁ በተለይ የኤዲ ሳቅ ከስከዛሬዉ ለየት ያለ ነበር፡፡ ፍንድቅድቅ አለች፡፡
..."ደግሞ ለሽሮ ሌላም አስተምረዋለሁ" አለቻት ረዲ ለፈቲ
..."ሌላ ሌላዉንማ እኔ አስተምሬዋለሁ" ብትላት በሳቁ ላይ ቢኒም ተሳትፎ ነበር ከት
ብለዉ ሳቁ፡፡ ሃሃሃሃ ሂሂሂ ኪኪኪኪ ...
..."ሆ" አለች ረዲ ..."ራትሽን የምትበይዉ ምላስ ነዉ እንዴ ወሬ ለቆብሻልሳ"
..."እረ እሱን ተይዉና ...ይልቅ የምወልዳት ልጅ ሴት ከሆነች ያንቺ ሞክሼ ነዉ የማረጋት ረድኤት ...እላታለሁ፤ ወንድ ከሆነ ግን ቢኒ ነው ስም የሚያወጣለት፡፡" ስትላት ረድኤት ደነገጠች፡፡
..."ኤዲዬ አረገዝሽ እንዴ?"
..."ዉይ ረዲዬ በደስታ ብዛትኮ የነገርኩሽ መስሎኝ ነዉ፡፡ አርግዣለሁ፡፡ ዛሬ ሆስፒታል ሂጄ የሶስት ወር እርጉዝ ነሽ አሉኝ" አለቻት፡፡ ረድኤት...


✎ ክፍል ሀያ ከ 150 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
14.6K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 20:06:45 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ስምንት▬▬▬


ለነሱ
ብዙም ቦታ ሳትሰጣቸዉ ቢኒያምን ወደራሷ ሳብ አደረገችዉና...
..."ከነገ ወዲያ ሀሙስ ቀለበት አትሰሩ፡፡" አለችዉ፡፡ ለማሜ ድንገታዊ ጥያቄ ነበር፡፡ ወዲያዉ
መልስ መስጠት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ይሄን ጥያቄ ስትጠይቀዉ የህመሟ ምክንያት የጧቱ
የአባባ ሀብታሙ ወሬ እንደሆነ ገምቷል፡፡ አባባ ሀብታሙን እናትና ልጅ ባንድ ሌሊት
አሳምነዋቸዉ እርሳቸዉም ልጃቸዉ እንዳትጎዳ፤ እንደገና ዩንቨርሲቲም ገብታ እንዳትበላሽ፤
በበፊት ባህሪዋ እንድትቀጥል ሲሉ ለቢኒ ለመዳር ቆርጠዋል፡፡
....ቢኒ ... እማማ በለጡንና ረድኤትን ዞር ብሎ እያፈራረቀ ከተመለከተ ቡኃላ እንደገና ወደ ፈቲ
ዞር ብሎ ሲመለከት፡፡...ሁሉም ተፋጠዋል፡፡ ኤዲ ቢኒን የጠየቀችዉ ጥያቄ ባሏን ብቻ ሳይሆን ረድኤትን ልቧን ቀጥ፤ የእማማ በለጡን አይን ፍጥጥ አድርጓቸዋል፡፡ ኤዲ በድንገት ባሏን ማጣት
አልፈለገችም፡፡ ለዚያም ነዉ ይሄን ጥያቄ እነሱ ፊት ያፈረጠችዉ።ቢኒ ምን እንደሚመልስ ግራገባው፡፡ 'እሺ ቀለበት አናስርም' ብሎ አያስደስታት ረድኤትና
እናቷ አጠገቡ ናቸዉ፡፡ ሊያዋርዳቸዉና ክብራቸዉን ዝቅ እንደማድረግ ሆኖ ተሰማዉ፡፡ 'አይ
አይሆንም ማግባት አለብኝ' እንዳይል ደግሞ ኤዲን ማሳዘንና መጉዳት አልፈለገም፡፡ ዝም
ብሎ በማሳዘን አይነት ስሜት እየተቅለሰለሰ ኤዲን ያያታል፡፡ ኤዲም ታየዋለች፡፡ እነሱም (ረድኤትና እማማ በለጡ) ያዩታል፡፡ ሁሉም ይተያያሉ፡፡ ቢኒ ምን ይመልስ፡፡ ዉድ ሚስቱ ኤዲ እንደተጨነቀ ስለተረዳች አይኑን በተመስጦ እያየች...
..."የኔ ፍቅር እኔ'ኮ አታግባት አላልኩህም (ዘወር ብላ እናትና ልጅንም አየቻቸዉ እንደገና ቢኒን እየተመለከተች) ቢኒ ... ታገባታለህ፡፡ ረድኤት ትወድሃለች፡፡ አንተም እንደዚያዉ በተለይ ደግሞ ልጅ መዉለድ አለብህ፡፡ እኔ ልሰጥህ ያልቻልኩትን ነገር እሷ ትሰጣሃለች፡፡ስለዚህ ትጋባላችሁ፡፡ ግን ትንሽ አቆዩት እባክ" ብላ ረድኤትንም በተማፅኖ ተመለከተቻት፡፡
..."እሺ ኤዲዬ እናቆየዋለን" አለና ቢኒ ወደ ረድኤት  ዘወር ብሎ ..."መቼ ነዉ ግቢ የምትገቢዉ
ረዲ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ የረድኤት መልስ አጭር ነበር "እሁድ" ብላዉ በረዥሙ ተነፈሰች፡፡
እህህህ አተነፋፈሷ ለሁሉም ይሰማ ነበር፡፡ ቢኒያምም ወደ እማማ በለጡ ዘወር አለና....
..."እማማ ረዲ ወደ ትምህርቷ ትሂድና ለእረፍት ስትመጣ ቀለበት እናስራለን፡፡ እስከዚያ
ኤዲም ትረጋጋ" አላቸዉ፡፡ከረጅም ፀጥታ በኃላ ቢኒያም ወደ ረድኤት ዘወር አለና
..."አይሻልም ረዲ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ረድኤትም በአዎንታ ራሷን ወደ ታችና ወደ ላይ
ነቀነቀች፡፡ እማማ በለጡ ቀጠል አደረጉና
"መቼ ይሆን እረፍትሽ?" ብለዉ ረድኤትን አተኩረዉ እያይዋት ጠየቋት
..."የካቲት ዉስጥ ነዉ የሚሆነዉ" አለቻቸዉ፡፡
..."የዛሬ አምስት ወር መሆኑ ነዉ?" አሉ እማማ፡፡
ኤዲ ይሄን ስሰማ የአምስት ወር ጊዜ
መሰጠቷ አስደስቷት ከሌሎቹ ቀደም ብላ
..."አዎ እማማ" አለቻቸዉ፡፡
በዚሁ ተስማሙና የካቲት ላይ የዛሬ አምስት ወር ቢኒ ለረድኤት ቀለበት እንደሚያስርላት ተወሰነ፡፡
....ከሶስት ወር ቡሃላ...

      ...ቢኒና ኤዲ አብረዉ በደስታ እየኖሩ ነዉ፡፡ ቢኒ ከረድኤትም ጋር አላቆሙም ይደዋወላሉ፡፡
ረድኤት ስትደዉል ቢኒን ብቻ ሳይሆን ኤዲንም ታዋራታለች፡፡ ሲያወሩና ሲጫወቱ በአንድ
ወንድ ላይ የሚሻሙ ተቀናቃኞች ሳይሆኑ ምርጥ ጓደኛሞች ይመስላሉ፡፡ ይጫወታሉ፤
ይቀላለዳሉ፡፡ ረድኤት ከቢኒ ይልቅ ኤዲ ጋር ለረጅም ሰዓት ታወራለች፡፡ እንደዉም አንዴ
እየቀለደች ቁም ነገር አስመስላ..."ኤዲዬ የወደፊት ባሌን ተንከባከቢልኝ እሺ!" አለቻት፡፡
ሁለቱም ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓታት ተሳሳቁ፡፡ ሂሂሂሂ...ክክክ....እሺ እንከባከብልሻለው በይ እንግዲህ በርትተሽ ተማሪ።አለቻት እሺ እደውልልሻለው ኤዲዬ ደህና ሁኝ ብላ ረዲ ስልኩን ዘጋችው።

✎ ክፍል አስራ ዘጠኝ ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
16.4K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 15:01:40
የኢድ-አልፈጥር በዓሉን ምክንያት በማድረግ አሁን online ላላችሁ ጥያቄና መልስ ልንጀምር ነው

ለወጣ 500 ብር ካርድ
ለወጣ  250 ብር ካርድ
ለወጣ  100 ብር ካርድ

ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
585 views Ɯ♬⩔៩ ƙɨ⩎❡ , 12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:54:55
TiKToK Ethiopia
በአጭር ጊዜ ተከፍቶ ብዙ ሰዎች የተቀላቀሉት የታዋቂ አርቲስቶች አዝናኝ የTiktok ቪዲዮችን በቴሌግራም በየቀኑ የሚለቀቅበት ቻናል ይቀላቀሉት እመኑኝ ይወዱታል።
ከስር ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5
590 views Ɯ♬⩔៩ ƙɨ⩎❡ , 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:54:53
Free ተለቋል።
ቤቲንግ ለጠመመባቹ ብቻ።

ከኛ ጋር የማይቻል ይቻላል
ድንቅ አዲስ ቻናል፣ ምን ትጠብቃላቹ፣ ተቀላቀሉ እና የድሉ ተካፋይ ሁኑ
2.4K viewsYehuans, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:51:27
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል

@melkam_lboch11
@melkam_lboch11
3.1K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:41:02 የቀድሞው የዙንባቤ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የቀለዳቸውን አዝናኝ አስተማሪ እና ቁም ነገር አዘል ቀልዶች ለማግኘት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ

እኔ በበኩሌ በጣም ያዝናናናኛል ጋብዣችኋለው
884 views₩ith £lia$§ , 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ