Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 70

2022-08-27 21:45:33 ​​​ ....

ፍቅር እውነት ካልሆነ እውነት በራሱ እውነት አይደለም።
በተግባር ያልተገለፀ ፍቅር ልብ_ወለድ
ነው።
ብዙ ፍቅር ባለበት ቦታ ስሕተት ሊኖር ይችላል።
ፍቅር ከሌለበት ቦታ ግን ሁሉም ስሕተት ነው።
የፍቅር ምሽት ይሁንለ
ላችሁ

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ሼር
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@Melkam_lboch11
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
9.1K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:06:05 አንቺን ለመሳም የመጨረሻው
እስከሆንኩ ድረስ መጀመሪያ ማንም
ቢስምሽ ግድ የለኝም።

ከልባቸው ሚያፈቅሩ ቶሎ አያረጁም።

ምን አልባት አንድ ቀን ምን ያክል
አፈቅርሽ እንደነበር ትረጅ ይሆናል
ታዲያ አንቺም ተፀፅተሽ ልታፈቅሪኝ
ትሞክሪ ይሆናል ያኔ ግን አንቺን
እየጠበኩ ላይሆን ይችላል

ከልብሽ የሚወድሽ ሰው
አይጎዳሽም።ም/ክ ከጎዳሽ ጉዳትሽ
አይኖችሽ ውስጥ ይመለከታልና።ይህ
ደሞ እሱንም ይጎዳዋል።

ላንቺ ሁሉንም ነገርሽ ለሆነ ለሱ ግን
ምንም እንዳልሆንሽ ከተረዳሽው ጎን
መቀመጥ በእርግጥ ያማል

ያገኘሀትን ሴት በቀላሉ እንዳገኘሀት
ከማሰብ ይልቅ በፍቅር ልትይዛት
ይገባል ም/ክ ድንጋይ ስትሰበስብ
እንቁህን ልታጣ ትችላለህና።

#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
12.4K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:04:18 አታውቂም!
ከጠረንሽ ጋራ ፣ ሱባኤ እንደገባሁ፤
አታውቂም!
“ወንድ አይደለም እንዴ”
እስከሚሉኝ ድረስ ፣ ቁጭ ብዬ አንዳነባሁ፡፡
አታውቂም!
ባገኘሁት ዘፈን ፣ ሆድ እንደሚብሰኝ፤
አታወቂም!
ስላንቺ ለማሰብ ፣ ዘመን እንደሚያንሰኝ፡፡
አታውቂም!
ከለበስሽው ጋራ ፣ መቀመጥ ማምሸቴን፤
አታውቂም!
እኩያ እስከማጣ ፣ ብቻዬን መቅረቴን፡፡
አታውቂም!
አታውቂም!
ብታውቂም አትመጪም፤
አትመጪም ፤ አታውቂም፤
ምን ብዬ ልጸልይ ፣ ከሕይወት ይዤ ቂም፡፡

❥❥__⚘_❥❥

#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
12.6K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:22:40 ​​​​❝አንዳንዶች የምናፈቅረዉን ሰው መጠበቅ በጣም ያማል ይላሉ አንዳንዶቹ ደግሞ የምናፈቅረዉን ሰው መርሳት በጣም ያማል ይላሉ።ግን የእዉነት የከፋው ህመም የምናፈቅረዉን ሰው መጠበቅ ወይም መርሳት እንዳለብን አለማወቅ ነው።❞

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!

#ሼር
‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
13.0K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:18:20 አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@Melkam_lboch11
13.9K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:32:37 #ብቻዬን_ላፍቅርሽ

ባልኖረ ሌላ አዳም ከምድር በጠፋ፣
የኔ ብቻ እንድትሆኝ ቢደላም ቢከፋ፣

በሰፊው አለም ላይ ለጥ ባለው ምድር፣
ምናለ አምላክ ፈቅዶ ብቻችንን ብንቀር፣
ሌላ አዳሞች ቀርተው ብቻዬን ባፈቅር፣
መሬት ባዶ ትሁን ማንም አይኑርባት ከኔና አንቺ በቀር፣

ሆንሽና ስስቴ የነፍሴ ጥም አርኪ፣
ቀኔን ምታበሪ ዘወትር ስትስቂ፣

እንዳትሆኝ የሌላ ልቤ ስለፈራ፣
አዳሞችን ጠላው ስላንቺ ስራራ፣

ብቻዬን ላፍቅርሽ ማንም ሳይጋራኝ፣
ከሄዋኔ በቀር አዳም አያሳየኝ፣

አደለም በውን ተኝቼ በህልሜ፣
ከሌላ አዳም ባይሽ ይብሳል ህመሜ፣
አልድነውም እንኳ በቅጡ ታክሜ፣

አዳሞች ራቁ ሽሹ ከኔ ሄዋን፣
ደርሶ የነካትን አልምረውም ነፍሱን፣

ድርድር አላውቅም እኔ በሷ ጉዳይ፣
ጦሬን እመዛለው ባልሆንም ሺ ገዳይ፣

የኔ ብቻ እንድትሆን አምላክ ባክህ እርዳኝ፣
ከኔ ሌላ አዳም በምድር አይገኝ፣
ልሁን ከሷ ጋራ ተጋፊ ሳይኖረኝ፣
ተው አትንካት ብሎ የሚከለክለኝ፣

የውበትሽ ማማር እጅግ ስለ በዛ፣
ሁሉም ይመኙሻል አይተውሽ በዋዛ፣

ሲረባረቡብሽ እጅግ አፈራለው፣
አዳም ከኔ ሌላ ባላይ እመርጣለው፣

ከሰዋራው ልቤ ውዴ ልደብቅሽ፣
ማንም ሳይነካብኝ ብቻዬን ላፍቅርሽ!!!

#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
16.2K viewsERMI ° , edited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:42:24 ዳግማዊ ታምራት
(ይሆን እንዴ)

New Ethiopian Music
የታምራት ደስታ ልጅ
13.7K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 14:51:22 ​ ሀያል ፍቅር

ያሉትን ይበሉ ተዋቸው ይናገሩ
ሲያወሩ ውለው ሲያወሩ ይደሩ

ወረኛው ቢበዛ ስራ ፈት አሳባቂ
አምላክ አለን ለኛ የፍቅራችን ጠባቂ

"እንዲ ሆነ" ቢሉ ቢመሰክሩ በየተራ
ፍቅራችን ላይቆም ምንም ቢወራ

መሰረታችን ፍቅር ነው መቼም ማይለካ
ህይወት ነው እስትንፋስ በምንም የማይተካ


#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
14.3K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:36:15 ሳቄን መልስልኝ
.
.
ተግባር ላይ ያልዋለ ቃልህን አምኜ፤

አንተን ብቻ እያሰብኩ ሰማይ ምድር ሆኜ፤

ፊደል አሳምረህ በሰጠኽኝ ተስፋ፤

ድንገት ብትለየኝ ሳቄን ይዞት ጠፋ፤

ሳቄን መልስልኝ ልቤን ትቼዋለሁ፤

ልብ ማለት ቀርቶ መስማት ጠልቻለው።


#ሼር


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :@Melkam_lboch11
14.0K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:37:55
ዘወትር ከአይኔ የማጠፋው
መከታ ክብሬ የሆንከው
ወንድሜ የኔ ትዝታ
ሰላም ሁን ጠዋትም ማታ

ክብር ለወንድሞች


𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@Melkam_lboch11
14.7K views ◁ ▯𝚣𝚎𝚛𝚞𝚋𝚊𝚋𝚎𝚕 ▯▷ , edited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ