Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-08-08 22:12:19   አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ስድስት▬▬





    ለፊርዶስ ምን ልበላት እንደባለፈዉ በቤተሰብ የመጣ አለ ብየ ልዋሻት እንዴ  ??? ወይስ እዉነቱን ልንገራት እያልኩ ሁለት ልብ ሆንክ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ

በመጨረሻም አንድ ዉሳኔ ወሰንኩ ነገ....ፊርዶስን ሳገኛት ጓደኛየ ናት ለኔም ለወንድሟም እያሰበች አንድ ከጎኔ ላለችዉ ፊርዶስ የኔን ማንነት ከመጀመሪያዉ እስከመጨረሻዉ ልነግራት ወሰንኩ፡፡
   እንደምንም ብሎ የወፎቸ ጫጫታ ንጋትን ሊያበስር ብቅ አለ ፡፡ እኔም ቁርሴን በልቼ እናቴ የምታቃቸዉ ሰዎች ስለሞቱ ለቅሶ ደርሼ ልምጣ ቤት ጠብቂኝ ብላ ከቤት ወጣች፡፡ እኔም ጊዜ መግደል አልፈለኩም እኔ ለዙበይር እንደማልሆነዉ እራሴን እንደረከሰ ሴት ስለምቆጥር ....በእኔ ፍቅር ሳይጎዳ በጊዜ እኔን እንዲረሳ እኔን እንዳያስታዉስ ለእህቱ ፊርዶስ ልነግራት ወሰንኩ፡፡
        ስልኬን ማታ እንዳጠፋሁት ነበር ወዳዉ ስልኬን አብርቼ ለፊርዶስ ደወልኩ
....ፊርዶስም ሂኩ ዛሬ አዳሬን ስጨነቅ እንቅልፍ ሳይወስደኝ አደረ ትናንት ለሰራሁት ስራ አዉፍ በይኝ ዙበይር ጋር ለማገናኘት መጀመሪያ አንቺን ማስፈቀድ ነበረብኝ ብላ እንባ እየተናነቃት ጠየቀችኝ
......እኔም ፊርዱ አንቺ ምንም ጥፋት የለብሽም ስታጠፊ ነዉ አዉፍ የምልሽ ...አንድ ነገር ላማክርሽ ነዉ አሁን የደወልኩልሽ ....ፊርዱ አንቺን የማይሽ እንደእህቴ ነዉ ደስታየንም ሀዘኔንም ልትካፈይኝ በምነግርሽ ነገር ላትርቂኝ በሆዴ አፍኜ የያዝኩትን የሆድ እሳት የሆነብኝ ሚስጥር ልነግርሽ ወስኛለሁ  እኔን ልታዳምጪኝ ልትረጂኝ ዝግጁ ነሽ??? አልኳት
......ፊርዶስም እንደመደንገጥ ብላ እሺ ዝግጁ ነኝ አለችኝ
......አሁን ከተመቸሽ እቤት መምጣት ትችያለሽ ???አልኳት
......እሷም እሺ ሂኩ አሁን መጣሁ አለችኝ፡፡
  
 ፊርዶስም ጊዜ ሳትፈጅ በፍጥነት እኛ ቤት ከተወሰኑ ደቂቃዎች ቡሀላ መጣች፡፡ ስገባ ሂኩ አሰላሙ አለይኩም ትናንትና አንቺን ሳላስፈቅድ በሰራሁት ስራ አዉፍ በይኝ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በይኝ እያለች እኔን መለመን ጀመረቸ፡፡
...... ወላሂ ከአንቺ ምንም ጥፋት የለም በራሴ ችግር ነዉ እንደዚህ የሆንኩት ዛሬ ኢንሻ አላህ ትረጂኛለሽ ብየ አስባለሁ ....
  ፊርዱ በማወራሽ ሚስጥር እኔ እና አላህ ነን የምናቀዉ አሁን አንቺን የዚህ ሚስጥር የምታቂዉ ከአላህ ከእኔ ቀጥሎ አንቺን ላማክርሽ ልነግርሽ ነዉ ግን ስነግርሽ ጠንካራ ልትሆኝ ይገባል እንደ አጋጣሚ እንባየ ቢፈስ አንቺም ማልቀስ የለብሽም አደራ አልኳት
ፊርዶስም በመደናገጥ እሺ አለችኝ
       እኔም ከረጅም ዝማታ ቡሀላ በፊት ስለትምህርቴ ስለጉብዝናየ .. ስለtelegram profile አርጌ......ሀይደር የሚባል ተዋወቄ......አምኘዉ እስከ ደብረዘይት ያሳለፍነዉን በመንታ እንባ የታጀበ እያወረሆት እንባየ ልብሴን እስከሚያርሰዉ አንድ ባንድ ነገርኳት ቂርአትም የገባሁት በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ሁሉንም እያለቀስኩ ለፊርዶስ ነገርኳት ፊርዶስም አብራኝ ታለቅሳለች....
   ባለፈዉ ሲሀም ዘመዴ ነዉ ያለችኝ ቁጥሬን የሰጠነዉ ቢክራ ነሽ ወይ ???ብሎ ሲጠይቀኝ ይሄ በሆዴ ያፈንኩት ሚስጥር ስላለኝ በመዋሸት በቤተሰቦቼ የመጣ ትዳር አለ ብየ መለስኩኝ ..አሁንም ይህን ሁላ የነገርኩሽ ያለምክንያት አይደለም እኔ ለወንድምሽ ለዙበይር የትዳር አጋር መሆን አልችልም የቆሸሸ ማንነት ነዉ ያለኝ ዙበይር ከአሁን ቡሀላ እኔን ይወደኝ እንደሆነ ከአሁን ቡሀላ ከኔ ተስፋ ይቁረጥ ፡፡
     እኔ ማለት ይህን ነገር ደብቄ ቤተሰቦቼ ሲጨናነቁ አንዱ ከአንዱ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በዚሁ የተነሳ ቁርአን ይቀራብሽ ተብየ ደሴ ከተማ ድረስ እንደሄድኩ ....እናቴ ስታለቅስ ስትዉል አጎቶቼን አስጨንቄ ነዉ የኖርኩት አላህ ይምረኝ ይሆን ?? ደግሞ በሀይደር ተናድጄ ከቅርብ ቀናት በፊት ሚስቱን በFace book አግኝቻት ልነግራት የእሱንም ሂወት ላበላሽበት ወስኜ ስልኳን እስከ መቀበል የደረሰ ተግባብተን ደዉየ ልነግራት ብየ ለወለደቻቸዉ ልጆች እና የወደፊት የእሷ ሂወት አሳዝኖኝ ተዉኩት ፡፡ ፊርዶስ የኔ ወንጀል ብዙ ነዉ አላህ ይምረኝ ይሆን?? አላህ ይምረኝ ይሆን ??
   አላህ ያለልኝን እጠብቃለሁ ግን እኔ ለዙበይር የምገባ ሴት አይደለሁም ለዙበይር ሌላ ፈልጊለት እኔ መፈቀር የሚገባኝ ሰዉ አይደለሁም እኔ ማለት ከአንዱ ወንጀል ወደ አንዱ ስረማመድ አሁን ድረስ እኔ በማንነቴ የማፍር..........ብየ ንግግሬን ለፊርዶስ አስረድቼ እምባየን እየጠረኩ ከፊርዶስ ጎን ተነሳሁ፡፡ ፊርዶስ አብራኝ ተነስታ .......እኔ ከተቀመኩበት ስነሳ ፊርዶስ አብራኝ ተነስታ .......
እንባየን ከጉንጬ እየጠረገች ሂኩየ አንቺኮ አሁንም ንፁህ ሰዉ ነሽ ወንጀል ሸይጧን አሳስቶሽ ልሰሪ ትችያለሽ ግን ወደአላህ ተመልሰሽ ማረኝ እያልሽ እያለቀሽ ነዉ፡፡
አላህ መሀሪ ነዉ የወንጀል ጉዳቱ ወንጀል መሆኑን እያወቁ እዛዉ ያለተዉበት በዛዉ ወንጀል ላይ ሁኖ ሳይቶብት መቼ እንደምንሞት ሳናቅ ዛሬ ወይ ነገ እቶብታለሁ እያልን ወይም ሀዲስ ስንሰማ መስጊድ ስንገባ ደአዋ ስናዳምጥ አልቅሰን ወንጀሎኞች ነን ከአሁን ቡሀላ ወደ ወንጀል አልሄድም ብለን እንቶብታለን ግን ወይ ከመስጊድ ስንወጣ ወይ ደአዋዉ ሲያልቅ የቶበትነዉን እንረሳዉና ወደ እዛ ወንጀል እንሄዳለን ይሄ አይነት ደግሞ መቶበት ሳይሆን በራስ ጭንቅላት ላይ ጌም እንደመጨዋት ነዉ...አሁን ብዙ ሰዉ ጋር የሚታየዉ ጥርት ያለ ተዉበት ሳያረጉ  አላህ ጋር መገናኘታቸዉ ነዉ፡፡

✎ ክፍል  አስራ ሰባት ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch1
1
20.3K views亗🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-08 11:36:39   #ምን_አስነክታኝ_ነው?

ምን አስነክታኝ ነው እንዲ የወደድኳት
ከአንቺ በቀር ሌላ በአይኔ አላይ ያልኳት
በእርግጥ ወዳታለው፤
በጣም አፈቅራታለው
የእሷ ፍቅር ለእኔ ከምንም በላይ ነው
ግን ምን አስነክታኝ ነው እንዲ የሆንኩላት
ከዚህ ሁሉ ሴት መሀል እሷን የመረጥኳት
ቁጣዋን ይያየው የኔ ውድ የምላት
ምን አስነክታኝ ነው እንዲህ ያፈቀርኳት!!
                            
ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
18.9K views 𝙿𝙾𝙿 𝙼𝚄𝙱𝙰❦, 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-07 21:53:28   አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ አምስት▬▬




     ስልኬን አዉጥቼ ለኢክራም ደዉየ ልነግራት ወስንኩ

ግን ጨነቀኝ የኔ ሂወት አንዴ ተበላሽቷል ግን የሶስት ሰዉ ሒወት ላበላሽ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡  ሁለት ልጆቿ እና ኢክራም ..ደግሞ ወደ ፍች ከሄዱ ልጆቹ ካለቤተሰብ ፍቅር ተለያይተዉ ኢክራም ወደ ቤተሰቦቻ ትሄዳለች ሌላም ችግር ፈጠርኩ ማለት ነዉ ..ቤተሰቦች ፀብ ብዙ ነገር  ስልኬን ይዤ ማሰብ ጀመርኩኝ .... ግን ሀይደር የሰራኝ ስራ መልሶ አእምሮየ ጋር ብልጭ ይልብኛል፡፡

ግን ምን ይደረጋል የእኔነ በደል ብሸከም ይሻለኛል የሌላ ሰዉ ሒወት ከማበላሽ....ሁሉንም ነገር ለፈጣሪየ ለአላህ ሰጠሁኝ፡፡  ስልኬን አቅፌ እንደ ወራጅ ወንዝ ማልቀስ ሆነ ያረቢ እርዳኝ ያረቢ እርዳኝ እያልኩ
........የኢክራምን ስልክ ለወደፊት እንደዚህ አይነት ዉሳኔ እንዳልወስን ብየ ከContact ላይ አጠፋሁ፡ Facebook ላልጠቀም ከአሁን ቡሀላ የሀይደርን ሚስት ኢክራምን ላላወራ ብየ ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ በአላህ ተወከልኩ እስከአሁንም የሰራሁትን ስራ አላህ ይማረኝ..ሀይደርን ከነቤተሰቦቹ  ልጎዳዉ ነበር ይቅርብኝ አላህ እሱንም ያስተካክለዉ እኔንም አላህ የተሻለ ይስጠኝ ብየ ዱአየን አርጌ ለመጨረሻ ጊዜ ከሀይደር ለመበቀል ያሰብኩት ሀሳብ ሰረዝኩኝ፡፡
  
   Face book መጠቀም አቆምኩ ግን ሀይደር የሰራኝ ጉድ ለማን ሰዉ እንደምተነፍሰዉ አላቅም ብቻየን ማታ ተኛሁ ብየ  አዳሬን ብቻ ማልቀስ ሁኗል ስራየ ፡፡

   የማይነጋ የለም የወፊት ጫጫታ መንጋቱን አበሰረኝ......ወደ ቂርአት ሄድኩ ፊርዶስን አገኘሇት፡፡
 ዛሬ እናንተ ቤት ሂጄ  እናትሽን መተዋወቅ እፈልጋለሁ አለችኝ
..እኔም ከቂርአት መልስ እቤት ወስጃት ከእናቴ ጋር አስተዋወኳት፡፡ እናቴን ካስተዋወኳት ቡሀላ  ፊርዶስ በረፍት ሰአቷ እኛ ቤት እየመጣች ቤተሰብም ጓደኛም ሆነች አላህ የሰጠኝ የዲን እህቴ ፊርዶስ ነች.....

ፊርዶስ እሁድ እንደምትጋብዘኝ ነገረችኝ .......ሸገር ላይ በሚገኘዉ ታላቁ ወበሪ ሆቴል....ከአሱር ቡሀላ እንሄዳለን አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ ፊርዱ አልኳት፡፡

ቀናቶች በተቆጠሩ ቁጥር እሁድ ደረሰ ፊርዶስ አሱር ሶላት አካባቢ እኛ ቤት መጥታ ሰግደን አብረን ወደ ወበሪ ሆቴል ሔድን፡፡  እዛ ስደርስ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ ወንድም ዙበይር ቀድሞን መጥቶ  ቁጭ ብሎ እየጠበቀን ነዉ፡፡
  ዙበይርን በፊርዶስ ስልክ በፎቶ  አንዴ ስላየሁት እሱ እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ ፊርዶስ ግን ዙበይርም ነዉም አይደለምም አላለችኝም...እሷ ሶስት ወንድሞች ስላሏት ዙበይር  ላይሆን ይችላል ብየ ጠረጠርኩ፡፡ ትኩስ ነገር አዘን አንዳንድ ወሬ እያነሳን ተጨዋዉተን  ተጠቀምን ስንጨርስ እኔን ወደ ቤቴ ሸኝተዉኝ እነሱም ወደ ቤታችን ተመለሱ

ግን ማን ይሆን??? እያልኩ ሳስብ ሳስብ ....ዙበይር ይሆን እንዴ እያልኩ ብቻየን ባዶ ቤት ቁጭ ብየ እኔዉ  ስከራከር.... ዳኛ ከሌለዉ ክርክር ዉስጥ ስልኬ ጮኸ ስልኬም ከክርክሩ ገላገለኝ...ስልኬን ሳየዉ የደወለችዉ ፊርዶስ ነበረች
,,...አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ አለች
......እኔም ወአለይኩም ሰላም ፊርዱ ደህና ነሽ
.......አልሀምዱሊላህ በሰላም እቤት ገባሽ??? አለችኝ
.....እኔም አዎ ገብቻለሁ ፊርዱ
ብዙ ተራ ወሬዎች ካወራን ቡሀላ

....ሂኩየ ቅድም አብሮኝ የመጣዉ ማን እነንደሆነ አዉቀሽዋል ????አለችኝ
.....እኔም መቼም አንቺ ከአጂ ነብይ ጋር እንደማትሄጅ አቃለሁ፡፡ ከሶስት ወንድሞችሽ አንዱ ይሆናል ፊርዱ አልኳት፡፡
.....አዎ አልተሳሳትሽም ዙበይር ነዉ ፡፡ በአካል አገናኚኝ እያለ ረበሸኝ ምን ላድርግ ፡፡ ፊርዱ አንቺ  ለኔ እኮ አይቴ(የወንድሜ ሚስት ለማለት ነዉ) ዙበይርም ወንድሜ ነዉ ፡፡ ዙበይር ናፈቀችኝ ናፈቀችኝ ሲለኝ ነዉ እስከዛሬ በሩቅ ነበር የሚያይሽ ዛሬ ፊት ለፊት እንዲያይሽ ያረኩት አለችኝ ፊርዱ
.....እሷ ባለችኝ ነገር ደርቄ ቀረሁ የምመልሰዉ አጣሁ መልሴ ዝም ሆነ ...

....ፊርዶስም ሄሎ ሄሎ ሄሎ ሂክማ ምነዉ ዝም አልሽ ...አረ በአላህ አጥፍቼ ከሆነ ይቅርታ እንደዚህ ይከፋሻል አላልኩም ሂክማ ..አረ አናግሪኝ አስጨነቅሽኝ .....ሂክማ አረ ሂክማ እያለች እሰማታለሁ ስልኩን አልዘጋሁትም ነበር፡፡

እኔ ምንም የምመልሰዉ መልስ የለም ብቻ እንባየ ቁልቁል ሲወርድ ይታወሰኛል

ፊርዱም ሄሎ ሄሎዉ ማለቷን አላቆመችም በድንጋጤ ..እኔም ስልኩን ዘጋሁት መልሳ ፊርዶ ደወለች እኔም አላነሳሁኝ.....ፊርዶስ በመደወል ትደጋግም ይዛለች.....እኔም በtext ነገ የማወራሽ ነገር አለ ብየ በmessgae ልኬ..ስልኬን አጠፋሁት፡፡ ለፊርዶስ ምን ልበላት እንደባለፈዉ በቤተሰብ የመጣ አለ ብየ ልዋሻት እንዴ  ??? ወይስ እዉነቱን ልንገራት እያልኩ ሁለት ልብ ሆንኩ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በመጨረሻም አንድ ዉሳኔ ወሰንኩ ነገ....ፊርዶስን ሳገኛት.........

ለፊርዶስ በሆዷ ያፈነችዉን ሚስጥር ለሂክማ ትነግራት ይሆን ??? ለሂክማ ነገረች ማለት ዙበይር ሊርቃት ይችላል እናንተ ምን ትላላችሁ ??
በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን፡፡

✎ ክፍል  አስራ ስድስት ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪
𝙨 : @melkam_lboch11
19.3K views亗🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-05 13:00:18   አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ አራት▬▬



    በጣም ተናደድኩ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁ መኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ
    Face book ገብቼ  የሀይደርን የfb ጓደኞች እያየሁኝ ነዉ፡፡ ሚስቱን በprofile ስላየሆት የfb ጓደኛዉ እንደሆነች ብየ መፈለግ ጀመርኩኝ፡፡ ጓደኞችን ስመለከት ብዙዎቹ ጓደኞቼ ሴት ነበሩ ገረመኝ፡፡ Fb ላይ ከ3000 በላይ ጓደኞቼ ነበሩት በስንት ድካም ልፋት ቡሀላ አንድ ፎቶ አየሁ የእሱ እና የእሷ profie የሆነ፡፡ time line ገብቼ ስመለከት የእሷ የብቻ ፎቶም አለ ፡፡ ሲጋቡ የተነሱ ፎቶዉ ላይ መብሩክ በሉኝ ብላ ፅፋለች፡፡

     ያሰብኩት ተሳካ አሁን frind አርጌ የእኔን ሂወት እንዳበላሸብኝ የእሱን ላበላሽበት ወሰንኩኝ፡፡ እኔ እያለቀስኩ እሱ ስቆ እንደማይኖር ወሰንኩኝ ...frind request ላኩላት ከአንድ ቀን ቡሀላ ተቀበለችኝ ...በጣም ደስ አለኝ ሀይደር የእኔ ሂወት አበላሽቶታል የእሱንም ሒወት አበላሸዋለሁ እያልኩ ብቻየን እየዛትኩ ነዉ፡፡

  face book ላይ online ቀን ቀን አትጠፋም  ፡፡ ነገሮችን ሁሉ ሳስበዉ እሱ ማታ ማታ በስልኩ ይጀናጀናል እሷም ቀን ላይ ታወራለች ብየ አሰብኩ በትዳር በመሀላቸዉ የሆነ ክፍተት እንዳለ ያስታዉቃል፡፡ እኔም  እያወረሇት ነዉ በሂደት  ተዋወቅን ግን ለክፉም ለደጉም ብየ ትክክለኛ ስሜን አልነገርኳትም ፡፡ ሚስቱ የአዲስ አበባ የመርካቶ ሰፈር ልጅ እንደሆነች ስሟም ኢክራም እንደምትባልና የባሏም ስም ሀይደር እንደሚባል እና የሁለት ልጆች እናት እንደሆነች ..... ቤተሰቦቿ ባለሀብት እንደሆኑ እና ..የባሏ ስም ሀይደር እንደሆነ  በጣም እንደምወደዉና ፡፡ በፊት ሹፌር ነበር ተዋወቅን ተዋደን ተጋባን ....ከዛም አባቴ ሀይደርን ከሹፍርና ስራ አቁም ብሎት አሁን  መርካቶ ሱቅ ከፈተልን ከዛም የቤት መኪናም ዶልፊን አባቴ ገዝቶ እንደሰጠዉ አጫወተችኝ፡፡

      ኢክራም በጣም ግልፅ ልጅ ናት ሁለ ነገሯ ተመቸችኝ ፡፡
አንቺስ ??ብላ ጠየቀችኝ
....እኔ ቂርአት እየቀራሁ እንደሆነ ነገርኳት፡፡ ስለ ሀይደር ምንም አላነሳሁ፡፡ ግን በጣም ገረመኝ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ ለማጥመድ በእጁ አድርጎ የሚፈልገዉን ለመዉሰድ የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም ዉሸታቸዉ ከባድ እንደሆነ ተረዳሁ ፡፡ ጥፋቱ የኔ ነዉ የነገረኝን ማመኔ ብቻ ወደ ጆሮየ የገባዉ ሁሉ እዉነት ይመስለኝ ነበር ፡፡ ሚስጥሩ እያደር ገባኝ ማታ ማታ ስደዉል አይመችም ስልክ ለማንሳት በtelegram እናወራለን የሚለኝ ሚስቱ ኢክራም  ሲያወራ እንዳትሰማዉ እንደሆነ ገባኝ፡፡
     ግን ለምን ?? አረ ለምን?? ኢክራም ፍቅር ያሸንፋል  ከሹፍርና ኑሮ ገላግላዉ በቤተሰቦቿ ጥረት ሱቅ ተከፍቶለት መኪና ተገዝቶለት.... እሷ ባለዉለታዉ ሁና በመኪናዉ ሴት ሲሸወድ እንደ እኔ ያለዉን የተዘነጋ በማዘናጋት እንደዚህ መሆኑ ለኢክራም አዘንኩ፡፡ ወይ ጎራ ሁን ወይ ጎራ ተጠጋ አይደል የሚባለዉ ሀይደር ጎራ ተጠግቶ ይሄዉ በኢክራም ጥረት እና በቤተሰቦቻ ሀብት ለሌላ ለሀራም አላማ እየተጠቀመበት በመሆኑ ያሳፍራል፡፡

ደግሞ ለኔ የዋሸኝ ዉሸት ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ፡፡ ምነዉ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ንገሪያት ንገሪያት የሚል መንፈስ ከጀርባየ አለ፡፡ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ፅፌዉ ልልከዉ ብየ ቆይ ለሁሉም ሰአት አለዉ አልኩና
  ባልሽን ትወጅዋለሽ ???ብየ ጠየኳት
....በጣም እንጂ ሀይደር ሁለ ነገሬ ነዉ በጣም እወደዋለሁ ያለ እሱ መኖር አልችልም በስራም ጎበዝ ነዉ ዉይ ሲወደኝ እኮ ብላ ታወራኝ ይዛለች በfb
......ግን ስለ እሱ መጥፎ ነገር ብሰሚ..ትጠይዋለሽ?? ወይስ አጠይዉም?? ብየ ጠየኳት

.....እሷም እንዴ ሀይደር መጥፎ ነገር የለዉም የሚሰራዉን የሆነዉን ሁሉን ይነግረኛል እኔን ሳያማክር ፈፅሞ አያቅም ፡፡ በህይወቴ እሱ ነዉ የመጀመሪያየ ወንድ በጣም ነዉ የምወደዉ፡፡ ምንም መጥፎ አይሰራም እተማመንበታለሁ አለችኝ፡፡

...እኔም አይ ግን ሰርቶ ብታገኝዉስ?? አልኳት
.......ጭራሽ አያረገዉም ጥያቄዉ መልስ የለዉም ሁሌም ቢሆን በሀይደር የምተማመንበት ጨዋ ልጅ ነዉ፡፡አላህ በስንት ዱአ መሰለሽ የሰጠኝ አለችኝ፡፡

በጣም ደስ የምትል ሚስት አለችዉ ግልፅ ናት እኔም ማንነቴን ደብቄ እናወራ ይዘናል ከመግባባት ብዛት ስልክ ቁጥሯን ተቀበልኳት፡፡  ስልክ ቁጥሯም0911....2372 ብላ በfb text አረገችልኝ ፡፡

 
እቤቴ ሁኜ ማሰብ ጀመርኩኝ ሀይደር የእኔን ሂወት እንዳበላሸ ላበላሽበት??? ወይስ እኔን አላህ አለኝ ቶብቻለሁ  ለሚስቱ እና ለሁለት ልጆቹ ሒወት ብየ ልተወዉ?? እያልኩ ተወዛገብኩ፡፡ ያሳለፍኳቸዉ የደብረዘይት ጊዚያቶች እና አሁን ትዳር ሲመጣ የምጨነቃቸዉ ጭንቀቶች ፊቴ ላይ ድቅን ይላሉ፡፡
 ይህን ጉዳይ ለፊርዶስ አላማከርኳትም ...ፊርዶስ ብሰማ ምን ትለኝ ይሆን ?
ስልኬን አንስቼ ቀጥታ ለኢክራም ልደዉል ቁጥሯን አዉጥቼ የሀይደርን ጉድ ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ሀይደር እኔን እንደሸወደ ሚስቱን ሲሸዉድ አይኖርም ...ስልኬን አንስቼ ወደ ሀይደር ሚስት ኢክራም ልደዉል ስልክ ቁጥሯን  አወጣሁ....ከዛም

ይቀጥላል ...

✎ ክፍል  አስራ አምስት ከ 200 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11
21.9K views亗🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-05 07:54:00 .  በዝች ምድር ላይ በሀብት
     በገንዘብ የማይገዛው
            ፍቅር ነው።
       ንፁህ ፍቅር የፈጣሪ
           ስጦታ ነው።
         ፈጣሪ አብዝቶ
           ለሁላችንም
         ፍቅር ይስጠን።

Share||
@melkam_lboch11
16.5K viewsᴀʙᴅᴜʟᴋᴇʀɪᴍ, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-04 19:03:39
እሄንን በሚገባ በደንብ እንቃወማለን!

በእየተተገበሰ የመጣው ግብረ ሰዶማዊነት ጉዳይ ችላ ልንል አይገባንም ... ይሄ ዝም ብሎ ትሮል ወይም ቀልድ አይደለም ... እሄ የአንድ ሀገር አሳሳቢ የሆነ ጉዳይ ነው።

እሄ ባህል በኢሮፓ ሃገሮች እየተስፋፋ እየመጣ ቢሆንም ... በሀገራችን እሄንን ባህል ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይመጣ መቃወም አለብን።

የአውርፓ ሀገሮች ንፁህ የሆኑ ሀገሮችንን ሀገራችንን ኢትዮጵያም የመበከል ግስጋሴያቸውን በተቻለን አቅም ማደናቀፍ አለብን።

እሄ ጉዳይ በማንኛውም ሃይማኖት እምነት የሚበረታታ አደለም ... ግብረ ሰዶማዊነትን እኛ ኢትዮጵያዊያን እንቃወማለን።

መልካም ልቦች

Share|| @melkam_lboch11
18.0K viewsᴀʙᴅᴜʟᴋᴇʀɪᴍ, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-04 11:07:15 አበባ ያለ ፀሀይ አይፈካም።
ሰውም ያለ ፍቅር አይኖርም።

Share||
@melkam_lboch11
16.5K viewsᴀʙᴅᴜʟᴋᴇʀɪᴍ, edited  08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-03 21:01:18 አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ሶስት▬▬



   ግን ለእሱ አንድ ዉሸት ዋሸሁት አላህ ይቅር ይበለኝ
ደዉሎ  ምን ወሰንሽ ???ብሎ ጠየቀኝ እኔም
......በዉሸት ወንድሜዋ ከአንተ ከተለያየን ቡሀላ  እናቴን ሚስጥር ስለማልደብቃት ማታ ሁሉንም ነገርኳት...እናቴም እኛ ያዘጋጀነዉ አባትሽ የመረጠልሽ ልጅ አለ አለችኝ ....ወንድም አላህ ከኔ የተሻለ ይስጥህ ከአሁን ቡሀላ መደዋወል እና በtelegram አናወራም ለምን ብትለኝ የወደፊት የትዳር አጋሬ መሆን ስለማንችል ከቤተሰቦቼ ትእዛዝ ዉጭ መፈፀም አልፈልግም አልኩት፡፡
...እሱም መርሀባ ብሎኝ  በዚሁ ተለያየን ክፉም ከአፌ ሳይወጣ እሱም ክፉ ሳይናገረኝ ወደድኩህ ወደድኩሽ የለአንቺ መኖር አልችልም ያለ አንተ መኖር አልችልም ሳንባባል በሀላል መንገድ ጀመርን፡፡ በሰላም ተለያየን አላህ ከእኔ የተሻለ የትዳር አጋር ይስጠዉ፡፡

     ምን ላርግ የጠየቀኝ ጥያቄ ላይ ድንግል አይደለሁም ብለዉ አላህ ወንጀሉን ነዉሩን የሸፈነ እኔ እሸፍንነታለሁ ብሏል እኔ ቶብቻለሁ በወንጀሌ ተፀፅቻለሁ ግን የእሱን ሂወት ዋሽቼ ገብቼ ማበላሸት አልፈለኩም፡፡ እኔ ሀይደር ሸወደኝና ማንኛዉንም ወንድ በክፉ አላይም፡፡ ለምን  አባቴ ወንድ ልጅ ነዉ፡፡ ወንዶች ገደል ይግቡ ካልኩ እኔን ለማሳደግ ለመንከባከብ ከቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ሁኖ የሚኖረዉ አባቴን ተሳደብኩ ማለት ነዉ ፡፡ ይህ ደግሞ የወላጆቼን ሀቅ አልተወጣሁም ማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም ጥሩ ወንዶች አሉ በተዘዋዋሪም ጥሩ ያልሆነ ወንዶች አሉ እነሱንም ከመሳደብ አላህ ልቦና ይስጣቸዉ ግን ይህ ጭካኔ በእህቱ በእናቱ ቢሆን የማይወደዉን በሌላ ሴት ልጅ መጨዋት ግን ያሳፍራል፡፡
      በየሳምንት ከጁምአ ሶላት ቡሀላ የደአዋ ዝግጅት አለ ሴቶች አሚራችን ፊርዶስ ደአዋ ታረግልናለች፡፡ እንደ አጋጣሚ እሷ አሟት ሳትመጣ ቀረች....
     ከዛም አንቺ አድርጊ እያሉ ሌሎች የጀመአ አባላችን ግፊት አርጉብኝ ...እኔም እሺ ብየ  ደአዋ አደረኩኝ፡፡
 የሚገርመኝ የመጀመሪያ ቢሆንም  በጣም የሚያምር ደአዋ አደረኩ የደአዋዉ ርዕስ በወንድ ተኩላዎች እንዳትሸወጅ ነበር፡፡ እኔም የተሰማኝን በደአዋዉ እያለቀስኩኝ ሀይደር የሰራኝ ስራ የሸወደኝ ትዝ እያለኝ እልክ በያዘኝ መልኩ ደአዋ አረኩላቸዉ ...የትምህርቱ ጠቃሚነት ብዙዎቹ አብረዉኝ ያለቅሱ ነበር፡፡ ደአዋዉን ሳረግ ለእህቶቼ ቢጠነቀቁ ብየ በኔ ሂወት የደረሰዉን ጠባሳ  በተለያዩ ዘዴዎች የደአዋ ሲስተም ነገርኳቸዉ  እንዲጠነቀቁ እና የtelegram group ጥቅም እና ጉዳቱን ዘርዝሬ ነገርኳቸዉ ከዛ ደአዋየን ጨርሼ ተቀመኩኝ፡፡

    ከዛ ቡሀላ ጁምአ ሶላት ቡሀላ አሚራችን ፊርዶስ አንቺ አድርጊ ባለፈዉ ሳልመጣ ቀርቼ ያደረግሽዉ ደአዋ በጣም እንደሚያምር ነግረዉኛል ....እንደዚህ የደአዋ ብቃት አለሽ ማለት ነዉ ማሻ አላህ ብያለሁ አለችኝ ፊርዶስ ፡፡
እኔም እኔ ደአዋ አላደርግ አንቺ ስለቀረሽ ነዉ ያረኩት  ብላት
.......እንዴ አላማችን አንቺ አንቺ ልንባባል ሳይሆን ያወቅነዉን ለማሳወቅ ነዉ ሂኩ ፡፡ እኔ ማረግ በምፈልግ ሰአት አረጋለሁ አንቺ አድርጊ አለችኝ...ፊርዶስ አበረታታችኝ ጁምአ ከሶላት ቡሀላ ተሰብስበን ደአዋ አድራጊዉ እኔ ሆንኩ ...

አላህ የሰራሁትን ወንጀል እንዲምረኝ በምሰግድ ሰአት ብቻየን ስሆን ረከአተይን ከሰገድኩ ቡሀላ አላህንም ማረኝ እያልኩ ባገኘሁት አጋጣሚ እያለቀስኩ ነዉ....
     
   እቤት ገብቼ ልተኛ አካባቢ ፊርዶስ አንድ ነገር አማክርሻለሁ ብላ ደወለችልኝ  ከአሱር ቡሀላ ልንገናኝ ተቀጣጠርን፡፡
ከአሱር ቡሀላ ከፊርዶስ ጋር ተገናኝተን አንድ  ያልጠበኩትን ነገር ነገረችኝ፡፡

   ሂክማ ባለፈዉ  የነገርሽኝ ነገር ሲሀም ለትዳር የሚፈልግሽ አለ ብላ እንደነገረችሽ እኔ ሳልነግርሽ አረፈድኩና ግን ዛሬ ልነግርሽ ወስኛለሁ፡፡ ወንድሜ አብረን ስንሄድ አይቶናል አንቺ ጓደኛየ እንደሆንሽ ያቃል ለትዳር እንደሚፈልገኝ ነገረችኝ ፡፡  ሂኩ ወንድሜ  ዲን አለዉ አላህን ፈሪ አንቺን ከጓደኝነት አልፎ ለወንድሜ ዙበይር ብታገቢዉ ደስ ይለኛል ሂኩ ማስተዳደሪያም አልሀምዱሊላህ አላህ እርዚቅ ሰጥቶታል  .... አንቺን እንዲያገባሽ እፈልጋለሁ አለችኝ፡፡ ባለፈዉ የሲሀም ዘመድ ይፈልገኛል ብለሽ ስታማክሪኝ ደነገጥኩ ወንድሜ ዙበይር እሷን ማግባት እፈልጋለሁ እያለ እኔም ወንድሜን እንድታገቢ እየተመኘሁ ያንን ወሬ ስሰማ ለዙበይር ነግሬዉ እንዴት እስከ አሁን ሳነግሪያት ብሎ ተቆጣኝ አለችኝ፡፡
.....እኔም ደነገጥኩኝ እስኪ ቆይ ልሰብበት አልኳት


ከዛም እቤቴ ሂጄ አሰብኩበት ለሚመጣዉ አመት ትምህርት የመማር እቅድ ነበረኝ..... እናቴም ብዙም ትምህርቴን እንድማር አትፈልግም...አባትሽ ተምሮ ለስራ የሚኖረዉ ደብረዘይት, ነዉ፡፡ የእኔን ፍቅር የልጁን ፍቅር ሳይሰጥ ይሄዉ እየኖረ ነዉ፡፡ መማር እንደዚህ ከሆነ ይቅር ትለኝ ነበር፡፡
መኝታ ክፍል ሁኜ ዙበይርስ  ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እያሰብኩ ነዉ፡፡

በጣም ተናደድኩ ሳላስበዉ ሸይጧን ወሰወሰኝ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁመኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ ፡፡ ብዙ ሀይደርን የምጎዳበት ነገሮች መኝታ ክፍሌ ሁኜ የቤታችንን ኮርኒስ  እያየሁ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ቀላል ዘዴ አገኘሁ ...እኛን የቸገረን ኸይር መስራቱ እንጂ ተንኮል መስራቱ መቼ ያቅተናል ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ እስከአሁን ትዝ ሳይለኝ ብየ ተቆጨሁ፡፡ ...የሀይደርን .....


ይቀጥላል ...


✎ ክፍል አስራ አራት ከ 200 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄

𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11
18.1K views₩𝖎𝖙𝖍 €𝖑𝖎𝖆$§ , 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:01:01 #ፍራቻ

በትንሿ እልፍኝ
እኔነቴ ሲሞት ድምፅሽ ይጠራኛል
እቅፍ አርገህ ሳመኝ ምትይ ይመስለኛል
አቅፌ እንዳልስምሽ ማጣት ያስፈራኛል

ማጣት እየፈራው
እጄን አንከርፍፌ
እራሴን አቅፌ ወዳንቺ ሳዘግም
ፈሪው እኔነቴ አንቺን አያሰርግም
ለምን?
ወድጄሽ ነው ልበል
አፍቅሬሽ ነው ልበል
አምኜ ልቀበል
እርምጃውን ሁሉ አንፆ በስጋት
መራቅ ለመጠጋት
ባዶ ተስፍ መጋት
ጀንበርን መናፈቅ እየሸሹ ንጋት
ምን ይሉት ነው ደግሞ
ለመድረስ መጓጓት እርምጃን አቁሞ
የጥያቄ ናዳ መልሴን እያራቀው
እንዲ ነው ለማለት <<አፌን ቃል አነቀወ>>

ማጣትን ፍራቻ
ከሰፈሩት ይልቅ እየሻቱ ልቅም
በሀሰት ቋጠሮ ይታጎላል ሀቅም
እንባ ይጎርፋል ለካ ለደስታ ቢሳቅም

ይኸው
በታነቀው ቃሌ
አንቺን እየሻትኩ
ሀቄን እየሳትኩ ስደክም ስለፋ
ለጠየኩት ሁሉ
ጥያቄ ነው እንጂ መልስ ሚሆን ጠፋ


#Join
          
ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
2.0K views𝖘𝖔𝖚𝖑 ☻︎, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:00:20 https://t.me/+1vYsOw7APBA1ZDQ0
መርጌታ ይትባረክ የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ #0917468918
   0917468918 በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሄ ሀብት
2 ለህማም
3 ለመስተፋቅር
4 ቡዳ ለበላው
5 ለገበያ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ስራይ
14 ጋኔን ለያዘው ሰው
16 ለቁራኛ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
35 በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ

1የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
2. ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
3. ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
4. ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
6. ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
7. ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8. ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
10. መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
11. ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን


ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር  በስልክ ቁጥራችን
0917468918  ይደውሉልን

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/+1vYsOw7APBA1ZDQ0
https://t.me/+1vYsOw7APBA1ZDQ0
1.7K views𝖘𝖔𝖚𝖑 ☻︎, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ