Get Mystery Box with random crypto!

#ፍራቻ በትንሿ እልፍኝ እኔነቴ ሲሞት ድምፅሽ ይጠራኛል እቅፍ አርገህ ሳመኝ ምትይ ይመስለኛል አ | Best disk

#ፍራቻ

በትንሿ እልፍኝ
እኔነቴ ሲሞት ድምፅሽ ይጠራኛል
እቅፍ አርገህ ሳመኝ ምትይ ይመስለኛል
አቅፌ እንዳልስምሽ ማጣት ያስፈራኛል

ማጣት እየፈራው
እጄን አንከርፍፌ
እራሴን አቅፌ ወዳንቺ ሳዘግም
ፈሪው እኔነቴ አንቺን አያሰርግም
ለምን?
ወድጄሽ ነው ልበል
አፍቅሬሽ ነው ልበል
አምኜ ልቀበል
እርምጃውን ሁሉ አንፆ በስጋት
መራቅ ለመጠጋት
ባዶ ተስፍ መጋት
ጀንበርን መናፈቅ እየሸሹ ንጋት
ምን ይሉት ነው ደግሞ
ለመድረስ መጓጓት እርምጃን አቁሞ
የጥያቄ ናዳ መልሴን እያራቀው
እንዲ ነው ለማለት <<አፌን ቃል አነቀወ>>

ማጣትን ፍራቻ
ከሰፈሩት ይልቅ እየሻቱ ልቅም
በሀሰት ቋጠሮ ይታጎላል ሀቅም
እንባ ይጎርፋል ለካ ለደስታ ቢሳቅም

ይኸው
በታነቀው ቃሌ
አንቺን እየሻትኩ
ሀቄን እየሳትኩ ስደክም ስለፋ
ለጠየኩት ሁሉ
ጥያቄ ነው እንጂ መልስ ሚሆን ጠፋ


#Join
          
ከወደዱት ሼር

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11