Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-19 22:44:58
ፍጠኑ አየር መንገድ ዛሬ ያወጣው 245 ክፍት የስራ ቦታ ላይ አሁኑኑ ተመዝገቡ በጣም በርካታ መስኮች ላይ ወቷል ከታች መርጠው ይጫኑ
1.6K viewsYehuans, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 15:46:11 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ሰባት▬▬▬


."ስትተኚ ይበልጥ የምታምሪዉ ለምንድን ነዉ? በጣም ዉብብ ሆነሻልኮ" አላት፡፡ ጉንጯን
እንደመሳም.... እያረገ ነበር፡፡ ኤዲም ...
..."እሺ የኔ ፍቅር  እንቅልፍ ሲወስደኝ ደግሞ ይበልጥ ስለሚያምርብኝ ልተኛ" አለችዉና
እሷም ሳም አድርጋዉ ራሷን ከእቅፉ አዉጥታ ጀርባዋን ሰጥታዉ ተኛች፡፡

...ኤዲና ቢኒ ሰሞኑን በረድኤት ጉዳይ የተነሳ አልተኙም  ቢኒ  በለሊቱ ተነስቶ ወደ ስራ ለመሄድ ወደ ስራ ይዟቸዉ የሚሄደዉን እቃዎች እያዘጋጀ ነጋ፡፡
        እቃዎቹን አዘገጃጅቶ ከጨረሰ ቡሃላ ወደ ስራ ሊወጣ ሲል "ኤዲዬ ልሄድ ነዉ" አላት፡፡
...."ቆይ የኔ ፍቅር በር ድረስ ልሸኝህ"  አለችዉና ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደሱ መጣች፡፡ ተያይዘዉ አብረዉ ሲወጡ አባባ ሀብታሙ በጧቱ ከቤታቸዉ
በር ስር ተቀምጠዉ ነበርና አገኟቸዉ፡፡
..."ደህና አደራችሁ የኔ ልጆች እንዴት አደራችሁ?" አሏቸዉ፡፡
ሰላምታዉን ከመለሱላቸዉ ቡኃላ... አባባ ሀብታሙም ..."ኤዲ አንቺም ፈቅደሻል አሉ፡፡ እሁን
ቢኒያምን ልትድሪዉ ነዉ ለረድኤት" ብለዉ ጠየቋት፡፡ የአባባ ሀብታሙ ንግግር ልቧን ለሁለት
ስንጥቅ ነበር ያደረጋት፡፡ እንደምንም እራሷን ካረጋጋች ቡኃላ ፈገግ ለማለት እየሞከረች...
"አዎ አባባ ፈቅጀለታለሁ፡፡" ብላ መልሷን አሳጠረች፡፡ ደስታዋ ነበር ኤዲ፡፡ በጣም ነበር
የደነገጠችዉ፤ ዉስጧ ተሸበረ፡፡ ቢኒ የኤዲን እንዲህ መሆን ከሁኔታዋ ሲረዳ ..."በቃ አባባ
ስራ ስለረፈደ ስመለስ እናወራለን፡፡" አላቸዉ፡፡
..."ደግ እንግዲህ...." አሉና አባባ ወደ ቤታቸዉ ገቡ፡፡
..."ኤዲዬ ወደ ቤት ግቢና አረፍ በይ እደዉልልሻለሁ" አላትና ግንባሯን ሳም አድርጓት
ከግቢዉ ወጣ፡፡
ኤዲ እንደምንም ብላ ቤቷ ገባች፡፡ የሰማችዉን ማመን አቅቷታል ሀሙስ ማለት ከሁለት ቀን
ቡሃላ ነዉ፡፡
"እና ከሁለት ቀን ቡሃላ ረድኤት ቢኒን ልትጋራኝ ነዉ ማለት ነዉ" ስትል አስበች፡፡ ብዙም
ሳትቆይ ከባድ ራስ ምታት አመማት፡፡ በጣም አመማት፡፡ ቁርሷን ሰርታ መብላት ሁሉ
አልቻለችም፡፡ አቃታት፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኳን አነሳችና ወደ ቢኒያም ደወለች፡፡
..."ሄሎ ኤዲዬ እደዉላለሁ ብዬ ቆየሁ እንዴ?" አላት ቢኒ
..."በጣም አሞኛል ቢኒ ናልኝ፡፡ ቶሎ በል" አለችዉና ስልኳን ዘጋችዉ፡፡ እየተንቀጠቀጠች
ነበር ያወራችዉ፡፡ እንደምንም ብላ ቀስ ብላ ተኛች፡፡ ወዲያዉ እማማ በለጡና ረድኤት
እየተሯሯጡ መጡና "ኤዲ ምን ሁነሽ ነዉ?" ብለዉ አይን አይኗን አይዋት፡፡
ኤዲ ራሷን በሻርብ ግጥም አድርጋ አስራዉ ነበር፡፡፡ እማማ በለጡ ኤዲን
ግንባሯን እያሻሹ "ትኩሳትም የለሽ ምን ሁነሽ ነዉ ኢዲዬ" ብለዉ ጠየቋት፡፡ኤዲም ..."ትንሽ
ራሴን አሞኝ ነዉ" አለቻቸዉ፡፡
..."እኔኮ ቢኒያም ሲደዉልልኝ ምን አጋጠመሽ ብዬ ነበር፡፡ለራስ ምታት ነው ውይ ፈጣሪ ይመስገን" ብለዉ ፈጣሪን አመሰገኑ፡፡ ቢኒ ለእማማ በለጡ ደዉሎ ሲነግራቸዉ በጣም የተጎዳችና ድንገታዊ
አደጋ የደረሰባት አስመስሎ ነበር፡፡ እማማ በለጡና ረዲ ከኤዲ አጠገብ ሳይነሱ ወዲያዉ ላብ
በላብ ሆኖ እያለከለከ ቢኒ ብቅ አለ፡፡
..."ኤዲዬ ምን ሆንሽብኝ? ምን አግኝቶሽ ነዉ?" በጣም አመመሽ?" እያለ ከተኛችበት ቀና
እያደረገ በጥያቄ አጣደፋት፡፡
..."የኔ ፍቅር መጣህልኝ!" አለችዉና ከተኛችበት ራሷ ቀጥ ብላ እቅፍ አደረገችዉ፡፡
..."ቢኒ..." አለችዉ፡፡ ቢኒም
..."ወዬ የኔ ማር!" አላት፡፡ እማማ በለጡና ረድኤት አጠገባቸዉ እንደተቀመጡ ነበር፡፡ ለነሱ
ብዙም ቦታ ሳትሰጣቸዉ ቢኒያምን ወደራሷ ሳብ አደረገችዉና...

✎ ክፍል አስራ ስምንት ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
4.6K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:19:50 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ስድስት▬▬▬


መቼ ነዉ ወደ ዩንቨርስቲ የምትገቢዉ የኔ ልጅ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ ረድኤትምም ... " የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እሁድ እሄዳለሁ"  ስትላቸዉ እማማ በለጡ ደንገጥ አሉና..."እንግዲያዉስ ከመሄድሽ በፊት በዚህ ሳምንት ዉስጥ ቀለበት ማሰር አለብሽ!" አሉ፡፡አባትና ልጅ ሁለቱም ድንግጥ ብለዉ "እ..." አሉ፡፡ የረድኤት አደነጋገጥ እንዴት...
       ...አባባ ሀብታሙ ባለቤታቸዉ ላይ እንዳፈጠጡ ነዉ፡፡ መልስ ይፈልጋሉ፡፡ ልጃቸዉን በሚስጥር ልትድራት እንደ ሆነ ነገር ነዉ የገመቱት፡፡ "ከማን ጋር ነዉ ሴራ የምታሴረዉ?" ጥያቄያቸዉን ለማማ በለጡ ደገሙላቸዉ፡፡ እማማ በለጡና ረድኤት ይተያያሉ፡፡ አባባ ሀብታሙ ደግሞ ባለቤታቸዉ ና ልጃቸዉ ላይ አይን አይናቸዉን እያፈራረቁ ተመለከቷቸዉ፡፡
እማማ በለጡ በረዥሙ ትንፋሻቸዉን እህህህህ ብለዉ ካወጡ ቡኃላ ይሄዉልህ ሀብታሙ
ብለዉ ለማስረዳት ሊሞክሩ ሲሉ "ማንን ነዉ የምታገባዉ? እ!" ብለዉ መልሱን ለመስማት
ጓጉ... እማማ በለጡም ቀስ አሉና... "ረድኤት እንግዲህ ደርሳለች፡፡ ህፃን ልጅ የምትባል ልጅ
አይደለችም፡፡ ለማፍቀርም ለመፈቀርም፤ ለማግባትም ለመዉለድም ደርሳለች፡፡"  ...የጋሽ
ሀብታሙን አይን አይን እያዩ ነበር የሚያወሩት "አይደለም እንዴ ሀብታሙ?" ብለዉ የረድኤትን
መድረስ ለማረጋገጥ ባለቤታቸዉን አባባ ሀብታሙን ጠየቁ፡፡


..."አዎ ደርሳለች ግን...ለማን ነዉ የምትድሪያት? ማንን ነዉ የምታገባዉ?" ብለዉ ጠየቁ
የምታገባዉን ሰዉ ይበልጥ ለማወቅ እየጓጉ፡፡
"...እኔ አይደለሁም የምድራት፡፡ ልጄ ረዲ የምታገባዉን ሰዉ ራሷ መርጣለች" አሉ እማማ
በለጡ ረድኤትን እንደ ማቀፍ እያረጉ፡፡ ረድኤት አባቷን ለማየት ተሳናት፡፡
..."አትፍሪ የኔ ልጅ ንገሪኝ ማንን ነዉ የመረጥሽዉ?  እኔምኮ አባትሽ ነኝ ለናትሽ ብቻ ነዉ
እንዴ የምትነግሪያት" አሉ አባባ ሀብታሙ፡፡ ረድኤት ደፈር ብላ እንድትነግራቸዉ እየገፋፏት፡፡
ረድኤትም አባቷን በፍርሃት ቀጥ ብላ እያየች "አባዬ... ቢኒያምን ነዉ!" አለቻቸዉ፡፡ ይሄ
አባቷን ድፍረቷ ሳይሆን አሰተዳደጓ ነዉ፡፡ ምንም ነገር አጥብቀዉ ከጠየቋት አትዋሽም፡፡
እማማ በለጡም ስሙን ከረድኤት አፍ ነጠቅ አደረጉና "አዎዎ ቢኒያም ነዉ፡፡ የኤዲን ባል"
..."ምን?በስመአብ"  ብለዉ ከተቀመጡበት ብድግ እንደገና ቁጭ አሉና....፡፡አይሆንም?አታደርጉትም።

...ኤዲና ቢኒ አንድ ላይ ተኝተዉ እየተንሾካሾኩ ያወራሉ፡፡ ኤዲም ንዴቷን እረስተዋለች፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ ረድኤትን በጣም ወዳታለች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ከሜሴጁ ላይ ረድኤት
ለኤዲ እጅግ በጣም አሳቢ እንደሆነች ነዉ የተረዳችዉ፡፡ "ለኤዲ አንተ ቀድመህ
ንገራት"..."ኤዲ ትፍቀድ እንጂ" ...  ይሄ የረድኤት ንግግር ዉስጧ ገብቷል፡፡ እኔ የማልፈቅድ
ከሆነኮ ረድኤት ቢኒያምን አታገባዉም ማለት ነዉ እያለች ታስባለች፡፡ እንደ እዉነቱም ረድኤት
ለኤዲ ታዝንላታለች፤ ታከብራታለች፡፡ ፍቅር ሆኖባት እንጂ የኤዲን ባል ልትቀናቀናት
አትፈልግም ነበር፡፡
..."የኔ ፍቅር  እማማ በለጡ ሁሉንም ነግረዉኛል" አለችዉ ቢኒያምን፡፡ ቢኒም እቅፉን ይበልጥ
እያስተካከለ
..."ምን ነገሩሽ የኔ ቆንጆ!" ብሎ ጠየቃት፡፡
..."ረድኤትም በጣም እንደምትወድህና ልታገባህ እንደምትፈልግ እና ሌላም ብዙ..." ብላ
በቁጭት አይነት ወሬዋን አቋረጠችዉ፡፡ ትንፋሿ ይጋረፍ ነበር፡፡ ቢኒያም በዚሁ ርዕስ ወሬ
ከቀጠሉ ወደ ማኩረፍ እንደምትሄድ ስለተረዳ ወሬ ለመቀየር ያክል...
..."ኤዲዬ ..." አላት
..."ወዬ ቢኒ"
..."ስትተኚ ይበልጥ የምታምሪዉ ለምንድን ነዉ? በጣም ዉብብ ሆነሻልኮ" አላት፡፡ ጉንጯን
እንደመሳም

✎ ክፍል አስራ ሰባት ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
8.5K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:14:18 09 18 43 46 89
09 18 43 46 89
ሰላም እዴት ናችሁ ወድሞች እህቶች አንድ ሰው ላስተዋውቃትሁ መሪጌታ ይባላሉ እደኔ ከበሽታችሁ ከችግራችሁ መላቀቅ ለምትፈልጉ አዴ ብቻ አናግሯቸው የሳቸው መድሀኒት የደረሳችሁ ሼር አትርሱ እባካችሁ አዴ ብቻ አናግሯቸው

   መርጌታ ብናልፍ የባህል መድህኒት ቀማሚና ሰሪ ለማነኛውም በሽታ መዳን እዳለ አትርሱ ከምንሰራቸው በትንሹ
   09  18 43 46 89
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት በአለም ላይ የብዙ ትዳሮች መፍረስ  #የወሲብ_ግኑኝነት ጥሩ አለመሆን ነው። ስለዚህ የገጥመዎትን ችግር ቀጥታ በመጠዬቅ መፍትሔ በማግኘት ደስተኛ ህይወት ይኑራችሁ
ስንፈተ ወሲብን እንዴት ማከም ይቻላል?
የሀበሻ መድሃኒት ህክምና፡ መድሃኒቶች የደም ፍሰትን ይጨምራሉ እንዲሁም የፆታዊ ፍላጎት
በሚኖርበት ጊዜ ብልት በምላሹ እንዲቆም የሚያደርጉ ናቸው።
የብልት መጠንን መጨመር የሚችሉ መድሀኒቶችን አቅርበንላችኋል
1.የብልት አለመቆም ችግር
2.ቶሎ የመርጨት ችግር
3.የብልትን ቁመትና ውፍረት ማነስ ችግር
ካለብሆት በፍጥነት
09 18 43 46 89 ይደውሉ እና ያማክሩን
በፍጥነት ያሉበት ቦታ እናደርሳለን
ማሳሰቢያ  ከምንም የጎንዮሽ ጉዳት ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸውጨ
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት አለ
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
                   09 18 43 46 89
6.5K viewsYehuans, 12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 21:03:38 የኔታ ነህ ለኔ


ያ ሸንጋይ ምላስህ ቅቤ የሚያቀልጠው
ፎርጅድ ማንነትህ ከላይ የሚታየው

መታወቂያው ሌላ ማሞው ሌላ ሆነህ
ያንቺ ነኝ ስትለኝ ልብህን ሸሽገህ

ሰው አማኙ ልቤ ለፍቅርህ ሲሸነፍ
ምስኪን ማንነቴ አንተን አምኖ ሲከንፍ

የታሻለ ስታይ አቁስለኸው ልቤን
ትተኸኝ ስትሄድ ንቀኸው መውደዴን

እጅጉን ብጎዳም ባንተ ምክንያት ያኔ
አመሰግናለሁ የኔታ ነህ ለኔ
ስለሰው ማንነት ያዘረፍከኝ ቅኔ

Join us 

ሼር 
@melkam_lboch11
10.5K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:46:32 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ አምስት▬▬▬

        የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እሁድ
እሄዳለሁ"  ስትላቸዉ እማማ በለጡ ደንገጥ አሉና..."እንግዲያዉስ ከመሄድሽ በፊት በዚህ ሳምንት ዉስጥ ቀለበት ማሰር አለብሽ!" አሉ፡፡አባትና ልጅ ሁለቱም ድንግጥ ብለዉ "እ..." አሉ፡፡ የረድኤት አደነጋገጥ እንዴት ብለዉ ካወጡ ቡኃላ ይሄዉልህ ሀብታሙ
ብለዉ ለማስረዳት ሊሞክሩ ሲሉ "ማንን ነዉ የምታገባዉ? እ!" ብለዉ መልሱን ለመስማት
ጓጉ... እማማ በለጡም ቀስ አሉና... "ረድኤት እንግዲህ ደርሳለች፡፡ ህፃን ልጅ የምትባል ልጅ
አይደለችም፡፡ ለማፍቀርም ለመፈቀርም፤ ለማግባትም ለመዉለድም ደርሳለች፡፡"  ...የጋሽ
ሀብታሙን አይን አይን እያዩ ነበር የሚያወሩት "አይደለም እንዴ ሀብታሙ?" ብለዉ የረድኤትን
መድረስ ለማረጋገጥ ባለቤታቸዉን አባባ ሀብታሙን ጠየቁ፡፡


..."አዎ ደርሳለች ግን...ለማን ነዉ የምትድሪያት? ማንን ነዉ የምታገባዉ?" ብለዉ ጠየቁ
የምታገባዉን ሰዉ ይበልጥ ለማወቅ እየጓጉ፡፡
"...እኔ አይደለሁም የምድራት፡፡ ልጄ ረዲ የምታገባዉን ሰዉ ራሷ መርጣለች" አሉ እማማ
በለጡ ረድኤትን እንደ ማቀፍ እያረጉ፡፡ ረድኤት አባቷን ለማየት ተሳናት፡፡
..."አትፍሪ የኔ ልጅ ንገሪኝ ማንን ነዉ የመረጥሽዉ?  እኔምኮ አባትሽ ነኝ ለናትሽ ብቻ ነዉ
እንዴ የምትነግሪያት" አሉ አባባ ሀብታሙ፡፡ ረድኤት ደፈር ብላ እንድትነግራቸዉ እየገፋፏት፡፡
ረድኤትም አባቷን በፍርሃት ቀጥ ብላ እያየች "አባዬ... ቢኒያምን ነዉ!" አለቻቸዉ፡፡ ይሄ
አባቷን ድፍረቷ ሳይሆን አሰተዳደጓ ነዉ፡፡ ምንም ነገር አጥብቀዉ ከጠየቋት አትዋሽም፡፡
እማማ በለጡም ስሙን ከረድኤት አፍ ነጠቅ አደረጉና "አዎዎ ቢኒያም ነዉ፡፡ የኤዲን ባል"
..."ምን?በስመአብ"  ብለዉ ከተቀመጡበት ብድግ እንደገና ቁጭ አሉና....፡፡አይሆንም?አታደርጉትም።

...ኤዲና ቢኒ አንድ ላይ ተኝተዉ እየተንሾካሾኩ ያወራሉ፡፡ ኤዲም ንዴቷን እረስተዋለች፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ ረድኤትን በጣም ወዳታለች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ከሜሴጁ ላይ ረድኤት
ለኤዲ እጅግ በጣም አሳቢ እንደሆነች ነዉ የተረዳችዉ፡፡ "ለኤዲ አንተ ቀድመህ
ንገራት"..."ኤዲ ትፍቀድ እንጂ" ...  ይሄ የረድኤት ንግግር ዉስጧ ገብቷል፡፡ እኔ የማልፈቅድ
ከሆነኮ ረድኤት ቢኒያምን አታገባዉም ማለት ነዉ እያለች ታስባለች፡፡ እንደ እዉነቱም ረድኤት
ለኤዲ ታዝንላታለች፤ ታከብራታለች፡፡ ፍቅር ሆኖባት እንጂ የኤዲን ባል ልትቀናቀናት
አትፈልግም ነበር፡፡
..."የኔ ፍቅር  እማማ በለጡ ሁሉንም ነግረዉኛል" አለችዉ ቢኒያምን፡፡ ቢኒም እቅፉን ይበልጥ
እያስተካከለ
..."ምን ነገሩሽ የኔ ቆንጆ!" ብሎ ጠየቃት፡፡
..."ረድኤትም በጣም እንደምትወድህና ልታገባህ እንደምትፈልግ እና ሌላም ብዙ..." ብላ
በቁጭት አይነት ወሬዋን አቋረጠችዉ፡፡ ትንፋሿ ይጋረፍ ነበር፡፡ ቢኒያም በዚሁ ርዕስ ወሬ
ከቀጠሉ ወደ ማኩረፍ እንደምትሄድ ስለተረዳ ወሬ ለመቀየር ያክል...
..."ኤዲዬ ..." አላት
..."ወዬ ቢኒ"
..."ስትተኚ ይበልጥ የምታምሪዉ ለምንድን ነዉ? በጣም ዉብብ ሆነሻልኮ" አላት፡፡ ጉንጯን
እንደመሳም እያረገ ነበር፡፡ ኤዲም ...
..."እሺ የኔ ፍቅር  እንቅልፍ ሲወስደኝ ደግሞ ይበልጥ ስለሚያምርብኝ ልተኛ" አለችዉና
እሷም ሳም አድርጋዉ ራሷን ከእቅፉ አዉጥታ ጀርባዋን ሰጥታዉ ተኛች፡፡

...ኤዲና ቢኒ ሰሞኑን በረድኤት ጉዳይ የተነሳ አልተኙም  ቢኒ  በለሊቱ ተነስቶ ወደ ስራ ለመሄድ ወደ ስራ ይዟቸዉ የሚሄደዉን እቃዎች እያዘጋጀ ነጋ፡፡


✎ ክፍል አስራ ስድስት ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
11.0K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 14:35:58 "ትንሳኤ" በእንግሊዘኛ ምን ይባላል?
609 viewsBaruk, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:28:30 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ አራት▬▬▬

ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡፡ አንብቢዉና
የባልሽን ጉድ ተመልከቺ ይመስላል አሰጣጡ፡፡ ኤዲም ስልኩን ተቀበለችውና የላኪዉን
አድራሻ ስታይ እማማ በለጡ ይላል፡፡ "የኔ ፍቅር እማማ ደግሞ ምን ብለዉ ልከዉልህ
ነዉ?" ብላ ጠየቀችዉ፡፡
"ኤዲዬ ስልኩ እጂሽ ላይ አይደል? አንብቢዉ" አላት
..."ቢኒ ለእማዬ ነግሬያታለሁኝ ኤዲ ፍቃደኛ ትሁን እንጂ ..."ኤዲ ፊቷ እየተቀየረ ነበር፡፡
ቀጥ ብላ ቢኒያምን ተመለከተችዉ ትኩር ብላ አየችዉ፡፡ ቢኒያም የኤዲን የቁጣ አይኖች
መቋቋም አልቻለምና ጎንበስ አለ፡፡ኤዲ እንደገና ወደ መልዕክቱ ትኩረቷን አደረገች፡፡
ማንበብ ቀጠለች... "...አንተ እንድታገባኝ ፍቃደኛ እንደምትሆን ነግራኛለች፡፡ ግን ደግሞ
እሷ ራሷ እማዬ ለኤዲ እነግራታለሁኝ ብላለች፡፡ ቢኒ ፕሊስ እማዬ ለኤዲ ከመንገሯ በፊት
አንተ ቀድመህ ንገራት፡፡" ይላል መልዕክቱ፡፡
ፊቲ ሁለት ልብ ሁናለች፡፡ ደስተኛም ግን ደግሞ የብቸኝነት ስሜት የተሰማት ባዶ እንደሆነች
አድርጋ እራሷን አሰበች፡፡ ከዉስጧ ደስታ ይበልጥ ንዴቷ ፊቷ ላይ ገንፈሎ ወጣና "ቢኒ
እኔን ሳትነግረኝ ከረዲ ጋር ጀምረህ ነበራ?" ብላ ጠየቀችዉ፡፡ "የኔ ፍቅር እኔ ላንተ ድብቅ ነኝ
ማለት ነዉ?" ኤዲ ምን እንደምትናገር ሁሉ አቅቷታል፡፡ እምባ እየተናነቃት የምታወራዉ ሁሉ
ይቆራረጣል፡፡ቢኒ የዚህን ያህል ትቆጣለች፤ እንደዚህ ትሆናለች ብሎ አላሰበም ነበር...
..."እንደሱኮ አይደለም ኤዲዬ..."እያለ ወደሷ ጠጋ አለ
..."አትጠጋኝ! ደግሞ ምንም ነገር አትንገረኝ!" አለችዉ፡፡ በሂወቱ ኤዲ እንዲህ ስታመር
አይቷት አያዉቅም፡፡ ዛሬ በጣም ተለይታበታለች፡፡ ለማባባል እንኳ በሚያስቸግር ሁኔታ፡፡
ኤዲን እንዲህ እንድትሆን ያደረጋት ሁለተኛ ማግባቱ አይደለም፡፡ ይሄንን ደግሞ እራሷ
ፈቅዳለታለች፡፡ እሷዉ ሴት መርጣ ልትድረዉም ተዘጋጅታ ጨርሳ ነበር፡፡ ነገር ግን... ገና
ሳያገባ እንዲህ ሚደብቃት፤ ለሱ እየለፋችለት፤ ሁሉንም ነገር ለሱ እየሆነችለት እሱ ግን
ልቧን መስበሩ በጣም አዘነችበት፡፡
...ቢኒ ምን እንደሚያወራ አፉ ተያያዘበት፡፡ ተንተባተበ፡፡ ጥፋተኛ እንደሆነ አዉቆታል፡፡ ኤዲ
ጎንበስ ብላ ነበር ቀና ብላ ቢኒያምን ስትመለከተዉ እሱም የመለማመጥ አይነት አንገቱን
ሰብሮ አይኖቹን አቁለጨለጨ፡፡
..."ቢኒ ... እኔ እንደፈቀድኩና መጋባት እንደምትችሉ ፃፍላት" አለችዉ፡፡
..."ኤዲዬ መጀመሪያ ስለነበረዉ ነገር ላንቺ ልንገርሽ"
..."የኔ ፍቅር በፈጣሪ!? አሁን ምንም ነገር ለመስማት ዝግጁ አይደለሁም!"
..."እይዉልሽ ማሬ...." ብሎ ወሬ ሲጀምር ኤዲ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ ዉጭ
ወጣች፡፡ ከመዉጣቷ እማማ በለጡን ዉጭ ላይ አገኘቻቸዉ፡፡ ሰላምታ ቀድማ
አልሰጠቻቸዉም፡፡ እማማ በለጡም ኤዲን ሲያይዋት "ደህና ነሽ ኤዲ" አሏት፡፡ ኤዲም
ለሰላምታቸዉ መልስ ሰጠችና ከማንም ጋር ምንም ማዉራት ስላልፈለገች ተመልሳ ወደ
ቤት ልትገባ ስትል        "ኤዲ ስፈልግሽ ነበር...ስራ አለሽ እንዴ?" አሏት፡፡
..."አይ ስራ የለኝም፡፡ ለምን ፈለጉኝ እማማ" አለቻቸዉ ፊቷን ሳታዞር በቆመችበት፡፡
..."የሆነ የምነግርሽ ነበረኝ" አሉ እማማ በለጡ፡፡


✎ ክፍል አስራ አምስት ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
2.6K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:06:36 09 18 43 46 89
09 18 43 46 89
ሰላም እዴት ናችሁ ወድሞች እህቶች አንድ ሰው ላስተዋውቃትሁ መሪጌታ ይባላሉ እደኔ ከበሽታችሁ ከችግራችሁ መላቀቅ ለምትፈልጉ አዴ ብቻ አናግሯቸው የሳቸው መድሀኒት የደረሳችሁ ሼር አትርሱ እባካችሁ አዴ ብቻ አናግሯቸው

   መርጌታ ብናልፍ የባህል መድህኒት ቀማሚና ሰሪ ለማነኛውም በሽታ መዳን እዳለ አትርሱ ከምንሰራቸው በትንሹ
   09  18 43 46 89
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት በአለም ላይ የብዙ ትዳሮች መፍረስ  #የወሲብ_ግኑኝነት ጥሩ አለመሆን ነው። ስለዚህ የገጥመዎትን ችግር ቀጥታ በመጠዬቅ መፍትሔ በማግኘት ደስተኛ ህይወት ይኑራችሁ
ስንፈተ ወሲብን እንዴት ማከም ይቻላል?
የሀበሻ መድሃኒት ህክምና፡ መድሃኒቶች የደም ፍሰትን ይጨምራሉ እንዲሁም የፆታዊ ፍላጎት
በሚኖርበት ጊዜ ብልት በምላሹ እንዲቆም የሚያደርጉ ናቸው።
የብልት መጠንን መጨመር የሚችሉ መድሀኒቶችን አቅርበንላችኋል
1.የብልት አለመቆም ችግር
2.ቶሎ የመርጨት ችግር
3.የብልትን ቁመትና ውፍረት ማነስ ችግር
ካለብሆት በፍጥነት
09 18 43 46 89 ይደውሉ እና ያማክሩን
በፍጥነት ያሉበት ቦታ እናደርሳለን
ማሳሰቢያ  ከምንም የጎንዮሽ ጉዳት ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸውጨ
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት አለ
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
                   09 18 43 46 89
2.4K viewsYehuans, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:30:00 ‍ ምኞቴ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ሶስት▬▬▬

ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ፡፡ ንግግራቸዉ ወደ ቁጣ
እየተቀየረ ይመስላል፡፡
..."አይ አታዉቅም" አለች
..."የኔ ልጅ!" አሉ እማማ "ባለፈዉ ያባትሽ ሚስት በእኔ ምክንያት እንደሞተች
ነግሬሻለኃ?"
..."አዎ እማዬ ነግረሽኛል"
..."ስለዚህ የኔ ልጅ ኤዲም ባንቺ ምክንያት መጎዳት የለባትም፡፡ አንቺና ቢኒያም እንደሆናችሁ ሳጨርሱ አቀሩም፡፡ እኔ ለቢኒያም የምድርሽ የእናንተን መስማማት አይቼ ሳይሆን የኤዲን ፍቃደኝነት ጠይቄ ነዉ!"አሉት፡፡ ረድኤት ደስም አላት ግራ ተጋባችም፡፡ ቢኒያምን ልታገባዉ ነዉ ግን ደግሞ ኤዲ ባትፈቅድስ
..."እና ለኤዲ  ልትነግሪያት ነዉ እማዬ?"
..."አዎ ቀስ ብዬ እነግራታለሁ፡፡ አንቺ አታስቢ የኔ ልጅ" ብለዋት ከተቀመጡበት ተነስተዉ
ወደ ዉስጥ ገቡ፡፡ አባባ ሀብታሙ ከዘራቸዉን ይዘዉ ዉጭ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ እንደ አጋጣሚ ኤዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት አየቻቸዉና "አባባ ሀብታሙ ሰላም ኖት" አለቻቸዉ፡፡ እርሳቸዉም "ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን ሰላም ነሽ ወይ ኤዲ" ብለዉ መለሱላት፡፡
ከዚያም አጠገባቸዉ ቀረበችና ስለ ረዲ አንዳንድ ነገር ለማወቅ "አባባ ረዲን አትድሯትም እንዴ እድሜዋኮ እየሄደ ነዉ፡፡"አለቻቸዉ፡፡አባባ ሀብታሙም የሷን ጥያቄ ወደ ጎን አሉና "አንቺና ቢኒያም ከተጋባችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ኤዲ ይሄን ጥያቄ ከመለሰች ቡኋላ ቀጣዩ ጥያቄ ምን እንደሚሆን አዉቃለች፡፡ ለጥያቄያቸዉ
መልስ መስጠት ስላለባት ብቻ "አራተኛ አመታችንን ይዘናል" አለቻችዉ፡፡"ታዲያ ልጃችሁን ቤተሰቦችሽ ዘንድ አርጋችሁት ነዉ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡
..."አይይ አባባ..." አለቻቸዉ በረጅሙ የብሶት ትንፋሽ እየተነፈሰች፡፡ ተራርቀዉ
መቀመጣቸዉ እንጂ ትንፋሿ እንደ በርሃ ወበቅ ይጋረፋል፡፡
..."ምን ነዉ? የኔ ልጅ?" አሏት ጭንቀቷን ሲያዩ
..."አይ ምንም" አለችና አቀረቀረች ኤዲ፡፡ አባባ የሆነ ነገር እንዳለ ጠረጠሩ፡፡እሳቸዉም የልጅ ፍቅር ስላላቸዉ ጭንቀቷ ይገባቸዋል፡፡
"ልጅ አልወለድኩም አባባ..." አለቻቸዉ፡
አባባ ሁኔታዋን ሲያይዋት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባታል፡፡ እሷ ግን እንደምንም እየታገለች ፈገግ ለማለት ትሞክራለች፡፡ ምክንያቱም ልጃቸዉን ለባሏ ልትጠይቃቸዉ ነዉና፡፡ ከረጅም ዝምታና ፀጥታ ቡኃላ አባባ ተንፈስ አሉና "ባልሽ ቢኒያም ግን በጣም ጎበዝ ነዉ አደነቅኩት" አሏት፡፡ እሷም ለምን? እንዴት? በምን ምክንያት አደነቁት? ብላ አልጠየቀቻቸዉም፡፡ ቢኒ የሚደነቅ ጥሩ ሰዉ እንደሆነ ታዉቃለችና፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ እየሆነች ነዉ፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያም ረድኤትን ለትዳር ቢጠይቅ እምቢ እንደማይሉና በደስታ እንደሚድሩት
ከአባባ ሀብታሙ ሁኔታ መረዳት ችላለች፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያምን ይወዱታል፡፡ ደስ
አላት፡፡ ባሏን እሷዉ ልድረዉ ነዉ፡፡...ቢኒ ከስራ እንደመጣ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም፡፡
"ቢኒ ለረድኤት ቤተሰቦች ሽማግሌ መላክ አለብህ" አለችዉ፡፡
..."እንዴ ፈጠንሽሳ?" አላት ቢኒ
..."አዎ ፍቅሬ ሌላ የኔን ቢጤ ደሃ ካገባህኮ እኔን መፍታትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ አንተ
እንድትፈታኝ አልፈልግም፡፡ ሁሌም በፍቅርህ መኖር እፈልጋለሁ" አለችዉ እየተቅለሰለሰች፡፡
ይሄን ከማለቷ ብዙም ሳይቆዩ የቢኒያም ስልክ መልዕክት (ሜሴጅ) ገባ "ጢጢጥ
ጢጢጥ" ሜሴጁ ሲገባ የቢኒ ስልክ ያሰማዉ ድምፅ ነበር፡፡ ቢኒ ስልኩን አነሳና
የላኪዉን ስም ሲያይ በማማ በለጡ ስልክ ነዉ የተላከዉ "ረድኤት መሆን አለባት" አለ
በዉስጡ፡፡ ኤዲ እያየችዉ ነበር፡፡ ደንገጥ ብሎ ስታየዉ ፊቷ ክስም ይላል፡፡ እንደገና ፈገግ
ሲል እሷም አብራ ትፈካለች፡፡ ኤዲ ሁሌም ቢሆን በቢኒያም ደስታ ደስ ይላታል፡፡
"የኔ ፍቅር ምንድን ነዉ መልዕክቱ?" አለችዉ....ኤዲ ቢኒ ፈገግ ስላለበት ጉዳይ ለማወቅ ጓጓች፡፡ ቢኒ አሁንም እንደፈገገ ነዉ፡፡
" ንገረኛ ዉዴ?" አለችዉ፡፡ በአይኖቿ እየተማጸነች፡፡ ቢኒያም ሊነግራት ነበር ነገር ግን
ከረድኤት ጋር ከዚህ በፊት እንደተደዋወሉና በስልኩ መልዕክት እንደላከችለት ቀድሞ ለኤዲ
አልነገራትም ነበር፡፡ ትቆጣ ይሆን እንዴ? ፈራ፡፡ ከሷ መደበቅ ስላልፈለገና ኤዲ ብትቆጣም
ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡

✎ ክፍል አስራ አራት ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11 
     ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   
3.3K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ