Get Mystery Box with random crypto!

Best disk

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk B
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_lboch11 — Best disk
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_lboch11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42
የሰርጥ መግለጫ

🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩

📞 ስልክ፦ 0953873129
👉 @Z_afro02 ያነጋግሩ::

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-03 21:30:17 እበጂልኝ

ፍቅርሽ ክፉኛ ቢቀጣኝ
አንደበቴ ታስሮ
መናገር ቢያቅተኝ
መፍትሔ ፈልጌ
ደፍሬ መጣሁኝ።

ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ
አፌ ኩልትፍ ኩልትፍ
ላብድ ነዉ በፍቅርሽ
ብዬ ብጠይቅሽ
እስቲ አብደክ አሳዪኝ
ነበረ ምላሽኝ

ፍቅርሽ አጃጅሎኝ
እብደትን ሞከርኩት
ፀጉሬን አንጨብርሬ
ልብሴን ቀዳደድኩት
ወጣሁኝ ጎዳና
ብርዱን ተላመድኩት

ለካስ እብደት ውስጥ
ጥልቅ የሆነ ሚስጥር
የራስ ነፃ ዓለም
ጭንቀት የሌለበት
ፍቅርሽን ረስቼ
እብደት ተመችቶኝ
በዛው ቀጠልኩበት

ምን ይሆን ምላሽሽ
እንዲ ስሆን አይተሽ
መሥዋት መሆኔን
እንደፍላጐትሽ

ፀፀቱን ካልቻልሽው
እየነሳሽ ጤና
አንድ ላይ እንሁን
አንቺም እበጂና።

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
10.8K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 20:54:44 •••••● #ፍቅር_እና_ጉንፋን ●•••••
            ● ● ● ● ● ●
ከለታት አንድ ቀን ባንክ ቤት አየኋት
በጄ የያዝኩትን ብርቱካን ሰጠኋት
ሙሉ ማንነቴን ልቤን አስረከብኳት
                 ••●••
ና ካለች ሔዳለሁ ካለችበት ቦታ
ሰዓት አይገድበኝ ቀንም ሆነ ማታ
                 ••●••
    ሰኞለት ፒያሳ እሮብ መካኒሳ
ሀሙስ ደግሞ ቦሌ አርብ ቀን ጉለሌ
   እሁድና ቅዳሜ ከሷ ጋር ባብነት
አብረን እንውላለን በፍቅር ባንድነት
         ሚስቴ ስላት ባሌ
           ትለኛለች ሁሌ
አሁን ሁሉም ቀረ... ታሪክ ተቀየረ.....
                 ••●••
የኔ ውድ ፍቅር ብላ እንዳልጠራችኝ
ዛሬ ሁሉም ቀርቶ ለአይኗ ጠለ.....
ተመስገን ማለት ኑሮ አስተምሮኛል
ትናንት ፍቅር ይዞኝ ዛሬ ተሽሎኛል
የዘንድሮ ፍቅር ጉንፋን ሆኖብኛል
                 ••●••
     ፍቅር እንዲ ተራ በሆነባት አለም
አብሮ መዝለቅ እንጂ ማፍቀር ብርቅ አይደለም
                   ••●••
 
  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
9.5K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 22:10:12                      ወገኛ
   ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿» ‌✽‌┉┉┄┄

ልብሽ የሻተውን አልሻም የምትይ
ምንም እንዳልሆነ የምታስመስይ
ሀሳቤ እንዳልገባሽ ዞር በል የምትይ
ወገኛ ነሽ በጣም ጎበዝ አታላይ
          ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ፍቀጂልኝና አንድ እውነት ልናገር
አይንሽ አውርቶኛል አፍሽ ባይናገር
ፍቅርን ያህል ነገር ተሸክመሽ ባይሽ
ላግዝሽ ተጠጋሁ ሸክሙን ልካፈልሽ
አንቺ ግን ...
ወገኛ ነሽና አሻፈረኝ አልሺኝ
በፍቅር ብጠጋሽ በሀይል ገፋሺኝ
እኔማ አልተውሽም እከተልሻለሁ
ወገኛነትሽን ላስተውሽ ምያለሁ
           ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ያው ባትሰሚኝም ስላንቺ አወራለሁ
ያው ባታነቢውም ስላንቺ እፅፋለሁ
ያው ባንቃጠርም እጠብቅሻለሁ
ወገኛ ነሽና ምን ማድረግ እችላለሁ፡፡

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
11.4K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 20:50:10 ✦....

የኔ እህህ ማለት ላንተ ሙዚቃ ነው
ትዝታ ነው መውደድ ናፍቆት ነው ተረዳሁ
በትዝታ ሮሮ እዪኝ እንከሳው ...
አንደ ነበር እኮ ፍቅርህን ብረሳው
እድን ነበር እኮ ፍቅርህን ብረሳው

          ተኝቼ ላልተኛ መባነኑ ባሰኝ
          የት ሀገር ሆነህ ነው የምትቀሰቅኝ
Aster Awoke

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
10.3K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 18:18:41
በፅኑ እናወግዘዋለን !

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ አንዋር መስጊድ በሶላት ሰጋጅ ሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ቻናላችን መልካም ልቦች አጥብቃ ታወግዛለች !!

ፈጣሪ የቀደመ ሰላማችንን መልሶ ያድለን !

በፅኑ እናወግዘዋለን !

ይ ላ ሉን! ➢
@melkam_lboch11

#ሼር 
11.0K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 19:27:52 #የፍቅር_ፍቺዎች_ወይም_መዝገበ_ቃላት

የፍቅር ምንጭ - ፈጣሪ
የፍቅር መገለጫ - ድርጊት
የፍቅር ልጅ-ነፃነት
የፍቅር ውጤት - ደስታ
የፍቅር ቤተ ሙከራ - ልብ
የፍቅር መለኪያ - መስዋትነት
የፍቅር ጓደኞች - እምነትና ተስፋ
የፍቅር ዙፋን - ትዕግስት
የፍቅር ቋንቋ - ትህትና
የፍቅር መንገድ - ሠላም
የፍቅር ማሰሪያ - ይቅርታ

#ፍቅር_ያሸንፋል!

#ሠላማችሁ_ይብዛ!

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
12.4K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 21:50:12 . . .እንዳላጣሽ ፈራዉ. . .

በልጅነት ግዜ ገና በለጋ እድሜ
በማልችለው አቅሜ በፍቅር ታምሜ
ሳይፈታ ሲቀር የልጅነት ህልሜ
እንዳልሆነ ሁኖ ተሰበረ ቅስሜ
:
ከኔ ወድያ አፍቃሪ ከሷ ወድያ ፍቅር
ቢፈለግ ቢታሰሰ ላይገኝ በምድር
:
እኔም ከዛ ወድህ ብየ ነበር እኮ
ፍቅር በሷ ይብቃኝ ሌላም ሰው አይሻኝ
ብየ ነበር እኮ
:
ግና አንቺን ያየሁኝ ለት ያሁሉ ጀግንነት ፉከራየ ቀረ
ከእንግድህ ሰው በቃኝ ብሎ እንዳልነበረ
ልቤ ሰለ ፍቅርሽ ማሰብ መጨነቅ ጀመረ
:
መክፈቻውን ቁልፉን በጅሽ አስረክቤ
የከሰመው ህይወቴ በፍቅርሽ አበበ
:
የታመመው ልቤ ባንቺ አገገመ
መላው ሰውነቴ በፍቅርሽ ታከመ
     . . .ታዲያ ውዴ. . .
ያበበው ህይወቴን ፍሬውን ለማየት
እንዳላጣሽ ፈራሁ እኔም የእዛን እለት

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
13.1K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 08:12:27 ‍ ይድረስ ለ ፍቅሬ....

ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ፍቅሬ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለኔ
.........ይልቅስ ፍቅሬ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ከልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ምትመጭ ከሆነ መንገድ ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ከቀረሽም ቅሪ
ወደኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሸ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ባዶ ጮማ እንዳልጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፊቴም ውበት የለው
ልቤም የእባ ናዳ ክህደት ያቆሰለው
ግን ይሄን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ
ንፁህ ልቤ ገዝቶሽ ወደኔ ከመጣሽ
እጠብቅሻለሁ በደስታ ፈንጥዠ
በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅር ይዠ።

ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
14.7K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 10:53:20 . . .
ደሞ እንደ መስቀል ወፍ እንደ አደይ አበባ
ህይወት እንደሚያድስ መስከረም ሲጠባ
እናፍቃታለሁ እንደ ህጻን ልጅ
አትሂድብኝ የትም አትውጣ ከደጅ. . .
. . . እንደ ናርዶስ ሽቶ እንደ ፈዋሽ ጸበል
ማነው ያልተመኛት የኔናት የማይል
የትም ዞራ ውላ ስትመለስ ድንገት
ያጣል መሸሸጊያ አይኔ የሚገባበት
ማን ለምን ይላታል ማን አለ ጠያቂ
የቱ ሽማግሌ የትኛው አዋቂ. . .

ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
18.6K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 14:30:21 . . .
ደሞ እንደ መስቀል ወፍ እንደ አደይ አበባ
ህይወት እንደሚያድስ መስከረም ሲጠባ
እናፍቃታለሁ እንደ ህጻን ልጅ
አትሂድብኝ የትም አትውጣ ከደጅ. . .
. . . እንደ ናርዶስ ሽቶ እንደ ፈዋሽ ጸበል
ማነው ያልተመኛት የኔናት የማይል
የትም ዞራ ውላ ስትመለስ ድንገት
ያጣል መሸሸጊያ አይኔ የሚገባበት
ማን ለምን ይላታል ማን አለ ጠያቂ
የቱ ሽማግሌ የትኛው አዋቂ. . .

  ይ ላ ሉን! ➢

ሼር 
@melkam_lboch11
19.3K views 🅉ᴇʀᴜ αʙᴇʟ , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ