Get Mystery Box with random crypto!

ከመጽሐፍት መንደር💠💫

የቴሌግራም ቻናል አርማ manbabemulusewyaderegal — ከመጽሐፍት መንደር💠💫
የቴሌግራም ቻናል አርማ manbabemulusewyaderegal — ከመጽሐፍት መንደር💠💫
የሰርጥ አድራሻ: @manbabemulusewyaderegal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.80K
የሰርጥ መግለጫ

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና
🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨
🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥
ለማንኛውም አስተያየት
@manbabemuluyadergal_bot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-27 21:17:33 ሰላም እንዴት አመሻችሁ

ነፍስ ሲያፈቅር ልቦለድ ፡ለጠየቃችሁ ይለቀቃል በትዕግስት ጠብቁ አንባቢያን እስከሆናችሁ ድረስ እኛን ልትረዱን ይገባል ይለቀቃል
182 viewsጌሰም, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:15:28 ህይወት እጣፈንታ ወይስ ምርጫ?ምክንያት

ወንድሜ ሀሪፍ ጥያቄ ነዉ ያነሳኸዉ እስኪ ተወያዩበት ከነምክንያታችሁ
239 viewsጌሰም, edited  17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:25:15 ማንን በፍጥነት ይመልሰዋል

አንዲት ሴት አንድ ሆቴል ውስጥ አልጋ ይዛ ነበር፡ ምሽት ላይ በሯን አንድ ሰው አንኳኳው

በሩን ስትከፍተው ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ሰው ነው። ሰውየውም ‹‹ውይ በጣም ይቅርታ ተሳስቼ ነው...የራሴ ክፍል ስለመሠለኝ ነው በማለት ሄደ ሴትዮዋ ግን ሰውየው ሌባ ወይም ነፍሰ ገዳይ ይሆናል ብላ በመጠራጠር ወዲያውኑ ለፖሊስ ደወለች

ጥያቄው ሴትየዋ ሰውየውን ለምን ሌባ ወይም ነፍሰ ገዳይ ነው ብላ ጠረጠረችው
299 viewsጌሰም, 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:07:06 መኪናዋን አንቀሳቀሰችና ወደ መንገድ አስገባችው..በዝግታ መንዳት ጀመረች.. በእስፖኪዬና ወደኃላ ተመለከተች …አዎ እነሱም እንደእሷ ነው ያደረጉት …እየተከተሏት ነው፡፡ ‹‹ይሄውልህ አቶ ሄኖክ በደንብ ስማኝ ..በሚቀጥለው መጠመዘዣ ታጥፈው ወደኃላ ካልተመለሱ ለፖሊስ ደውዬ አሳስራቸዋለው፡›› ‹‹ተይ እንጂ… ምንን መሰለሽ?…..››አላስጨረሰችውም ስልኳን ጠረቀመችው፡፡. ወዲያው መልሶ ደወለላት.. .ዘጋችበትና…
305 viewsጌሰም, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:50:01 መኪናዋን አንቀሳቀሰችና ወደ መንገድ አስገባችው..በዝግታ መንዳት ጀመረች.. በእስፖኪዬና ወደኃላ ተመለከተች …አዎ እነሱም እንደእሷ ነው ያደረጉት …እየተከተሏት ነው፡፡
‹‹ይሄውልህ አቶ ሄኖክ በደንብ ስማኝ ..በሚቀጥለው መጠመዘዣ ታጥፈው ወደኃላ ካልተመለሱ ለፖሊስ ደውዬ አሳስራቸዋለው፡››
‹‹ተይ እንጂ… ምንን መሰለሽ?…..››አላስጨረሰችውም ስልኳን ጠረቀመችው፡፡.
ወዲያው መልሶ ደወለላት.. .ዘጋችበትና አንድ ደህንነት የሚሰራ ባለስልጣን ወዳጆን ስልክ ከስልኳ ውስጥ ፈለገችና ዝግጁ ሆና መጠባበቅ ጀመረች፡፡ መታጠፊያውን አልፋ ነዳች ...ከኃላ ያሉት አጃቢዎቾ ምን እንደሚያደርጉ በጉጉት እና በስጋት እየተጠባበቀች ነው ‹‹ወይ እግዜር ይሰጣችሁ›አለች.ደስ ያላት እንደፈለገችው ባለችው መታጠፊያ ታጥፈው ወደኃላ ስለተመለሱ ነው.፡፡፡


ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@itsmezeeddr
አድርሱኝ


ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ እንዳይረሳ
387 viewsጌሰም, 20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:48:42 ‹‹እንደዛ ይከሰታል እንዴ?››
‹አዎ…ይሄ እኮ የተለመደ ነው፡፡አእምሮችንን ልከ እንደኮምፒተር በይው…በሆነ አጋጣሚ የሆነ ቫይረስ ወደ ኮምፒተራችን ውሰጥ ሲገባና ሲያጠቃ እንደየጥቃቱ መጠን የተከማቹ መረጃዎች መሰረዝ እና ኮራብትድ መሆን እንደሚያጋጥም ሁሉ አዕምሮም በሆነ አጋጣሚ ሲጎዳ ተመሳሳዩ ነው የሚከሰተው፡፡በነገራችን ላይ ብዙ ጊዜ በጋዜጣ ፎቶውን በማስወጣት ቤተሰቦቹ እንዲያገኙት ሞክሬያለው..ሲደክመኝ ነው የተውኩት…ምን አልባት ከአዲስ አበባ በጣም አርቀው ሚኖሩ የገጠር ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡››
‹‹እና አሁን ምን ይሻላል?››ሲፈን ነች የበለጠ ግራ በመጋባት የማያልቅ ጥያቄዋን ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ …እኔም በጣም ፈርቼያለው…አየሽ አሁን ጭንቅ ላይ ሰላለን እና የግድ ማወቅ አለብሽ ብዬ ስለወሰንኩ ነው እውነቱን የነገርኩሽ እንጂ ..ቢላል ማለት ለእኔ አሁንም እውነተኛ ልጄ ነው…ብዙ መስዋዕትነት የከፈልኩበት በጥልቀት የምወደው ልጄ ነው…..ምን አልባትም ህይወቴን ልሰጥለት የምችል ብቸኛ ሰው ቢኖር እሱ ብቻ ነው..ለእሱ ስል ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬለው...ላገባው ከምፈልገው ከ5 አመት የፍቅር ጎደኛዬ ተለያይቼያለው….ምክንያቱም ከእሱ እና ከእኔ አንዳችንን ምረጪ ስላለኝ…..፡፡ብዙ ገንዘቤን ለህክምናውም ሆነ ያስደስቱታል ብዬ የማስበውን ነገር ለማሟላት አውጥቼያለው.ጎደኞቼ በሚያገኙት ገቢ ኪኒሊክ ሲገነቡ እኔ እሱ ላይ ነው ኢንቨስት ያደረኩት..እንደዛም በማድረጌ በዛም በጣም ደስተኛ ነኝ..ግን ቢሆንም መስዋዕትነቴ ሁሉ እንዲህ በቀላሉ መና እንዲቀር አልፈልግም… ልጄ እንዲገኝልኝ እፈልጋለው..ልጄ ሙሉ በሙሉ ድኖ ልክ እንደእኩየቹ ያፈቀራትን አግብቶ ልጅ እንዲወልድና አያት እንደያደርገኝ እፈልጋለው…ልጄ ጭንቅላቱ ውስጥ ያለውን ጥልቅ እውቀት ወደመጽሀፍ ቀይሮ አስደማሚ መረጃዎችን ለትውልዱ እንዲያስተላልፍ እፈልጋለው..ልጅ ፓሪስ ወይም ሎንዶን ላይ አስደማሚ ስዕሎቹን ይዞ በመሄድ ከአለም አቀፍ ሰዓሊዎች ጋር የስእል ኤግዚቪሽን እንዲያቀርብና አለምን ሁሉ እንዲያስደምም እፈልጋለው…ልጄ ባለው አስደማሚ የአስትሪኖሚ ዕውቀት ናሳ ተቀጥሮ የሚወዳት ማርሰ ላይ ደርሶ እንዲመጣ እፈልጋለው…ከእዚህ ሁሉ በላይ ግን ልጄ ተገኝቶልኝ ማቀፍ ነው የምፈልገው…አዎ ጥዋት ከእንቅልፌ ባንኚ አይኔን ስገልጥ አልጋዬ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብሎ መንቃቴን ሲጠብቅ እንዳገኘው ነው የምፈልገው…‹‹እማዬ ተነሽ ቁርሴን እንድትሰጪኝ ፈልጋለው›› ሲለኝ መስማት ነው የምፈልገው...አዎ አሁን ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቼ ልጄን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው››
‹‹እኔም እንደዛው››አለች ሲፈን በተሰበረ ድምፅ ….የፕሮፌሰሯ ንግግር ይበልጥ ልቧ እንዲሰባበር እና ሀዘኗም ጥልቅ ሆነ እንዲያማት ነው ያደረገው. .ስልኳን አነሳችና ደወለች
‹‹ኤርሚ ይቅርታ አሁንም መልሼ ደወልኩ››
‹‹ችግር የለም.ምን ልታዝ?››
‹‹ሽልማቱን 500ሺ አድርገው››
‹‹እርግጠኛ ነኝ?››
‹‹አዎ መላው የአዲስ አባ ህዝብ በየጉራንጉሩና በየጎደናው ግር ብሎ ወጥቶ እዲፈልገውና በአፋጣኝ እንዲያገኙልኝ እፈልጋለው..አጥቼወው ብዙ መቆየት አልችል››
‹‹እሺ ባልሺው አስተካክለዋለው››
ስልኩን ዘጋችው.እና ካቆመችበት ለፕሮፌሰሯ ማውራቷን ጀመረች
‹‹በቃ አይዞሽ.እናገኘዋለን››
‹‹እንደአፈፍሽ ያድርግልን..ለማንኛውም አንቺ እራስሽን ጠብቂ….እንደ አጋጣሚ ብቻሽን አግኝቶሽ እንዳይጎዳሽ››
‹‹አንቺም ሊገድለኝ እንደሚችል ታስቢያለሽ?››
‹‹እኔ አላውቅም.ልጄን እንደማውቀው ዝንብም ለመግደል እንኳን ጭካኔው የለውም ይሁን እንጂ አንድ በጣም የሚያፈቅራት ልጅ ጥላው እንደሄደችና ጥላው የሄደችው ደግሞ ከእሱ የተሻለ ሌላ ተመራጭ ሰው ለማግባት እንደሆነ የሚያስብ አንድ የአዕምሮ ህመምተኛ ሰው የተባለውን ነገር አያደርግም ብሎ በድፍረት መናገር አይደለም ለእኔ ለባለሞያዋ ለተራውም ሰው ይከብዳል...በዛ ላይ ሊያደርገወ እንደሚችል ግልፅ ማመላከቻ በተደጋጋሚ ሰጥቶናል
‹እኔን ለማጥቃት አስቦ እንኳን ከተደበቀበት መውጣት ችሎ ብናገኘው ምኞቴ ነው››ሲፈን ነቸ ግራ ገብቶት ግራ የተጋባ ንግግር የተናገረችው፡፡
‹‹ልጄ ከአለበት ተገኝቶ ቀጥታ ወደእኔ ወደእናቱ ወይም የህክምና እርዳታ ወደሚያገኝበት ሆስፒታል ነው መሄድ ያለበት …ቀጥታ አንቺን አግኝቶ ጥቃት ከሰነዘረብሽ ቡኃላ ምን እንደሚደርግ ታውቂያለሽ ..ወዲያውነው የሚያጠፋው፡፡››
‹‹እሺ እጠነቃለው.አሁን ልሄድ›ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡ሁለቱም .እየተደዋወሉ መረጃ ሊለዋወጡ ተነጋረው ተለያዩ..
ሲፈን መኪናዋ ውስጥ ገባችና ወደቤተሰቦቾ ቤት መንዳት ጀመረቸ…ወዲያው ግን አንድ ነገር ታዘበች.ቅድም ከፕሮፌሰሯ ጋር ተቀጣጥራ ከቤት ወደእዚህ ሰትመጣ ከኃላዋ ሚከታሏት ሁለት ጥቋቁር ማርቼዲስ ሚኪኖች እንዳሉ የሆነ መጠራራር በውስጥ ገብታ ነበር ግን ደግሞ ወዲያው ዘንግታው ነበር.አሁን መኪናዋን አስነስታ ስትሄድ እነዛው ተመሳሳይ መኪናዎች በቅርብ እርቀት ሲከተሏት እያች ነው..ይበልጥ አርግጠኛ ለመሆን በማትፈልገው መንገድ ታጠፈች.. አልተሳሳተችም .. አብረዋት ታጠፉ.
ምንድነው ጉዱ…‹‹ደግሞ የገባውበትን ጣጣ ሳልወጣ ሌላ ጣጣ ሊመጣኘ ነው እንዴ..?አሁን የመንግስት ግብር በማጭበርበር ብለው እስር ቤት ቢወረውሩኝስ.?››እንዴት አድርጌ ነው በደቂቃዎች ሽርፍራፊ ዝም ብሎ ከአየር ላይ በውስጦ የተሰነቀረ ስጋት ነበር.
‹‹እንዴት ላድርግ?›› እራሷን ነው ምትጠይቀው…መልስ ከማግኘቷ በፊት ስልኳ ጠራ….. ዳር ይዛ መኪናዋን አቆመች...ከኃላዋ እየተከተሏት የነበሩት መኪኖችም ርቀታቸውን እንደጠበቁ ቆሙ…ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ ሆነባት ..በሀሳቡ እየተብሰለሰለች ስልኩን አነሳችው፡፡
‹እሺ ሄኖክ›
‹‹ሰላም ነሽ እኔ ፍቅር?››
‹‹ሰላም ነኝ..››
‹‹በሚቀጥለው ሳምንት .ማለቴ የፊታችን እሁድ ሽማግሌ ልልክ መሆኑን ልነግርሽ ነው››
‹‹የምን ሽማግሌ? ማን ጋ?››
‹‹እናንተ ቤት ነዋ…እናትና አባሽ ጋር….ቆንጅዬ ልጃቸውን እንዲሰጡኝ››አንጀቷ ቅጥል አለ...እሷ ሰማይ ምድሩ ተገለባብጦባት የምትይዘውን የምትጨብጠውን አጥታ በስቃይ ላይ እያለች እሱ በቅንጦት ቀን ስለሚደረግ ሽማግሌ መላክ ያወራል…አሁን ከእሱ ጋር ለመጨቃጨቅ አቅሙም ፍላጎቱም የላትም…
‹‹እንደፈለክ›
‹‹ለምን አሁን ወዳአለሁበት አትመጪም.ስለሁኔታው በዝርዝር እንነጋጋራለን፡››
‹‹አልችልም ስራ ይዤያለው››
‹‹አረ ተይ..ስለምንሽ የእኔ ፍቅር››
‹‹አልችልም አልኩህ …በዛ ላይ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ የማናጀምንት ስብሰባ አለብኝ›
‹‹ማናጀመንት ማለት ከእናትና ከአባትሽ ጋር ነው?››ሳያስበው አመለጠው
‹‹አንተ ቆይቆይ .. ምን አልክ?›››
‹‹አይ ማለቴ..››
‹‹የምን ማለቴ ነው..ያለውበትን እንዴት አወቅክ?››
‹‹ያው አለ አይደል.ማለቴ….አዎ ስልክ ስደውልልሽ እኮ ያለሽበትን ቦታ….››
አላስጨረሰችውም‹‹<በቃ በቃ..አሁኑኑ ከኃላ እንዲከተሉኝ ያሰማረሀቸውን ውሾችህን አስወግድልኝ››
‹‹ለራስሽው ብዬ እኮ ነው.እባክሽ እንደዛ አታድርጊ ከአደጋ ሊጠብቁሽ ነው የሚከታተሉሽ›
307 viewsጌሰም, 20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:48:42 ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ-18
//
ቢላል የገባበት ከጠፋ አምስት ቀን አልፎታል፡፡የሲፈንን ቤት መስታወት አርግፎ ከወጣ ቡኃላ እዚህ ቦታ አይቼዋለው የሚል አንድ ሰውም አልተገኘም፡፡በዚህን ወቅት ለሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ተደርጎና ፎቶውም ተበትሎ በቤተሰቦቹም በመንግስትም እየታሰሰ ይገኛል፡፡
ሲፈን እና ፕሮፈሰር ቦሌ ካሊዲስ ካፌ አንድ ጠረጵዛ ከበው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ሁለቱም በጥልቅ ሀዘን ላይ ናቸው..ሁለቱም አይናቸው ከወዲህ ወዲያ እየተንከባለለ የሆነ ሰው ፊት ለማየት ይቅበዘበዛል…
‹‹-አሁን ምን ብናደርግ ይሻለናል?››ፕሮፈሰሯ ነች ጠያቂዋ
‹‹እኔም እኮ ግራ ግብት አለኝ.እንደው የሚቀርበው ዘመድ ወይም ሌላ ቦታ የሚኖር የቤተሰብ አበላት ጋር እየዞርን ብንፈልገው››
‹‹ምን መሰለሽ…››ፕሮፌሰሯ መልስ ልትሰጣት አፎን ስትከፍት የሲፈን ስልክ ጠራ… አነሳችው፡፡
‹‹ወ.ሪት ሲፈን ኤርሚያስ ነኝ… ፈልገሺኝ ነበር መሰለኝ….ይቅርታ ከሸሪኮቻችን ጋ ስብሰባ ላይ ነበርኩ››
‹‹ጥሩ ነው...አዎ ፈልጌህ ነበር››አለችው.፡፡ኤርሚያስ ማለት የሲፈን ካማፓኒ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ የሚሰራ ከፍተኛ የኮሚኒኬሽን ኤከስፐርት ነው፡፡ከሞያው ጋር ተያይዞ ከሚዲያ ተቋማት ገርም ሆነ ከሚያስተዳድሯቸው ሰዎቹ ጋ ከፍተኛ ግንኙነት ነው ያለው…እና የፈለገችው ይሄንን ችሎታውን ልትጠቀምበት ነው፡፡
‹‹እሺ ምን ልታዝ?››
‹‹አንድ ውለታ አንድትውልልኝ እፈልገለው››
‹‹ደስ ይለኛል…ምንድነበር?››
‹‹ካምፓኒው ውስጥ ያለህን ኃላፊነት ላልተወሰነ ጊዜ ለሌላ ሰው ውክልና ስጥ››
‹‹ምነው በሰላም….?የተበላሸ ነገር አለ እንዴ?››ምቾት ባጣና በደነገጠ ቃና ጠየቃት...እሱ የሚያውቀው ስራውን በትጋት እና ብቃት እየሰራ እንዳለ ነው…‹‹ከስራ የሚያሳግድ ምን እንከን ተገኘብኝ?››እራሱን በራሱ የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡››.እርግጥ ነው ከስራው ቢሰናበት ወዲያው በእለቱ የፈለግውን አይነት ስራ ብዙ ቦታ አማርጧ መቀጠር እንደሚችለው ያውቃል….ግን አሁን ያለበትን ካምፓኒ ይወደዋል...የስራ ነፃነቱን ይወደዋል…አሁን ደውላ ስራህን በውክልና አስተላልፍ በሚል ዜና እያስደነገጠችው ያለችውን ሀለቃውን በጣም ያከብራታል….ለእሷ ስኬት ከልቡ ይጥራል.እና ምን ተፈጠረ…?
ሲፈን ማብራራቷን ቀጠለች‹‹ሰላም ነው…ምን መሰለህ አሁን የቅርቤ ሰው ጠፍቶብኝ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ነው ያለውት….የጠፋው ሰው ትንሽ የእምሮ በሽተኛ ነው…ፎቶውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በኢሜልህ አያይዤልሀለው..››
‹‹ይህን በመስማቴ በጣም አዝናለው…እንዳደርግ የምትፈልጊውን ነገር ንገሪኝ…የምችልውን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ሙሉ ትኩረትህን እዚህ ጉዳይ ላይ አድርገህ ሁሉንም ኮኔክሽኖችህን ተጠቀምና አፋልግልኘ ፤በቴሌቪዝን ጣቢያዎች፤ በኤፍ ኤም ጣቢያዎች፤ በፌስ ቡክ ብቻ ይሆና ባልከው መንገድ ሁሉ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ይበተን…ለደላሎች፤ ለታክሲ ሺፌሮች እኔ እንጃ ብቻ መደረግ ያለበትህን ሁሉ አድረርግ…የ ወጪው መጠን ከግምት ውስጥ አይገባም››
‹‹እሺ… እንዳልሽ አደርጋለው… አንቺ ምንም አታስቢ ››
‹‹ይሄውልህ ኤርሚ.. ይንን ልጅ እንዳገኘው ከረዳሀኝ የእድሜ ልክ ውለታ እንደጣልክብኝ ቁጠረው››
‹ኸረ ግድ የለም….ደግሞ ላንቺ እንኳን ይሄን ..››
‹‹ከዚህ በላይ ልታደርግልኝ የምትችለው ነገር አይኖርም...ይሄ በሌላ ሰው ለእኔ ሊያደርግልኝ የሚችለው የመጨረሻ ውለታ ነው፡፡እሱ እስኪገኝ እኔም እንደጠፋው ቁጠረው...እሱን ስትፈልገው እኔን እየፈለከኝ እንደሆነ እየያሰብክ አድርገው፡፡››
‹‹እሺ ገብቶኛል›አለ.እውነታው ግን አልገባውም ነበር..ጭንቅላቱ ሙሉ በጥያቄ እንደተሞላ ነበር…ጠፋ የተባለው ወንድሟ እንዳልሆነ ያውቃል…ለቤተሰቦቾ ብቸኛ ልጅ እንደሆነች የታወቀ ነው….‹‹.እና ይሄን ያህል ከራሷ ጋር የመታነፃፅረው ምኗ ቢሆን ነው…?ለዛውም የእምሮ ህመምተኛ ለሆነ ሰው››
ስልኩን ዘጋችውና ትኩረቷን ፊት ለፊቷ ወደተቀመጠችው ፕሮፌሰር ለመመለስ እየጣረች
‹‹ምን እያወራን ነበር?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹የሚሄድበት ዘመድ ወይም የቅርብ ሰው ካለ እያልሽኝ ነበር..?››
‹‹አዎ …ቆይ አንድ የረሳውት ነገር አለ..››አለችና ስልኳን መልሳ ደወለች
‹‹ሄሎ ኤርሚ››
‹‹አቤት ?
‹‹አንድ ነገር እረስቼ .. ላገኘው 200 ሺ ብር ሽልማት ወዲያው እንደምንከፍል ጨምርበት.›
‹‹ሀለት መቶ ሺ ብር?››
‹‹ምነው ?አነሰ ?››
‹‹አረ እንደውም በዛ››
‹‹እንግዲያው ይሁን 200ሺ ብር ሽልማት እከፍላለው››ስልኩን ዘጋችው፡፡
‹‹ይቅርታ ፕሮፌሰር የቅርብ ዘመድ ወይም ቤተሰብ የለውም?››
‹‹ማንም የለም››
‹‹እንዴት? ቢያነስ አባቱስ?››
ፕሮፌሰሯ አንገቷን አቀረቀረችና በፀጥታ ተዋጠች…ሲፈን ግራ ገባት.‹‹ምነው ችግር አለ..?አባቱ በህይወት የለም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ስለአባቱ ምንም አላውቅም››
ማይታመን ነገር ነው እንደ ፕሮፌሰሯ አይነት ለምድር ለሰማዩ የከበደ ስብዕና ያላት ሰው ከማይታወቅ አባት ወላደች ብሎ ማን ያምናል?.ተደፋራ ነው….?.ጭፈራ ቤት አንድ ቀን ከተዋወቀችውና አብራው ካደረችው ሰው ነው ያረገዘችው…?ብዙ ብዙ የቢሆናል መላ ምቶች በአእምሮዋ ተመላለሱባት..የፕሮፌሰሯ መልስ ግን ከግምቷ በተቃራኒ ነበር
‹‹ቢላል ከእኔ ሌላ የሚያውቀው ሰው መኖሩን እኔ አላውቅም…››
‹አሁንም አልገባኝም?››
‹‹ሲፈን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ….ቢላል የወለድኩት ልጄ አይደለም››
‹‹ምን ?በፈጣሪ…እና ወላጆቹ የት ናቸው?››
‹‹ማንም የሚያውቅ ሰው የለም…እኔ ያገኘው ከማስተማር ስራዬ ጎን ለጎን አማንኤል ሆስፒታል አሰራ ስለነበር እዛ ህክምና ላይ ሳለ የዛሬ 8 ዓመት ገዳማ ነው፡፡እዛ የገባው ከመንገድ ላይ ሰዎችን ተተናኮለ ተብሎ በመንግስት የፃጥታ አካሎቸ አስገዳጅነት ነበር፡፡በወቅቱ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ እኔ እንድከታተለው ተመደብኩ..ከዛ በሂደት ሳጠናውበጣም የተለየ ስብዕና ያለው..በእውቀቱ የመጠቀ፤ ከአምስት ቋንቋዎች በላይ አቀላጥፎ የሚናገር፤በማንኛውም ርዕስ ላይ ከአቭሬጅ በላይ እውቀት ያለው..በተወሰኑት ለምሳሌ በአስትሮኖሚ ፤በስነፅሁፍ፤ በፍልስፍና ላይ በጣም የጠለቀ እውቀት ያለው…እንደቀልድ እየጫጨረ የሚጥላቸው ስዕሎች አስደማሚ የሆኑ ተአምረኛ ሰው ሆኖ አገኘውት፡..ይህም ቢሆን ግን የጤንነቱ ሁኔታ በጣም ከባድና ክሪቲካል የሚባል አይነት ነበር፡፡..ቡኃለ ግን ከአምስት አመት አታካቸ የህክምና ክትትል ቡኃላ በጣም አበረታችና አስደሳች የጤና መሻሻል አመጣ..ከእኔ ጋርም ያለን ቀረቤታ በጣም የጠበቀ ሆነ ...ልጄ ቢሆን ስል ተመኘው…ልጄ ሁን ብዬ ስጠይቀው እናቴ ብሎ ጠራኝ….በደስታ ፈነጠዝኩ…ኃላፊነቱን ወስጄ ከሆስፒታል አስወጣውት…ልጄ ብዬ ወደቤቴ ወሰድኩት….የእውነትም ፍፅም ልጄ ሆነ….እኔም እናቱ ሆንኩ፡፡
‹‹እየነገርሺኝ ያለውን ነገር ማመን ይቸግረኘኛል››
‹‹እመኚ እውነታው ነው የነገርኩሽ›››
‹‹እሺ ይሁን አንቺ ጋር ጤናው ተሻሽሎ ከመጣ ቡኃላ ስለቤተሰቡ አልጠየቅሺውም?››
‹‹ብዙ ጊዜ ጠይቄው ነበር…መልሱ አላውቅም ነው፡፡የልጅነት ጊዜውን ትዝታ ሙሉ በሙሉ ከእምሮው የተሰረዘ ይመሰለኛል፡፡››
278 viewsጌሰም, 20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:47:27 አዳም እና ሔዋን

ሴት ግጥም ስትገጥም ሔዋን ትወሳለች
በስንኞች ሽሙጥ አዳምን ታማለች
ለምሳሌ
ሰይጣን እኔን ሳይሆን አዳምን ተጠግቶ
ቢሰብከው ሊያስተው በለስ አመልክቶ
ግንዱን ያስቀር ነበር ዛፉን ሙሉ በለቶ
ወንድ ግጥም ሲገጥም አዳም ይሞካሻል
ዘፍጥረት ተጠቅሶ በስንኝ ይሟሻል
ምሳሌ ካላቹኝ
አንተ አዳም እራስ ነክ ይላል ቅዱስ ቃሉ
ሄዋን ደግሞ አንገት ነሽ በለው ያወራሉ
ታዲያ ይች ሔዋን ሞትን ባታመጣ
አፈር ባልቀመስን ባልደረሰን ጣጣ

እኔን ግን ሲገባኝ አዳም እና ሔዋን የሚያቆራኛቸው
ሰው የሚባል ሙጫ አለ መሀላቸው

  የአብ ቃል
309 viewsጌሰም, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:47:27   ፈጣሪያችን _ሥማ
     °°°°°°°°_
     ጦርነት ረሀብ የለዉም ማቆሚኣ
      ይብቃ በለን አንተ ፈጣሪያችን ስማኣ
      እኛ የሰዉ ልጅ ነን አንችል መከራ
      ከጠላት ጠብቀን ሰይጣናዊ ሴራ
      ህይወት ረከሰ ረገፈ እንደቅጠል
      ህፃን ትልቅ ሳይል አለቀ በጥቅል
     ሠላም ርቆናል በመጣብን ጣጣ
    ይበቃችሁ በልና መለካሙን ቀን አምጣ
   
             አሜን

    ግጥም :እርስትአብ /ፍፄ/
          @Erstabfiza
298 viewsጌሰም, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:24:25 የተመስጦ በየትኛው ስፍራ

ተመስጦ /አርምሞ/ ውስጣዊና ውጫዊ ማንነታችንን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። በአካላዊ,አዕምሮአዊ,ስሜታዊና መንፈሳዊ ማንነታችን መሀከል ሚዛናዊና የተጣጣመ መስተጋብር እንዲኖር በድልድይነት ያገለግላል።
ከውስጣዊና ውጫዊው አላማችሁ የሰመረ ግንኙነትን በፈጠራችሁ ቁጥር በሁሉ መልኩ ሚዛናዊ የሆነ ህይወትን ትመራላችሁ።
                        
                             ግሪር አሊካ

     ከአመታት በፊት ለተወሰነ ጊዜያት በማንኛውም ነገር እርካታ የማጣት የድብርት ስሜት  ውስጥ ገብቼ ነበር። በዚህ ወቅት በአለም ላይ ይህን ስሜቴን የሚቀይር ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለ ይሰማኝ ነበር። መልካም ጓደኞች፣ ቆንጆ ቆንጆ ልጆች ፣ የተሟላ ጤና ፣ ድንቅ የፈጠራ ክሕሎትና ሌሎችን ነገሮች የነበሩኝ ብሆንም በነዚህ ሁሉ ምንም አይነት የእርካታና የደስታ ስሜትን ልጎናፀፍ አልቻልኩም። ምድራዊ አለም ባቀረበልኝ መልካም ስጦታ በመደሰት ፈንታ የብቸኝነትን የባዶነት ስሜቴ እየበረታ ሄደ። ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ስለመንፈሳዊ ተግባራት ስለተመስጦ ሳነብ አዳዲስ አለማት ይገለፁልኝ ጀመር። በተስፋ ከመጠበቅ አንዱ በር ሲዘጋ ብዙ በሮች ይፈታሉ። የሚለው አባባል እውነት ነው።

    ተመስጦ ከውስጣዊ ማንነቴ ጋር የሰመረ ቁርኝት እንድፈጥር እንደሚያደርግ ባውቅም በፀጥታ ይህን ተግባር መከወኑ በመጀመሪያ አካባቢ ከብዶኝ ነበር። አለማዊ ግዴታዎችን ከመወጣት ልጆቼ ጋር ሆኜ እየከወንኩ ከመንፈሳዊው አለም ጋር ያልተቋረጠ መስተጋብር እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር። በዚህ ያልተቋረጠ ጥልቅ ፍለጋዬ ውስጥ ሳለው ተመስጦን የፈለጉትን ስራ እየሰሩና በየትኛውም ስፍራ ሆነው መከናወን የሚቻልበትን የተግባራዊ መንፈሳዊነት ቴክኒክን ለመግኘት ቻልኩ። ይህ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነውና አዕምሮን የሚያጎለብተው ቴክኒክ ፈጣሪ ሩሲያዊው ፈላስፋ ጆርጅ ጉርዲዮፍ ነበር። ጉርዲዮፍ ይህን የተመስጦ ሂደት  "ራስን ማስታወስ" በማለት ከሰየመ ከዋኙ የታዛቢነት ሚና እንዲኖረው የሚያደርግን ጽንሰ-ሀሳብ ፈጥሯል።

የተገኘ #ራስን መሆን ከሚል መፅሀፍ
352 viewsጌሰም, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ