Get Mystery Box with random crypto!

ነፍስ ስታፈቅር ምዕራፍ-18 // ቢላል የገባበት ከጠፋ አምስት ቀን አልፎታል፡፡የሲፈንን ቤት መስታ | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ-18
//
ቢላል የገባበት ከጠፋ አምስት ቀን አልፎታል፡፡የሲፈንን ቤት መስታወት አርግፎ ከወጣ ቡኃላ እዚህ ቦታ አይቼዋለው የሚል አንድ ሰውም አልተገኘም፡፡በዚህን ወቅት ለሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ተደርጎና ፎቶውም ተበትሎ በቤተሰቦቹም በመንግስትም እየታሰሰ ይገኛል፡፡
ሲፈን እና ፕሮፈሰር ቦሌ ካሊዲስ ካፌ አንድ ጠረጵዛ ከበው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ሁለቱም በጥልቅ ሀዘን ላይ ናቸው..ሁለቱም አይናቸው ከወዲህ ወዲያ እየተንከባለለ የሆነ ሰው ፊት ለማየት ይቅበዘበዛል…
‹‹-አሁን ምን ብናደርግ ይሻለናል?››ፕሮፈሰሯ ነች ጠያቂዋ
‹‹እኔም እኮ ግራ ግብት አለኝ.እንደው የሚቀርበው ዘመድ ወይም ሌላ ቦታ የሚኖር የቤተሰብ አበላት ጋር እየዞርን ብንፈልገው››
‹‹ምን መሰለሽ…››ፕሮፌሰሯ መልስ ልትሰጣት አፎን ስትከፍት የሲፈን ስልክ ጠራ… አነሳችው፡፡
‹‹ወ.ሪት ሲፈን ኤርሚያስ ነኝ… ፈልገሺኝ ነበር መሰለኝ….ይቅርታ ከሸሪኮቻችን ጋ ስብሰባ ላይ ነበርኩ››
‹‹ጥሩ ነው...አዎ ፈልጌህ ነበር››አለችው.፡፡ኤርሚያስ ማለት የሲፈን ካማፓኒ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ የሚሰራ ከፍተኛ የኮሚኒኬሽን ኤከስፐርት ነው፡፡ከሞያው ጋር ተያይዞ ከሚዲያ ተቋማት ገርም ሆነ ከሚያስተዳድሯቸው ሰዎቹ ጋ ከፍተኛ ግንኙነት ነው ያለው…እና የፈለገችው ይሄንን ችሎታውን ልትጠቀምበት ነው፡፡
‹‹እሺ ምን ልታዝ?››
‹‹አንድ ውለታ አንድትውልልኝ እፈልገለው››
‹‹ደስ ይለኛል…ምንድነበር?››
‹‹ካምፓኒው ውስጥ ያለህን ኃላፊነት ላልተወሰነ ጊዜ ለሌላ ሰው ውክልና ስጥ››
‹‹ምነው በሰላም….?የተበላሸ ነገር አለ እንዴ?››ምቾት ባጣና በደነገጠ ቃና ጠየቃት...እሱ የሚያውቀው ስራውን በትጋት እና ብቃት እየሰራ እንዳለ ነው…‹‹ከስራ የሚያሳግድ ምን እንከን ተገኘብኝ?››እራሱን በራሱ የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡››.እርግጥ ነው ከስራው ቢሰናበት ወዲያው በእለቱ የፈለግውን አይነት ስራ ብዙ ቦታ አማርጧ መቀጠር እንደሚችለው ያውቃል….ግን አሁን ያለበትን ካምፓኒ ይወደዋል...የስራ ነፃነቱን ይወደዋል…አሁን ደውላ ስራህን በውክልና አስተላልፍ በሚል ዜና እያስደነገጠችው ያለችውን ሀለቃውን በጣም ያከብራታል….ለእሷ ስኬት ከልቡ ይጥራል.እና ምን ተፈጠረ…?
ሲፈን ማብራራቷን ቀጠለች‹‹ሰላም ነው…ምን መሰለህ አሁን የቅርቤ ሰው ጠፍቶብኝ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ነው ያለውት….የጠፋው ሰው ትንሽ የእምሮ በሽተኛ ነው…ፎቶውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በኢሜልህ አያይዤልሀለው..››
‹‹ይህን በመስማቴ በጣም አዝናለው…እንዳደርግ የምትፈልጊውን ነገር ንገሪኝ…የምችልውን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ሙሉ ትኩረትህን እዚህ ጉዳይ ላይ አድርገህ ሁሉንም ኮኔክሽኖችህን ተጠቀምና አፋልግልኘ ፤በቴሌቪዝን ጣቢያዎች፤ በኤፍ ኤም ጣቢያዎች፤ በፌስ ቡክ ብቻ ይሆና ባልከው መንገድ ሁሉ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ይበተን…ለደላሎች፤ ለታክሲ ሺፌሮች እኔ እንጃ ብቻ መደረግ ያለበትህን ሁሉ አድረርግ…የ ወጪው መጠን ከግምት ውስጥ አይገባም››
‹‹እሺ… እንዳልሽ አደርጋለው… አንቺ ምንም አታስቢ ››
‹‹ይሄውልህ ኤርሚ.. ይንን ልጅ እንዳገኘው ከረዳሀኝ የእድሜ ልክ ውለታ እንደጣልክብኝ ቁጠረው››
‹ኸረ ግድ የለም….ደግሞ ላንቺ እንኳን ይሄን ..››
‹‹ከዚህ በላይ ልታደርግልኝ የምትችለው ነገር አይኖርም...ይሄ በሌላ ሰው ለእኔ ሊያደርግልኝ የሚችለው የመጨረሻ ውለታ ነው፡፡እሱ እስኪገኝ እኔም እንደጠፋው ቁጠረው...እሱን ስትፈልገው እኔን እየፈለከኝ እንደሆነ እየያሰብክ አድርገው፡፡››
‹‹እሺ ገብቶኛል›አለ.እውነታው ግን አልገባውም ነበር..ጭንቅላቱ ሙሉ በጥያቄ እንደተሞላ ነበር…ጠፋ የተባለው ወንድሟ እንዳልሆነ ያውቃል…ለቤተሰቦቾ ብቸኛ ልጅ እንደሆነች የታወቀ ነው….‹‹.እና ይሄን ያህል ከራሷ ጋር የመታነፃፅረው ምኗ ቢሆን ነው…?ለዛውም የእምሮ ህመምተኛ ለሆነ ሰው››
ስልኩን ዘጋችውና ትኩረቷን ፊት ለፊቷ ወደተቀመጠችው ፕሮፌሰር ለመመለስ እየጣረች
‹‹ምን እያወራን ነበር?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹የሚሄድበት ዘመድ ወይም የቅርብ ሰው ካለ እያልሽኝ ነበር..?››
‹‹አዎ …ቆይ አንድ የረሳውት ነገር አለ..››አለችና ስልኳን መልሳ ደወለች
‹‹ሄሎ ኤርሚ››
‹‹አቤት ?
‹‹አንድ ነገር እረስቼ .. ላገኘው 200 ሺ ብር ሽልማት ወዲያው እንደምንከፍል ጨምርበት.›
‹‹ሀለት መቶ ሺ ብር?››
‹‹ምነው ?አነሰ ?››
‹‹አረ እንደውም በዛ››
‹‹እንግዲያው ይሁን 200ሺ ብር ሽልማት እከፍላለው››ስልኩን ዘጋችው፡፡
‹‹ይቅርታ ፕሮፌሰር የቅርብ ዘመድ ወይም ቤተሰብ የለውም?››
‹‹ማንም የለም››
‹‹እንዴት? ቢያነስ አባቱስ?››
ፕሮፌሰሯ አንገቷን አቀረቀረችና በፀጥታ ተዋጠች…ሲፈን ግራ ገባት.‹‹ምነው ችግር አለ..?አባቱ በህይወት የለም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ስለአባቱ ምንም አላውቅም››
ማይታመን ነገር ነው እንደ ፕሮፌሰሯ አይነት ለምድር ለሰማዩ የከበደ ስብዕና ያላት ሰው ከማይታወቅ አባት ወላደች ብሎ ማን ያምናል?.ተደፋራ ነው….?.ጭፈራ ቤት አንድ ቀን ከተዋወቀችውና አብራው ካደረችው ሰው ነው ያረገዘችው…?ብዙ ብዙ የቢሆናል መላ ምቶች በአእምሮዋ ተመላለሱባት..የፕሮፌሰሯ መልስ ግን ከግምቷ በተቃራኒ ነበር
‹‹ቢላል ከእኔ ሌላ የሚያውቀው ሰው መኖሩን እኔ አላውቅም…››
‹አሁንም አልገባኝም?››
‹‹ሲፈን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ….ቢላል የወለድኩት ልጄ አይደለም››
‹‹ምን ?በፈጣሪ…እና ወላጆቹ የት ናቸው?››
‹‹ማንም የሚያውቅ ሰው የለም…እኔ ያገኘው ከማስተማር ስራዬ ጎን ለጎን አማንኤል ሆስፒታል አሰራ ስለነበር እዛ ህክምና ላይ ሳለ የዛሬ 8 ዓመት ገዳማ ነው፡፡እዛ የገባው ከመንገድ ላይ ሰዎችን ተተናኮለ ተብሎ በመንግስት የፃጥታ አካሎቸ አስገዳጅነት ነበር፡፡በወቅቱ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ እኔ እንድከታተለው ተመደብኩ..ከዛ በሂደት ሳጠናውበጣም የተለየ ስብዕና ያለው..በእውቀቱ የመጠቀ፤ ከአምስት ቋንቋዎች በላይ አቀላጥፎ የሚናገር፤በማንኛውም ርዕስ ላይ ከአቭሬጅ በላይ እውቀት ያለው..በተወሰኑት ለምሳሌ በአስትሮኖሚ ፤በስነፅሁፍ፤ በፍልስፍና ላይ በጣም የጠለቀ እውቀት ያለው…እንደቀልድ እየጫጨረ የሚጥላቸው ስዕሎች አስደማሚ የሆኑ ተአምረኛ ሰው ሆኖ አገኘውት፡..ይህም ቢሆን ግን የጤንነቱ ሁኔታ በጣም ከባድና ክሪቲካል የሚባል አይነት ነበር፡፡..ቡኃለ ግን ከአምስት አመት አታካቸ የህክምና ክትትል ቡኃላ በጣም አበረታችና አስደሳች የጤና መሻሻል አመጣ..ከእኔ ጋርም ያለን ቀረቤታ በጣም የጠበቀ ሆነ ...ልጄ ቢሆን ስል ተመኘው…ልጄ ሁን ብዬ ስጠይቀው እናቴ ብሎ ጠራኝ….በደስታ ፈነጠዝኩ…ኃላፊነቱን ወስጄ ከሆስፒታል አስወጣውት…ልጄ ብዬ ወደቤቴ ወሰድኩት….የእውነትም ፍፅም ልጄ ሆነ….እኔም እናቱ ሆንኩ፡፡
‹‹እየነገርሺኝ ያለውን ነገር ማመን ይቸግረኘኛል››
‹‹እመኚ እውነታው ነው የነገርኩሽ›››
‹‹እሺ ይሁን አንቺ ጋር ጤናው ተሻሽሎ ከመጣ ቡኃላ ስለቤተሰቡ አልጠየቅሺውም?››
‹‹ብዙ ጊዜ ጠይቄው ነበር…መልሱ አላውቅም ነው፡፡የልጅነት ጊዜውን ትዝታ ሙሉ በሙሉ ከእምሮው የተሰረዘ ይመሰለኛል፡፡››