Get Mystery Box with random crypto!

‹‹እንደዛ ይከሰታል እንዴ?›› ‹አዎ…ይሄ እኮ የተለመደ ነው፡፡አእምሮችንን ልከ እንደኮምፒተር በይ | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

‹‹እንደዛ ይከሰታል እንዴ?››
‹አዎ…ይሄ እኮ የተለመደ ነው፡፡አእምሮችንን ልከ እንደኮምፒተር በይው…በሆነ አጋጣሚ የሆነ ቫይረስ ወደ ኮምፒተራችን ውሰጥ ሲገባና ሲያጠቃ እንደየጥቃቱ መጠን የተከማቹ መረጃዎች መሰረዝ እና ኮራብትድ መሆን እንደሚያጋጥም ሁሉ አዕምሮም በሆነ አጋጣሚ ሲጎዳ ተመሳሳዩ ነው የሚከሰተው፡፡በነገራችን ላይ ብዙ ጊዜ በጋዜጣ ፎቶውን በማስወጣት ቤተሰቦቹ እንዲያገኙት ሞክሬያለው..ሲደክመኝ ነው የተውኩት…ምን አልባት ከአዲስ አበባ በጣም አርቀው ሚኖሩ የገጠር ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡››
‹‹እና አሁን ምን ይሻላል?››ሲፈን ነች የበለጠ ግራ በመጋባት የማያልቅ ጥያቄዋን ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ …እኔም በጣም ፈርቼያለው…አየሽ አሁን ጭንቅ ላይ ሰላለን እና የግድ ማወቅ አለብሽ ብዬ ስለወሰንኩ ነው እውነቱን የነገርኩሽ እንጂ ..ቢላል ማለት ለእኔ አሁንም እውነተኛ ልጄ ነው…ብዙ መስዋዕትነት የከፈልኩበት በጥልቀት የምወደው ልጄ ነው…..ምን አልባትም ህይወቴን ልሰጥለት የምችል ብቸኛ ሰው ቢኖር እሱ ብቻ ነው..ለእሱ ስል ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬለው...ላገባው ከምፈልገው ከ5 አመት የፍቅር ጎደኛዬ ተለያይቼያለው….ምክንያቱም ከእሱ እና ከእኔ አንዳችንን ምረጪ ስላለኝ…..፡፡ብዙ ገንዘቤን ለህክምናውም ሆነ ያስደስቱታል ብዬ የማስበውን ነገር ለማሟላት አውጥቼያለው.ጎደኞቼ በሚያገኙት ገቢ ኪኒሊክ ሲገነቡ እኔ እሱ ላይ ነው ኢንቨስት ያደረኩት..እንደዛም በማድረጌ በዛም በጣም ደስተኛ ነኝ..ግን ቢሆንም መስዋዕትነቴ ሁሉ እንዲህ በቀላሉ መና እንዲቀር አልፈልግም… ልጄ እንዲገኝልኝ እፈልጋለው..ልጄ ሙሉ በሙሉ ድኖ ልክ እንደእኩየቹ ያፈቀራትን አግብቶ ልጅ እንዲወልድና አያት እንደያደርገኝ እፈልጋለው…ልጄ ጭንቅላቱ ውስጥ ያለውን ጥልቅ እውቀት ወደመጽሀፍ ቀይሮ አስደማሚ መረጃዎችን ለትውልዱ እንዲያስተላልፍ እፈልጋለው..ልጅ ፓሪስ ወይም ሎንዶን ላይ አስደማሚ ስዕሎቹን ይዞ በመሄድ ከአለም አቀፍ ሰዓሊዎች ጋር የስእል ኤግዚቪሽን እንዲያቀርብና አለምን ሁሉ እንዲያስደምም እፈልጋለው…ልጄ ባለው አስደማሚ የአስትሪኖሚ ዕውቀት ናሳ ተቀጥሮ የሚወዳት ማርሰ ላይ ደርሶ እንዲመጣ እፈልጋለው…ከእዚህ ሁሉ በላይ ግን ልጄ ተገኝቶልኝ ማቀፍ ነው የምፈልገው…አዎ ጥዋት ከእንቅልፌ ባንኚ አይኔን ስገልጥ አልጋዬ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብሎ መንቃቴን ሲጠብቅ እንዳገኘው ነው የምፈልገው…‹‹እማዬ ተነሽ ቁርሴን እንድትሰጪኝ ፈልጋለው›› ሲለኝ መስማት ነው የምፈልገው...አዎ አሁን ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቼ ልጄን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው››
‹‹እኔም እንደዛው››አለች ሲፈን በተሰበረ ድምፅ ….የፕሮፌሰሯ ንግግር ይበልጥ ልቧ እንዲሰባበር እና ሀዘኗም ጥልቅ ሆነ እንዲያማት ነው ያደረገው. .ስልኳን አነሳችና ደወለች
‹‹ኤርሚ ይቅርታ አሁንም መልሼ ደወልኩ››
‹‹ችግር የለም.ምን ልታዝ?››
‹‹ሽልማቱን 500ሺ አድርገው››
‹‹እርግጠኛ ነኝ?››
‹‹አዎ መላው የአዲስ አባ ህዝብ በየጉራንጉሩና በየጎደናው ግር ብሎ ወጥቶ እዲፈልገውና በአፋጣኝ እንዲያገኙልኝ እፈልጋለው..አጥቼወው ብዙ መቆየት አልችል››
‹‹እሺ ባልሺው አስተካክለዋለው››
ስልኩን ዘጋችው.እና ካቆመችበት ለፕሮፌሰሯ ማውራቷን ጀመረች
‹‹በቃ አይዞሽ.እናገኘዋለን››
‹‹እንደአፈፍሽ ያድርግልን..ለማንኛውም አንቺ እራስሽን ጠብቂ….እንደ አጋጣሚ ብቻሽን አግኝቶሽ እንዳይጎዳሽ››
‹‹አንቺም ሊገድለኝ እንደሚችል ታስቢያለሽ?››
‹‹እኔ አላውቅም.ልጄን እንደማውቀው ዝንብም ለመግደል እንኳን ጭካኔው የለውም ይሁን እንጂ አንድ በጣም የሚያፈቅራት ልጅ ጥላው እንደሄደችና ጥላው የሄደችው ደግሞ ከእሱ የተሻለ ሌላ ተመራጭ ሰው ለማግባት እንደሆነ የሚያስብ አንድ የአዕምሮ ህመምተኛ ሰው የተባለውን ነገር አያደርግም ብሎ በድፍረት መናገር አይደለም ለእኔ ለባለሞያዋ ለተራውም ሰው ይከብዳል...በዛ ላይ ሊያደርገወ እንደሚችል ግልፅ ማመላከቻ በተደጋጋሚ ሰጥቶናል
‹እኔን ለማጥቃት አስቦ እንኳን ከተደበቀበት መውጣት ችሎ ብናገኘው ምኞቴ ነው››ሲፈን ነቸ ግራ ገብቶት ግራ የተጋባ ንግግር የተናገረችው፡፡
‹‹ልጄ ከአለበት ተገኝቶ ቀጥታ ወደእኔ ወደእናቱ ወይም የህክምና እርዳታ ወደሚያገኝበት ሆስፒታል ነው መሄድ ያለበት …ቀጥታ አንቺን አግኝቶ ጥቃት ከሰነዘረብሽ ቡኃላ ምን እንደሚደርግ ታውቂያለሽ ..ወዲያውነው የሚያጠፋው፡፡››
‹‹እሺ እጠነቃለው.አሁን ልሄድ›ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡ሁለቱም .እየተደዋወሉ መረጃ ሊለዋወጡ ተነጋረው ተለያዩ..
ሲፈን መኪናዋ ውስጥ ገባችና ወደቤተሰቦቾ ቤት መንዳት ጀመረቸ…ወዲያው ግን አንድ ነገር ታዘበች.ቅድም ከፕሮፌሰሯ ጋር ተቀጣጥራ ከቤት ወደእዚህ ሰትመጣ ከኃላዋ ሚከታሏት ሁለት ጥቋቁር ማርቼዲስ ሚኪኖች እንዳሉ የሆነ መጠራራር በውስጥ ገብታ ነበር ግን ደግሞ ወዲያው ዘንግታው ነበር.አሁን መኪናዋን አስነስታ ስትሄድ እነዛው ተመሳሳይ መኪናዎች በቅርብ እርቀት ሲከተሏት እያች ነው..ይበልጥ አርግጠኛ ለመሆን በማትፈልገው መንገድ ታጠፈች.. አልተሳሳተችም .. አብረዋት ታጠፉ.
ምንድነው ጉዱ…‹‹ደግሞ የገባውበትን ጣጣ ሳልወጣ ሌላ ጣጣ ሊመጣኘ ነው እንዴ..?አሁን የመንግስት ግብር በማጭበርበር ብለው እስር ቤት ቢወረውሩኝስ.?››እንዴት አድርጌ ነው በደቂቃዎች ሽርፍራፊ ዝም ብሎ ከአየር ላይ በውስጦ የተሰነቀረ ስጋት ነበር.
‹‹እንዴት ላድርግ?›› እራሷን ነው ምትጠይቀው…መልስ ከማግኘቷ በፊት ስልኳ ጠራ….. ዳር ይዛ መኪናዋን አቆመች...ከኃላዋ እየተከተሏት የነበሩት መኪኖችም ርቀታቸውን እንደጠበቁ ቆሙ…ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ ሆነባት ..በሀሳቡ እየተብሰለሰለች ስልኩን አነሳችው፡፡
‹እሺ ሄኖክ›
‹‹ሰላም ነሽ እኔ ፍቅር?››
‹‹ሰላም ነኝ..››
‹‹በሚቀጥለው ሳምንት .ማለቴ የፊታችን እሁድ ሽማግሌ ልልክ መሆኑን ልነግርሽ ነው››
‹‹የምን ሽማግሌ? ማን ጋ?››
‹‹እናንተ ቤት ነዋ…እናትና አባሽ ጋር….ቆንጅዬ ልጃቸውን እንዲሰጡኝ››አንጀቷ ቅጥል አለ...እሷ ሰማይ ምድሩ ተገለባብጦባት የምትይዘውን የምትጨብጠውን አጥታ በስቃይ ላይ እያለች እሱ በቅንጦት ቀን ስለሚደረግ ሽማግሌ መላክ ያወራል…አሁን ከእሱ ጋር ለመጨቃጨቅ አቅሙም ፍላጎቱም የላትም…
‹‹እንደፈለክ›
‹‹ለምን አሁን ወዳአለሁበት አትመጪም.ስለሁኔታው በዝርዝር እንነጋጋራለን፡››
‹‹አልችልም ስራ ይዤያለው››
‹‹አረ ተይ..ስለምንሽ የእኔ ፍቅር››
‹‹አልችልም አልኩህ …በዛ ላይ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ የማናጀምንት ስብሰባ አለብኝ›
‹‹ማናጀመንት ማለት ከእናትና ከአባትሽ ጋር ነው?››ሳያስበው አመለጠው
‹‹አንተ ቆይቆይ .. ምን አልክ?›››
‹‹አይ ማለቴ..››
‹‹የምን ማለቴ ነው..ያለውበትን እንዴት አወቅክ?››
‹‹ያው አለ አይደል.ማለቴ….አዎ ስልክ ስደውልልሽ እኮ ያለሽበትን ቦታ….››
አላስጨረሰችውም‹‹<በቃ በቃ..አሁኑኑ ከኃላ እንዲከተሉኝ ያሰማረሀቸውን ውሾችህን አስወግድልኝ››
‹‹ለራስሽው ብዬ እኮ ነው.እባክሽ እንደዛ አታድርጊ ከአደጋ ሊጠብቁሽ ነው የሚከታተሉሽ›