ከላይ ከላዩ ስታይው ይመስላል..ሰውየውን አንቺ ስለማታውቂያቸው ብትጠራጠሪ አይገርመኝም..እንደኔ ግን ሲናገሩ ከአንደበታቸው እየሰማሽ በማስታወሻሽ ከፃፍሻቸው ከ50 በላይ ትንቢቶች መካከል በሰላሳ አመታት , ውስጥ ከ45 በላዩ ምንም ሳይዛነፉ እንዳሉት ሆነው ብታይና የቀሩትም በመከናወን ላይ መሆናቸውን ምልክት እያየሽ ቢሆን ከመሀከሉ አንዱን ነጥለሽ የምትጠራጠሪበት አቅም ይኖርሻል?…ለምሳሌ ከመሞታቸው ከአመት በፊት እራሷቸው የሚመቱበትን ቀን ሰዓቱን ከነደቂቃው እኔ በአካል ባለውበት ተናግረው ነበር.የሆነው እንዳሉት ነበር..ለዛ ደግሞ ምስክር ነኝ..ባለቤቴ በሞተች ጊዜ እምረሬ እንዳላዝን በህይወት ሳለው ተመልሳ ባላሰብኩት ሁኔታ እቤቴ ድረስ መጥታ ዳግም እንደማገኛት ነግረውኛል..ለዛም ነው ሀያአምስት አመት ሙሉ ከቤቴ ብዙም ሳርቅ መስኮት አቅራቢያና በረንዳ ላይ ሳይተክተኝ በመቀመጥ ውጭ ውጭ እያየው ስጠብቃት ማለቴ ስጠብቅሽ የነበረው››ብለው ክፍሉን ለብቻዋ ትተውላት ወጡ፡፡
አየር ወደውስጧ በረጅሙ ሳበች .መልሳ ለቀችች…መልሳ ሳበችት..ከዛ ወደውጭ መልሳ ለቀቀችው.. ከነበረችበት ቅዣት መሳይ እውነታ ውስጥ ለመውጣት እያደረገችው ያለ ጥረትነው…የተረጋጋች ሲመስላት የተሰጣትን ሳጥኑን ቀስ ብላ ከፈተች….ውስጡ በፎቶዎችና በደብዳቤዎች ተሞልቷል.. ደብዳቤዎቹን ባሉበት ትታ ፎቶዎቹን አነሳችና ለማየት ተዘጋጀች…
ልቧ ትርትር አለባት…..የሆነ የሚቀስፍ አይነት ስሜት…ትንፋሽ ሚያቆራርጥ ...ከጀርባ ማጅራትን የሚጨመድድ አስጨናቂ ስሜት….ለምንድነውእንዲህ አይነት ስሜት የተሰማት? አታውቅም፡፡. ሁለት የአስራዎቹ መጨረሻ ላይ ያሉ ልጆች እርስ በርስ ተጣብቀው የተነሷቸው ፎቶዎችን ነው የምታየው፡፡ስትገምት የሄኖክ እናትና አባት ፎቶ ነው፡፡.በፍቅር እፍ ብለው ያበዱ አፍላ ወጣቶች ፎቶ…አናም ደግሞ የእህትና ወንድም ፎቶ…፡፡እሷን ምን አስደነገጣት..?የልጁን አይን የሆነ ቦታ ታውቀዋለች….፡፡የት ነው?.በጣም ቅርቧ የሆነ ግን ደግሞ የዘነጋችው ሰው አይኖች ናቸው፡፡
ሁለተኛውን ፎቶ ማየት ጀመረች..ጎረምሳው ለብቻውን የተነሳው ነው...የሆነ ጥቅጥቅ ያለ የባህርዛፍ ደን ውስጥ ከተራራ ላይ የሚንፎለፎል ፏፏቴ ያለበት ድንቅ መልካአ ምድር ያለበት ቦታ… ውሀውን በእጆቹ እየዘገነ የተነሳው ፎቶ ነው…
ሶስተኛው የቤተሰብ ፎቶ ነው .አባተና እናታቸውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ባሉበት ሁለቱ ፍቅረኛሞች ጎን ለጎን ሆነው እጃቸው ተቆላልፎ እየተያ የተነሱት…
ምንድነው ነገሩ? የምታያቸው ፎቶዎች ሁሉ ዛሬ ለመጀመሪያ ቀን እንዳየቻቸው ሳይሆን ከአመታት በፊት አገላብጣ አስኪሰለቻት አይታ ያስቀመጠችውና ዛሬ ከረሳችበት ቦታ ፈልጋ በማውጣት ከአመታት ቡኃላ ከእንደገና አቧራውን እያራገፈች እያየችው ያለ የራሷ ታሪክ ነጋሪ ፎቶ መስሎ ነው እየተሰማት ያለው…
እስኪሰለቻት እያንዳንዱን ፎቶ እያገላበጠች አየች .አዝነው በመኮሳትር የተነሱት..ተደስተው በፈግግታ የተነሱት...በጋለ ፍቅር ላይ ሆነወ የተነሱት...በኩርፊያ ተገፋፍተው የተነሱት ..ከጓደኞቻቸው መካከል በመሰራረቅ እየተያዩ የተነሱት...ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው የተነሱት. በጥምቀት ጭፈራ ላይ የተነሱት….በዘመድ ሰርግ ላይ የተነሱት….ፎቶው ቁጥር ስፍር የለውም….ግን ሳትጠግብ ለጊዜውም ቢሆን ማየቱን አቆረጠችና ሰብስባ አንድ ላይ አስቀመጠች…..ከዛ ወደ ደብዳቤው ለመግባት ተዘጋጀች…
አንድን ወረቀት ከውስጡ መዘዘችና ከፈተች.. አትኩራ አየችው..ፊደሎቹ ከወረቀቱ ላይ እየተነሱ በአየር ላይ ሲከረባባቱ እየታያት ነው..የቤቱ ኮርኒስም አብሮቸው እየተገለባበጠባት ነው…ከተቀመጠችበት የአልጋው ጠርዝ .ሸርተት አለችና ወደኃላዋ ወደቀች….እሷም ልክ እንደፊደሎቹ እየተገለባበጠች በደመና ሰረገላ ተጭና ወደ ሰማየ ሰማያት ነጎደች.. ከስንት ደቂቃ ቡኃላ እንደሆነ ባታውቅም ከሆነ ከማታውቀው ፕላኔት ላይ ስትንሳፈፍ ቆይታ እንደተመለሰች አይነት ስሜት ተሰማት …ቀስ በቀስ ዓይኖቾን ስትገልጥ በቀኟ ሽማግሌው በግራዋ ደግሞ የሄኖክ እህት ከበዋት በድንጋጤና በፍራቻ ግንባሯን እና ልቧን በቀዝቀዛ ውሀ በረጠበ ጨርቅ ሲያረሰርሱላት አገኘች
‹‹ምን ሆኜ ነው?››ለመጀመሪያ ጊዜ የጠየቀችው ጥያቄ ነበር፡
‹‹ሰላም ነሽ…?ትንሽ ደክሞሽ ነው?››ሽማግሌው ናቸው የመለሱላት
‹‹እህቴ አሁን ደህና ነሽ..?.ምን ይሰማሻል?››
‹‹ምንም አይሰማኝም.. ደህና ነኝ››
‹‹ምን ላምጣልሽ…? ምን ትፈልጊያለሽ?››
‹‹ተያት አታድክሚያት .አሁን እርፍት ታድርግበት…ተነሽ እንውጣላት.››ሽማግሌው ቀድመው ተነስተው ወደውጭ መራመድ ጀመሩ…ልጅቷም ተከተለቻቸው
‹‹አንዴ ላስቸግርሽ..ቦርሳየን ከሄኖክ ክፍል ፈልጌ ነበር››
‹‹አሁን አመጣልሻለው…››ብላ ወጣች….ወዲያው አምጥታ ሰጠቻትና ብቻዋን እንድትሆን በራፉን ዘግታላት ሄደች፡፡
እየፈራች በሚንቀጠቀጥ እጇ ቦርሳዋን ከፈተች…በቀደም የልደቷ ቀን ቢላል በአናቱ በኩል በስጦታ መልክ የላከላትን መልዕክት ነው ያወጣችው...ስዕሉን እዛው ተወችና ፅሁፉን አውጥታ ገለጠች .ቅድም ከየችው ደብዳቤ ጋር ጎን ለጎን አድርጋ አስተያየችው….የፈጣሪ ያለህ !!!እንዴት የሁለት የተለያዩ ሰዎች የእጅ ፅሁፍ በዚህ መጠን ሊመሳሰል ይችላል?፡፡የአያንደንደ ፊደል ቅርፅ…የፊደል አጠጣጣሉ…መጫረሻ ላይ የሚያሳርፋችው ፊርማዎች ሳይቀሩ ፍፅም የተመሳሰሉ ብቻ ሳይሆኑ አንድ አይነት ናቸው፡፡ምን አይነት አጋጣሚ ነው?፡፡
የቢላላን ደብዳቤ ወደቦርሳዋ መልሳ አስቀመጠችና ከሳጥኑ ከወጡት ደብዳቤዎች አንዱን መዛ ማንበብ ጀመረች፡፡
//
ግንቦት 2/1976
ሁለት ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ በሱፍ አበባ መካክል እንደሚስማሩ እንደ ሚዳቆ ግልገሎች ናቸው፡፡
መግቢያው ከመፅሀፍ ቅዱስ ነው የወሰድኩት ..
ውዴ እክፍሌ ፊት ለፊት የተከልሻቸው አበቦች አድጋውና አብበው ዛሬ የተወሰኑት ከውስጣቸው መፈንዳት ጀምረዋል.. ሌሎቹ ደግሞ ከዛም አልፋው ባለቀለም አበባዎችና ማፍራት ላይ ናቸው፡፡አበቦቹ ባንቺ ጣቶች ተዳብሰው በፍቅር የተተከሉ የተፈጥሮ ፀጋዎች ስለሆኑ በማለዳ ተነሽቼ ከማደሪያዋ እየወጣች ባለችው ፀሀይ እየተደመምኩ ስራቸውን እኮተኩታላው…የእለት ምግባቸውን በተገቢው መጠን እና አይነት ያገኙ ዘንድ አፈር አስታቅፋቸዋለው…ከጥማቸው እስኪረኩ ድረስ ተራ በተራ የጠራና የጠለለ ንፅህ ውሀ አጠጣቸዋለው፡፡እናም በወጣው በገባው ቁጥር አጠገባቸው በርከክ ብዬ በሹክሹክታ ሳላዋራቸውና ለእንቺ ያለኝን የሚንበለብ ፍቅር ሳልነግራቸው አልፌ አላውቅም፡፡እና ደግሞ በፅሞና እንደሚሰሙኝ አውቀለው….፡፡
ከንፈሮቼ ተነቃንቀው አንቺን በተመለከተ ውዳሴ ማሰማት በሚጀምሩበት ቅፅበት ቅጠሎቻቸውን ማርገብገብ ይጀምራሉ፡፡ወዲያው ደግሞ የሚያደነዝዝ ገነታዊ ማዕዛቸውን ማህደራቸውን ከፍተው በመልቀቅ አካባቢውን ሲያውዱት እታዘበለው…..የተወሰኑት አበቦች ደግሞ ከመካከላቸው ልክ ትርኢት እንደሚያሳይ አስማተኛ ቀለማቸውን እያየዋቸው ይቀያይራሉ…እያለ ይቀጥላል
መጀመሪያውን ደብዳቤ አንብባ በመጨረስ ሀለተኛውን ከፈተች...በሌላ ቀን በተለየ ስሜት የተፃፈ ነው..፡፡ለሞቾ የሄኖክ እናት ከፍቅረኛዋ ከሀያ ምናምን አመት በፊት የተፃፈ ደብዳቤ….አሁን በዚህን ሰዓት ለእሷ አንደተፃፈ የልቧን ምት እያናረ….የደም ዝውውሯን እያፈጠነ ያለ ስሜት ቀሳፊ መልዕክት እንዴት ሆነ..?ማንበቧን ቀጠለች፡፡