Get Mystery Box with random crypto!

አዳም እና ሔዋን ሴት ግጥም ስትገጥም ሔዋን ትወሳለች በስንኞች ሽሙጥ አዳምን ታማለች ለምሳሌ ሰይ | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

አዳም እና ሔዋን

ሴት ግጥም ስትገጥም ሔዋን ትወሳለች
በስንኞች ሽሙጥ አዳምን ታማለች
ለምሳሌ
ሰይጣን እኔን ሳይሆን አዳምን ተጠግቶ
ቢሰብከው ሊያስተው በለስ አመልክቶ
ግንዱን ያስቀር ነበር ዛፉን ሙሉ በለቶ
ወንድ ግጥም ሲገጥም አዳም ይሞካሻል
ዘፍጥረት ተጠቅሶ በስንኝ ይሟሻል
ምሳሌ ካላቹኝ
አንተ አዳም እራስ ነክ ይላል ቅዱስ ቃሉ
ሄዋን ደግሞ አንገት ነሽ በለው ያወራሉ
ታዲያ ይች ሔዋን ሞትን ባታመጣ
አፈር ባልቀመስን ባልደረሰን ጣጣ

እኔን ግን ሲገባኝ አዳም እና ሔዋን የሚያቆራኛቸው
ሰው የሚባል ሙጫ አለ መሀላቸው

  የአብ ቃል