Get Mystery Box with random crypto!

የተመስጦ በየትኛው ስፍራ ተመስጦ /አርምሞ/ ውስጣዊና ውጫዊ ማንነታችንን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

የተመስጦ በየትኛው ስፍራ

ተመስጦ /አርምሞ/ ውስጣዊና ውጫዊ ማንነታችንን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። በአካላዊ,አዕምሮአዊ,ስሜታዊና መንፈሳዊ ማንነታችን መሀከል ሚዛናዊና የተጣጣመ መስተጋብር እንዲኖር በድልድይነት ያገለግላል።
ከውስጣዊና ውጫዊው አላማችሁ የሰመረ ግንኙነትን በፈጠራችሁ ቁጥር በሁሉ መልኩ ሚዛናዊ የሆነ ህይወትን ትመራላችሁ።
                        
                             ግሪር አሊካ

     ከአመታት በፊት ለተወሰነ ጊዜያት በማንኛውም ነገር እርካታ የማጣት የድብርት ስሜት  ውስጥ ገብቼ ነበር። በዚህ ወቅት በአለም ላይ ይህን ስሜቴን የሚቀይር ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለ ይሰማኝ ነበር። መልካም ጓደኞች፣ ቆንጆ ቆንጆ ልጆች ፣ የተሟላ ጤና ፣ ድንቅ የፈጠራ ክሕሎትና ሌሎችን ነገሮች የነበሩኝ ብሆንም በነዚህ ሁሉ ምንም አይነት የእርካታና የደስታ ስሜትን ልጎናፀፍ አልቻልኩም። ምድራዊ አለም ባቀረበልኝ መልካም ስጦታ በመደሰት ፈንታ የብቸኝነትን የባዶነት ስሜቴ እየበረታ ሄደ። ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ስለመንፈሳዊ ተግባራት ስለተመስጦ ሳነብ አዳዲስ አለማት ይገለፁልኝ ጀመር። በተስፋ ከመጠበቅ አንዱ በር ሲዘጋ ብዙ በሮች ይፈታሉ። የሚለው አባባል እውነት ነው።

    ተመስጦ ከውስጣዊ ማንነቴ ጋር የሰመረ ቁርኝት እንድፈጥር እንደሚያደርግ ባውቅም በፀጥታ ይህን ተግባር መከወኑ በመጀመሪያ አካባቢ ከብዶኝ ነበር። አለማዊ ግዴታዎችን ከመወጣት ልጆቼ ጋር ሆኜ እየከወንኩ ከመንፈሳዊው አለም ጋር ያልተቋረጠ መስተጋብር እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር። በዚህ ያልተቋረጠ ጥልቅ ፍለጋዬ ውስጥ ሳለው ተመስጦን የፈለጉትን ስራ እየሰሩና በየትኛውም ስፍራ ሆነው መከናወን የሚቻልበትን የተግባራዊ መንፈሳዊነት ቴክኒክን ለመግኘት ቻልኩ። ይህ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነውና አዕምሮን የሚያጎለብተው ቴክኒክ ፈጣሪ ሩሲያዊው ፈላስፋ ጆርጅ ጉርዲዮፍ ነበር። ጉርዲዮፍ ይህን የተመስጦ ሂደት  "ራስን ማስታወስ" በማለት ከሰየመ ከዋኙ የታዛቢነት ሚና እንዲኖረው የሚያደርግን ጽንሰ-ሀሳብ ፈጥሯል።

የተገኘ #ራስን መሆን ከሚል መፅሀፍ