Get Mystery Box with random crypto!

‹‹እንደዛ ማድረግ በፍፅም አልችልም፡፡አሁን በእሱ ቦታ አንተ ብትሆን እንደዛ የማደርግ ይመስልሀል? | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

‹‹እንደዛ ማድረግ በፍፅም አልችልም፡፡አሁን በእሱ ቦታ አንተ ብትሆን እንደዛ የማደርግ ይመስልሀል?››
አንቺ ግን ጤነኛ ነሽ..?ምኑን ከምን ነው የምታወዳድሪው..? እኔ እኮ እጮኛሽ ነኝ፡፡ ፍቅርሽ …የነገ ባልሽ››
የለበጣ ፈገግታ ፈገግ አለችና‹‹አሁን ለጭቅጭቅ ጊዜ የለኝም…አረፍ ብለህ ጠብቀኝ ወይም ወደቤት ተመልሰህ ሂድ .እኔ መሄዴ ነው››
‹‹ወዴት ?››
‹‹እየሰማኸኝ አይደለም እንዴ…?ሁኔታውን ማየት አለብኝ.. ደህንነቱ አሳስቦኛል..››
‹‹እኔ የምሰማውን ማመን አልችልም››በንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት,,,
ዝም ብላው ሳሎንኑ ለቃ በመውጣት ወደመኪናዋ መራመድ ጀመረች…ከኃላዋ ተከተላት
‹‹እንድትሄጂ ፈፅም አልፈቅድልሽም….አትሔጂም…››
‹‹እኔም ፍቀድ አልጠየኩህም..መኪናው ውስጥ ገባች..የሚያደርገው ጠፋው…በደመነፍስ ተንደርድሮ ገቢናውን ከፍቶ ገባ››
‹‹ምን እየሆንክ ነው?››
‹‹አንገትሽን ቀንጥሶ ሲገድልሽ ምስክር ለመሆን አብሬሽ መሄድ አለብኝ››
‹‹ቀለድክ ማለት ነው?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ በገዛ ነፍስሽም በወደፊት የጋራ ህይወታችንም እየቀለድሽ ያለሽው…እንዴት አንድ ጤነኛ ሰው ከለየለት እብድ ጋር ሌባና ፖሊስ ይጫወታል?››
‹‹ስለማታውቀው ነገረ ብዙ አታውራ…እኛስ ስላልተመረመርን አንጂ አለማበዳችንን በምን እናውቃለን? ››በንዴት ጦፈች
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ….በተለይ አንቺ መመርመር አለብሽ…››
‹‹ጥሩ ምክር ነው፡፡አይዞህ አታስብ ከመጋባታችን በፊት እመረመራለው….ለአሁኑ ግን… ››
ጭቅጭቃቸውን እልባት ሳያበጁለት እነቢላል ቤት ደረሱ....መኪናዋን መንገዱ ጠርዝ ላይ ፓርከ አድርጋ ሞተሩን አጠፋችና በጥድፊየ ትደርድራ ወረደች…ተከትሎት ወረደ፡፡
የግቢውን መጥሪያ ብትጫን..በረፍን አጇን እስኪያማት ብታንኳኳ ሰሚ አላገኘችም…ግቢው ውስጥ የሰው ዘር ያለ አይመስልም …ግራ ገባት… ድንጋጤዋ ከመጠን እያለፈ ሄደ..ስልኳን አወጣችና ፕሮፌሰሯ ጋር ደወለች… ይጠራል አይነሳም…ደጋግማ ሞከረች ይባስ ብሎ ተዘገ..ጩኸ ጩኺ አላት…ሄኖክ አጠገቧ ቆሞ ሁኔታዋን በንዴትም በትዝብትም በዝምታ እየተመለከተ ነው፡፡


ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@itsmezeeddr
አድርሱኝ


አይረሳ እንዲቀጥል