Get Mystery Box with random crypto!

ነፍስ ሲያፈቅር ምዕራፍ -17 /// ልክ ልብአንጠልጣይ ልብ ወለድ እያነበበ እንዳለ ልክፍተኛ አንባ | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

ነፍስ ሲያፈቅር
ምዕራፍ -17
///
ልክ ልብአንጠልጣይ ልብ ወለድ እያነበበ እንዳለ ልክፍተኛ አንባቢ እጅግ በተስገበገበ ፍላጎት ሶስተኛውን ደብዳቤ ለማንበብ አንስታ እየገለጠች ባለችበት ቅፅበት ስልኳ ጠራ …በአንድ እጇ ካስቀመጠችበት ተንጠራርታ አነሳችና ተመለከተች...ከራሷ ቤት ነው የተደወለው…..የተዘራ ስልክ ቁጥር ነው፡፡አነሳችው
‹‹.አትዬ.እትይ….››የተቆራረጠና በድንጋጤ የተሰባበረ ድምፅ
‹‹ምን ሆንክ ተዘራ…?.››
‹‹ኸረ አለቅን እትዬ …ምን ላድርግ ?ማጅራቱን ቀንድቤ ልጠቅልለው…?››
‹‹የማንን ማጅራት…?.ምንድነው የምታወራው…?ወረቀቱን አስቀመጠችና ከአልጋው ላይ ወርዳ ወለሉ ላይ ቆመች››
‹‹እብዱ ልጅ እየጨረሰን ነው….እኔ እንደወትሮ ሰላም መስሎኝ በራፍን ከፍቼ ወደውስጥ አስገባውት.. እሱ ግን የቤቱን መስታወት እየሰበበረ ነው….እኔ ልመታው ነው….በከዘራዬ ልጠቀልለው ነው››
‹‹ተዘራ እንዳትነካው… ጫፉን እንዳትነካው..››አንቧረቀቸ፡፡
‹‹ምን ማለት ነው እትይ…?የቤቱን መስታወት ሁሉ እያረገፈው ነው እያልኩሸ እኮ ነው››
‹‹ከፈለገ ያቃጥለው…ጫፉን እንዳተነካው…መስታወቱ እንዳይቆርጠው የምትችለውን አድርግ››
‹‹ጭራሽ››
‹‹አዎ ነገርኩህ መጣው››
‹‹እሺ ለፖሊስ ልደውል?››
‹‹ነገርኩህ እኮ …ምንም እንዳታደርግ …መጣው››ስልኩን ዘግታ ቀና ስትል ሄኖክ በፋሻ የተጠቀለለ እጁን አንከርፍፎ ፊቷ ቆሞ ነበር፡፡
‹‹ምነው ፍቅር…?ምንድነወ የምታወሪው?››
‹‹አንድ የሚያመው ወዳጄ ነበር ….እቤት መጥቶ ትንሽ እየረበሸ ነው አሉ...ዘበኛው ነው የደወለው…መሄድ አለብኝ›› ቦርሳዋን ከአልጋዋ ላይ አንስታ መራመድ ጀመረች››
የምታወራው ምንም አልገባውም…..ዝም ብሎ ብቻ ከኃላ ተከተላት….ግቢ ውስጥ ያቆመቻት መኪናዋ ውስጥ ከፍታ ስትገባ እሱም ተከትሏት ገቢና ገባ..
ከእሷ ጋረ ለመሄድ መኪና ውስጥ መግቱን ባለማመን ጠየቀችው‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹ስለቤት መሰባበር እና መቃጠል እያወረሽ ብቻሽን ስትሄጂ እንዴት እተውሻለው? .››
‹‹ምን እሆናለው …?.ቀላል ነገር እኮ ነው….አንተ ለመንቀሳቀስ ገና አላገገምክም እኮ››
‹‹ይልቅ እሺ ብዬሽ ስለማልቀር ጊዜ እትግደይ.››ፍርጥም ብሎ የመጨረሻ ውሳኔውን አሳወቃት፡፡
ተበሳጨች ግን ደግሞ ከእሱ ጋር በመከራከር ከዚህ በላይ ጊዜ ማጥፋት ስላልፈለገች መኪናዋን አስነሳች፡፡
እሱን ሊከተላት ቆርጧ የተነሳው የእሷ ሁኔታ አሳስቦት ብቻ አይደለም..ይሄ ያማዋል የሚባለው ልጅ ማን ነው ?ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማወቅ ሰለፈለገ ነው..እቤቷ የሚመላለስ አንድ የአእምሮ ህመምተኛ እንዳለ ሁለት ሶስቴ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰምቷል…ከዚህ በፊትም አብረው በሚዝናኑበት ሰዓት ይሄ ልጅ ታመመ ተብሎ ሲደወልላት ያለምንም ማቅማማት እሱን የተጠቀመጠበት ሆቴል ትታው በራለች…እና አውጥቶ ባይተነፍሰውም በውስጡ ሲብላላ የነበረ ጉዳይ ነበር…እና ይሄንን አጋጣሚ ተጠቅሞ በቂ መረጃ ማግኘት ፈልጎል፡፡
• ከ40 ደቆቃ ቡኃላ ሲፈን ቤት ደረሱ…ተዘራ በሀዘን የጨለመ ፊት ይዞ ዱላውን በቁጭት እያወዛወዘ በራፍ ላይ ሲንጎራድ ነበር ያገኙት…እንዳያቸው ከፈተላቸው…መኪናውን ወደውስጥ አስገብተው አቆሙና ተከታትለወ ወረዱ
‹‹ተዘራ የታለ…?››
‹‹አሁንማ ሄዶል››
‹‹ሰላም ነው…ምንም አላደረከውም አይደል..?››
‹‹እኔማ አንዳትነካው ብለሺኝ ምን ማድረግ እችላለው…መስታወት ግን እጁንና ፊቱን ቆርጦታል
‹‹በጣም ተጎዳ…››
‹‹አይ ሲቆርጠው ወደሰውነቱ የጠለቀ አይመስለኝም ..ደም ግን እየፈሰው ነበር››
‹‹እና እየደማ ሲሄድ ለምን ዘም አልከው?››በተዘረ ከተገቢው በላይ ተበሳጨችበት፡፡
‹‹እንዴ እትዬ…ይ ሰበበኛ ሰው በእጄ ላይ ደመከልብ ሳይሆን በሰላም በራሱ ጊዜ እቤቱን ለቆ ሲወጣልኝ አይ ቆይ ብዬ ልይዘው…?አረ አላደርገውም…››እሱም በምሬት ብሶቱን አንበለበለው፡፡
‹‹በቃ እሺ.. ሄኖኬ እዚህ ጠብቀኘ ….እቤቱ ቅርበ ስለሆነ ሀኔታውን ሄጄ ልይ››
‹ምኑም እየገባኝ አይደለም….ይሄ ልጅ ማን ነው?››ሄኖክ እንደቆፍጣና አባ ወራ በንዴት ጠየቀ
‹‹ቢላል ይባላል››
‹‹ስሙን አይደለም የፈለኩት ..ለአንቺ ያለውን ዋጋ ነው?››
‹‹የማይተመን ካልኩህ ይበቃል…በል ቸው..›› ብላ በቆመበት ጥላው ልትሄድ ስትል …. ተዘራ አስቆማት‹እትዬ የወደመውን ቤት ሳታይው? ››
‹‹እቤቱ ቁስ ነው… የገንዘበብ ጉዳይ ነው...ለጊዜው የሚያስጨንቀኝ የቢላል ደህንነት ብቻነው››ለተዘራ ጥያቄ መልስ የምትሰጥ ይመስላል እንጂ ስመቱ ግን ሁለቱም ለማስረዳት ይመስላል፡፡
‹‹አምጥቶ ጥሎት የሄደውንስ ስዕል ማየት አትፈልጊም?››
‹‹ስዕል ነው ያልከኝ? የታለ?››ግራ በመጋባት እና በጉጉት ጠየቀችው፡፡
‹‹ሳሎን ነው››
ሀሳቧን ቀይራ ወደሳሎን መራመድ ጀመረች…ሄኖክ ከኃላው ተከተላት…ፍሬንች ዶሩ አፅሙ ብቻ ነው ያለው...ሙሉ በረንዳው በመስታወት ስብርባሪ ተሞልቷል…..ፈት ለፊት ያሉ መስኮቶችም ተመሳሳይ እጣ ነው የደረሳቸው….በመስታወት ክምር ላይ የተዝረከረከ ደም እዚህም እዛም ተንጠባጥቧ ይታያል..ደሙን ስታይ ልቧ እስክተኮማተር ድረስ ጥልቅ ሀዘና ተሰማት…ከገዛ ሰውነቷ የደም ቧንቧ ተበጥሶ እዲፈስ የተደረገ የራሷ ደም መስሎ ነው የተሰማት. በጥንቃቄ እየተራመዱ ወደውስጥ ገቡ…ቢላል አመጣው የተባለው ሰስዕል ሳሎን መግቢያ አካባቢ ግድግዳ ተደገፎ ይታየል፡፡ትልቅ ነው …በግምት 80 በ 60 ሴንቲ.ሜትር ስፋት አለው፡፡
የስዕሉን ምንነት እንደተመለከቱ ሁለቱም ነበር በፍዘት አፋቸውን የከፈቱት…ቢሆንም ግን ከሲፈን ይልቀ በእጥፍ መጠን የደነገጠው ሄኖክ ነው….፡፡
‹‹.ምንድነው አንደዚህ አይነት ጨለማና አስፈሪ ስዕል….?ይህቺ እኮ አንቺ ነሸ..ልክ አንደ መስዋዋት በግ ታርደሻል …. አንገትሽ ተቀንጠሶ ወድቋል ….ሰውነትሽና የተኛሽበት ፍራሽ በደም ጨቅይቷል››
‹‹አዎ ትክክል ነህ እኔም እያየውት እኮ ነው››
‹‹ይሄስ ዛፍ ላይ የተንጠለጠለው?በገዛ ቀበቶው እኮ አንገቱን የወይራ ዛፍ ላይ አንጠልጥሎ እራሱን አሰናብቷል››
‹‹እራሱን ማነቁን በምን አወቅክ?››
‹‹አታይውም እንዴ እግሩ አካባቢ እኮ ተከንብሎ የወደቀ ወንበር አለ….››
‹‹አዎ ገባኝ ››አለችው ድክም ባለ ድምፅ….የእሷ የታረደ አንገት ሳይሆን የእሱ የተንጠለጠለ አንገት ነበር ውስጧን በፍራቻ ያደከማት››
‹‹ለመሆኑ የተንጠለጠለው ማን እንደሆነ ታውቂያለሽ..?መቼሰ እኔ አይደለውም አይደል?››አላት ፍራት ባረበበት ስሜት፡፡
ጥያቄው ቢያበሳጫትም መለሰችለት‹‹እሱ ነወ ቢላል፡፡
‹‹ስዕሉን ማን ነው የሳለለት?›››ሌላ ጥያቄ
‹‹እራሱ ነው የሳለው…ከዚህ በፊትም ተመሳሳይን ስዕል ስሎ ልኮልኛል››
‹‹እና ዝም አልሽ?››
‹‹ ምን ማድረግ ነበረብኝ?..ከእሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ስሜቴ እኮ ነው የሚስለው…ስዕሎቹ ልክ እንደትንቢት ናቸው››
‹‹ትርጉሙ ግን ገብቶሻል…ማለቴ ስዕሉ ግልፅ ነው..ገድዬሽ ሞታለው እያለ ነው…አንቺ ግን አሁንም እያሰብሽ ያለው ስለእሱ ደህንነት ነው…ከእሱ ለመራቅ ምንም ጥረት እያደረግሽ አይደለም…ወይንም ለሚመለከተው የመንግስት አካል አመልክተሸ አማኑኤል ወስደው እንዲቆልፉበት አላደረግሺም፡፡››