Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.95K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-29 07:11:35
ይህ ሸይኽ ሙሐመድ አስ-ሳዊ በአንደበታቸው የተናገሩት እውነተኛ ታሪክ ነው።
የዙሑር ሰላት ከተሰገደ ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ወጣት በፍጥነት ሲነጉድ በነበረ ባቡሩ ተገጭቶ የሲቃ ድምፅን ሲያሰማ ለአደጋው ቅርብ የነበሩ ሰዎች በዙሪያው ተሰበሰቡ። ባቡሩ ሰውነቱን ደፍጥጦታል። አጥንቱ ተሰባብሮ አካባቢው በደም ተጨማልቋል። ሮጠው ሲደርሱ እስትንፋሱ አለች። ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ ልቡ በኃይል ይመታል። ደረቱ ተቀዶ ሳንባው ሲተነፍስ ይታያል። በህይወት አለ። አንድ አዛውንት ላኢላሃ ኢለላህ በል በማለት ወደ ጆሮው ተጠግተው ሹክ አሉት።

"ከአላህ በስተቀር የሚገዙት ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ" እያለ እስትንፋሱ ተቋረጠ። በሸሃዳ ሞተ። አድራሻውን ለማግኘት ኪሱን መፈተሽ ጀመሩ። ቀኝ እጁ ላይ የመስቀል ምልክትን አዩ። መታወቂያውን ሲገልጡ ክርስቲያን መሆኑን አወቁ።
ግራ ተጋቡ "ሸሃዳ ይዞ እንዴት ሞተ?!" ተባባሉ

በዝምታም በዝግታም ጀናዛውን ተሸክመው ወደ አባቱ መንደር ይዘውት አቀኑ። የተፈጠረውን ዘርዝረው አስረዱ። አባት አንገቱን ዝቅ አድርጎ እያለቀሰ እንዲህ አለ፡-
"ልጄ ክርስቲያን ነው ቁርኣንን መስማት ግን አብዝቶ ይወድ ነበር። ወደ ክፍሉ ስገባ ሁል ጊዜ ሄርፎን በጆሮው ላይ ሰክቶ አገኘዋለሁ። ምንድነው የምትሰማው ብዬ ስጠይቀው ደስ የሚል ዘፈን ይለኛል። ወደ ጆሮ ማዳመጫው ጠጋ ብዬ ስሰማ ቁርኣን መሆኑን አስተውላለሁ" አሉና ተንሰቅስቀው አነቡ

"ልጅዎ ነፍሱ ልትወጣ እስትንፋሱ ልትቋረጥ በሞት አፋፍ ላይ እየተሰቃየ የአላህን ብቸኛ አምላክነት መስክሮ ሞቷል" አልናቸው።
ሀዘንተኛው አባት "ልጄ የመሰከረውን እኔም እመሰክራለሁ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ" በማለት ሸሃዳን ይዘው ሰለሙ።
592 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 11:32:38 አሁንስ አትገረሚም???
        ዩምና ሙሀመድ

        ምን ያስገርመኛል መሰለሽ ሁሌ የረህማኑን አዛኝነት እኔ የእሱ ባሪያው እንድሆን የመሻቱ ስፋት በእኔ  መታወስ የፍላጎቱን ጥግ አስተውለሽው ይሁን?
እኔ ባላስታውሰው እኮ ሚጎድልበት ነገር የለም እሱ እኮ ስንት እሚዋደቁለት ባሪያዎች አሉት እሱ እኮ ምድር ላይ ያለች ትንሿ ጠጠር ሳትቀር የፈጠረ ጌታ እኔን ማስታወሱ አይገርምሽም?

^ ቢተወኝስ ቆይ ሲጀመር ባይፈጥረኝስ ስንት እህት እና ወንድሞቼን እናቴ ሆድ ውስጥ ባክነው እኔ መፈጠሬ ስለወደደኝም አይደለምን?
ታዲያ አይደለም የወደደኝ ጌታ የወደደኝ ሰው እኔ ላይ መብት የለውም እንዴ?
ምሳሌ ላንሳልሽ ምድር ላይ በጣም በጣም ከሚሳሱልኝ ሰዎች ውስጥ ከእናቴ ወይ ከአባቴ በላይ ፍጥረት የለም እኮ አይደል!! 
እስኪ ልጅኘታችንን ዞረሽ እይው ልጅ ናቸው በሚል ሀላፊነት የሚባል አልነበረብንም ሀላፊነት መውሰድን በትንሽ በትንሹ እንድንማር አደረጉን
አላሄዋም እስከ 15 አመት ወይም እራሳችንን እስክናውቅ ነፃነት ሰጠን ምንም ቅጣት እንደሌለብን አሳወቀን ለቤተሰቦቻችን ግን የኛን የመኮትኮት ሀላፊነት ሰጣቸው  አትገረሚም!!


.....ቡሗላ እንዳንደክም ግራ እንዳንጋባ እኮ ነው ከዛማ ልክ ስናድግ ቤተሰቦቻችን ለማስደሰት ውለታቸውን ለመመለስ እያልን ሀላፊነት እንዳለብን ሁላ ከእልጅነት እስከእውቀት  የለፉብንን  ለመመለስ ስንል እኛ ላይ መብት አላቸው እያልን እነሱን ለማስደሰት መብታቸውን ለመጠበቅ ደፋ ቀና እንላለን ታዲያ ያኡኽታ ይሄንን ሁላ ነገር አንቺ ካለነበርሽበት አስገኝቶ ጭራሽ እማያውቁሽ እማታውቂያቸውን ፍጡሮች እናት እና አባት ያውም ከእዝነት ጋር የለገሰሽ ጌታ አንቺ ላይ መብት የለውምን?

>>>>> ብርጭቆ ስትሰብሪ ሁላ እኮ እናትሽ ወይ ትቆጣሻለች ወይ ትመታሻለች እና ስለምን ሲባል የፈጠረሽ ጌታ በነገሮች ሲቆነጥጥሽ ቢጠላኝ ነው አስባለሽ?ምን ባደርገው ነው እያልሽ ከእሱ ጋር ግብግብ አስፈጠረሽ?

^^ደሞ እኮ በተከበረው ቃሉ ሲፈትንሽ እያላቀሽ  ስለመሆኑ አማኝ ስለመሆንሽ እንዲህ እያለ ነግሮሻል "አሊፍ ላም ሚም አሀሲበናሱ አዩትረኩ አመና ፈሁም ላዩፍተኑን"
^የሰው ልጆች አምነናል ካሉ ቡሗላ እንፈተናለን ብለው አላሰቡንም አልገመቱምን^ ይለናል አየሽልኝ ኡኽታ በእሱ ስለማመኔ ማመልከቻው ወይ ደሞ መለያው በሚያመጣልኝ ነገር መታገሴ ነው::
* ለትምህርት ፈተና ስል ስንቴ አነባለው ለሊት አዳር እያነጋሁኝ  እየተጨነኩኝ ካለፋሁኝ እንደምወድቅ አውቃለዋ ከወደኩኝ ደሞ ያኔ ለቤተሰቦቼ ተገቢውን ምላሽ አልሰጠሁም ማለት ነው የት ት ፈተናውን ማለፌ
ከእኔ በላይ ቤተሰቦቼ ያስደስታቸዋል አላሄዋም ሲሞክረኝ ወደእሱ እንድቀርብ አጥብቆ ይሻብኛል::

>>>>>አስተውዪማ የሆነ መስሪያ ቤት እራስሽን አስቀጥረሽ ሳዩው ከዛማ አሰሪሽ አንቺን ይወድሻል ሊያጣሽ አይፈልግም እንድትቀርቢው ይፈልጋል ምን እሚያደርግሽ ይመስልሻል?
በጣም ከምትፈልጊው እሱ ጋር ካለ ነገር ይቀንስብሻል ወይም ያስቀርብሻል ለምሳሌ ደሞዝሽን ግማሹን ወይም እሩቡን እሱ ጋር አስቀርቶ ቀሪውን ቢሰጥሽ እመኚኝ ቀሪውን ደሞዝሽ ፍለጋ አሰሪሽ ቢሮ ትመላለሻለሽ አሰሪሽም እሱ እሚፈልጋትን ሴት እስክትሆኚለት በመመላለስሽ እርካታን አግኝቶ ይቀመጣል::
____አላሄዋም ከአሰሪሽ በላይ ላንቺ እሚያስፈልግሽን ነገር ሲነጥቅሽ መርጦሽ ነው ወደእሱ እራስሽን እንድታዞሪ እየጠየቀሽ ነው ግን እኛ መመረጥን እምናውቀው ሁላ አይመስለኝም::
*ደሞ እኮ አያቆምም በቃ ተስፋ ቆርጫለው የፈጠረኝንም አስከፍቻለው ብለን ስናስብ እንዲህም አይደል የሚለን
"ቁል ያኢባዲየለዚነ አስረፋ አላ አንፉሲሂም ላተቅነጡ ሚን ራህመቲላህ ኢነላሀ ገፉሩን ረሂም"
(እናንተ በነፍሶቻቹ ላይ ድንበር ያለፋቹ ባሪያዎቼ ሆይ በአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ አላህኮ አዛኝና ማሀሪ ነው)
  ይለናል እሺ አሁንስ አትገረሚም?



አምፀነውም ወዶን በሞከረን ነገር ላይም እንዴት ብለን የእሱን መብት ለእራሳችን ሰጥተንበትም አሁንም ኑኑኑኑ ቅረቡኝ እያለን እኮ ነው::  ከእዝነቱ እንዳንሸሽ ይነግረናል ምን ያክል ለእኛ ቅርብ እንደሆነ ያሳውቀናል የእሱ እዝነት ትልቅ ስለመሆኑ ከእዝነቱ ያሻንን እንደምንወስድ እየወስድንም እንደሆነ
"ወኢን ተኡዱ ኒእመላሂ ፈላቱአዱሀ"
(የአላህን ፀጋ ብትቆጥሩት አትዘልቁትም)እያለ ያበስረናል በሰፊው እዝነቱ እንደምንኖር ስለምን በእዝነቱ እና በፀጋው ተከበን ተስፋን እንቆርጣለን አንቺዬ?
^መለስ አድርጎ ደሞ ፈተናዎቹ ብቻቸውን እንዳልመጡ ነገራቶች ሁላ መሞከሪያዎች ከእዛም ብርሀናዊ ፀጋዎች ስለመሆናተው እንዲህ ይለናል አይደል "ፈኢነማአል ኡስሪ ዩስራ" (በእርግጥም ከችግር ቡሓላ ምቾት አለ)
ብሎ ከፀጋዎቹ ውስጥ የሆነኛውን ይገልፅልናል እናም ኡኽታ ጨንቆሻል ከፍቶሻል ወይ የሆነ ይሳካልኛል ያልሽው ነገር አለመሳካቱ አዘንብሎብሻል ተሳሰቢውማ ተነሺና ውዱእ አድርገሽ መስገጃሽ ላይ ተደፍተሽ ማድረግ እየፈለግሽ ይቺን ትልቋን ነፍሲያሽን አሸንፈሽ ለአላሄዋ ብለሽ በተወሽው ነገር ተሳሰቢው ያኔ ግን ለእሱ ብለሽ የተወሽው ነገር ካጣሽ ቀድመሽ ነፍስሽን ተሳሰቢያት
1.4K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 15:10:09 ልብሽን ምክንያት እየሰጠሽ አታድክሚዉ
   ዩምና ሙሀመድ

እራስሽን ልክ እንደ ሙሳ ቀይ ባህር መሀል ላይ አኑሪው ከጀርባሽ ፊርአውንን እሚያክል ጠላት ወይ ችግር አለብሽ ከበላይሽ የተሰነጠቀ ባህር እሚያክል አንቺ ላይ ሊደርስ እሚችል ችግሮች ተከምረው ታይተውሻል ወደ ጎን አትይም መካከል ላይ ነሽ ብቻሽን አይደለሽም በአንቺ ስር ያሉ የብዙዎችን ህይወት ከአላህ በታች ይዘሻል ....ልክ ሙሳ ተከታዮቹን እንደያዘው ነፍሴን ብቻ አይልም ነፍሳችንን እንጂ ከእራሱ ሩህ በላይ እሚያስጨንቀው የተከታዮቹን ነገር ነው ምናልባትም አንቺ የብዙ ሀላፊነት ባለቤት ሆነሽ ይሆናል፡፡

ታዲያ ሙሳ ከባህሩ አልወጡምን? በየትኛው መንገድ? ከፊት ለፊታቸው በምትታያቸው አንድ መንገድ ያቺን መንገድ እስኪያገኟት ድረስ ወደ ሗላ አልዞሩም ወደ ሗላ ችግራቸው ነው ያለው ፊት ለፊታቸው ግን ነፃነት ከብዙ የነፍሶች ሀላፊነት ማረፍ ሀቀኝነትን ብቻ ቡዙ ተአምሮችን ይዟል ያቺ የታየቻቸውን መንገድ በጀሊሉ ፍቃድ ደረሱባት ዞር ብለው ወደ ችግሮቻቸው ሲያዩ ግን ቢወርድ ሊያጠፋቸው እሚችለው ባህር ሲከተላቸው የነበረውን ችግር ድምጥማጡን አጠፋላቸው

አንቺም ያሉብሽን ችግር እስክታልፊያቸው ዞረሽ አትመልከቻቸው ይደርሱብኛል እምትያቸው ችግሮችሽ ምናልባት የደረሱብሽን ችግሮች ማጥፊያ ናቸው ፡፡ መውጫሽን ተመልከቺ ግን ስለሁሉም ጌታሽን አጥብቀሽ ያዢው በእሱ ያለሽ እምነት ከልብሽ አድርጊው የተፃፈልሽ ሙሲባ በሙሉ ሊስትሽ አልነበረም የሳተሽ በሙሉ ሊያገኝሽ አልነበረም ልብሽን ምክኒያት እየሰጠሽ አታድክሚው

☞  አንቺ ማለት ሳትጠይቂው ለእሱ ባሪያው እንድትሆኚ የፈጠረሽ ባሪያው ነሽ
☞አንቺ ማለት ከስንት ሚሊዮን እህት እና ወንድሞችሽ ተመርጠሽ የተፈጠርሽ ፍጡር ነሽ
☞አንቺ ማለት በዱንያው እሳት ፈትኖሽ እንደ ወርቅ ሊያስከብርሽ ሊያስወድድሽ እሚያደርግ ጌታ ነው ያለሽ

>>> እናም ያኡኽታ ረህማኑን አጥብቂው የተጣበቀብሽ ይለቅሻል
1.3K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:54:35 በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ አንደሉስ ምድር መናገሻ ከተማ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ ጠዋት ነበር። ሰራዊቱ በፈረሶቻቸው ላይ ተፈናጠው በድካም የሚንጠፈጠፈውን ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠራረጉ አቧራ ባጨማለቀው ልብሳቸው ኢድ ወደ ሚሰገድበት ሜዳ በማቅናት ላይ ሳሉ ነበር አንዲት እድሜዋ የገፋ አዛውንት ከሡልጣን መንሱር ፊት ቆማ የፈረሱን ልጓም ይዛ ከመንገዱ በማስተጓጎል እንዲህ ያለችው:-


"በዛሬው የዒድ ቀን ከእኔ በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ደስተኞች ናቸው"
ሐጂብ መንሱር ንግግሯን ሲሰማ ደነገጠ "ለምን?" ሲልም ጠየቀ።
ዕንባ ባቀረረው ዓይኗ እየተመለከተችው እንዲህ አለችው "በረባህ ምሽግ ከመስቀል ጦረኞች ጋር ሲፋለም የተማረከ አንድ ፍሬ ሙጃሂድ ልጅ አለኝ እሱ በጠላት እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት መደሰት ይቻለኛል?"

ዘመኑ 380 ዓመተ ሂጅራ ግዛቶች በሐጂብ አል መንሱር ይተዳደሩ ነበር። የአንደሉስ ኢስላማዊ መንግስት በጥንካሬና በከፍታ ማማ ላይ የደረሰበት ወርቃማ ዘመን! የፉቱሐትና የዘመቻ የፍትህና የእኩልነት ጊዜ!

ሐጂብ ንግግሯን ሲሰማ በፍጥነት ፊቱን ወደሠራዊቱ አዞረ። የፈረሱን ልጓም አጥብቆ ያዘና በጂሃድ ሜዳ የአፈር ትቢያውን ገና ላላራገፈው ሙጃሂድ፣ ከድካም ጀርባውን ላላሳረፈው ሠራዊት እንዲህ ሲል ትዕዛዙን አስተላለፈ "ከፈረሳችሁ ጀርባ እንዳትወርዱ" አለ።

የፈረሱን ልጓም እየጎተተ ጀርባው ላይ እንደተፈናጠጠ ወደ ረባህ ምሽግ ሰራዊቱን ይዞ ገሰገሰ። የአሮጊቷን ልጅ ጨምሮ ሙስሊም እስረኞችን አስፈትቶ ከተማዋን በድል ከፍቶ ወደ አንደሉስ ምድር ተመለሰ።

ይህ ስለኢስላም መስራት በማንደክምበት ዕለት የተከሰተ የጀግንነት ታሪካችን ነው።


ለሁላችሁም ኢድ ሙባረክ ብያለሁ
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን....ከረመዷን በፊት ወደነበርንበት አመፅና ወንጀል የማንመለስ ያርገን
....ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን  ሩሀችን   እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን ያረብ

የቻናል ቤተሰቦች መልካም በአል ተመኘሁ
376 viewsedited  11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 05:43:49
ሙነሺዶች

ዘንቦል ዘንጠል ዘንፈል ዘንፈልፈል ወዝወዝ ሲሉ አጃቢዎቹንም ተመልከቱ ፌመስ ለመሆን ጥረትና ዉጥረት...

ቆይ ግን እሽክምክም እሽክምክም እያለች ከምዘፍነዉ ዘፋኝ በምን ተለዩ



የሚገርመዉ ዘንድሮ ሙነሺዶች ብዙዎቹ በረመዳን መካ ኡምራ አድርገዋል...በአዳማጩ በyoutube ብር አግኝተዉ መካ አሳለፉ...
አዳማጩ ግን ቁርአን መሸምደድ መቅራት ዚክር ማድረገዉ ትተዉ በተለይ ሴቱ ወይኔ ድምፁ ሲያምር የእሱን ድምፅ ሳልሰማ መዋል ከብዶኛል ብለዉ የእነሱን ድምፅ ካልሰሙ ራሳቸዉን የሚያማቸዉ የሚያቃዣቸዉም አሉ... አንዳንድም የምታለቅስ አለች

ሀያቴን ለርሶ ብያለሁ ጀባ ይሉሀል ይሄ ጀመአ
ተመልከቱ ካሜራ ማን

የሙስሊም ሴቶች ለእስልምና መስራት አለባቸዉ በሁሉም ነገር ሴት መጨቆን የለባትም ይሉሀል
ድንበር ያለፈ ለሴት ልጅ መቆርቆር መምሰል መጨረሻዉ ዉጤቱ ይሄ ነዉ......

አጂ ነብይ ጋር በዲን ስም አብሮ መሆን...
809 viewsedited  02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 11:13:56
በየመን የዘካተል ፊጥር ሶደቃን ለመቀበል በተፈጠረ ግፊና ትርምስ ቢያንስ የ 78 ሰዎች ህይወት አለፈ !

ነገሩ እጅግ አሳዛኝ ነው !
በአሳዛኝ ረሀብና ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የመን ከ 17 ሚሊዮን በላይ ረሀብተኞችን የያዘች ሀገር ናት ። ሳኡዲና አጋሮቿ ከላይ በቦንብ ያነዷታል ከሁቲዎች ጋር እየተፋለሙ ። ከስር የረሀብ አለን ህዝቧን እየገረፈ የመናዊያን ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው መኖር ከጀመሩ አመታት ተቆጠሩ ።

በዛሬው የተሻሉ የሚባሉት የየመን ነጋዴዎች ለችግረኞች ዘካተል ፊጥር ለማከፋፈል በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ሰብስበው የነበረ ቢሆንም እርዳታውን ለመቀበል በተፈፀ ግፊ ከ 78 በላይ ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶቹ ቆስለዋል ።

የሚገርመው የሚከፋፈለው እርዳታ ለአንድ ሰው 10 ዶላር ብቻ የነበረ ቢሆን እርሷን ለማግኘት ሲጋፉ ህይወታቸውን አጥተዋል ። በበርካታ የአረብ ሙስሊም ሀብታም ሀገራት የተከበበቺው የመን እርሷ ግን የረሀብና ጠኔ ምሳሌ ናት ።

ረሀብ እያሰቃየ ከሚገድለን ተጋፍተን በቶሎ እንሙት ብለው ይሆን

አላህ የሞቱትን ይማራቸው ! የመንንም ከመከራዋ ያውጣት !
944 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:07:57
የ26 አመቱ ፈረንሳዊ ሙስሊም #ኒል_ዳውዞስ
#ከፈረንሳይ በመነሳት 3,900 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዞ የተከበረው አል አቅሳ መስጅድ መድረስ ችሏል ጉዞውም 10 ወራት የፈጀ ሲሆን ቱርክን ጨምሯ አስራ አንድ ሀገራትንም አቋርጣል

በመስጅድ አል አቅሳ ሲደርስም ፍልስጤማውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

#ኒል ቀጣይ አላማው "በአንድ ወር ተኩል ውስጥ #ሃጅ ለማድረግ ወደ #መካ መጓዝ እንደሆነ ገልፇል። አላህ ያሳካለት ።
1.0K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:06:48
ሸይጧን ከኢድ ሶላት ቡሀላ...
1.1K viewsedited  04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:03:32
‟ኢማም መሆን እፈልጋለሁ።” ምን ያምር ኒያ

የባየር ሙኒኩ እና የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነው ናስር ማዝሮይ እንዲህ አለ ...

‟ከአለም ዋንጫ በኋላ ሀፊዘል ቁርአን ለመሆን ወስኛለሁ። በምሰግድበት ወቅት የተወሰኑ ሱራዎችን ብቻ ነው የምቀራው ሌሎቹን አላውቃቸውም በዛ ወቅትም እፍረት ይሰማኛል። ቁርአንን በቃሌ ለመያዝ ይኸው የመጀመሪያ እርምጃዬን ጀምሬያለሁ። አላማዬ ቁርአንን መሸምደድ ነው ፤ ከዛ ቁርአንን መረዳት እና ቁርአንን ህይወቴ ማድረግ። ይሄን እውቀት ቅርቤ ለሆኑ ሰዎች ማጋራትም እፈልጋለሁ በመጨረሻም ኢማም መሆን እፈልጋለሁ።”
921 views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:58:14 ሸረሪት በሳይንስ እና በኢስላም እይታ

ንዱ ሸረሪት የዘር ፈሳሹን ወደ እንስቷ ሸረሪት ካስተላለፈ በኃላ አብዛኃኛውን ጊዜ እጣ ፈንታው ምን እንደሆነ ያውቃሉ? ከእንስቷ ሸረሪት <እሰይ አበጀህ> የሚል የሙገሳ ቃል ሳይሆን የሚጎርፍለት ግድያ ነው የሚጠብቀው። ትገድለዋለች። ትበላዋለች። ሲያሻትም ሬሳውን ከቤቱ ውጭ አሸንቀጥራ ትጥለዋለች። ያ የዘር ፈሳሽ ግን አይመክንም። ልጆች ይፈጠራሉ።

ልጆቹ ካደጉ በኃላ በአባታቸው ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ማን ሹክ እንዳላቸው በማናውቀው መንገድ ብቀላ ቢጤ ይጀምራሉ። የአባታቸውን ገዳይ ይበቀላሉ። እናታቸውን አፈር ድሜ ያበሏታል። ይገድሏታል። በአባታቸው የደረሰውን እጣ በእርሷም ላይ ይደግሙታል። ሬሳዋን ከቤቱ ውጭ አምዘግዝገው ይጥሉታል።

ከቤቶች ሁሉ በአስቀያሚነቱ ወደር የማይገኝለት ቤት ይህ ነው - የሸረሪት ቤት። ከቤቶች ሁሉ ደካማው ቤት።

የቁርዓን ተዝቆ የማያልቅ ሚስጢር ከብዙ አቅጣጫ የሚፈተሸ ነው። ቆፋሪ ይቀፍራል እንጂ የጥበቡን ስር ማክተሚያ መቼም አያገኘውም - ማክተሚያም የለው። ነገር ግን በቁፋሮው ሂደት የአቅሙን ያክል ዘርፈ ብዙ ጥበቦችን ያገኛል። በዚያም ይረካል። እስኪ ቁርዓን ከላይ ያየነውን ክፉ ቤት እንዴት አድርጎ በአንዲት አንቀፅ እንደሚገልፀው አብረን እንመልከት ፡-

مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاء كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتاً وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

<እነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙት (ለራሷ) ቤት በሰራች ሸረሪት ይመሰላሉ። ከቤቶች ሁሉ ደካማው የሸረሪት ቤት ነው። (የአማልክቶቻቸውን ድክመት) የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ (ባላመለኳቸው) ነበር።>

የሸረሪት ቤት ምን ያክል ደካማ እንደሆነ በግልፅ ሊታይ የሚችል ከመሆኑ አኳያ ሰዎች ይህንን ማወቃቸው አይደንቅም። ተጨባጭ የሆነም እውነታ ነውና። ሚስጢራዊ ደካማነቱን ግን ያወቁት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። ከላይ የሰፈረው አንቀፅ ማሳረጊያውም እንዲህ ይላል لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ - "የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ"

ይህ አንቀፅ የትኛው ምዕራፍ ውስጥ እንዳለ ያውቃሉ?
ሱረቱል አንከቡት ይሰኛል። የሸረሪት ምዕራፍ ማለት ነው። የምዕራፏ አብይ ርዕስ እምነትና ለእምነት ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነት ፥ ለእምነት ሲባል የሚደርስ ፈተና ነው። ይህንኑ በማጉላት ትወጠናለች። እምነት በቃል ብቻ የሚባል ሳይሆን ፥ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ አማኞችም እውነተኛነታቸው በእሳት (በመከራ ፥ በገንዘብ) እንደሚፈተን ትገልፃለች። ከምዕራፉ የመጀመሪያ አንቀፅ እስከ ፍፃሜው ማለት ይቻላል የሚያትተው ስለ <ፈተናዎች> ነው።
ምዕራፉ በዚህች ነፍሳት ስያሜውን አግኝቷል።

ፈተናዎችን እና ሸረሪትን ምን አገናኛቸው የሚል አንዳች ጥያቄ አእምሮዎ ካጫረ እንዲህ እንላለን ፡-
የፈተና መልኩ እና ቅርፁ የሸረሪት ድርን ይመስላል። ፈተና የነገሰበት ክልል ውስብስብ ነው። የፈተና ቀጠና ጥልፍልፍ ነው። ክፉውን ከበጎው ለመለየት አዳጋች ነው። የተቆላለፈ መስክ ነው። መውጫ ቀዳዳው በውል አይታወቅም። ጠልፎ ይጥላል። አይነቱ ብዙ ነው። እጅግ በጣም ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ ይፈታተናል። ነገር ግን ያ ጥልፍልፉ የድር መከራ በአላህ ኃይል ብቻ ይበጣጠሳል። በእርሱ እገዛ ይንኮታኮታል።

በሌላ መልኩ ከላይ የሰፈረው አንቀፅ በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ያሉ ኃይላትን ትክክለኛ ባህሪና ማንነት የገለፀ ምሳሌ ነው። ሰዎች ብዙ ጊዜ ይህን እውነታ ይዘነጉታል። በመሆኑም አመለካከታቸው ሲዛባ ፥ እይታቸው ሲበከል ፥ መዞር ወደሌለባቸው ኃይል ሲዞሩ ፥ መመካት በሌለባቸው አካል ሲመኩና ሊማፀኑት የማይገባውን ፍጡር ሲማፀኑ ይስተዋላል። እውነተኛ ኃይል የአላህ ኃይል ብቻ ነው። ከርሱ ውጭ ያሉ ኃይላት ጉልበታቸው እንደ ሸረሪት ድር ደካማ ነው። በነርሱ የተመካም ደካማ ቤት እንደያዘ ሸረሪት ይመሰላል። የተጠለለችበት ቤት ጉልበት ከርሷ ቢደክም እንጂ አይጠነክርም።
ሰዎች ይህን እውነት ይዘነጋሉ። ገንዘብ ፥ ስልጣን ወይም እውቀት ምድር ላይ ያሻቸውን ለማድረግ የሚያስችሏቸው ኃይሎች እንደሆኑ ያስባሉ። ለእነርሱ ያድራሉ። ይፈሯቸዋል። ያከብሯቸዋል። የእነርሱን ትሩፋት ለመማግኘት ፥ እነርሱን ላለማጣት ይጓጓሉ። ለነኝህ ኃይላት በማጎብደድ እውነተኛውን ኃይል (አላህን) ይዘነጋሉ። የእነኝህ ኃይላት ጉልበት ከሸረሪት ድር የጠነከረ እንዳልሆነ አይረዱም። ከአላህ ኃይል ውጭ ሌላ ኃይል የለም። ከአላህ ጥበቃ ውጭ ሌላ ጥበቃ የለም።

ሙስሊም ላልሆኑት ጥያቄ አለኝ! ታድያ ይህንን ሁሉ ጥልቅ ዕውቀት ያልተማረ፣ መፃፍና ማንበብ የማይችል ነብይ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?

እንጠይቅ፣ እንመርምር።
859 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ