Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.95K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-02 11:32:14
ስሜቱ ያሸነፈው ሠው እና ፍሬኑ ተበጥሶ መሪው የማይሠራ በፍጥነት የሚገሠግስ መኪና አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም ፍጥነታቸውን እና መዳረሻቸውን በመላምት ከመገመት በቀር አያውቁትም ጥፋት ወይስ ልማት? እኔንጃ ብቻ ነው መልሳቸው።

የሠው ልጅ ስሜቱን እንዲመራው እንጂ በስሜቱ እንዲመራ አልተፈጠረምና ስሜትህን ምራው እንጂ አይምራህ ግዛው እንጂ አይግዛህ ሰከን በል።
3.6K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 11:07:00 ውበቴን _ በፊትህ
"ልጄን አሳዩኝ?" አለች በደከመ ድምፅዋ ከወሊድ ስቃዩዋ ገና እፎይ ሳትል። አምጥተው ክንዶችዋ ላይ አደረጉላት። ህፃኑ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገላለጠችው። ክው ብላ ደነገጠች።
ዶክተሩ ሁለት እጆቹን እንዳጣጠፈ ፊቱን ወደ መስኮቱ አዙሮ ከሆስፒታሉ ክፍል ወደ ውጭ ማየት ጀመረ።....ተፈጥሮ ሰሰተች። ህፃኑ ያለ ጆሮ ነበር የተወለደው ። የእናት እንባ ህፃኑ ፊት ላይ ተንጠባጠበ።
ከዓመታት በኋላ ግን ምንም እንኳ ሁለቱ የጆሮዎቹ ቅጠሎች ባይኖሩም የልጁ የመስማት ሁኔታ ጤናማ እንደሆነ ታወቀ። ይሁንና ሁልጊዜ ከትም/ት ቤት መልስ ሮጦ እናቱ ላይ እየተጠመጠመ ያለቅሳል። "አስፈሪው ልጅ! እያሉ ይሰድቡኛል" ይላታል።
ጊዜው ይሮጣል። ......ልጁ አደገ።....ጆሮ ከማጣቱ በስተቀር ፍፁም ውብና ደመ-ግቡ የሆነ ታዳጋ ሆነ።.....እናት ግን ዘወትር በሀዘን ትቆራመዳለች። " ነገ ከሰው ጋር ሲቀላቀል እንዴት ይኖር ይሆን?" እያለች ትተክዛለች።
አባቱ በበኩሉ ዶክተሩን እየተመላለሰ ይወተውተዋል። " በቃ ልጄን ምንም ልትረዱት አትችሉም ማለት ነው?" .....ተስፋ ባለ መቁረጥ ይጠይቃል። " ሁለቱን የጆሮ ቅጠሎች ብናገኝ እኮ ቀላል ነበር" አለው ዶክተሩ።
ፍለጋው ተጀመረ ለዚህ ለጋ ታዳጊ ከሞት በኋላ ጆሮዎቹን ለመለገስ ሊናዘዝ የሚችል ሰው ተፈለገ።
ከሁለት ዓመት በኋላ አባት ልጁን ጠራውና " ነገ ሆስፒታል እንሄዳለን። ሁለት ጆሮ የሚሰጥ ፈቃደኛ ተገኝቷል!..... "አለው።  " ነገር ግን የበጎ አድራጊው ስምና ማንነት ቢያንስ ለተወሰኑ ጊዚያት ሚስጥር ነው! "አለው። በነገታው እናትና አባት ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ።.......የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደረገ፣ አዲስና ይበልጥ ውብ የሆነ ታዳጊ ደግ ተከሰተ። በቃ ዓለምን በድጋሚ ተቀላቀላት። በራስ መተማመኑ ሲጨምር በእውቀትም የተካነ እየሆነ መጣ።
ሀይስኩልና ዩኒቨርሲቲን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀቀ።......ትዳር መሰረተ።....ጥሩ ስራ ያዘ።......" አሁን ግን ማወቅ አለብኝ!" ሲል አባቱን ጠየቀው። "ይህን የህይወቴን ታላቅ ስጦታ የቸረኝ ማነው? ምንም በደርግለት ነፍሴ የምትረካ አይመስለኝም!" አለው።
".......አይይ ምንም ልታደርግለት የምትችል አይመስለኝም!" ሲል መለሰለት። "በውላችን መሰረት ደግሞ የለጋሹ ማንነት በሚስጥር መያዝ አለብን!.....ቢያንስ ለጥቂት ዓመታት!" ሲል አግባባው።
...ቀናት ይህን ሚስጥር በሆዳቸው እንደታቀፉ ከነፉ!.....ነጎዱ!.....ሚስጥሩ ይፋ የሚሆንበት ጊዜ ደረሰ።
አንድ ቀን ቤተሰቡ ተሰበሰበ። አባት ሄዶ ከእናት ጎን ቆመ። ....ልጁ በጭንቀት ተዋጠ።....አባት የእናትን ዞማ ፀጉሮች ወደ ላይ ቀስ ብሎ ከፍ አደረጋቸው።......እናት ጆሮ አልባ ነበረች!.......ልጁ ዓይኖቹ በእናቱ ጆሮ አልባ ፊት ላይ እንደተተከሉ እንባ አንጠባጠቡ.... "ልጄ...." አለችው " የኔ ውበት ያንተ ፊት ላይ አለ!" አለችው።
**
ወዳጆቼ እናት  ማለት እንግዲህ እንደዚህ ነች.......
እናት
3.3K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 11:06:37
ውበቴን _ በፊትህ
"ልጄን አሳዩኝ?" አለች በደከመ ድምፅዋ ከወሊድ ስቃዩዋ ገና እፎይ ሳትል። አምጥተው ክንዶችዋ ላይ አደረጉላት። ህፃኑ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገላለጠችው። ክው ብላ ደነገጠች ።
2.3K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 11:03:02
"ህልም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ፤ ለአሁኑ ጊዜም ኃይል ይሰጠናል።

--ጆን ማክስዌል

"በልበሙሉነት ወደ ሕልምህ አቅጣጫ ሂድ። ያሰብከውን ህይወት ኑር። "

-- ሄንሪ ዴቪድ ቶሬው

ሁላችንም በህይወታችን ልናደርገው የሚገባ ጠቃሚ ነገር እንፈልጋለን።
ህልም ያንን ይሰጠናል!

ህልም የምንጓዝበትን አቅጣጫ ይነግረናል ፤ እንደ ኮምፓስ ያገለግለናል።

ህልም እምቅ አቅማችንን እንድንገነዘብ እና በውስጣችን እና በአካባቢያችን ያሉትን ታላላቅ ሀብቶቻችንን እንድንረዳና እንድንጠቀም ይረዳናል።

በህልም ራሳችንን በአዲስ ብርሃን ማየት እንጀምራለን፣ የበለጠ አቅም እንዳለን እንረዳለን።

የምናገኛቸው አጋጣሚዎች፣ ያገኘናቸው ሀብቶች፣ የምናዳብረው እያንዳንዱ ችሎታ ወደዚያ ህልም የማደግ አቅማችን አካል ይሆናል።

ሕልማችን ትልቅ በሆነ ቁጥር አቅማችን ይጨምራል።

ራዕይህ - ህልምህ - ታላቅ ከሆነ ስኬታማ የመሆን አቅምህም እንዲሁ ነው።

ህልም በህይወታችን ወሳኝ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ እንድንሰጥ ይረዳናል።

ምርጫዎቻችንን እንድናመዛዝን እና ለእኛ አስፈላጊ በሆነው ላይ በመመስረት ውሳኔ ለመወሰን እንድንችል ይረዳናል።

ህልም በምናደርገው ነገር ሁሉ በህይወታችን ውስጥ ዋጋ ላለው ነገር ቅድሚያ እንድንሰጥ ያስችለናል።

አንድ ህልም ያለው ሰው ወደ ላይ ለመውጣት መተው ያለበትን ያውቃል። የሚያደርገውን ሁሉ የሚለካው ለህልሙ መሳካት የሚያበረክተውን በማሰብ ነው።
2.7K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 16:32:10
ታላቅ የምስራች ተጅዊድን መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች

#ዚክራ_ኦንላይን_የቁርአን_ማእከል_የሁለተኛ #ዙር_ምዝገባ_መጀመራችንን_ስናበስር_በደስታ_ነው
#የሁለት_ወር_ጥቅል_የተጅዊድ_ትምሀርት


    
            #የትምህርቱ_አሰጣጥ

1,በዙም አፕልኪሼን
2,በቴሌግራም አፕልኬሽን

    
        #የቆይታ_ጊዜ
በሳምንት 3 ቀን


#ትምህርቱን_ለመከታተል_የሚያስፈልጉ
ዋይፋይ(ፈጣን ኔትወርክ)
ስማርት ስልክ


        #ያሉን_ቦታዎች

##በጀመአ (በግሩፕ)
##vip (በ ግል)

ከተሟላ በሰርተፍኬት ጋር

በግል ለመመዝገብ

@redwan6910

ዋትስ አፕ https://chat.whatsapp.com/I6YyupqN1TW8Nzf6DgVZXz

ወደ ተጅዊድ ትምህርት መስጫ ግሩፕ
https://t.me/+V3lxqKjWQHxiYzFk

ወደ public group

https://t.me/+-zHkXQeSZdc4MjY0

#zikra_Qur'anic_academy
601 views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 06:33:25
አግኝቶ ማጣት
1.3K viewsedited  03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 00:58:13
እናቱ. ..ይህን አሮጌ ብስክሌት ይዘህ አትውጣ ብላ ደጋግማ ነግራዋለች ። ልክ ይህን ስትለው እሽ ሌላ ግዥልኝ ይላታል ። በዚህ ጊዜ አቅሟን ስለምታውቅ ዝም ትላለች ። ብስክሌቱን ይዞ ይወጣል። አሁንም ያደረገው እንደዚሁ ነው ። ይህን ብስክሌት ይዞ በወጣ ቁጥር ወይ ከግንብ ጋር ወይ ከሌሎች ልጆች ብስክሌት ጋር ስለነበር ማንም ጠይቆት አያውቅም ነበር። ዛሬ ግን ከቤቱ በቅርብ ርቀት አሮጌ ሳይክሉን እየነዳ ሳለ ቆሞ ከነበረ መኪና ጋር ተጋጨ ፡ ዘመናዊ መኪና ይነዳ የነበረው ሰው ወጥቶ መኪናውን አየው ቀለሙ ተጭሯል። ደንግጦ የቆመውን ልጅ ተመለከተ ፡ ይቅርታ ሚስተር ፍሬኑ አልሰራ ብሎኝ ነው ፡ እያለ ወደቤቱ ሮጠ ። ሰውየው ትንሽ ተከትሎት ተመለሰ ።
......
በማግስቱ የልጁ ቤት ተንኳኳ ፡ የልጁ እናት ከፈተች ፡ ልጅሽን ፈልጌ ነበር አላት ትናንት መኪናዬን ገጭቶ እዚህ ሲገባ አይቼዋለሁ ። አላት አዎ ነግሮኛል ይቅርታ ፡ የሚከፈለውን ንገሩኝና ለመክፈል እንሞክራለን አለችው።ጥሩ እሱን እንነጋገራለን አሁን ልጁ የታለ አላት ፡ ጠራችውና ወጣ። መኪናዬን እንዴት አድርጎ እንደጫረብን ነይ ላሳይሽ አላትና ፡ መኪናው ወዳለበት ቦታ ሰውየውን ተከትላ ከልጇ ጋር ሄደች።
እና መኪናዋን ስታይ እናትና ልጅ ደነገጡ ። ሰውየው አዲስ እና ዋጋው ውድ የሆነ ብስክሌት ጭኖ ይዞለት መጥቷል። እና ይሄ ብስክሌት ያንተ ነው ፡ ፍሬን የሌለው አሮጌ ሳይክል መንዳትህ ለሌላ ጉዳት ሊዳርግህ ስለሚችል አዲስ ገዝቼልሀለሁ ። አለና ሳይክሉን አውርዶ ሰጠው ፡ ታዳጊው ይህን ሲያይ በደስታ አለቀሰ ፡ ደጉ ሰውዬ የልጁን ደስታ ሲያይ ደስ አለው ። የሰፈሩ ልጆች በአድናቆት ከበቡት ፡ እናም ይህን ቅፅበት እናትየው በስልኳ እንዲህ እንደምታዩት አስቀርታው ሁኔታውን እኛም ማየት ቻልን።

ደግ ልቦች ለዘለአለም ይኑሩ ።
1.2K views21:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 07:52:57
ውርጭ ያዘለ ልቤን
1.9K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 07:05:33
አዲስ አበባ ያላችሁ


አዲስ አበባ ላይ ኢፋዳን ምስሉ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች በመሄድ ይግዙ። በቴሌግራም @ifadasales ላይ ቀድመው ኦርደር ማድረግና ክፍያ መፈፀምም ይችላሉ። ከዚያም ከዚያ የሚሰጥዎትን ቁጥር በማሳየት ብቻ መፅሀፉን ከሚቀርብዎ ቦታ መውሰድ ይችላሉ።

ቀዳሚ አንባቢ ይሁኑ!
.
2.7K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 07:03:09
አሰላሙ አለይኩም ፉአድ ሙና ኢፋዳ የሚል መፅሀፍ አዘጋጅቶ ገበያ ላይ ከኢድ ጀምሮ ለአንባቢዎች አድርሷል፡፡ ሙስሊም ፀሀፊዎችን ማበረታታት ለወደፊት ለሚሰሩት ስራ ሞራል መስጠት ነዉ፡፡ እኔ ይሄን መፅሀፍ የገዛሁት ገበያ ላይ እንደዋላ order ሲደረግ በኢዱ ቀን ነበር...ይሄዉ ትናንት ደሴ መጥቶ ተረከብኩ፡፡
ማንበብ ጀምሪያለሁ፡፡
እናም ፉአድ ሙናን ማጠናከር ማበረታታት አለብን፡፡ አዲስ አበባም በክልል ከተሞችም
ስለተሰራጨ መፅሀፉን በመግዛት ከጎንህ ነን ልንለበዉ ይገባል

ክፍለ ሀገሮች ኢፋዳን በተጠቀሱት አድራሻዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

ኢፋዳን በክልል ከተሞች!
.
★ወራቤ
ወራቤ ከቴሌ ጎን(ፓርክ ሆቴል ፊትለፊት) አቅሷ የኪታብ መሸጫ መደብር

★ሀዋሳ
ሀዋሳ ፒያሳ ኬርአውድ ሆቴል ፊትለፊት ሁሴን ሞል ሳኒ ሞባይል አክሰሰሪ ሱቅ ቁ.29

★ጅማ
ጅማ +251944842429 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።

★ደሴ
ደሴ +251982674095 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።

★አዳማ
ፖስታ ቤት ወደ ፒኮክ በሚወስደው አስፓልት በኩል አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ አሰብ አዳማ የገበያ ማዕከል መግቢያ ላይ በሚገኘው ፖስታ ስቴሽነሪ

★ድሬዳዋ
ድሬዳዋ አሸዋ በሚገኘው ሲትራ ሱፐርማርኬት
ቦታው ከጠፋችሁ+251929065110 ደውሉ

★ሀረር
ሀረር ሲጋፋ ተራ kim Cafe ፊትለፊት መካ ኤሌክትሮኒክስ
ቦታው ከጠፋችሁ +251968209420 ይደውሉ።
.
#Ifadasales

.
በመሆኑም ቀድማችሁ @ifadasales ላይ ክፍያ የፈፀማችሁ የተላከላችሁን ቁጥር በማሳየት መረከብ የምትችሉ ይሆናል።
በሞባይል ባንኪንግ @ifadasales ላይ መክፈል የማትችሉ በካሽ እየከፈላችሁ መግዛት ትችላላችሁ
2.2K viewsedited  04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ