Get Mystery Box with random crypto!

እናቱ. ..ይህን አሮጌ ብስክሌት ይዘህ አትውጣ ብላ ደጋግማ ነግራዋለች ። ልክ ይህን ስትለው እሽ | ISLAM IS UNIVERSITY

እናቱ. ..ይህን አሮጌ ብስክሌት ይዘህ አትውጣ ብላ ደጋግማ ነግራዋለች ። ልክ ይህን ስትለው እሽ ሌላ ግዥልኝ ይላታል ። በዚህ ጊዜ አቅሟን ስለምታውቅ ዝም ትላለች ። ብስክሌቱን ይዞ ይወጣል። አሁንም ያደረገው እንደዚሁ ነው ። ይህን ብስክሌት ይዞ በወጣ ቁጥር ወይ ከግንብ ጋር ወይ ከሌሎች ልጆች ብስክሌት ጋር ስለነበር ማንም ጠይቆት አያውቅም ነበር። ዛሬ ግን ከቤቱ በቅርብ ርቀት አሮጌ ሳይክሉን እየነዳ ሳለ ቆሞ ከነበረ መኪና ጋር ተጋጨ ፡ ዘመናዊ መኪና ይነዳ የነበረው ሰው ወጥቶ መኪናውን አየው ቀለሙ ተጭሯል። ደንግጦ የቆመውን ልጅ ተመለከተ ፡ ይቅርታ ሚስተር ፍሬኑ አልሰራ ብሎኝ ነው ፡ እያለ ወደቤቱ ሮጠ ። ሰውየው ትንሽ ተከትሎት ተመለሰ ።
......
በማግስቱ የልጁ ቤት ተንኳኳ ፡ የልጁ እናት ከፈተች ፡ ልጅሽን ፈልጌ ነበር አላት ትናንት መኪናዬን ገጭቶ እዚህ ሲገባ አይቼዋለሁ ። አላት አዎ ነግሮኛል ይቅርታ ፡ የሚከፈለውን ንገሩኝና ለመክፈል እንሞክራለን አለችው።ጥሩ እሱን እንነጋገራለን አሁን ልጁ የታለ አላት ፡ ጠራችውና ወጣ። መኪናዬን እንዴት አድርጎ እንደጫረብን ነይ ላሳይሽ አላትና ፡ መኪናው ወዳለበት ቦታ ሰውየውን ተከትላ ከልጇ ጋር ሄደች።
እና መኪናዋን ስታይ እናትና ልጅ ደነገጡ ። ሰውየው አዲስ እና ዋጋው ውድ የሆነ ብስክሌት ጭኖ ይዞለት መጥቷል። እና ይሄ ብስክሌት ያንተ ነው ፡ ፍሬን የሌለው አሮጌ ሳይክል መንዳትህ ለሌላ ጉዳት ሊዳርግህ ስለሚችል አዲስ ገዝቼልሀለሁ ። አለና ሳይክሉን አውርዶ ሰጠው ፡ ታዳጊው ይህን ሲያይ በደስታ አለቀሰ ፡ ደጉ ሰውዬ የልጁን ደስታ ሲያይ ደስ አለው ። የሰፈሩ ልጆች በአድናቆት ከበቡት ፡ እናም ይህን ቅፅበት እናትየው በስልኳ እንዲህ እንደምታዩት አስቀርታው ሁኔታውን እኛም ማየት ቻልን።

ደግ ልቦች ለዘለአለም ይኑሩ ።