Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.95K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-20 06:29:50 #ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም
                  አሚር ሰይድ

          
           
#ክፍል አስራ ሶስት



ጊዜዉ ከባድ ነዉ ልንገራችሁ እስኪ ብዙ መንገር ይቻላል
ግን ለመስማት የሚዘገንን ነዉ ግን ይሄ ከሌላዉ አንፃር ይሻላል ብየ ነዉ፡፡


  አንዲት እህታችን 7 ልጅ አላት..ባሏ የከባድ መኪና ሹፌር ነዉ እናም ብዙ ቀን እቤት አያድርም፡፡ እቤት ስለማያድር ሚስቲቱን ሌላ ወንድ ጋር እኔ ሳልኖር ብትሄድ ወይ ብትተኛብኝስ??ብሎ ይጠረጥራታል ፡፡
ጊዜ የማያመጣዉ የለም የመጨረሻዉ ልጅ ይታመምና እኛ ሰፈር ያለ ሩቃ የሚያደርግ አንድ ብር የማይቀበል ለአላህ ብሎ የሚሰራ ነበር እሱ ጋር መጣች ልጁን በተወሰነ ደቂቃ በአላህ ፍቃድ በአፉ ብዙ ነገር ወጥቶ ሻረ....እናቲቱም እስኪ እኔም ለሊት ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስትለዉ በቁርአን ገና ጀመር ሲያደርግ...ለማመን ይከብዳል እርይ ማለት ጀመረች...ጂኑ ተነቃብኝ ተጋለጥኩ ተጋለጥኩ ማለት ጀመረ...
ከዛ ልጁ ጅኑን መጠየቅ ጀመረ...ጂኑ ሲናገር...
ባሏ እሷን አያምናትም ሹፌር ስለሆነ ሌላ ጋር ብትማግጥስ ብሎ ስለሚያስብ ሶስት አይነት ሲህር(ድግምት) ጎጃም ሂዶ 10,000 ብር ከፍሎ አሰራ እሱ እያሰራ ለእሷ ግን የአስቤዛ የለኝም ይላታል፡፡ የተሰራዉ የተላክነዉ 3 ጂኖች ነን የተሰጠን ስራ
➊ ቤተሰብ ጋር እንዳትስማማ ልጆቿ እንዳይወዷት አንቺ ነገረኛ ነሽ አባታችን ነዉ ለኛ የሚያስብልን ብለዉ እሷን
እንዲጠሏት...የእሷም የእሱም ዘመዶች ነገረኛ ከፉ ነች ተብላ እንድትጠላ
➋ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን እንድናጠፋ
➌ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች በአደባባይ እንድትጋለጥ በዛ እፍረት እብድ እንድትሆን ነዉ ያስደገመባት ...

ድግምቱን ይዘን መጥተናል የመጀመሪያ ከልጆቿ ከቤተሰቦች እንዳትስማማ አሳክተናል፡፡ ግን ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን አጥፍተን እብድ ለማድረግ በሰከንድ ከእኛ እይታ ተደብቃ አታቅም በየሰከንዱ እንሰልላታለን እሷ ግን የዋህ ታማኝ ነች እንኳን ከሌላ ወንድ ጋር ልትተኛ ..ልጆቿ እሷን ባይወዷትም  በሰገደች ቁጥር ለልጆቿ ለባሏ  ዱአ ታደርግላቸዋለች...
ከዛ ትለቃላችሁ ሲባል አዎ እንለቃለን ግን እሱ መጥፎ ሰዉ ነዉ ይቺ ምንም የማታቅ ሚስኪን 7ልጅ ለማሳደግ እየተጨነቀች እሷን በዚና ጠርጥሮ እንደዚህ አድርጓታል አንለቀዉም ብለዉ ከእሷ ሰዉነት ጅኖቹ ወጡ

እናም ጊዜዉ ከብዷል ጎበዝ
ወላሂ እኔ ብዙ የማቀዉ ብነግራችሁ ጓደኞ ዘመድ ቤተሰብ ጋር ያለን ግንኙነት ትንሽ እንዳይሻክር በመፍራት ብዙዉን ከመፃፍ ተቆጥቢያለሁ
☞ እህት በእህት/እህት በወንድም/ወንድም በእህት
☞ሁለተኛ ወይ የመጀመሪያ ሚስት በባሏ
እስኪ አስተዉሉ ሸሪአዉ ፈቅዶ አቅም ኑሮት ሁለተኛ ሲያገባ በጣም ከባድ ፀብ ጭቅጭቅ በአንዷ ቤት ይኖራል ..ከአንዷ ጋር በጣም ፍቅር ከአንዷ ጋር ፀብ ምናምን በቃ ያገባዉ የተለያዩ ባህሪ ፀባይ እስከ ፍች ወይም ለሁለቱም ሚስቶቹ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ እንጃ ወንዶች መጠርጠሩ አይጎዳም
☞ የዘመድ የጎረቤት ያለ ጉድ ከባድ ነዉ...ብቻ የሚሻለዉ #ከሰዉ_ጋር_ያለንን_ግንኙነት_በዉዱዕ_መሆን_ነዉ_ያለብን

በደንብ አዉቀን ልናሳዉቅ ለሌች ትምህርት ልንሰጥ የሚገባዉ አንዳንዴ በዲን እዉቀት ጠለቅ ብለን የማናቅ ሙስሊሞች ላይ ሸክ ጥርጣሬ የሚገባን ጉዳይ አለ እሱም ...ጂንን ሲህር ድግምትን
ክርስቲያኖቹ በፀበል እያስለቀቁት አይደል እንዴ
ጴንጤዎች አሜን እያሉ እያተበተቡ ያስለቅቁ የለ እንዴ
አንዳንድ ሸሆች እየቃሙ ያስለቅቁ የለ እንዴ
ጠንቋዮችም ሲያስለቅቁ እያየን አይደል እንዴ


አንዳንዶቹ ሲሞግቱ ከባድ ጂን ወይም ብዙ ሲህር አይነጥላ ከሆነ ቀናቶች ይፈጃሉ በቁርአን ይሄን ያህል ቀን ይፈጃል በፀበል ጠንቋይ ቤት ግን በአንድ ቀን ይለቃል ታዳ ከቁርአን ዉጭ ፀበልም የጴንጤዎች ቦታ የታመዉ መሻሉ እንጂ ለምን አንወስድም?? እያሉ እየወሰዱም ነዉ...ግን ክርስቲያኖችም ጴንጤዎች  እንዴት ማስለቀቅ ቻሉ??የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ

#ለምሳሌ በቫቲካኖች (ካቶሊኮች)  ህክምና እነርሱ ዘንድ ሊታከም የመጣ ሰው በኮከብ ውስጥ አስረው እና ጥላሸት ቀብተው እነሱ ትልልቅ ጂኖችን እያዘዙ ሰዉየዉን የያዘዉን ትንሽ  ጂን ከቦታው ያስወጣሉ። አዎ ይህ ህክምና ይሰራል ምክንያቱም ለደካማ ጅን ሁሌም ቢሆን ጠንካራ ጅን አለ ። ይሁንና ይህ ታካሚ ኢፍሪት የያዘው ወቅት ላለመውጣት ታካሚውን ሙሉ ለሙሉ ገድሎና ሰውነቱን ቀጭቶ ይወጣል። ከ 100% 25%ድንገተኛ ሟቾች ናቸው።

ይህ አይነቱ ህክምናም በተለያዩ እምነቶች ያለ ሲሆን ህክምናቸውም ሲህርን በሲህር በጅን እያደረጉ አስማት ነው በማለት ሰዎችን ይሸነግላሉ ።

አስማትን በአስማት ማከም መታከም ለድንገተኛ ሞት ይጋልጣል።ለምን የሚያዟቸዉ ትልቅ ጅንን ነዉ ሰዉየዉ የያዘዉ ከሚታዘዘዉ ጅን በላይ አቅም ካለዉ ከባድ ነዉ ሰዉየዉን በሂደት እስከመግደል ይደርሳል፡፡

ለምሳሌ እስኪ እሰቡት እስኪ በወንዶች በፊት ስናድግ በሰፈራችን የሰፈር አለቃ አለ እንበል....እሱ የፈለገ ቦታ ይልከናል እምቢ ብንል ይመታናል ያለን አማራጭ መታዘዝ ነዉ፡፡ ወይም መንግስት ግዴታ ይሄን አድርግ ካለን ምን አማራጭ አለን??? ምንም ግዴታ ከማረግ ዉጭ..,,እናም ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ ተፈሪ የሆኑ ጅንኖች ትናንሽ ደካማን ፈሪን ከሰዉየዉ ገላ  የማስወጣት አቅም አላቸዉ

በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡

ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።
ጂኒዎች እንደኛዉ ናቸዉ እነሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ ስለሆን ነዉ እንጂ

#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡

ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ወራትም አመታትም ሊሆን ይችላል ጠንቋዩ ጋር ጅኑ እንደስምምነታቸዉ ነዉ ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ማካሄድ አለባቸዉ መቼም አይለቅም  ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡

በፀበል ደግሞ ላላችሁት በሚዲያ ላይ ማዉጣት ይከብዳል የሆነ የሚሰማ የማቀዉ ስላለ ነዉ፡፡ወሎ ሲባል ቅልቅል ነን እኔም ብዙ ቤተሰቦቼ ክርስቲያን ናቸዉ
1.6K viewsedited  03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 16:53:28

Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.7K viewsedited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 03:04:17 አንድ የጓደኛየ እህት ታሪክ ላጫዉታችሁ...
ያዉ መቼም አሁን እወድሻለሁ እወድሀለሁ የሚለዉ ቃላት ህፃን ልጅ እናቴ ቁርስ ምሳ እራት እራበኝ የሚበላ ስጭኝ በቀን ብዙ ጊዜ ከምላሱ የማይጠፋ ነዉ አሁንም እወድሀለሁ አፍቅርሀለሁ ቋንቋ እንደዚህ ህፃን ልጅ ምግብ ፍላጎት ጋር የተመሳሰለ ነዉ....
እናም ይዋደዱሉ ግን የሚገርመዉ ሲገናኙ እሱ ሲርየስ ይሆናል ግን ማታ እቤቱ ሲሄድ ምነዉ አዉርቻት በነበር እያለ ያለቅሳል በዚህ አይነት ሲጣሉ ሲታረቁ 8ወር ያህል አሳልፈዉ ፌንት መዉደቅ መጨናነቅ የፀባይ መከረባበት ሲገጥም ወንድሟ በዲኑ የተሻለ ስለሆነ ሌላ ጓደኛዉም በዲኑ ጎበዝ ስለሆነ እሱም ጓደኛዉ ሲቀራ ቢያንስ ሁለት ወር ፈጀ...

የሚገርማችሁ ቁርአን እየቀራባት እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገዉ ቁርአን ሲቀራ ጂኑ ከፊት ስለሚሆን ስልክ አንስቶ ለምወደዉ ልጅ ይደዉልና ናፈከኝ እወድሀለሁ እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ ናፈቅከኝ ምናምን እያለ ያወረዋል የሚገርም የሚገርም የፍቅር ወሬ ከዛ ከእንቅልፉ ሲባንን መልሼ እደዉልልሀለሁ ቤተሰብ መጣ ወይ ወንድሜ መጣ ብሎ ስልኩን ይዘጋዉና....ጂኑ ይስቃል ለምትወደዉ ለሚወዳት ፍቅረኛዋ ደዉየ ተጫወትኩበትን እንደምወደዉ ነግሬዋለሁ ዛሬ ሲደሰት ያድራል ነገ ደግሞ አጣላቸዋለሁ ይላል...ከዛ ትምህርት ስትሄድ እንዳለዉም እዛ ይጣላሉ በቃ እሷን የሚያሽከረክራት ጂኑ ነበር...
የሚገርማችሁ ልጁ ስልክ ጋር በmessage በtelegram የሚያወራዉ ጂኑ ነበር እሱ ማታ በtg በmessage እንደዚህ ብለሽኝ አረ አላልኩህም ትለዋለች
ከእሷ የለም ይጠፋል mesage እሱ ጋር ይኖራል በቃ ግራ የሚያጋባ ሁለት የሚዋደዱ ተብየ ግራ የሚያጋባ ፀብ የበዛበት ፍቅር ሆኖ ነበር፡፡

  ወንድሟ ቁርአን ቀን ማታ  ያለመሰልቸት ሲቀራ ሩቃ ሲያደርግ በስንት ጥረት  ጂኒዉ ብዙ ነገሮችን ተናገረ በፍቅር ስም እሱንም እሷንም ሲቆጣጠራቸዉ ሲያስለቅሳቸዉ ከአንተ መኖር አልችልም ካለ አንቺ መኖር አልችልም ሲል የነበረዉ በmesaage አልፎ አልፎ ሲያወራ የነበረዉ  ይሄዉ እሷን ተቆጣጥሯት የነበረዉ በሲህር የተላከ ጂን ነበር
ከዛ ከእሷ ላይ ጅኑ ሲለቅ የሚገርመዉ ነገር እሷም እሱም እንደበፊቱ መሆን አልቻሉም... አለ አይደል ያ ፍቅር ሲባል የነበረዉ ነገር ህልም ሁኖ ቀረ .....

ጅኑ(ሲህሩ) ከለቀቀ ከተወሰኑ ቀን ቡሀላ የወንድሟ ጓደኛ ወንድሟን እሷን እንዲድረዉ ይጠይቀዋል ...ወንድሟም  ያለዉን ነግር የበፊት ታሪኳን በፊት የነበረዉን በሩቃ እንደተሻላት ይነግረዋል....ከዛ ትዳር የጠየቀዉ ይስማማል....

የሚገርመዉ ነገር እሷም ስትጠየቅ የምወደዉ አለኝ አላለችም መርሀባ በትዳሩ እስማማለሁ አለች...
በፊት የሚወዳትም ከመታጨቱ በፊት ሰምቶ ማሻ አላህ ደስ ይላል ታግቧ ኸይር ነዉ ነበር ያለዉ...እናም ሁለቱም አንድ ላይ ሆኑም አልሆኑም ጂኑ(ሲህሩ) ከለቀቀ ቡሀላ በቃ ሁለቱም ኖርማል ሁነዋል፡፡በጣም ነዉ የገረመኝ..
ከዛም ልጂቱ አገባች ግን በኢማኗ ትንሽ ደከም ያለች ስለሆነች በተወሰኑ ወራት ልዩነት ሲህሩን ያሳድሱባታል መልሳ የተወሰነ ትሰቃያለች ግን ባልየዉ መጀመሪያ ስለሰማ ታጋሽ አስተዋይ ነዉ በሩቃ እሱዉ እየቀራ ይዟታል፡፡የሚገርማችሁ ባሏ ጋር እንድትፋታ ሳሂሩ ያላደረገዉ ጥረት የለም ግን ባልየዉ ታገሽ መሆኑ ትዳሩን እድሜ እንዲረዝሞ አደረገዉ....አሁን ከሁለት ወር በፊት ጂኑ መፍትሄ ሲያጣ አዉቆ የበፊት ፍቅረኛዋን ስም እየጠራ ናፈቀኝ ይላል...አዉቆ ጂኑ ዉሸቱን አንተን ከማግባቴ በፊት እሱ ጋር ይሄን ይሄን አሳልፊያለሁ ላይፍ ቀጭቻለሁ አንተን ያገባሁት እሱ ጋር ላይፌን ቀጭቼ ነዉ እያለ ሲህሩ ሲታደስባት የተላከዉ ጅን በእሷ አስመስሎ ያወራል ...በጣም ከባድ ነዉ ግን ባልየዉ የዲን እዉቀት ስላለዉ በሰከነ መልኩ በሩቃ ይታገል ይዟል....

አስባችሁታል ወንዶች?? ያገባሀት ምስት ጂን ይዟት ወይም ሲህር ተደርግባት ከትዳር በፊት ያለፈ ተብሎ እዉነቱንም ዉሸቱንም ቢነግርህ ለባልየዉ አቅል አይከብድም??? አሁን ደህና ሁናለች ግን ሲህር ያደረገባት ሲያሳድሰዉ በጣም እሷም ባልየዉም ይፈተናሉ፡፡
ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ይሄ ታሪክ የጓደኛየ እህት ታሪክ ነዉ፡፡ ግን እስኪ ሲህር ወይ አይነጥላ ቡዳ ወይ ጂን ይዟችሁ ሩቃ ተደርጎ በአላህ እገዛ ስትሽሩ ከዛ በፊት ፍቅር ተብየ ከነበረባችሁ ፍቅሩ ከሩቃ ቡሀላ ለቋችሆል ወይስ አለቀቃችሁም?? እስኪ ለጠቅላላ እዉቀት ነዉ ገጠመኝ ካለ አሳዉቁኝ...በተጨማሪ እዚህ ቻናል የስነ ልቦና ባለሙያ ካላችሁ እስኪ ሀሳብ ስጡበት ከምር ግራ ነዉ የገባኝ...
4any cmt
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

 ግን ማወቅ ያለብን አፍቃሪ ጅኖች የሚባል አለን!!
አሺቅ ጅን ማለት በቀጥታ ፍቺው አፍቃሪ ጅን ማለት ነው፡፡
ጅኖች ከሴትም ይሁን ከወንድ ጋር ፍቅር ይይዛቸዋል፡፡ ይህንም እጅግ በጣም በሚዘገንን ሁኔታ ፍቅራቸውን ገላጮች ናቸው እስኪ ምልክታቸውን እንይ!!
ምልክቶቻቸው!!
➊ ህልማችን በሙሉ ወሲባዊ ይሆናል!! በህልም ስትዳሪ አንሶላ ስትጋፈፊ በህልምህ ዚናን ስትሰራ እላይህ ላይ ዘርህን ስታፈስ የምትነቃ ከሆነ ይህ የመጀመርያው ምልክታቸው ነው፡፡

➋  ከእንቅልፋችን ስንነቃ ሰውነታችን ላይ የመበለዝ ምልክቶችን እናያለን፡፡ ልክ ሌላ ሰው እንደደበደበን አይነት ምልክት!! ይህ እጅ ላይ እግር ላይ ይሆናል ምልክቱ!! የሚገርመው ግን ከግማሽ በላይ ታካሚዎቻችን ላይ የሂና ከለር የመሰለ ጥቁር ምልክቶች ይታይባቸዋል


➌ ለሊቱን ተደባድቦ እንዳደረ ሰው ወይም ተደብድቦ እንዳደረ ሰው ሰውነታችን ስብርብር ብሎ ማደር፡፡ ይህ ለየት የሚያደርገው የጅን ምልክት ነው!!

➍ ሰውነትህ ወይም ሰውነትሽ ምንም ብታደርጉበት ይሸታል፡፡ ይህን ሽታ በምንም ነገር ልትቆጣጠረው አትችልም ወይም አትችይም፡፡ ሽታውን ለማጥፋት ታጥበን ተኩል ደቂቃ በሞላ ግዜ ውስጥ የሚያስጠላ ሽታ ይኖረናል፡፡ አሏህም ይጠብቀን!! ይህ በሽቶ በዶድራንት ሊደበቅ አይቻለውም፡፡

➎ ይህ ጥቃት በሴቶችም በወንዶችም ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ጥቃት ላይ ያሉ ሰዎች ከምንግዜውም በላይ ሊወፍሩ ይችላሉ አልያም ሊከሱ ይችላሉ!! ይህም ሌላው ተመልካች በነርሱ ላይ ፍላጎት እንዳይኖረው የማድረግያ ጥበቡ ነው!! አሏህም ከጅን ተንኮሎች ይጠብቃችሁ!!

➏ በተጠቂው ጆሮ ላይ መጥፎ ነገሮችን በሙሉ በማምጣት መካሪ ነው፡፡ ለምሳሌ
☞ ሴት ከሆነች ‹‹ገና ነሽ ቆንጆ ነሽ ሰው ይፈልግሻል እንዳትሞኚ›› ሲል ይሸነግላል
☞ ኋላ ላይ አስወፍሮ ጉድ ሊሰራ ወይ ደግሚ ‹‹በቃ የሚፈልግሽ የለም ትዳር የለም ላንቺ የሚመጣ ወንድ የለም፡፡
☞ ላንቺ መስዋአትነት የሚከፍል የለም ተፈላጊ አይደለሽም ›› ሲል በጆሮ በመምጣት ይመክራል!!

➐ ሰላትና ኢባዳ ላይ ደካማ ያደርገናል፡፡ በሙሉ ለሙሉ ተስፋ ቆራጮች ብንሆንም በዚህ ግዜ የቀረችን የነበረችውን ሰላታችንን ያጠፋብናል፡፡ በዚያም ላይ እርካታ እንዳይኖረን ይገፋፋናል፡፡ ይህም ብዙውን ግዜ ከሱብሂ ይጀምራል በማዘናጋት አስር ላይ ይጠነክራል ኢሻእ ላይ ይጥላል ወደ እንቅልፍ፡፡ ይህ በጅኑ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ላይ ስትሆኑ ነውና፡፡

በሚቀጥለዉ ክፍል
አንዲት እናት 7 ልጅ ያላት ባሏ ሹፌር ነበር ስላላመናት ስላደረገባት ሲህር እዉነተኛ ታሪክ ይዤ እቀርባለሁ

#ክፍል

ይቀጥላል....
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
1.8K views00:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 03:02:07 #ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም
                  አሚር ሰይድ
             
          
                
#ክፍል አስራ ሁለት


  በተከታታይ ➊➊ ፓርቶች ድግሞትና ሲህር ከሚለዉ መፅሀፍ 70% በራሴ ካነበብኳቸዉ ከማቃቸዉ 30% ጨምሬ ከሰዎች ታሪክ በመጨመር በምሳሌ አቅርቢያለሁ ..ከpart ➊➋ ጀምሬ እስኪ ከሰማሁት ከማቀዉና መረጃዎችን በማጣቀስ ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡


መጀመሪያ ብዙሀን ሰዉ አናምንም እኛን አይነካንም እንላለን ...ግን በራስ ሲደርስ ነዉ የሚታወቀዉ  የኢማን የመጠንከር የመላላት ጉዳይ አይደለም የሆነ የምንዘናጋበት ቀን አለ በዛ ቀን በሰዉ ምቀኛ በተለይ በቅርብ ጓደኛ በቅርብ ዘመዶች ሊያነጣጥሩብን ይችላሉ ....የት ይሰራል ብላችሁ ካሰባችሁ ...ብዙዎች እነሸህ እነ ወልይ የወደፊት ያቃሉ እያሉ እየሄዱ እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ ጀለብያ ጥምጣም ለብሰዉ ሳሂር ደጋሚ የሆኑ እንዳሉ አንዘንጋ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዉ ከሙስሊሙም ሌላም ሀይማኖት ተከታዮች የሚሄዱት ደብተራዎች ጋር ነዉ፡፡ 
ደብተራዎች face book እና tg ቻናል አላቸዉ ለምሳሌ ሁለት የማቀዉን ከtg ያገኘሁትን ከታች ተመልከቱ


መርጌታ ገብረ መድን በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ለማይችሉ ባሉበት እንሰራለን የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል     09 ... 03 .... ስልኩን ያጠፋሁት ደግሞ እንዳደዉሉ ብየ ነዉ
ለገበያ>>ለሀብት>>ለስንፈተ ወሲብ (ለቁመት:ለውፍረት: ቶሎ ለሚያበቃ) >> ለመስተፋቅር >>ጥይት ለማያስመታ >> ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ >> ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)>> ለፀር (ለጠላት)>>ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)>> ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)>>ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)>>ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)>> #መስተፋቅር>> ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
>> ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ>> ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)>> የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ>>ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)>> መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)>> መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)>> ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)>>ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)>> ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ>> ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ>> ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)>> ለሙግት>> ለሰላቢ>> ለስንፈት ወሲብ>> ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)>> ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)>> ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)>> ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)>> መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)>> ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)>> ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)>> በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው >> እንቅልፍ መብዛት>> የእንቅልፍ ማነስ >> የወር አበባ ችግር ካለ

09...  03 ....
ይደውሉልን

በተጨማሪ የሌላዉን በtg የሚፓስተዉን ልላክላችሁ

09 4............5  የባህል መድህኒት  ጥበብ አስማት ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
መፍትሄ ሀብት መስተፋቅር = የገበያ  ለቀለም= ትምህርት ለአይነ ጥላ= ለመፍትሔ ስራይ= ለህማም = ጋኔን ለያዘው ሰው = ቡዳ ለበላው = የዛር ውላጅ ለተዋረሰው = ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) =  ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) =  ለቀለም(ለትምህርት) = ሰላቢ የማያስጠጋ =  ለመፍትሔ ሀብት =ለመስተፋቅር =  ለገብያ =  ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) = ለመድፍነ ፀር =  ሌባ የማያስነካ = ለበረከት
= ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) = አፍዝዝ አደንግዝ = ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) = ለግርማ ሞገስ =  ለዓይነ ጥላ
=  ለሁሉ መስተፋቅር =  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ = ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) = ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ =  ለድምፅ =  ለብልት እንደመቆም =  ለኤች አይቪ መድሀኒት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

ለጥያቄወ 09 4........5 ይደውሉልን በአካል መቅረብ ለማትችሉ በሙሉ ወደ አሉበት ቦታ ድረስ ይደርሶዎታል

ይላል በTelegram በfacebook በጣም ብዙ አሉ ይሄን የላኩላችሁ ሲህር ድግምት ለእናንተ መጥፎ የሚስቡ መጥፎ ሰዎች እነዚህ ቦታ ቢሄዱ አስባችሁታል?? እነዚህ ቦታ ሂደዉ መስተፋቅር ወይ ገበያ እንድንከሰር ወይ ሌላ ነገር ቢያሰሩበን በእኛ ኢማን ድክመት በጣም ከባድ ነዉ ፡፡ እናም ብዙ ሰዉ የለም የሚል ካለ ራስን ማሞኘት ነዉ ደጋሚዎች ደብተራዎች በየሀገሩ በየመንደሩ አሉ፡፡


ማወቅ ያለብን የደብተራ ብቻ አይደለም ..በጣም በዙ ሙስሊም ተብለዉ በየገጠሩ የሚሰሩ አሉ ዱአ ላስደርግ ምናምን ጫት የሚቃምበት በጣም የሚበዛ ከሆነ ..ወይም በጫት እናስለቅቃለን ካሉ ዛር አለባቸዉ በጫት የሚያስለቅቀዉ ለትልቅ ጅን ይገብራል ማለት ነዉ እንወቅ እባካችሁሁሁሁ  ....

ወልዮች ሸሆች ጋር እያልን ጫት የሚቅሙ ጋር እየሄድን ባንዘናጋ ኸይር ነዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደዚህ እያለ የሚሄድን ወጣትም ሆነ ትልቅ ሰዉ ሰዉየዉን ባንቀርብ ወይ ሰዉየዉን ከቀረቡ እራቅ ብሎ በዉዲዕ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

የሚገርመዉ ነገር አንድ የገጠር ሰዉ የማምነዉ ለጅን ማረድ ከተወ ቡሀላ ሲያወራኝ ለጅን የሚያርድልን ሰዉ የመስጊድ ኢማማችን ነዉ ብሎኛል ...

አሏሁ የስቱርና


--------- ------ ------ ------ -----
    ግን አንዳንድ ፍቅሮች እንዴት ነዉ ???

አሁን ላይ ግራ የገባኝ ነገር አለ ፍቅር እንዴት ነዉ???
ፍቅር አለ ወይስ የለም ማለት ለማለት እየከበደ ነዉ ..ፍቅር አንዳንዴ የሲህር በሽታም ሊሆንም ይችላል ብቻ እኔ አሁን ግራ እየገባኝ ያለ ፍቅርን እንዴት መገለፅ ይቻላል መልስ የሌለዉ ጥያቄ...

ግን እስኪ ከዚህ በታች አይነት ታሪክ የደረሰባችሁ ካለ በአስተያየት መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ...ግን በፊት እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ወይም እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ ብለዉ በፍቅር ሲያለቅሱ ሲሰቃዩ የነበሩ..እንደ አጋጣሚ ወይም በሌላ ምክንያትም ቢሆን ታመዉ ሩቃ ሲገባ እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ያሉትን ሰዎች 80% እሱ ጋር ቢኖሩም ባይኖሩም ምንም አይመስላቸዉም...ከሩቃ ቡሀላ አፍቃሪዉ ሲህር ወይ ጂን ከነበረበት ከለቀቀ አፍቅረዋለሁ የሚለዉ ሰዉ ረጋ ማለት እና መረጋጋት ይታይበታል፡፡
1.6K viewsedited  00:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 20:23:27
ትልቅ ሰፕራይዝ የባል በቀል

ናይጄሪያ ውስጥ ነው፣ ባል ሚስቱ የሱን እግር እየጠበቀች እንደምትማግጥበት ይጠረጥራል። አውጥቶ አውርዶ ለስራ ፊልድ በሚወጣበት ጊዜ ከመኝታ ክፍሉ ውስጥ ድብቅ ካሜራ ይገጥማል።
ከስራ ሲመለስም በድብቅ የተገጠመው ካሜራ ያስቀረውን ተነቀሳቃሽ ምስል ሲፈትሽ እውነትም ሚስት የገዛ አልጋው ላይ ከጎረምሳ ጋራ አንሶላ ስትጋፈፍ ቀድቶ ኖሮ ከሀ እስከ ፐ ለባል ያሳየዋል።

በዚህ የሚስቱ ድርጊት ቆሽቱ ያረረው አቶ ባል የሆዱን በሆዱ ይዞ ሚስቱን ለልደቷ ቤተሰቦቿን ሁሉ እንድትጠራ፣ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋት እንደሚፈልግ ይነግራታል። ሚስትም አንደታዘዘችው ቤተሰቦቿን በሞላ ለልደቷ ትጠራለች። ባልም እሱ ቤት ባልነበረበት ወቅት በገዛ መኝታ ክፍሉ ውስጥከጎረምሳ ጋራ ስትዛለል ያስቀረውን ፎቶ በፍሬም ውስጥ አድርጎ በስጦታ ወረቀትም ጠቅልሎ የልደት ስጦታ ያበረክትላታል። ምንነቱን ለማየት የጓጉት ቤተሰቦች እንድትከፍተው በሞራል ይገፋፏትና ወረቀቱን ስትገልጠው የራሷ ጉድ መሆኑን ስታይ በድንጋጤ እራሷን ሳተች።

ሰውየው የሰራው ስራ ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ በናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያ የጭቅጭቅ አርዕስት ሆኖአል።
1.8K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 06:34:57 ወደ መፀዳጃ ቤት ከመገባት በፊት ከሰይጣናት በአላህ መጠበቅ

ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ ማለት ..

   መፀዳጃ ቤቶች የሰይጣናት መኖሪያዎች ናቸዉ፡ የሙስሊምን እነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰይጣን ሊገባበት ይችላል፤ በሩቃ  ጊዜ አንዳንዴ ጂኖቹ  ከሰይጣናት ሳይጠበቅ ወደ መፀዳጃ ቤት በመግባቱ ምክንያት ነዉ ልገባበት የቻልኩት" በማለት ይናገራሉ

(ዉዳሴዎች) ናቸዉ” በማለት መለሰልኝ፡ ነብዩ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ የሚከተለዉን ዚክር (ጸሎት) ይሉ ነበር፡-

‎ (بسم الله اللهم إني أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْحُبْثِ وَالْخَالِيث ‎ ቢስሚ አላህ አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነ አል ኹቡሲ ወ አል ኸባኢስ” (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ትርጉም፡- በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ

እጠበቃለሁ፡፡

የሶላት መከፈቻ ዚክር

የሚከተለዉን ጾለት በሶላት መክፈቻ ወቅት ማለት፡፡ ጁበይር ኢብን አል ሙጥዒም የሚከተለዉን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እንዲህ አሉ፡- ነብዩ ሲሰግዱ አየሁዋቸዉ እንዲህም ሲሉ ሰማሁ፡-


“አሏሁ አክበር ከቢራ፤ ወል ሃምዱ ሊላሂ ከሲራ፣ ወሱብሃነ አልሏሂ ቡክረተን ወአሲላ (ሶስት ግዜ)።
☞ አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ሚን ነፍኺኽ ወነፍሲኺ ወሀምዚሂ

ትርጉም፡- አላህ ታላቅ ነዉ፡፡ አላህ በብዙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጠዋት በማታ አላህ ፍፁም ነዉ፡፡ ከተረገመዉ ስይጣን ከትምክህቱ፤ ከግጥሙ እና ከእብደቱ በአላህ እጠበቃለሁ፡

የጋብቻ ህይወትን በሶላት መጀመር

ዓብደላህ ኢብን አል መስዑድ የሚከተለዉን አስተምረዋል። “ከመጀመሪያዉ የጫጉላ ግንኙነታችሁ በፊት ሚስትህ ሁለት ረክዓ ሶላት እንድትሰግድ አድርግ፡፡ አንተም ስገድ፡፡ ከዚያም የሚከተለዉን ፀሎት አድርግ፡-


አሏሁመ ባሪክ ሊ ፊ አኽሊ ወባሪክ ለኁም ፊዬ፣አሏሁመ ኢጅመዕ በይነና ማ ጀመዕተ በኸይሪን.. ወፈሪቅ በይነና ኢዛ ፈረቀተ ኢለ አል ኸይር” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

ትርጉም፡- አላህ ሆይ በረካ ያላት ሚስት አድርግልኝ፣ በእኔ ላይም በረካ አድርግ ለበጎ እስከተስበለብን ድረስ አንድ አድርገን፡፡ ወደ መልካም በምትለያየን ጊዜ ለያየን፡፡

በግንኙነት ወቅት የሚባል ዱዓዕ

ነብዩ የሚከተለዉን አስተምረዉናል “ማንኛዉም ሰዉ ከባለቤቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሊፈፅም ሲል የሚከተለዉን ዱዓዕ ካለ በዚህ ግንኙነታቸዉ ልጀ ቢፈጠር ልጁን ሰይጣን በፍጹም ሊጎዳዉ አይችልም ::

‎ بِسْمِ اللهِ اللَّهُمَّ جَنِّبْنَا الشَّيْطَانَ፣ وَجَنْبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنا ‎ ቢስሚላህ። አሏሁመ ጀኒብና አል ሸይጣን፤ ወ ጀኒብ አል ሸይጣን ማ ረዘቅተና

ትርጉም፡- አላህ ሆይ! ከኛ ሰይጣንን አርቅልን፡፡ ከሰጠኸን ሲሳይ ላይም ሰይጣንን አርቅልን፡፡

በአንድ ወቅት በጂኒ የተለከፈን ሰዉ ሩቃ ሲቀራበት፡፡ ጂኒዉ እስልምናን ከተቀበለ እና ንስሃ ከገባ በኋላ ታካሚዉ ይህን ፀሎት ሳይል ሚስቱን ይገናኛት ስለነበረ ሚስቱን በወሲብ እጋራዉ ነበር ብሏል፡፡

ሱብሃን አላህ! ስንት እና ስንት እንቁ ስጦታዎች እያሉን ዋጋቸዉን ዘነጋናቸዉ!



ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት፡፡


ከዚያም እንቅልፍ እንስከሚያሸንፍህ ድረስ ዚክር  ማለት፡፡ ከመተኛቱ በፊት አያት አል ኩርሲይን የቀራ ከአላህ የተላከ ጠባቂ : አይለየዉም፡፡ እስከሚነጋ ድረስም ሰይጣን አይቀርበዉም የሚለዉን ሀዲስ አቡ ሁረይራ አስተላልፈዉልናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)


በየቀኑ ከመገሪብ ሶላት በኋላ የሚከተሱትን የቁርአን አንቀጾች መቅራት።
➊ የአል በቀራ ምዕራፍን ከቁጥር 1 - 5 ያለዉን
➋  አያት አል ኩርስይን እና ቀጥለዉ ያሉትን ሁለት አንቀጾች
➌ አል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎችን ሶስት አንቀፆች
   እነዚህን አንቀፆች በቀራህባቸዉ ቀናት ሌሊቱንና ቀኑን ከድግምትና ከጂኒ ልክፍት በአላህ ፈቃድ ትጠበቃለህ፡፡

ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት፡፡


ይህንን በማስመልከት የሚከተለዉ ሃዲስ ተላልፎልናል። ይህን ፀሎት በቀን መቶ ጊዜ ያለ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ መቶ ምንዳ ይፃፍለታል። መቶ ሀጢያቶችን ይማራል። በዚያ ቀን እስከሚመሽ ድረስ ከሰይጣን መከላከያ ይሆነዋል፤ ይህ ሰዉ ከስራዉ ሥራ የሚበልጥ ማንም አያመጣም ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በስተቀር፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

ወደ መስጊድ ስትገባ የሚከተለዉን ዱአ ማለት፡-

‎አኡዙቢላሂል አዚም፣ ወቢወጂብ አል ከሪም ወ ሱልጣኒሂ አል ቀዲም ሚነ አል ሸይጧን አል ረጅም (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

ከቤትህ ስትወጣ የሚከተለው ዱዓዕ ማለት
‎ بسم الله توكلت عَلى اللهِ፣ وَلا حول ولا قوة إلا بِاللَّهِ ‎

ይህን ዱዓዕ በምትልበት ግዜ ሰይጣን እንዲህ ይላል “ተጠበክ ተመራህ፤ ተብቃቃህ እንግዲህማ ሰይጣን ይሸሽሃል ....ሌላ ሰይጣንም ሲያገኝ እንዲህ ይለዋል የተጠበቀን የተመራን የተብቃቃን ሰዉ ምንስ ልታደርገዉ ትችላለህ? ምንም ልታደርገዉ አትችልም” (አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


#ክፍል
ይቀጥላል....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.8K views03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 06:34:49 #ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                #ክፍል #አስራ_አንድ1


   #በምቀኝነትና_በቡዳ_መካከል_ያለ_ልዩነት

➊ ምቀኛ ሲባል ቡዳን ይጨምራል።
>> ቡዳ ማለት ልዩ የሆነ ምቀኛ ማለት ነዉ፡፡
>> ቡዳ ሁሉ ምቀኛ ነዉ፡፡
>> ምቀኛ ሁሉ ግን ቡዳ አይደለም፡፡ ከምቀኛ አላህ እንዲጠብቀን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን ከአል ፈለቅ ምዕራፍ እንማራለን፡፡

አንድ ሙስሊም አላህ ከምቀኛ እንዲጠብቀዉ ዱዓ (ጾለት) ሲያደርግ ከቡዳም ጭምር እንዲጠብቀዉ ዱዓ አድርጓል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ምቀኛ የሚለዉ ቃል ቡዳንም ምቀኛንም ሁለቱን ያጣመረ አገላለፅ በመሆኑ፡፡ ይህ እንግዲህ የቁርአን ታዓምራዊነት መገለጫ ነዉ።

➋  ምቀኝነት ከመመቅኘት፣ ከጥላቻ ወይም ሰዉ እንዲያጣ ከመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን በተቃራነዉ ደግሞ የቡዳ መንስኤ ማድነቅና መገረም ነዉ፡፡

➌ ምቀኝነትና ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት በማድረስ በዉጤት ሲመሳሰሉ በመንስኤዎቻቸዉ ደግሞ ይለያያሉ፡፡
>> የምቀኝነት መንስኤ የሰዉን ፀጋ መመቅኘት፣ በሰዉ ነገር መንገብገብ እና መቃጠል፣ እንዲያጣ መፈለግ ሲሆን በተቃራኒዉ
>>  የቡዳ መንስኤ ማየት እና መመልከት ነዉ። በዚህም ምክንያት ቡዳ ያልተመቀኘዉን ሰብል፣ ግዑዝ እቃ ወይም ንብረት ሊበላ ይቻላል፡፡ እንዲያዉም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል፡፡ ቡዳ አንድን ነገር በአድናቆትና በአግርሞት በመመልከቱ ምክንያት ነፍሱ ወደ ዚህ ሁኔታ ትለውጥና በምታየዉ ነገር ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡

➍ ምቀኛ ያልተከስተንና ገና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ነገር ሊመቀኝ እና ሊጎዳ ይችላል፡፡
>> ቡዳ ግን በተግባር የሌለን ነገር ሊበላ አይችልም፡፡

➎ ሰዉ እራሱን ወይም ንብረቱን አይመቀኝም፡፡ ነገር ግን እራሱን ወይም ንብረቱን በቡዳ ሊበላ ይችላል፡፡

➏ ምቀኝነት ከምቀኛና ተንኮለኛ ብቻ የሚከሰት ሲሆን
>>  ቡዳ ግን ከመልካም እና ደጋግ ሰዎች ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያስደነቃቸዉ ነገር እንዲጠፋ ባይፈልጉም በመደነቃቸዉ ብቻ ጉዳት ሊደርስ ይችላልና፡፡

➐ አንድ ሰዉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሲያይ አላህ በረካ (ረድኤት) እንዲያደርግበት ዱዓ (ፆለት) ማድረግ አለበት፡፡ ያስደነቀዉ ነገር የራሱ ይሁን የሌላ ለዉጥ አያመጣም፡፡ ይህ ዱዓዕ አስደናቂዉን ነገር በቡዳ እንዳይጎዳ ያደርገዋል፡፡

     #ጂኒዎች_ሰዎችን_በቡዳ_ይበላሉ

➊ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ እንዲህ ይላሉ>>> ነብዩ ከጂኒ ዓይንና ከሰዉ ዓይን አላህ እንዲጠብቃቸዉ ዱዓዕ ያደርጉ ነበር፡፡ የእል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎች ሲወርዱ በእነዚህ በመጠቀም ሌሎችን (ዱዓዎች) ትተዋል” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብላዋል)፡፡

የአል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎችን በመቅራት ከጂኒ እና ከሰዉ ቡዳ መከላከል እና መጠበቅ እንደሚቻል ከዚህ ሃዲስ እንማራለን


➋ እናታችን ኡሙ ሰለማ እንዲህ ይላሉ፡ በቤቱ ዉስጥ በፊቷ ላይ ጥቁረት ያለባትን ልጅ ነብዩ ተመለከቱና እንዲህ አሉ የጂኒ ቡዳ ስላለባት ሩቅያ አድርጉላት” (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

ቡዳ ከ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን  ከጂኒዎችም : (ከሰይጣናትም) ሊከስት እንደሚችል ከእነዚህ ሁለት ሀዲሶች እንገነዘባለን፡፡

ስለዚህ ማንኛዉም ሙስሊም
>> ልብሱን ሲያወልቅ፧
>> መስታዎት ሲያይ ማንኛዉንምስራ ሲጀምር ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ማለት ይኖርበታል፡፡ ይህም ከጂኒ ቡዳ፣ ከሰዎች ቡዳ እና ከሌሎች ጉዳቶችም ይከላከልለታል፡፡

   #የሰዉ_ዓይን (የቡዳ) #ህክምና

የሰዉ ዓይን (ቡዳን) ለማከም የሚያገለግሉ በርካታ ዘዴዎች አሉ። የተወሰኑትን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡


         #መታጠብ

በዓይነ ጉዳት ያደረሰዉ ሰዉ _ የሚታወቅ ከሆነ እንዲታጠብ ይደረጋል፡፡ ከዚያም የታጠበበትን ዉሀ በመዉሰድ በታመመዉ ሰዉ ገላ ላይ በጀርባዉ በኩል ማፍሰስ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡


የትጥበቱ አፈፃፀም

ኢብን ሺሀብ አል ዙህሪ እንዲህ አሉ "ኡለማዎች ትጥበቱን በሚከተለዉ መልኩ ሲገልጹት አስተዉያለሁ፡፡ ይኸዉም በዓይኑ ጉዳት ላደረሰዉ ሰዉ በሳፋ ዉሃ ይቀርብለታል፤ ይህም ስዉ ከዉሃዉ በመዝገን ተጉመጥምጦ መልሶ ሳፋዉ ዉስጥ ይተፋዋል፡፡ ከዚያም ፊቱን ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን በግራ እጁ ያጥባል። ከዚያም ግራ እጅን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን ክርን በግራ እጁ የግራ እጁን ከርን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን በግራ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ ጉልበቱን በግራ እጁ የግራ ጉልበቱን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም በሽርጡ የተሸፈነዉን የአካሉን ክፍል ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳፋዉ መሬት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ከዚያም ዉሃዉን በታመመዉ ሰዉ ላይ በጀርባዉ በኩል ባንድ ግዜ ማፍሰስ፡፡"

ከዚህ በተረፈ በተማሚዉ ራስ እጅን አኑሮ የተለያዩ የሩቃ ምዕራፎችንና ቁርአንን መቅራት ነዉ፡፡




      #ከድግሞት_ከሲህር_ከአይንናስ_ከስንፈተ_ወሲብ_መከላከያ_መንገዶች


#ዉዱዕ_አድርጎ_መንቀሳቀስ
በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊምን ድግምት ሊነካዉ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊም ከአላህ በተላኩ መላእክት ስለሚጠበቅ ነዉ፡፡ ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ “የአካላችሁን ንጽህና ጠብቁ! አላህ ንፁሀ ያድርጋችሁ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ዉዱዕ አድርጎ ሲያድር መላኢካ ከጎኑ ያድራል፡፡ ይህ ስዉ በመኝታዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ መላኢካዉ እንዲህ እያለ ጸሎት ያደርግለታል “አላህ ሆይ! ይህን አገልጋይህን  ይቅር በለው ዉዱዕ አድርጎ ነዉ ያደረዉና።" (ሳራኒ ዘግበዉታል ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)


ሶላት አል ጀማዓህ (የህብረት ስግደትን) መከታተል

የህብረት ስግደትን መከታተል ለሙስሊም ከሰይጣናት ተንኮል ሰላምን ታመጣለታለች፡፡ አንድ ሰዉ ሶላትን  በጀምዓ ከመስገድ ከተዘናጋ የሰይጣናት መፈንጫ ይሆናል፡፡ በልክፍት፣ በድግምት፣ በቡዳ እና በመሳሰሉት ሰይጣናት ይዘባበቱበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- ሶስት ሰዎች የጀምዓ ስገደት በማይሰገድባት ከተማ ወይም የገጠር መንደር ዉስጥ ከኖሩ ሰይጣን ይሰለጥንባቸዋል፡፡ ህብረትን (ጀማዓን) አደራ!! ተኩላ የሚያድነዉ እኮ ከመንጋ ያፈነገጠን በግ ነው” (አቡ ዳዉድ በኢስናዲን ሀሰን ዘግበዉታል)


የሌሊት ሶላት (ስግደት)

እራሱን ከድግምት ለመከላከል የፈለገ የሌሊት ሶላት ይሰገድ፡ ከዚህም ሊዘናጋ አይገባም፤ የሌሊት ሰላትን አለመስገድ ሰይጣን በሰዎች ላይ እንዲሰለጥን በር ይከፍትለታል፤ ሰይጣን ከሰለጠነብህ ደግሞ ለድግምት ምቹ ሆንክ ማለት ነዉ ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ቀን ነብዩ ዘንድ የሌሊት ሰላት ሳይሰግድ ስላደረ ሰዉ ጥያቄ ተነስቶ ነብዩ እንዲህ አሉ፡
“ይህ ሰዉ በጆሮዎቹ ሰይጣን ሸንተታል" (ኻሪ ዘግበታል)

ኢብን ዑመር እንዲህ ይላሉ - “ማንም ሰዉ የዊትር ሰላት ሳይሰገድ ካደረ ሰባ ክንድ ሰንሰስት ባንገቱ ላይ ታስሮበት ያህል " (አል ሃፈዝ.ፈትሁል ባሪ ዉስጥ ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)
1.5K views03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 06:34:40
30 አመት ወደ ኋላ የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1992

በተሞሸረች በ3 ቀኗ የሠርጉ ድባብ በቅጡ ሳይቀዘቅዝ ፍቺው ፀድቆ ወደወላጆቿ ቤት ተመለሰች። ያለምንም ምክንያት ተፋተው ወደ እናቷ ቤት ተሸኘች። ያ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ውብ የፍቅራቸው ጊዜ በድንገት አከተመ። ሚስት የስቃይ ህይወትን መግፋት ጀመረች። እሱም ከሷ በኋላ ሳያገባ ድፍን ሰላሳ ዓመታት አለፈ። ሲህር ነበር ያለያያቸው የሠርግ ቬሎዋን ጠቅልለው ከሞተ ሰው አስክሬን አፍ ላይ ፎቷቸውን አስረው ቆፍረው ከመቃብር ስፍራው ቀበረው በስቃያቸው ተደሰቱ።

ሲህሩ ተገኝቶ ከተቀበረበት እንደወጣ ሚስቱ ድና ወደመልካም የጤንነት ሁኔታዋ ተመለሰች። ባል ወደ ቤተሰቦቿ አቀና። ሚስቱን በድጋሜ ተንበርክኮ ጠየቀ። አዲስ ፍቅር ቤታቸው ገባ። ጤንነት ከደጃፋቸው ደረሰ። ፍቅራቸውም አገረሸ። በ2022 ዳግም በእልልታ ተሞሸሩ።

የአክስቷ ልጅ ነበረች ሲህሩን ያሰራችባት። ቬሎዋን ቀዳ ለደጋሚው የሰጠች። ሳሂሩ ጥቁር ዶሮ አሽከርክሮ አንገቱን በጠሰና ደሙን ከፎቷቸው ጋር ለውሶ ከጀናዛ አፍ ጋር አስሮ ህይወታቸውን በስቃይ እንዲገፉ አደረጋቸው። አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ አዘነላቸው ከድፍን ሰላሳ አመታት በኋላ ከአፊያው ዳብሶ ዳግም አገናኛቸው።
1.4K views03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 06:33:40 ➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ አንድን ሰዉ ከፍታ ላይ ወጥቶ እስኪፈጠፈጥ ድረስ ታጠቃዋለች” (አህመድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
  ይህም ማለት የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ስታገኘዉ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ወጥቶ እንዲፈጠፈጥ ልታደርገዉ ትችላለች።

➏ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ የሰዉ ዓይን አይነት እዉነት ነው ፡፡ ከፍታ ቦታ (ከተራራ ላይ) ትወረራለች (አህመድ ዘግበዉታል አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

➐  ጃቢር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ>>>  የሰዉ ዓይን ሰዉን ቀብር ዉስጥ፤ ግመልን ድስት ዉስጥ ትከታለች (አቡ ነዒም ዘግበዉታል። አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

የዚህ ሀዲስ መልዕክት፡- የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ታገኘዉና እንዲሞት አድርጋ ቀብር ዉስጥ ይገባ፡፡ ግመልንም ታገኝና ሊሞት ሲል ይታረዳል ድስት ዉስጥ ገብቶ ይቀቀላል፡፡

➑ ጃቢር የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል። ነብዩ እንዲህ አሉ ፡- ከአላህ ቀዷዕ እና ቀድር በሆላ አብዛኛዉ ኡመቴ(ህዝቦቼ) የሚሞቱት በሰዉ አይን ሳቢያ ነዉ፡፡(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➒ ዐዒሻ እንዲህ አሉ >>ከሰዉ ዓይን በሩቅያ እንድታከም ነብዩ አዘዉኛል(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➓ አነስ አብኑ ማሊክ የሚከተለዉን ብለዋል "ከሰዉ ዓይን፣ ከአል ሁማ (መርዛማ የእባብ ጊንጥ መነደፍ) እና ከአል ነመነህ (በጀርባ ላይ የሚከሰት የቁስል አይነት ነዉ)  ህመሞች በ አል ሩቅያ መታከምን ነብዩ ፈቅደዋል  (ሙስሊም ዘግበዉታል)

➊➊ ኡሙ ሰለማህ የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡፡ እኔ ቤት የነበረች ልጅን ፊቷ ላይ ጥቁር ወይም ዳልቻ ነገር ተመልክተዉ ነብዩ "ይህች ልጅ የሰዉ ዓይን አባት፡፡ ስሊዚህ በአል ሩቅያ አክሟት” አሉን፡
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዉታል)


#ስለ_ስዉ_ዓይን(ቡዳ) የሙስሊም  ሊቃዉንት አስተያየት

አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ....የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም እዉነት ነዉ፡፡ አልሃፊዝ ኢብን ሃጀር እንዲህ ይላሉ

እርኩስ ባህሪ የተጠናወተዉ ሰዉ ከምቀኝነት ጋር በተቀራኜ አድናቆት ወደ አንድ ሰዉ ሲመለከትና በዚህ ሰዉ ላይ ጉዳት ሲደርስበት ይህ ነዉ እንግዲህ የሰዉ ዓይን ማለት፡:

ኢብን አሰር እንዲህ ይላሉ “ጠላት ወይም ምቀኛ አንድን ሰዉ ሊያየዉ እና በዚህም ሳቢያ ሰዉዬዉ ከታመመ የሰዉ ዓይን አገኘዉ ይባላል

አል ሃፊዝ ኢብን ቀዩም እንዲህ ይላሉ “ከፍተኛ የእዉቀት እጥረት ያለባቸዉ አንዳንድ ሰዎች የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ ይክዳሉ። የሰዉ ዓይን ተጨባጭነት የሌለዉ ተረት ነዉ በማለት ይከራከራሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከእዉነት እና ከእዉቀት የራቁ ስለ ነፍስ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ስለባህሪያቶቻቸዉ፣ ሊያደርሱት ስለሚችሉት ዉጤት እና ሊያስከትሉት ስለሚችሉት ተፅእኖ አንዳች ግንዛቤ የሌላቸዉ ናቸዉ፡፡

  የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ጠቢባን የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ አይክዱም፡፡ ምንም እንኳን ስለ መንስኤዎቹና ሊያስከትል ስለሚችለዉ ጉዳት የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸዉም፡፡

አላህ የሰዉ ልጆችን አካላትና ነፍሶቻቸዉን በዉስጣቸዉ የተለያየ ሀይላት እና ስብዕና አድርጎ እንደፈጠራቸዉ አያከራክርም፡፡ በአንዳንድ በርከት ባሉት ላይ ደግሞ ልዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህሪያት አድርጎባቸዋል። ነፍስ በአካል ላይ ልታደርስ የምትችለዉን ተጽዕኖ ማንም አስተዋይ ሰዉ አይክድም፡፡ ምክንያቱም ተጨባጭ ነገር ነዉና፡፡

#ለምሳሌ፡- የሚወደዉና የሚያከበረዉ ሰዉ የአንድን ሰዉ ፊት ሲመለከት ሲፈካ፣ በተቃራኒዉ ደግሞ የሚፈራዉ (በቁጣ) ሲያየዉ ፍም ሲመስል ይስተዋላል፡፡ ሰዉ ስላያቸዉ ብቻ የታመሙ የተዝለፈለፉ ሰዎች ማየታቸዉን ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነዉ እንግዲህ በሰዉ ልጆች ነፍስ ተፅዕኖ ሳቢያ ነዉ። በሰዎች ነፍሶች እና በአይኖቻቸዉ መካከል ከፍተኛ ቁርኝት ስላለ ነዉ.... ይህ በነፍሶቻቸዉ የደረሰዉ ጉዳት በዓይን እንደደረሰ ተደርጎ ይቆጠራል። እዉነታዉ ግን ይህን ጉዳት የሚያስከትሉት የሰዉ ልጅ ዓይኖች ሳይሆኑ ነፍሶቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ነፍሶች ደግም ባላቸዉ ሃይል፣ ባህሪያት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ገጽታዎች ከሰዉ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ።

የምቀኛ ነፍስ ለምትመቀኘዉ ሰዉ ጎጂ ናት። ለዚህም ነዉ ነብዩን ከምቀኛ ተንኮል እንዲጠብቃቸዉ እንዲፀልዩ አላህ ያዘዛቸዉ፡፡ ምቀኛ በሚመቀኘዉ ሰዉ ላይ ስለሚያስከትለዉ ጉዳት ስለ ሰዎች አዉቀት የሌለዉ ካልሆነ በቀር ማንም አይክድም፡፡

.የሰዉ ዓይን ልክፍት መሰረቱ እንዲህ ነዉ፡፡ እርኩስ የሆነች ነፍስ በእርኩስ ባህሪይ ተገልጣ የምትመቀኘዉን ሰዉ ስታገኘዉ በዚህ ልዩ በሆነዉ እርኩስ ባህሪዋ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡


ለዚህ ደግሞ ኮብራ እባብን በንፅፅር መዉሰድ ይቻላል። በኮብራ ዉስጥ መርዝ ከሃይል ጋር ይገኛል፡፡ ኮብራዉ ጠላቶቹን ሲያይ በሃይል እና በቁጣ ይነሳሳል። መጥፎና ጎጂ በሆነዉ ባህሪዉ ይገለጣል፡፡ ይህ መጥፎ የሃይልና የቁጣ ባህሪዉ ሲብስ ጽንስ እስከማስወረድ እና ዓይን እስከ ማጥፋት ይደርሳል፡፡

አብተር እና ዙጡፍየተይን ስለሚባሉ የእባብ ዓይነቶች እነዚህ ዓይን ያጠፋሉ ፅንስ ያስወርዳሉ፡፡ በማለት ነብዩ አስተምረዉናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

በመገናኘት!
ድንገት በማግኘት፣
በማየት፣ በነፍስ በማሰብ፣
ድግምት በማነብነብ፤ በማማተብ፣
በምናብ በመሳል ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡


የቡዳ ነፍስ በማየት ብቻ አይደለም ጉዳት የምታደርሰዉ፡፡ ቡዳዉ ማየት የተሳነዉ ቢሆንም እንኳ ስለ ሆነ ነገር በሚነገረዉ ወይም በሚሰማዉ ብቻ ተመስርቶ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በርካታ ቡዳዎች ሰዉየዉን ሳያዩት ስለ እርሱ በተነገራቸዉ ላይ ብቻ ተመስርተዉ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ቡዳ ከቡዳዉ ሰዉ በዓይኑ በኩል ውጥታ እንደ ቀስት ትወረወራለች። ዒላማዋን ልትስት ወይም ልታገኝ ትችላለች። ዒላማዉ
>> የጠዋት የማታ አዝካር የሚል
>> ሶላት የሚሰግድ
>> ቁርአን የሚቀራ ከሆን ቡዳዉ ሊጎዳዉ አይችልም።

# ባጭሩ የቡዳ ጉዳት የተመሰረተዉ እንዲህ ነዉ፡- ቡዳዉን አንድ ነገር ያስደንቀዋል፡፡ በዚህ ግዜ እርኩስ ነፍሱ  ወደ  አስደነቃት ነገር በዓይን በኩል መርዟን ትረጫለች፡፡ አንዳንዴም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል። ሌሎችንም ቢሆን ያለፍላጎቱ ይበላል።

ክፍል
ይቀጥላል....


4any cmt
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.7K viewsedited  03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 04:08:12 አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ፡፡

☞በጂን
☞ በሲህር(ድግምት)
☞ አይነ ጥላ(ቡዳ)
ላይ ያተኮሩ ፁሁፎች ከቁርአንና ከሀዲስ በማስረጃ
ምልክቶች እና ሁሉም በቤቱ ያሉ መፍትሄዎች መከለከያዉ ያተኮረ ፁሁፍ ኢንሻ አላህ ቅዳሜ ሀምሌ ➊ ባልተንዛዛ ክፍል እጥር ምጥን ያለ የሚጠቅም ፁሁፍ ይቀርባል፡፡

የተዘጋጀዉ ፁሁፍ 70% መፅሀፍ ሲሆን
የመፅሀፉም ርዕስ
#ድግምት_ሲህር_ምንነቱና_ፈዉሱ  ከሚለወዉ መፅሀፍ ወሂድ አብዱሰላም ፅፎት ሰይድ አሸንፍ ወደ አማረኛ ተርጉሞት ገበያ ላይ ካለ መፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ፡፡
እናንተም ገዝታችሁ መፅሀፉን ሙሉዉን ብታነቡት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ፡፡

30% ደግሞ  የዲን እዉቀት ያላቸዉን በመጠየቅና ...ሩቃ ለአላህ ብሎ የሚሰሩትን ከሚነግሩኝ ገጠመኝ አንፃር አተኩሮ የተፃፈ ነዉ፡፡

በዚህ ፁሁፍ 70% ከመፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ ከመፅሀፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነዉ ጊዜ ይፈጃል ..አይንንም ይፈታተናል በዛዉ አሁን ትምህርት የተጠናቀቀበት ጊዜ ስለሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ርቀን ማንበብ ላይ ብናተኩር የማንበብ ባህላችን ይጨምራል እናም ይሄን ስለሲህር ድግምት ከጨረስኩ ጊዜ እንደምንም ከተመቻቸልኝ ሌላ ርዕስ ተይዞ ከመፅሀፍ እና ከሚያቁ በመጠየቅ አዘጋጃለሁ፡፡
እናም በማቀርባቸዉ ፁሁፎች መፅሀፍ ማንበብ ማቆማችን ምን ያህል እዉቀት እያነሰን እንደሆነ
ሁላችንም ራሳችንን ፈትሸን ....
ከተስማማን በጀመአ መፅሀፍ ማንበብ program
እንጀምር ይሆናል፡፡


ይህን ስለሲህር ጂን ቡዳ የሚያተኩር ፁሁፍ በቻላችሁት አቅም ለዘመድ ጓደኛ ቤተሰብ ሼር በማድረግ ራሳችንን ፈትሸን ሌሎች እንዲፈትሹ እናድርግ፡፡

ፁሁፍ ማቅረብ ታሪክ ማቅረብ ስላቆምኩ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ  የቻናል ቤተሰብ ከቻናል አምልጧል...ለወደፊት ያለዉ በቂ ነዉ ፡፡ ግን ይጠቀማሉ ብላችሁ ካሰባችሁ አዲስ እንዲገቡ  የምፈልጉ ካለ ሼር በማድረግ ለሚመቻችሁ ቤተሰብ ይጋብዙ

መልካም ንባብ ...አንብበን የምናስተነትን ራሳችንን የምንፈትሽ ፈጣሪ ያድርገን

አሚር ሰይድ


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group
892 views01:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ