Get Mystery Box with random crypto!

#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም                   አሚር ሰይድ       | ISLAM IS UNIVERSITY

#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                #ክፍል #አስራ_አንድ1


   #በምቀኝነትና_በቡዳ_መካከል_ያለ_ልዩነት

➊ ምቀኛ ሲባል ቡዳን ይጨምራል።
>> ቡዳ ማለት ልዩ የሆነ ምቀኛ ማለት ነዉ፡፡
>> ቡዳ ሁሉ ምቀኛ ነዉ፡፡
>> ምቀኛ ሁሉ ግን ቡዳ አይደለም፡፡ ከምቀኛ አላህ እንዲጠብቀን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን ከአል ፈለቅ ምዕራፍ እንማራለን፡፡

አንድ ሙስሊም አላህ ከምቀኛ እንዲጠብቀዉ ዱዓ (ጾለት) ሲያደርግ ከቡዳም ጭምር እንዲጠብቀዉ ዱዓ አድርጓል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ምቀኛ የሚለዉ ቃል ቡዳንም ምቀኛንም ሁለቱን ያጣመረ አገላለፅ በመሆኑ፡፡ ይህ እንግዲህ የቁርአን ታዓምራዊነት መገለጫ ነዉ።

➋  ምቀኝነት ከመመቅኘት፣ ከጥላቻ ወይም ሰዉ እንዲያጣ ከመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን በተቃራነዉ ደግሞ የቡዳ መንስኤ ማድነቅና መገረም ነዉ፡፡

➌ ምቀኝነትና ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት በማድረስ በዉጤት ሲመሳሰሉ በመንስኤዎቻቸዉ ደግሞ ይለያያሉ፡፡
>> የምቀኝነት መንስኤ የሰዉን ፀጋ መመቅኘት፣ በሰዉ ነገር መንገብገብ እና መቃጠል፣ እንዲያጣ መፈለግ ሲሆን በተቃራኒዉ
>>  የቡዳ መንስኤ ማየት እና መመልከት ነዉ። በዚህም ምክንያት ቡዳ ያልተመቀኘዉን ሰብል፣ ግዑዝ እቃ ወይም ንብረት ሊበላ ይቻላል፡፡ እንዲያዉም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል፡፡ ቡዳ አንድን ነገር በአድናቆትና በአግርሞት በመመልከቱ ምክንያት ነፍሱ ወደ ዚህ ሁኔታ ትለውጥና በምታየዉ ነገር ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡

➍ ምቀኛ ያልተከስተንና ገና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ነገር ሊመቀኝ እና ሊጎዳ ይችላል፡፡
>> ቡዳ ግን በተግባር የሌለን ነገር ሊበላ አይችልም፡፡

➎ ሰዉ እራሱን ወይም ንብረቱን አይመቀኝም፡፡ ነገር ግን እራሱን ወይም ንብረቱን በቡዳ ሊበላ ይችላል፡፡

➏ ምቀኝነት ከምቀኛና ተንኮለኛ ብቻ የሚከሰት ሲሆን
>>  ቡዳ ግን ከመልካም እና ደጋግ ሰዎች ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያስደነቃቸዉ ነገር እንዲጠፋ ባይፈልጉም በመደነቃቸዉ ብቻ ጉዳት ሊደርስ ይችላልና፡፡

➐ አንድ ሰዉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሲያይ አላህ በረካ (ረድኤት) እንዲያደርግበት ዱዓ (ፆለት) ማድረግ አለበት፡፡ ያስደነቀዉ ነገር የራሱ ይሁን የሌላ ለዉጥ አያመጣም፡፡ ይህ ዱዓዕ አስደናቂዉን ነገር በቡዳ እንዳይጎዳ ያደርገዋል፡፡

     #ጂኒዎች_ሰዎችን_በቡዳ_ይበላሉ

➊ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ እንዲህ ይላሉ>>> ነብዩ ከጂኒ ዓይንና ከሰዉ ዓይን አላህ እንዲጠብቃቸዉ ዱዓዕ ያደርጉ ነበር፡፡ የእል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎች ሲወርዱ በእነዚህ በመጠቀም ሌሎችን (ዱዓዎች) ትተዋል” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብላዋል)፡፡

የአል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎችን በመቅራት ከጂኒ እና ከሰዉ ቡዳ መከላከል እና መጠበቅ እንደሚቻል ከዚህ ሃዲስ እንማራለን


➋ እናታችን ኡሙ ሰለማ እንዲህ ይላሉ፡ በቤቱ ዉስጥ በፊቷ ላይ ጥቁረት ያለባትን ልጅ ነብዩ ተመለከቱና እንዲህ አሉ የጂኒ ቡዳ ስላለባት ሩቅያ አድርጉላት” (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

ቡዳ ከ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን  ከጂኒዎችም : (ከሰይጣናትም) ሊከስት እንደሚችል ከእነዚህ ሁለት ሀዲሶች እንገነዘባለን፡፡

ስለዚህ ማንኛዉም ሙስሊም
>> ልብሱን ሲያወልቅ፧
>> መስታዎት ሲያይ ማንኛዉንምስራ ሲጀምር ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ማለት ይኖርበታል፡፡ ይህም ከጂኒ ቡዳ፣ ከሰዎች ቡዳ እና ከሌሎች ጉዳቶችም ይከላከልለታል፡፡

   #የሰዉ_ዓይን (የቡዳ) #ህክምና

የሰዉ ዓይን (ቡዳን) ለማከም የሚያገለግሉ በርካታ ዘዴዎች አሉ። የተወሰኑትን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡


         #መታጠብ

በዓይነ ጉዳት ያደረሰዉ ሰዉ _ የሚታወቅ ከሆነ እንዲታጠብ ይደረጋል፡፡ ከዚያም የታጠበበትን ዉሀ በመዉሰድ በታመመዉ ሰዉ ገላ ላይ በጀርባዉ በኩል ማፍሰስ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡


የትጥበቱ አፈፃፀም

ኢብን ሺሀብ አል ዙህሪ እንዲህ አሉ "ኡለማዎች ትጥበቱን በሚከተለዉ መልኩ ሲገልጹት አስተዉያለሁ፡፡ ይኸዉም በዓይኑ ጉዳት ላደረሰዉ ሰዉ በሳፋ ዉሃ ይቀርብለታል፤ ይህም ስዉ ከዉሃዉ በመዝገን ተጉመጥምጦ መልሶ ሳፋዉ ዉስጥ ይተፋዋል፡፡ ከዚያም ፊቱን ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን በግራ እጁ ያጥባል። ከዚያም ግራ እጅን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን ክርን በግራ እጁ የግራ እጁን ከርን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን በግራ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ ጉልበቱን በግራ እጁ የግራ ጉልበቱን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም በሽርጡ የተሸፈነዉን የአካሉን ክፍል ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳፋዉ መሬት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ከዚያም ዉሃዉን በታመመዉ ሰዉ ላይ በጀርባዉ በኩል ባንድ ግዜ ማፍሰስ፡፡"

ከዚህ በተረፈ በተማሚዉ ራስ እጅን አኑሮ የተለያዩ የሩቃ ምዕራፎችንና ቁርአንን መቅራት ነዉ፡፡




      #ከድግሞት_ከሲህር_ከአይንናስ_ከስንፈተ_ወሲብ_መከላከያ_መንገዶች


#ዉዱዕ_አድርጎ_መንቀሳቀስ
በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊምን ድግምት ሊነካዉ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊም ከአላህ በተላኩ መላእክት ስለሚጠበቅ ነዉ፡፡ ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ “የአካላችሁን ንጽህና ጠብቁ! አላህ ንፁሀ ያድርጋችሁ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ዉዱዕ አድርጎ ሲያድር መላኢካ ከጎኑ ያድራል፡፡ ይህ ስዉ በመኝታዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ መላኢካዉ እንዲህ እያለ ጸሎት ያደርግለታል “አላህ ሆይ! ይህን አገልጋይህን  ይቅር በለው ዉዱዕ አድርጎ ነዉ ያደረዉና።" (ሳራኒ ዘግበዉታል ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)


ሶላት አል ጀማዓህ (የህብረት ስግደትን) መከታተል

የህብረት ስግደትን መከታተል ለሙስሊም ከሰይጣናት ተንኮል ሰላምን ታመጣለታለች፡፡ አንድ ሰዉ ሶላትን  በጀምዓ ከመስገድ ከተዘናጋ የሰይጣናት መፈንጫ ይሆናል፡፡ በልክፍት፣ በድግምት፣ በቡዳ እና በመሳሰሉት ሰይጣናት ይዘባበቱበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- ሶስት ሰዎች የጀምዓ ስገደት በማይሰገድባት ከተማ ወይም የገጠር መንደር ዉስጥ ከኖሩ ሰይጣን ይሰለጥንባቸዋል፡፡ ህብረትን (ጀማዓን) አደራ!! ተኩላ የሚያድነዉ እኮ ከመንጋ ያፈነገጠን በግ ነው” (አቡ ዳዉድ በኢስናዲን ሀሰን ዘግበዉታል)


የሌሊት ሶላት (ስግደት)

እራሱን ከድግምት ለመከላከል የፈለገ የሌሊት ሶላት ይሰገድ፡ ከዚህም ሊዘናጋ አይገባም፤ የሌሊት ሰላትን አለመስገድ ሰይጣን በሰዎች ላይ እንዲሰለጥን በር ይከፍትለታል፤ ሰይጣን ከሰለጠነብህ ደግሞ ለድግምት ምቹ ሆንክ ማለት ነዉ ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ቀን ነብዩ ዘንድ የሌሊት ሰላት ሳይሰግድ ስላደረ ሰዉ ጥያቄ ተነስቶ ነብዩ እንዲህ አሉ፡
“ይህ ሰዉ በጆሮዎቹ ሰይጣን ሸንተታል" (ኻሪ ዘግበታል)

ኢብን ዑመር እንዲህ ይላሉ - “ማንም ሰዉ የዊትር ሰላት ሳይሰገድ ካደረ ሰባ ክንድ ሰንሰስት ባንገቱ ላይ ታስሮበት ያህል " (አል ሃፈዝ.ፈትሁል ባሪ ዉስጥ ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)