Get Mystery Box with random crypto!

➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን | ISLAM IS UNIVERSITY

➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ አንድን ሰዉ ከፍታ ላይ ወጥቶ እስኪፈጠፈጥ ድረስ ታጠቃዋለች” (አህመድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
  ይህም ማለት የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ስታገኘዉ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ወጥቶ እንዲፈጠፈጥ ልታደርገዉ ትችላለች።

➏ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ የሰዉ ዓይን አይነት እዉነት ነው ፡፡ ከፍታ ቦታ (ከተራራ ላይ) ትወረራለች (አህመድ ዘግበዉታል አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

➐  ጃቢር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ>>>  የሰዉ ዓይን ሰዉን ቀብር ዉስጥ፤ ግመልን ድስት ዉስጥ ትከታለች (አቡ ነዒም ዘግበዉታል። አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

የዚህ ሀዲስ መልዕክት፡- የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ታገኘዉና እንዲሞት አድርጋ ቀብር ዉስጥ ይገባ፡፡ ግመልንም ታገኝና ሊሞት ሲል ይታረዳል ድስት ዉስጥ ገብቶ ይቀቀላል፡፡

➑ ጃቢር የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል። ነብዩ እንዲህ አሉ ፡- ከአላህ ቀዷዕ እና ቀድር በሆላ አብዛኛዉ ኡመቴ(ህዝቦቼ) የሚሞቱት በሰዉ አይን ሳቢያ ነዉ፡፡(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➒ ዐዒሻ እንዲህ አሉ >>ከሰዉ ዓይን በሩቅያ እንድታከም ነብዩ አዘዉኛል(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➓ አነስ አብኑ ማሊክ የሚከተለዉን ብለዋል "ከሰዉ ዓይን፣ ከአል ሁማ (መርዛማ የእባብ ጊንጥ መነደፍ) እና ከአል ነመነህ (በጀርባ ላይ የሚከሰት የቁስል አይነት ነዉ)  ህመሞች በ አል ሩቅያ መታከምን ነብዩ ፈቅደዋል  (ሙስሊም ዘግበዉታል)

➊➊ ኡሙ ሰለማህ የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡፡ እኔ ቤት የነበረች ልጅን ፊቷ ላይ ጥቁር ወይም ዳልቻ ነገር ተመልክተዉ ነብዩ "ይህች ልጅ የሰዉ ዓይን አባት፡፡ ስሊዚህ በአል ሩቅያ አክሟት” አሉን፡
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዉታል)


#ስለ_ስዉ_ዓይን(ቡዳ) የሙስሊም  ሊቃዉንት አስተያየት

አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ....የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም እዉነት ነዉ፡፡ አልሃፊዝ ኢብን ሃጀር እንዲህ ይላሉ

እርኩስ ባህሪ የተጠናወተዉ ሰዉ ከምቀኝነት ጋር በተቀራኜ አድናቆት ወደ አንድ ሰዉ ሲመለከትና በዚህ ሰዉ ላይ ጉዳት ሲደርስበት ይህ ነዉ እንግዲህ የሰዉ ዓይን ማለት፡:

ኢብን አሰር እንዲህ ይላሉ “ጠላት ወይም ምቀኛ አንድን ሰዉ ሊያየዉ እና በዚህም ሳቢያ ሰዉዬዉ ከታመመ የሰዉ ዓይን አገኘዉ ይባላል

አል ሃፊዝ ኢብን ቀዩም እንዲህ ይላሉ “ከፍተኛ የእዉቀት እጥረት ያለባቸዉ አንዳንድ ሰዎች የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ ይክዳሉ። የሰዉ ዓይን ተጨባጭነት የሌለዉ ተረት ነዉ በማለት ይከራከራሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከእዉነት እና ከእዉቀት የራቁ ስለ ነፍስ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ስለባህሪያቶቻቸዉ፣ ሊያደርሱት ስለሚችሉት ዉጤት እና ሊያስከትሉት ስለሚችሉት ተፅእኖ አንዳች ግንዛቤ የሌላቸዉ ናቸዉ፡፡

  የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ጠቢባን የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ አይክዱም፡፡ ምንም እንኳን ስለ መንስኤዎቹና ሊያስከትል ስለሚችለዉ ጉዳት የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸዉም፡፡

አላህ የሰዉ ልጆችን አካላትና ነፍሶቻቸዉን በዉስጣቸዉ የተለያየ ሀይላት እና ስብዕና አድርጎ እንደፈጠራቸዉ አያከራክርም፡፡ በአንዳንድ በርከት ባሉት ላይ ደግሞ ልዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህሪያት አድርጎባቸዋል። ነፍስ በአካል ላይ ልታደርስ የምትችለዉን ተጽዕኖ ማንም አስተዋይ ሰዉ አይክድም፡፡ ምክንያቱም ተጨባጭ ነገር ነዉና፡፡

#ለምሳሌ፡- የሚወደዉና የሚያከበረዉ ሰዉ የአንድን ሰዉ ፊት ሲመለከት ሲፈካ፣ በተቃራኒዉ ደግሞ የሚፈራዉ (በቁጣ) ሲያየዉ ፍም ሲመስል ይስተዋላል፡፡ ሰዉ ስላያቸዉ ብቻ የታመሙ የተዝለፈለፉ ሰዎች ማየታቸዉን ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነዉ እንግዲህ በሰዉ ልጆች ነፍስ ተፅዕኖ ሳቢያ ነዉ። በሰዎች ነፍሶች እና በአይኖቻቸዉ መካከል ከፍተኛ ቁርኝት ስላለ ነዉ.... ይህ በነፍሶቻቸዉ የደረሰዉ ጉዳት በዓይን እንደደረሰ ተደርጎ ይቆጠራል። እዉነታዉ ግን ይህን ጉዳት የሚያስከትሉት የሰዉ ልጅ ዓይኖች ሳይሆኑ ነፍሶቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ነፍሶች ደግም ባላቸዉ ሃይል፣ ባህሪያት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ገጽታዎች ከሰዉ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ።

የምቀኛ ነፍስ ለምትመቀኘዉ ሰዉ ጎጂ ናት። ለዚህም ነዉ ነብዩን ከምቀኛ ተንኮል እንዲጠብቃቸዉ እንዲፀልዩ አላህ ያዘዛቸዉ፡፡ ምቀኛ በሚመቀኘዉ ሰዉ ላይ ስለሚያስከትለዉ ጉዳት ስለ ሰዎች አዉቀት የሌለዉ ካልሆነ በቀር ማንም አይክድም፡፡

.የሰዉ ዓይን ልክፍት መሰረቱ እንዲህ ነዉ፡፡ እርኩስ የሆነች ነፍስ በእርኩስ ባህሪይ ተገልጣ የምትመቀኘዉን ሰዉ ስታገኘዉ በዚህ ልዩ በሆነዉ እርኩስ ባህሪዋ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡


ለዚህ ደግሞ ኮብራ እባብን በንፅፅር መዉሰድ ይቻላል። በኮብራ ዉስጥ መርዝ ከሃይል ጋር ይገኛል፡፡ ኮብራዉ ጠላቶቹን ሲያይ በሃይል እና በቁጣ ይነሳሳል። መጥፎና ጎጂ በሆነዉ ባህሪዉ ይገለጣል፡፡ ይህ መጥፎ የሃይልና የቁጣ ባህሪዉ ሲብስ ጽንስ እስከማስወረድ እና ዓይን እስከ ማጥፋት ይደርሳል፡፡

አብተር እና ዙጡፍየተይን ስለሚባሉ የእባብ ዓይነቶች እነዚህ ዓይን ያጠፋሉ ፅንስ ያስወርዳሉ፡፡ በማለት ነብዩ አስተምረዉናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

በመገናኘት!
ድንገት በማግኘት፣
በማየት፣ በነፍስ በማሰብ፣
ድግምት በማነብነብ፤ በማማተብ፣
በምናብ በመሳል ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡


የቡዳ ነፍስ በማየት ብቻ አይደለም ጉዳት የምታደርሰዉ፡፡ ቡዳዉ ማየት የተሳነዉ ቢሆንም እንኳ ስለ ሆነ ነገር በሚነገረዉ ወይም በሚሰማዉ ብቻ ተመስርቶ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በርካታ ቡዳዎች ሰዉየዉን ሳያዩት ስለ እርሱ በተነገራቸዉ ላይ ብቻ ተመስርተዉ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ቡዳ ከቡዳዉ ሰዉ በዓይኑ በኩል ውጥታ እንደ ቀስት ትወረወራለች። ዒላማዋን ልትስት ወይም ልታገኝ ትችላለች። ዒላማዉ
>> የጠዋት የማታ አዝካር የሚል
>> ሶላት የሚሰግድ
>> ቁርአን የሚቀራ ከሆን ቡዳዉ ሊጎዳዉ አይችልም።

# ባጭሩ የቡዳ ጉዳት የተመሰረተዉ እንዲህ ነዉ፡- ቡዳዉን አንድ ነገር ያስደንቀዋል፡፡ በዚህ ግዜ እርኩስ ነፍሱ  ወደ  አስደነቃት ነገር በዓይን በኩል መርዟን ትረጫለች፡፡ አንዳንዴም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል። ሌሎችንም ቢሆን ያለፍላጎቱ ይበላል።

ክፍል
ይቀጥላል....


4any cmt
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group