Get Mystery Box with random crypto!

ትልቅ ሰፕራይዝ የባል በቀል ናይጄሪያ ውስጥ ነው፣ ባል ሚስቱ የሱን እግር እየጠበቀች እንደምትማ | ISLAM IS UNIVERSITY

ትልቅ ሰፕራይዝ የባል በቀል

ናይጄሪያ ውስጥ ነው፣ ባል ሚስቱ የሱን እግር እየጠበቀች እንደምትማግጥበት ይጠረጥራል። አውጥቶ አውርዶ ለስራ ፊልድ በሚወጣበት ጊዜ ከመኝታ ክፍሉ ውስጥ ድብቅ ካሜራ ይገጥማል።
ከስራ ሲመለስም በድብቅ የተገጠመው ካሜራ ያስቀረውን ተነቀሳቃሽ ምስል ሲፈትሽ እውነትም ሚስት የገዛ አልጋው ላይ ከጎረምሳ ጋራ አንሶላ ስትጋፈፍ ቀድቶ ኖሮ ከሀ እስከ ፐ ለባል ያሳየዋል።

በዚህ የሚስቱ ድርጊት ቆሽቱ ያረረው አቶ ባል የሆዱን በሆዱ ይዞ ሚስቱን ለልደቷ ቤተሰቦቿን ሁሉ እንድትጠራ፣ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋት እንደሚፈልግ ይነግራታል። ሚስትም አንደታዘዘችው ቤተሰቦቿን በሞላ ለልደቷ ትጠራለች። ባልም እሱ ቤት ባልነበረበት ወቅት በገዛ መኝታ ክፍሉ ውስጥከጎረምሳ ጋራ ስትዛለል ያስቀረውን ፎቶ በፍሬም ውስጥ አድርጎ በስጦታ ወረቀትም ጠቅልሎ የልደት ስጦታ ያበረክትላታል። ምንነቱን ለማየት የጓጉት ቤተሰቦች እንድትከፍተው በሞራል ይገፋፏትና ወረቀቱን ስትገልጠው የራሷ ጉድ መሆኑን ስታይ በድንጋጤ እራሷን ሳተች።

ሰውየው የሰራው ስራ ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ በናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያ የጭቅጭቅ አርዕስት ሆኖአል።